ChatCrawlerпоиск по публичному Telegram Открыть приложение
E

Ethiopian Statistics

сообщение · 2026-09-02 02:54 UTC
[
Ссылка
нажмите — покажем
“ወጣትነህ ? “ ወጣት ነህን ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ዕድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህም አድርገህ አታስብ  ‹‹የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና›› 1ኛ ተሰ5፤2 ስለዚህ ምክንያት የእድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ በለጋ ዕድሜያችን ሲቀጩ በየቀኑ አታይምን ስለዚህም አንዱ ሲመክር እንዲህ ብሏል “ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልህ አትቁጠር” ሲራ 5፤8 ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ፤ ስለዚህ ሽማግሌውም ይህንን ምክር ልብ ይበል ወጣቱም ይህንን ነገር ተረድቶ ተግባራዊ ያርግ ዘንድ ይሁን ወይስ በምቾትና ሁሉ ነገር ተሟልቶልህ የምትኖር እስካሁን ችግር የሚባል ደርሶብህ የማታውቅ ባለጸጋ ነህን እንዲህም ቢሆን ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ስማው “ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” 1ኛ ተሰ 5፤3 የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው እኛ በራሳችን የወደፊት ሕይወትና ሁኔታ ላይ ማዘዝ የምንችልና የሰለጠን አይደለንም ነገር ግን በጽድቅ ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና›› #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ ገጽ 134 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ​👉 https://t.me/Agapeye ​👉 https://t.me/Agapeye
1.7K ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Открыть в Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

Слепок открытой публичной ленты из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог