Фотография
нажмите — покажем
нажмите — покажем
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችና የሚያስተምሩ መምህራን ወደ ሌላ ዩኒቨርስቲ " ቀይሩን " የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ።
በትግራይ በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያማሩ አንዳንድ ተማሪዎችና መምህራን በክልሉ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ አቤቱታ እያቀረቡ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
ጥያቄው የቀረበው በክልሉ በሚገኙት ፦
- መቐለ ፣
- አክሱም ፣
- ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚያምሩ ተማሪዎች እና መምህራን መሆኑ ተመላክቷል።
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ሓየሎም ስዩም እንደገለጹት፤ ተማሪዎችና መምህራን በጸጥታ ምክንያት የቅሬታ ወረቀት እያስገቡ ቢሆንም፣ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እስካሁን የተሰጠ የዝውውር ውሳኔም ሆነ የተገባ ቃል አለመኖሩን አስታውቀዋል።
|➲| @ASTU_Network
313 ·