ChatCrawlerпоиск по публичному Telegram Открыть приложение
E

ESS Study Tips Group

сообщение · 2026-08-22 17:01 UTC
I
Фотография
нажмите — покажем
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ   ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ። በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ ተመዝግቧል። ----------------------------- // ------------------------------- ‎ ‎(ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ   ወይም 70, 544 ተማሪዎች 50% እና በላይ ወጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል። ‎ ‎ባለፈው ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 8.9 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የማለፊያውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ20 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ‎ ‎በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆኑንም ተናግረዋል። ‎ ‎በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በወንድ  ፤ 583.03  በሴት  ሆኖ የተመዘገበ  መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 576.25 በሴት 569.17 ሆኖ መመዝገቡን አብራርተዋል። ‎ ‎ በዚህ ዓመት ተማሪዎችን ካስፈተኑ ት/ቤቶች መካከል 88 ት/ቤቶች 100% ተማሪዎቻቸውን ማሳለፋቸውን እና 565 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ተናግረው ከባለፈው ዓመት ምንም ካላሳለፉ 1232 ት/ቤቶች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል።
617 ·

Все сообщения за 22 августа 2026 · Вся лента · оригинал в Telegram

Открыть в Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

Слепок открытой публичной ленты из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог