Web appOpen in Telegram

Postበአንድ ወቅት አንዲት የሒሳብ መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦

14 September 2026
C
CodeForge Ethiopia
በአንድ ወቅት አንዲት የሒሳብ መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦ 9×1= 7 9×2= 18 9×3= 27 9×4= 36 9×5= 45 9×6= 54 9×7= 63 9×8= 72 9×9= 81 9×10= 90 ጽፋ እንደጨረሰችም ወደ ተማሪዎቿ ዞራ ስትመለከት ሁሉም እየሳቁባት ነው፣ የመጀመሪያውን እኩልታ (equation) ተሳስታለችና። ይህን ጊዜ መምህርቷ እንዲህ አለች፦ "የመጀመሪያውን ስህተት የጻፍኩት በዐላማ ነው፤ ከነገሩ ጠቃሚ ትምህርትን እንድትወስዱ ስለፈለኩኝ። ይኸውም፥ በውጪ ያለው ዓለም እንዴት እንደሚቀበላችሁ ታውቁ ዘንድ ነው። 9 ጊዜ ትክክለኛ ነገር እንደጻፍኩ ማየት ትችላላችሁ ይሁንና አንዳችሁም ስለዛ አላበረታታችሁኝም፤ ነገር ግን ሁላችሁም ስለ ሠራሁት አንድ ስህተት ሳቃችሁብኝ፣ ነቀፋችሁኝም። ትምህርቱም ይህ ነው፤ • ዓለሙ፥ ሚሊዮን መልካም ሥራን ብትሠሩ አያበረታታችሁም ግን አንድ የሠራችሁትን ስህተት ይዞ ይነቅፋችኋል። በዚህ ግን ተስፋ ልትቆርጡ አይገባም። ሁልጊዜም ቢሆን ከሳቅና ከነቀፋ በላይ ወጥታችሁ ቁሙ፣ ጽኑ፣ በርቱም!" ልብ በል፤ • መሳሳትን ከፈራህ መሞከር አትችልም፤ መሳሳት ያንተ መጨረሻ አይደለም የማወቅ መነሻ እንጂ። • ምናልባት የተማርከውን ትረሳ ይሆናል፣ የተሳሳትከውን ግን አትረሳም። • ከብዙዎች የስንፍና ፍፁምነት ይልቅ ያንተ የመሥራት ስህተት እንደሚሻል አስብ። • ከመሳሳትህ በላይ ሰው ምን ይለኛል?  የሚለው ነገር ያስጨንቅህ ይሆናል፤ ሰው ግን እንዳንተው የሚሳሳት መሆኑን አትርሳ። ኖረህ ስላልጨረስክ እንኳንም ተሳሳትክ!፤ ስህተትህ ላይ ከዘገየህ ብዙ ነገሮች ያልፉሃል፣ በቶሎ ከተማርክ ግን አዲስ ነገር ታውቃለህ፣ ትሠራለህም!!
1 · 71 ·

Nearby in the feed

CCodeForge EthiopiaHow to win at life: - Step 1: Commit to doing a hard thing. - Step 2: Do the hard thing. - Step 3: Feel good about doing the hard thing. - Step 4: Become someonCCodeForge EthiopiaIt’s scientifically proven that when the brain is stressed, the creative center in the brain shuts down.
this message
CCodeForge EthiopiaTo put it simply, success comes from discipline and consistency .CCodeForge EthiopiaLife is full of challenges, but every challenge is an opportunity to become stronger. 💪 Sometimes the road will be difficult. Sometimes you will fail, feel tire
CCodeForge EthiopiaCodeForge Ethiopia@freewebdevelopcourse · channel · Tech
190subscribers92average post reach
Venue feed Open in Telegram

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count