CodeForge Ethiopia
💸 ድሃ ለመሆን የሚረዱ 12 አስደናቂ መንገዶች 😂
1️⃣ ችግርህ እስኪቀሰቅስህ ድረስ ተኛ።
2️⃣ መጀመሪያ ገንዘብህን አጥፋ፤ በኋላ አስብ፤ መጨረሻ ላይ ኢኮኖሚውን ውቀስ።
3️⃣ የማይወዱህን ሰዎች ለማስደነቅ ውድ ዕቃዎችን ግዛ።
4️⃣ ቲክቶክ ላይ አምስት ሰዓት አሳልፈህ፣ “ምንም ጊዜ የለኝም!” በል።
5️⃣ ገንዘብ የሚያስገኝ ሙያ በጮራሽ እንዳትማር፤ አደገኛ ነው—ሕይወትህን ሊቀይርብህ ይችላል!
6️⃣ መነሳሳት እስኪመጣ ጠብቅ። ድንገት መብረቅ ወርዶ የሥራ ፍላጎት እስኪሰጥህ ድረስ አትንቀሳቀስ። ⚡
7️⃣ 20 ፕሮጀክቶችን ጀምር፤ አንዱንም እንዳትጨርስ!
8️⃣ ከስኬታማ ሰዎች ራቅ፤ ሥርዓትና ትጋታቸው እንዳይጋባብህ።
9️⃣ ገንዘብ ባገኘህ ቁጥር ሁሉንም አጥፋ። ቁጠባ ለአሰልቺ ሰዎች ነው!
🔟 ወላጆችህን፣ መንግሥትን፣ ጓደኞችህን፣ የአየር ሁኔታውን—ከራስህ በስተቀር ሁሉንሞ ውቀስ።
1️⃣1️⃣ ትንንሽ ዕድሎችን ናቅ፤ መጠበቅ ያለብህ ትልቅ እደል ብቻ ነው::
1️⃣2️⃣ “ሰኞ እጀምራለሁ” ማለትህን ቀጥል። የትኛው ሰኞ እንደሆነ ግን እንዳትናገር!
እነዚህን ምክሮች በትጋት ተከተል፤ እንኳን ደስ አለህ—የድሆች ባንዲራ ያዠ ሆነሃል! 🏆😂
የተለየ ሕይወት ከፈለግህ ግን ከላይ ያሉትን ሁሉ በተቃራኒው አድርግ።
ተማር። ሥራ። ቆጥብ። ገንባ። የጀመርከውንም ጨርስ!
1 · 138 ·