Веб-версияОткрыть в Telegram
AAddis Ababa City land Development And Administration Bureau

Addis Ababa City land Development And Administration Bureau

@AddisLand · канал · Новости · в индексе с 2026-09-30
5 466подписчиков
1 003средний охват поста
18.4%ER — охват к подписчикам
553постов за 30 дней
Emu Muluneh
Фотография
нажмите — покажем
ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ ***************** 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው። በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
536 ·
Фотография
нажмите — покажем
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
479 ·
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። #MedemerGovernment #PMOEthiopia
501 ·
Фотография
нажмите — покажем
"ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ አይኖራትም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
451 ·
Фотография
нажмите — покажем
አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ 7ኛውን ምርጫ በቀላሉ እንዳልመረጠ ጠቁመዋል። ነገር ግን ህልውናውን ለማጽናት ፈተናዎችን ሁሉ በጽናት አልፎ ውሳኔውን ማሳወቁን እና በዚህም ጠንካራ የመንግሥት ሥርዓት ለመሥራት የሚያስችል መሠረት መጣሉን ገልጸዋል። ዓለም በተለያየ መልኩ እየተቀያየረች እና አይገመቴነት በሰፈነበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ወሳኝ ሥራ መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ማንኛውም አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ዓለም በርካታ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን ሲያሳልፍ ለሀገራችን የደረሳት ትራፊው ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንደ ሀገር ቀድሞ ካለመዘጋጀት የሚመጣውን ችግር ለመቋቋም አሁናዊ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
469 ·
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ እና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል። በዲሞክራሲያዊ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል። እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደ ወንድማማች ስንጓዝ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዓለማችን በፍጥነትና በማይገመት ሁኔታ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መጪውን ዘመን በተጠንቀቅ መጠበቅ ትልቅ ምንዳ እንዳለው አስገንዝበዋል። ስለዚህም ለሀገር የሚበጀውን በጥበብ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቅ አደራ መሆኑን በንግግራቸው አስተላልፈዋል። ‎ ‎#MedemerGovernment ‎#PMOEthiopia
339 ·
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! ለመላው ሰላምና ልማት ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳንም ደስ አለን! የአለም የሰላም ሎሬት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልካም የሥራ ዘመን! ዛሬ የደስታ ቀን ብቻ ሳይሆን፣ የተስፋ፣ የድልና የኢትዮጵያን ስልጣኔ የመገንባት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው! ከብዙ ፈተናዎች በጽናት ተሻግረን፣ በጋራ ጥረታችንና በማይበገር አንድነታችን አዲስ የብልጽግና ጉዞ ጀምረናል። ዛሬ ከሁሉም በላይ የሚጠይቀን አንድነት ነው፤ የሚጠይቀንም ሰላም ነው። ልዩነታችንን እንደ ጥንካሬ፣ አንድነታችንን እንደ ኃይል እንጠቀም። የትኛውም ልዩነት ከኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት አይበልጥም! እጅ ለእጅ እንያያዝ፤ ልብ ለልብ እንቀራረብ፤ በሰላም እንደምር! በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሪነት፣ ለሀገራችን ሰላም፣ ሉዓላዊነት፣ ፍትሐዊነትና ሁለንተናዊ ብልጽግና በአንድነት እንቁም፤ እንተባበር፤ ተግተን እንሥራ! ሰላም መሠረታችን ነው፤ አንድነት ጉልበታችን ነው፤ ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት! ስንደመር ኃይላችን ይጨምራል፤ ስንተባበር እንቅፋቶች ይሰበራሉ፤ በአንድነት ስንቆም የኢትዮጵያ ታላቅነት ይገለጣል! ኢትዮጵያ ትበልጽጋለች! ኢትዮጵያ በሰላም ትጸናለች! ኢትዮጵያ በአንድነት ታሸንፋለች! 🇪🇹 ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ
277 ·
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
283 ·
‎ያለፉትን ስብራቶች መርምረን፣ በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው። ‎ ‎#የመደመርመንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
277 ·
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
290 ·
E
“ጥያቄው ታላቁን ርዕያችንን ማሳካት ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ አሁን ላይ የጀመረችው አዲስ የብልጽግና እና የስልጣኔ ጉዞ ባዶ ፉከራ ሳይሆን በመሬት ላይ በተጨባጭ የሚገለጥ የትውልድ ቃል ኪዳን መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋገጡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባላንጣዎች በተናጠል ተከፋፍለው ሊያጠቁ ሲከብዳቸው ለክፋትና ለሴራ ማበራቸውን በማስታወስ፤ አዲሱን የኢትዮጵያ ስልጣኔ የመገንባቱ ሂደት በመላው ሕዝብ ዘንድ ጽኑ እምነት የተጣለበት ታላቅ ሀገራዊ እውነት መሆኑን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በጽኑ መንፈስ ያበሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ “ጥያቄው ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል። አክለውም ትልቁ ፈተናና ዋነኛው ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ራዕዩን በምን መልኩና እንዴት አድርገን በተግባር እናሳካዋለን ለሚለው ስልታዊ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት ላይ መሆኑን አብራርተዋል። በመደመር እሳቤ ተጉዞ የታለመውን ሀገራዊ የከፍታ ማማ ለመጨበጥ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ እንደሌለ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለተቀመጠው ግብ መሳካት የሚያግዙ ቁልፍ መሣሪያዎችን በዝርዝር አመልክተዋል። በዚህም መሠረት እምቅ ሀገራዊ አቅሞችን በጥልቀት መረዳት፣ የአካሄድ ስልቶችን ከግብርና ከንባብ ጋር ማጣጣም፣ ከዓለም አቀፍ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ወስዶ ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማስማማት፣ በብሔራዊ አንድነት ላይ ጸንቶ መቆም፣ የቡድን እና የግል መብቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እንዲሁም ጠንካራ ሲቪክ ማንነትን ገንብቶ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳርን በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ ማጽናት ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በመንግሥትና በሕዝብ የማይበገር አብሮነትና በጽናት የያዘችውን የብልጽግና ርዕይ ከዳር በማድረስ፣ የነገዋን የበለጸገችና ሉዓላዊ ክብሯ የተጠበቀ ታላቅ ሀገር ለትውልድ ማውረሷ የማይቀር ታሪካዊ እውነታ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ አስታውቀዋል። #ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
344 ·

Открытая публичная лента из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог · Поиск · Как мы считаем