ChatCrawlerпоиск по публичному Telegram Открыть приложение
A

ASTU Network Group ®

сообщение · 2026-07-30 11:47 UTC
I
Фотография
нажмите — покажем
ግብር ሊከፍሉ ነው‼️ በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነዉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዋስሁን በላይ ይህ ግብር በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ተሽከርካሪዎቹ በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ ስለሚንቀሳቀሱ በየዓመቱ የሚከፈል ይሆናል ብለዋል። ይህም ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ወይም ቦሎ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ እንደገለፁት ፣ ግብር አጣጣሉም እንደ ተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና እንደሚያመነጩት ጭስ (ካርቦን) ሊለያይ እንደሚችል ተናግረዋል። ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ፣ አዳዲሶች ደግሞ ዝቅተኛ እንዲከፍሉ ሊደረግ ይችላል ተብሏል። ይህ አሰራር በሌሎች አገራት ለምሳሌ በኬንያ፣ በሩዋንዳና በአውሮፓ አገራት የተለመደ ሲሆን፥መንግስት ለመንገድ ጥገና የሚውል ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ያስችለዋል። ግብሩ በከተሞችና በክልሎች የሚሰበሰብ በመሆኑ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸውን የልማት በጀት እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል ስለሚፈጥርላቸው በፌዴራል መንግስት ላይ ያለውን የገንዘብ ጫና ይቀንሳል። አቶ ዋሲሁን አክለዉም ዝርዝር ደንቦችና መመሪያዎች ወጥተውለት ወደ ተግባር እንደሚገባና የኢኮኖሚው የገቢ ምንጭ እንደሚሆን እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ከዚህ ግብር የሚገኘው ገቢ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 0.2 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ  ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። #አዩዘሀበሻ |➲| @ASTU_Network
2.1K ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Открыть в Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

Слепок открытой публичной ленты из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог