Русский
Открыть в Telegram
BBiT SU Official Information Group

BiT SU Official Information Group

@BiTSUGP · группа · в индексе с 05.10.2026
1 958участников
70пишущих за 30 дней
140сообщений за 30 дней
8 894сообщений в индексе
F
ኢ
‎በነገራችን ላይ ... ‎ ‎አንቺ ሀገሬ ኢትዮጵያ እስኪ ልጠይቅሽ? ‎ ‎ስጋት በማይገባቸው እድሜ ሕይወታችን በስጋት የተሞላን፤ ለጋ እድሜያችን ከአንድ የጦርነት እሳት ወደሌላ የጦርነት እሳት የሚደረግ ሽግግር የሆነብን፤ ዙሪያ ገባችን በዘረኝነት ጨቅይቶ ሀገራዊነትን እንዳንማር እየተከለከልን ያለን፤ አለምን በማወቂያ እድሜያችን የብሔር ቀኖና የተደነገገብን፤ ይሄ ነው የሚባል ሞዴልና ይሄ ነው የሚባል ፍኖት በሌለበት የህይወት ዓላማ ለመጨበጥ የምንባዝን፤ ትምህርታችንም ዘመናችንም የለብ ለብ የሆነብን፤ በእውቀት ማትጊያ እድሜያችን  "ተምሬስ ወዴት?" የሚል ጥያቄ እንድንጠይቅ የተገደድን፤ ምሳሌ የምናደርጋቸው ተቋማትና መሪዎች ያጣን፤ ትምህርታቸውን ተገደው ያቋረጡ፤ የተስፋ ክንፋችን የተመታ፤ ለሁሉ ነገር አቋራጭ የምናሰላ፤ አንቺን እየወደድን ግን ለመሽሽ ስኮላር የምናፈላልግ፣ ዲቪ የምንማፀን፤  ...  ‎ወጣት ልጆችሽን ስታይ ምን ይሰማሻል? ‎ ‎ ‎በሀገር መሪው (ጠ/ሚ) ሳይቀር  እንኳን በወንድ አካል በመሳሪያም መደፈር አለ እየተባለ የሚዘበትባቸውን፤ በወላጆቻቸው ማደጋቸው የሚፈራላቸው፤ በዚህ በተሻሻለ ዓለም ፊት ብዙ ያላቀበልሻቸው፤ ኮሽ ባለ ቁጥር ገላቸው ጠላታቸው፤ ማደጋቸው እዳቸው የሆንባቸው፤ ከነሱ ያነሰ ትምህርት ባለው ሰው የሚናቁ፤ መሻሻላቸውን ለመግታት ማህበራዊ ኬላ በየቦታው የተተከለባቸውን ... ‎ሴት ልጆችሽን  ስታይስ ምን ይሰማሻል? ‎ ‎ሆኖ የማያውቀው ሲሆን በኑሮ ውድነቱ የተቀቀለው ህዝብሽ ግብር የሚከፍለው አጥቶ ተበድሮ ግብር ሲከፍል ስታይ ምን ተሰማሽ? ‎ ‎ ‎ደካማ ሕዝብ ->  ክፋትን የማስቀረት ፍላጎት አለው ግን አቅሙ የለውም። ‎ክፉና ዳተኛ ሕዝብ -> ክፋትን የማስቀረት አቅም አለው ግን ፍላጎቱ የለውም። ‎ሠይጣናዊ ሕዝብ -> ጉልበቱንና አቅሙን ሁሉ የሚያውለው ክፋቶችን እየፈጠረ ለመዝራትና ለማባዛት ነው። ‎ነፃና የነቃ ሕዝብ -> ክፋትን የማስቀረት ፍላጎቱም አቅሙም አለው። በመሆኑም ክፋት ሊፈፀም የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው። ‎ይባላል። ‎ ‎አንቺ ሀገሬ ታዲያ እኛ የትኛውን ሕዝብ ሆነን ነው ይሄ የምታይው ሁሉ ዶፍ የወረደው? ‎
❤1
𝐌
ዶላር መግዛት ሆነ መሸጥ ለምትፈልጉ ሁሉ እኛ ጋ ያገኛሉ... etb/usdt rate ~~~ በስምምነት ለበለጠ መረጃ DM ማድረግ ይቻላል... ከ 300$ በላይ ለምትፈልጉ በአካል መገናኘት እንችላለን Pis👍
❤1👍1
  1. C
    ችግር level up 🫢
    😁2❤1
Вся ветка · 3 ответа →
V
hiwot Asrat የሚል ID ከ ቤተክርስትያን ስትመለሱ ያገኛችሁ Dm adrgu please

Открытая публичная лента из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Границы индекса · Убрать страницу из выдачи · Каталог · Поиск · Как мы считаем