30 июля 2026
31 июля 2026
1 августа 2026
5 августа 2026
Видео
shoaa.mp4 · 42.4 МБ · нажмите — покажем
shoaa.mp4 · 42.4 МБ · нажмите — покажем
🎉 የክረምት ትልቅ ዜና! 🎉
ልጆቻችሁ በዚህ ክረምት ኮከብ ተማሪ ላይ እየተማሩ እና እየተጫወቱ ከሆነ፣ ከሸዋ ሾፒንግ ሴንተር በልጆች ዕቃዎች ላይ 30% ቅናሽ ያገኛሉ! 🎒✏️📚
📲 ኮከብ ተማሪን አሁኑኑ ከPlay Store ያውርዱ ወይም በ kokeb.et ይጎብኙ።
📱 የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን፣ ሽልማቶችን እና አዳዲስ ዝግጅቶችን ለማግኘት በ:
TikTok: https://www.tiktok.com/@kokebtemari?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Facebook: https://www.facebook.com/share/1B8qy7RXH8/?mibextid=wwXIfr
Playstore 🔗 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.kokebtemari.app
⭐️ ተማር፣ ተጫወት፣ ኮይኖችን በመሰብስብ፣ ሽልማትና ቅናሽ አግኝ!
10 августа 2026
15 августа 2026
17 августа 2026
እንደምን አደራችሁ
1. በቀን 07/12/2018ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤት የተሠሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በቅድመ1ኛ ፣ በ1ኛ ደረጃ እና በ2ኛ ደረጃ የተሠሩ ሥራዎችን መረጃ በመሰብሰባ እስከ ሰኞ ጠዋት 4፡00 ድረስ በላክነው ቅፅ መሠረት ቅፁን ሳትቀይሩ እንድትልኩ በማለት መልዕክት ማስተላለፋችን ይታወቃል፡፡ ስለዚህ አሁን በድጋሚ ይህን ለማስታውስ ዛሬ ሰኞ በቀን 11/12/2018ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ እንድትልኩ በማለት እንገልፃለን፡፡
2. የተማሪ የደንብ ልብስ ጋርመንቶች ይዘው በሚመጡበት ጊዜ የልብሱን የጥራት ሁኔታ በመመልከት በተጨማሪ በእያንዳንዱ የተማሪ ሹራብ ሎጎ የት/ቤቱ ስም መኖሩን በማረጋገጥ ርክክብ እንድትፈፅሙ በማለት በጥብቅ እያሳሰብን ለሚያጋጥማችሁ ማንኛውም ችግር ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በመደወል ከትምህርት ቢሮ ጋር በመገኛኘት መፍትሄ እንዲሰጣው ለማድረግ የመንችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በተጨማሪ የተረከባችሁትን የተማሪ የደንብ ልብስ ከ9፡00 በፊት በየዕለቱ በቅፁ መሠረት ሪፖርት እንድታደርጉ፡፡
18 августа 2026
22 августа 2026
አላስፈላጊ ሊንክ አትክፈቱ ዲጂታል ደህንነትን (Cybersecurity) ለመጠበቅ እና ከሳይበር ጥቃት፣ ከቫይረስ (Malware) ወይም ከግል መረጃ መስረቅ (Phishing) ለመጠበቅ አላስፈላጊና አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት በጣም ወሳኝ እርምጃ ነው።ሊንክ ከ መክፈትዎ በፊት ሊወስዷቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች፦ላኪውን ያረጋግጡ፦ መልእክቱ ወይም ሊንኩ የደረሰዎት ከማያውቁት ሰው ከሆነ ወይም ከሚያውቁት ሰው ሆኖ ነገር ግን ያልተለመደ መልእክት ከሆነ ሊንኩን አይክፈቱ።የሊንኩን አድራሻ (URL) በጥንቃቄ ይመልከቱ፦ ሊንኩን ከመንካታችሁ በፊት ሙሉ አድራሻውን ያንብቡ። ለምሳሌ እውነተኛ ድህረ ገጽ የሚመስሉ ነገር ግን የፊደል ስህተት ያለባቸውን (ምሳሌ፡ goog1e.com ይልቁንም google.com) አስተውሉ::ሚስጥራዊ መረጃ ከሚጠይቁ ሊንኮች ይጠንቀቁ፦ የባንክ መረጃ፣ የይለፍ ቃል (Password) ወይም የግል መረጃ እንድታስገቡ የሚጠይቁ ያልተረጋገጡ ሊንኮችን በፍጹም አትክፈቱ።የሽልማት እና የነፃ ስጦታ ማስታወቂያዎች፦ "እንኳን ደስ አለዎት፣ ይህን ሊንክ ተጭነው አሁኑኑ ተሸላሚ ይሁኑ" የሚሉ የሐሰት መልእክቶችን በፍጹም አትመኑ።የመከላከያ ሶፍትዌር ይጠቀሙ፦ በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ ላይ አፕዴት የተደረገ አንቲቫይረስ (Antivirus) እና ብራውዘር ሴኪዩሪቲ መጠቀም አጠራጣሪ ሊንኮችን ለመለየት ይረዳል።በተለይ በኢሜይል፣ በቴሌግራም ወይም በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚላኩ ያልተረጋገጡ ሊንኮችን አለመክፈት መረጃዎንና መሳሪያዎን ከአደጋ ለመጠበቅ የመጀመሪያው መከላከያ ነው
23 августа 2026
25 августа 2026
Фотография
нажмите — покажем
нажмите — покажем
Фотография
нажмите — покажем
нажмите — покажем
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም
26 августа 2026
27 августа 2026