ChatCrawlerпоиск по публичному Telegram Открыть приложение
A

ASTU Network Group ®

сообщение · 2026-07-22 06:54 UTC
I
Фотография
нажмите — покажем
ኮስትሸሪንግ ❌🇰🇪‼️ የኬንያ መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ በበጀት ሊሸፈን መሆኑን አስታወቀ‼️ የኬንያ መንግስት ከሚቀጥለው መስከረም 2026 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገቡ ሁሉንም ተማሪዎች ትምህርት ሙሉ በሙሉ በመንግስት በጀት እንደሚሸፈን ይፋ አደረገ። ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ አዲሱ የትምህርት ፋይናንስ ማዕቀፍ ከቤተሰብ ኢኮኖሚያዊ አቅም ውጪ በውጤት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንደሆነ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ተግባራዊ ተደርገው የነበሩት የዩኒቨርሲቲ በጀት አሰጣጥ ሥርዓቶችና የብድር ድብልቅ ሞዴሎች ተቋማቱንና ተማሪዎችን በቂ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻላቸው መቋረጣቸውን ተናግረዋል። አዲሱ ሥርዓት ወላጆች በፈቃደኝነት ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት የክፍያ ጫና እንዳይኖርባቸው የሚያደርግና ድህነት ትምህርት እንዳያስተጓጉል የሚያስችል ነው ተብሏል። ለዚህም እንዲመች ፓርላማው የከፍተኛ ትምህርት ብድር ቦርድን ጨምሮ አስፈላጊውን የህግ ማሻሻያ በፍጥነት እንዲያጸድቅ ተጠይቋል። #ካፒታል |➲| @ASTU_Network
3.3K ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Открыть в Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

Слепок открытой публичной ленты из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог