Веб-версияОткрыть в Telegram

Постኬንያ የኮምፒውተር ቋንቋን (Coding) በትምህርት ሥርዓቷ ውስጥ በማካተት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች።

11 августа 2022
C
Code-it Labs (Gemechis)
Фотография
нажмите — покажем
ኬንያ የኮምፒውተር ቋንቋን (Coding) በትምህርት ሥርዓቷ ውስጥ በማካተት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች። ኬንያ በአንደኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቿ የኮምፒውተር ቋንቋ (Coding) በስርዓተ ትምህርቶቿ ውስጥ በማካተት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከዚህ ውሳኔ ሀገሪቱ ብዙ ተጠቃሚ እንደምትሆን በርካቶች እየመሰከሩ ነው። በተጨማሪም ሀገሪቱ ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ስትራቴጂ 2022 ያዘጋጀች ሲሆን እስከ 2032 ይቆያል የተባለው የኬንያ ብሄራዊ ዲጂታል ማስተር ፕላንም ተመርቋል። ይህን አስመልክቶ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የስልጣን ዘመናቸው የሚያበቃው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ብሄራዊ ዲጂታል ማስተር ፕላኑ የስራ እድል ፈጠራን እንደሚያሳድግ፤ የአይሲቲ ሴክተሩ የሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፍ እድገት እንደሚያሳድግ ጥርጥር የለውም ሲሉ ተናግረዋል። የዲጂታል ማስተር ፕላኑ በመላ ሀገሪቱ ከ20,000 በላይ መንደሮች የዲጂታል ማዕከላትን የማቋቋም ግብ ያስቀመጠ ሲሆን 40,000 ወጣቶችን በመቅጠርም ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች እንዲያሰለጥኑ እንደሚደረግም ይገልጻል። ኬንያ በአህጉሪቱ ለዲጂታል ፈጠራዎችና ለዘርፉ ዋነኛ ቦታ መሆኗን ለማስመስከር ጥረቷን ቀጥላለች። ይህንን በሥርዓተ ትምህርቷ መደገፏም የዚህ ትልቅ ማሳያ ነው። በዚህ ዓመት ብቻ ማይክሮሶፍት፣ ቪዛ እና ጎግል በሀገሪቱ ዋና ከተማ የመጀመሪያ የልማት ማዕከላቸውን ከፍተዋል። @innovate_aastu
380 ·

Рядом в ленте

CCode-it Labs (Gemechis)Back to Moon\ ጉዞ ወደ ጨረቃ ================= ናሳ መጪውን ሰው አልባ የአርጤምስ I የጨረቃ ተልእኮ በተመለከተ እሮብ፣ ኦገስት 3 እና አርብ ኦገስት 5 አጭር መግለጫዎችን ያቀርባል። ኤጀንሲው በአሁኑ ጊዜ ከሰኞ ኦገስት 29 ባልበለጠ CCode-it Labs (Gemechis)An incredible high-quality image was taken recently by NASA on Mars. The image is so cristal you can analyze every rock, and even the hole drill that curiosity
это сообщение
CCode-it Labs (Gemechis)ውቅያኖስ ጠላቂው ሮቦት በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ኦሽን ዋን ኬ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰው መሰል ሮቦት የሰጠሙ የመርከብ ፍርስራሽ እና ሌሎች አካላትን ለማሰስ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ሮቦቱ አምስት መቶ ሜትር ድረስ በመጥለቅ በውሃ አካላቱ CCode-it Labs (Gemechis)የምስራች 🎉 የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡ #GERD
CCode-it Labs (Gemechis)Code-it Labs (Gemechis)@codeitlab · канал · Технологии
2 147подписчиков126постов в индексе
Лента площадки Открыть в Telegram

Открытая публичная лента из поискового индекса ChatCrawler — «Google по публичному Telegram»; обновляется по мере обхода площадки. Время — UTC.

Только публичный контент, официальный API Telegram. О проекте · Вопросы · Чего мы не делаем · Убрать страницу из выдачи · Каталог · Поиск · Как мы считаем