Фотография
нажмите — покажем
нажмите — покажем
🌼እንኳን ለአዲስ ዓመት በሰላም በፍቅር አደረሳችሁ።🌼 Officially 2019 ዓ.ም
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። [ መዝ 65÷11 ]
የክረምት ዘመን አልቆ ሲወጣ
አዲሱ ዓመት ማርቆስ መጣ
አሮጌው አልፎ አዲስ ሲተካ
በመስከረም ወር አበባው ፈካ🌼
በታላቅ ተስፋ ፍቅር ታጅቦ
ሰውና ምድሩ በጣም ተውቦ
ተቀበልነው በልዩ ደስታ
አዲሱን ዓመት ባማረ ሁኔታ
ለዛሬዋ ቀን ላደረሰን
ምስጋና አቅርበን ለአምላካችን
በአዲሱ ዓመት ልብ ታድሶ
ጥላቻ ጠፍቶ ፍቅራችን ነግሶ
አንድነት ደምቆ ክፋት ደብዝዞ
የሚሆንበት የምህረት ዓመት
ያድርግልን ጌታ በእውነት
የምንገዛ ለአምላክ ቃሉን
የምንማር ህገ ወንጌሉን
ንሰሐ ሱባኤ የምንገባበት
ለነብሳችንም የምንኖርበት
ጌታን አንግሰን በልባችን
ኃጢያት አርቀን ከሕይወታችን
የምንሮበት ያድርግልን
አዲሱን ዓመት ይባርክልን።
🌼🌼Happy New Year🌼🌼
❤1
49 ·