Фотография
нажмите — покажем
нажмите — покажем
#12_ክፍል_AAU
#ScholarshipOpportunity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን የሚተገበር #የመምህራን_ትምህርት ነጻ የትምህርት ዕድል ፕሮግራም (Teachers Education Scholarship Program) ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ ዕድል በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ፣ ብቁ እና ተነሳሽነት ያላቸው 500 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡
ነጻ የትምህርት ዕድሉ የአምስት ዓመት የተቀናጀ ፕሮግራም ሲሆን፤ በማስተማር የመጀመሪያ ዲግሪ እና የሁለተኛ ዲግሪ ብቃት በተለያዩ መስኮች ማለትም በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በማኅበራዊ ሳንስ እና በቋንቋዎች እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡
ነጻ የትምህርት ዕድሉ ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን እንዲሁም ጥሩ የሚባል የማበረታቻ ጥቅል (የኑሮ እና የትምህርት ወጪዎች) ያስገኛል፡፡
የዚህ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ቢያንስ ለአምስት ዓመት ለማገልገል የስምምነት ውል ይፈርማሉ፡፡
ለማመልከት 👇
https://admission.aau.edu.et/UGAnnouncements
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 09/2018 ዓ.ም
(የመምህራን ትምህርት ነጻ የትምህርት ዕድሉ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)
@alluexams
2 · 241 ·