Веб-версияОткрыть в Telegram

Постለአይነ ስውራን የቀረበ ዘመናዊ መሪ ወይም ኬን

13 августа 2022
C
Code-it Labs (Gemechis)
Фотография
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
ለአይነ ስውራን የቀረበ ዘመናዊ መሪ ወይም ኬን **** ተመራማሪዎች የእይታ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በእንቅስቃሴ የሚያግዝ ዘመናዊ ዘንግ ወይም ኬን ሰርተው አቀረቡ፡፡ በተለምዶ ነጩ ምርኩዝ በመባል የሚታወቀው ይህ አይነስውራን ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀሙበት ዘንግ ተጠቃሚዎቹ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ የተሸለ ቀላል እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ መደበኛው ዘንግ ከመሬት ጋር ሲጋጭ የሚኖረውን ድምጽ በመከተል አንድ አይነስውር በቀላሉ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡ ሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ይህንን መደበኛ ዘንግ እጅግ በማሻሻል አይነ ስውራን ከደህንነት ስጋት ነጻ ሆነው እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ በሚያስችል መልክ የሮቦት ቴክኖሎጂ አክሎበት ማቅረቡ ተነግሯል፡፡ ከራስ ነድ መኪኖች ቴክኖሎጂ ጋር ተጣምሮ የተሰራው ይህ ዘንግ በ400 ዶላር የቀረበ ሲሆን ተጠቃሚዎች እንደሚኖሩበትና እንደሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ምቹ የሆነ ድጋፍን የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡ ስማርት ዘንጉ በመንገድ ላይ ወይም በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ እንቅፋቶችን በመለየት በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ለመንቀሳቀስ ምቹ የሆኑ ቦታወችን በመምረጥ መጓዝ የሚያስችል ነው፡፡ በዘርፉ ሌሎች ሴንሰር የተገጠመላቸው መሪ ዘንጎች ያሉ ቢሆንም ከአጠቃላይ ክብደታቸው እና ከሚያወጡት ዋጋ አንጻር ተፈላጊነታቸው አነስተኛ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከቴክኖሎጂ አንጻር እጥረት ያለባቸው በመሆኑ ማለትም ሴንሰሩ ከተጠቃሚው ፊት ለፊት ያለን ነገር ብቻ የሚያሳውቅ በመሆኑ ይህ ተሻሽሎ የቀረበው መሪ ዘንግ እጅግ ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ #Daily_Tech_News ▬▭▬▭▬▭▬▭ Follow us: YouTube,  Telegram,  Tiktok @innovate_aastu @innovate_aastu
593 ·

Рядом в ленте

CCode-it Labs (Gemechis)የምስራች 🎉 የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡ #GERDCCode-it Labs (Gemechis)Фотография
это сообщение
CCode-it Labs (Gemechis)ОпросCCode-it Labs (Gemechis)ጥናት ላይ ላላችሁም፣ ለሌሎቻችሁም መሳጭ 😊 የጃዝ Instrumental Music ተጋበዙልን። #DawitGetachew #Jazz #Study #Focus @innovate_aastu @innovate_aastu
CCode-it Labs (Gemechis)Code-it Labs (Gemechis)@codeitlab · канал · Технологии
2 147подписчиков126постов в индексе
Лента площадки Открыть в Telegram

Открытая публичная лента из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог · Поиск · Как мы считаем