ChatCrawlerпоиск по публичному Telegram Открыть приложение
A

ASTU Network Group ®

сообщение · 2026-07-27 06:25 UTC
I
Фотография
нажмите — покажем
🚨 እባካችሁ እንርዳው! 🙏 ከላይ በምስሉ ላይ የምታዩት የ18 ዓመት ታዳጊ አቤል መለሰ ነው። የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በትምህርቱ ውጤታማና ተስፋ ሰጪ ወጣት ነበር። ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ለመመለስ በ4 ኪሎ አካባቢ ትራንስፖርት እየጠበቀ ሳለ፣ በአጠገቡ ከሚገነባ ሕንፃ 13ኛ ፎቅ ላይ የነበረ 37 ኪ.ግ. የሚመዝን ጣውላ በጭንቅላቱ ላይ ወድቆ ከባድ አደጋ ደረሰበት። በአስቸኳይ ወደ ላንሴት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስዶ የቀዶ ጥገና ተደርጎለት ሕክምናውን ጀመረ። የህንፃው ተቋራጭ ለ3 ወራት የህክምና ወጪውን ቢሸፍንም፣ ከዚያ በኋላ ክፍያውን ማቋረጡን ተከትሎ ቤተሰቡ በራሳቸው አቅም ሕክምናውን ለመቀጠል ተገደዋል። አሁንም አቤል በኮማ ውስጥ ይገኛል። ዶክተሮች ተገቢውን የሕክምና ክትትል ካገኘ ወደ ቀድሞ ሁኔታው የመመለስ ተስፋ እንዳለ ገልጸዋል። ሆኖም ቤተሰቡ የህክምና ወጪውን ለመሸፈን አቅም ስለሌላቸው የሁላችንን ድጋፍ እየጠየቁ ነው። ✅ ይህን ጥሪ ከመለጠፋችን በፊት የህክምና ሰነዶችንና አስፈላጊ ማረጋገጫዎችን በማየት አረጋግጠናል። 💳 CBE: 1000348860538 📞 ስልክ: 0911398024 / 0931534451 የባንክ ስም - እታለማሁ አስፋው ወ/መድህን 🙏 አቅም ያላችሁ የቻላችሁትን እርዳታ በማድረግ ይተባበሩ። አቅም የሌላችሁ ደግሞ ይህን መልዕክት በማጋራት ወይም በጸሎታችሁ በማሰብ ድጋፋችሁን አሳዩ።
2.7K ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Открыть в Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

Слепок открытой публичной ленты из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог