Zeynu 🖤
መውሊድን ማክበር ዒባዳ ነውን❓❗
መልሱ "ኣዎ" ከሆነ:-
ታላቁ ሰሓቢይ ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ
🔸( "ማንኛውም የነቢዩ صلى الله عليه وسلم ባልደረቦች ያልሰሩትን ዒባዳ አትስሩ እነሱ ከኋላ የሚመጡ ሰዎች ይስሩት ብለው የተውት ነገር ምንም የለም!") ብለዋል።
🔸መውሊድ ዒባዳ አይደለም ከተባለ ደግሞ፥ ዒባዳ ያልሆነ ነገር ወደ አላህ ሊያቃርብ ምንዳን ሊያሰጥ አይችልም! ስለዚህ አክባሪዎች ስራቸው ከንቱ ልፋትና ሞኝነት ነው!
🔸ወገኖቼ ሆይ፥ ዲን በስሜትና በእልህ አይደለም ስንትና ስንት በዲኑ የተደነገጉ ነገሮችን ትታችሁ ያልተደነገገውን አትስሩ ከነቢዩ ጋር ትጣላላችሁ!
⭕የብዙ መውሊድ አክባሪዎች ሁኔታ ሲታይ ምናልባትም መውሊድ በዲኑ ተደንግጎ ቢሆን አያከብሩትም ነበር!
🔖እኔ ነቢዬን የምወደው ሱናቸውን በመከተል እንጂ ዲናቸው ላይ አዲስን ነገር በመለጠፍ አይደለም❗
✍ ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
12/31439 ዓ. ሂ
57 ·