ቁጥጥር ክፍል
Ссылка
click to show
click to show
ሱባኤ እስር ነው
ሱባኤ ተፈጸመ ማለት ወደ ቀደመ ኑሮ መመለስ አይደለም ክርስትና ማለት በኖሩበት መቀጠል ማለት ነው እንደተማሩ መኖር ያነበቡትን የተማሩትን መኖር ነው።
ሱባኤ/ጾም/ ገንዘብ እንደመሰብሰብ ሥራ እንደመስራት ነው ሰው ለዘመናት የለፋበትን ለወራት እንቅልፍ አጥቶ የሰበሰበውን ገንዘብ በአንድ ቀን ከበተነው ይሄ ሰው ሞኝ ነው ለክርስቲያንም ጾም መጾም ሱባኤ ገብቶ መሰንበት ገንዘብ እንደመሰብሰብ አብዝቶ እንደመትጋት ነው ጾሙ ሲፈሰክ ጠብቆ ግን በዓለም መጥፋት ሰርቶ ሰርቶ ገንዘብን እንደመበተን ነው።
ሱባኤ መግባት ጾም መጾም እንደ ገበሬ መልፋት መጣር ነው በጭቃ ወድቆ በአፈር ተለውሶ ለወራት ያህል ጠብቆ ከአዕዋፍ ከእንስሳት ጠብቆ ያተረፈውን እህል በአንድ ቀን ካጠፋው ገበሬው ሞኝ ነው ክርስቲያንም የጾሙ ወቅት እንደዚህ ነው ጾሙን በፈሰከ ዕለት ግን በዓለም ግብር ተውጦ በጭፈራ በዳንኪራ ማሳለፍ የለበትም በረከቱን ከእርሱ ጋር መጠበቅ አለበት።
በጥቅሉ ጾም እስራት አይደለም ፋሲካው ሲደርስ ከእስራት እንደተፈታ ሰው ሁሉን መሞከር መልካም አይደለም ጾማችን በረከት ነው በጾሙ ያገኘነው በረከት ከእኛ ጋር መሰንበት አለበን እመቤታችን ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ሱባኤያችንን ሲፈጸመ ጾማችን ሲያልቅ በቤቱ ማክበር አለብን እንጂ እንደ አሕዛብ አብዝቶ በመብላት እና በስካር ሳይሆን ማክበር የለብንም።
https://t.me/saintgebreal
61 ·