ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ethioicons_discuss

113 members
17 August 2026
18 August 2026
11 September 2026
12 September 2026
13 September 2026
Ссылка
click to show
በመቅደላ ጦርነት የተወሰደውና የአጼ ቴዎድሮስ ሊሆን የሚችል መጽሐፍ ቅዱስ በ47.5 ሚሊዮን ብር ለሽያጭ ቀረበ #Ethiopia | በ1868 ዓ.ም. በመቅደላ ዘመቻ ወቅት ከኢትዮጵያ ተወስዶ እንደነበር የሚገመተውና የአጼ ቴዎድሮስ ዳግማዊ መጽሐፍ ቅዱስ ሊሆን እንደሚችል የሚታመን ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ቅዱስ በ47.5 ሚሊዮን ብር ወይም 250 ሺህ ዩሮ ለሽያጭ ቀርቧል። መጽሐፉ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአቡ ዳቢ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተገልጿል። በግዕዝ ቋንቋ በብራና ላይ የተጻፈው ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ የሉቃስን ወንጌል ሙሉ በሙሉ የያዘ ሲሆን፣ የዮሐንስ ወንጌልንም ከመጨረሻዎቹ 16 ጥቅሶች በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደያዘ ተገልጿል። መጽሐፉ በ1730–1740 ዓ.ም. አካባቢ በጎንደር ውስጥ የተጻፈ እንደሆነ የተገመተ ሲሆን፣ ተአምራትንና የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚያሳዩ 235 ሥዕሎችን እንደያዘ ታውቋል። በተለያዩ ዲዛይኖች የተሠራ የቆዳ ሽፋንም እንዳለው ተገልጿል። ዋና መቀመጫውን ኦስትሪያ ያደረገው “ኢንሊብሪስ” (Inlibris) የተባለ በተለይ ጥንታዊ መጻሕፍትን የሚሰበስብና የሚሸጥ ተቋም ነው መጽሐፉን በአቡ ዳቢ ለሽያጭ ያቀረበው። የኢትዮጵያ ቅርሶችን በማጥናትና የተወሰዱ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ በመሥራት የሚታወቁት ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት፣ መጽሐፉ በመቅደላ ዘመቻ ወቅት በእንግሊዝ ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል ሮበርት ናፒር ከኢትዮጵያ ተወስዶ እንደነበር ገልጸዋል። ከዚያም መጽሐፉ በወቅቱ በሕንድ የእንግሊዝ ግዛት ከፍተኛ አዛዥ ለነበረ አካል በስጦታ መሰጠቱን እና በቀጣዮቹ 158 ዓመታት ውስጥ ከአንድ ሙዚየም ወደ ሌላ፣ እንዲሁም ከአንድ ግለሰብ ወደ ሌላ በሽያጭ ሲተላለፍ መቆየቱን አስረድተዋል። ዶ/ር አሉላ እንደሚሉት፣ ከኢትዮጵያ በጦርነት ወቅት የተወሰደ ቅርስ በአሁኑ ወቅት ለግል ሽያጭ መቅረብ የለበትም የሚል ጠንካራ የሞራል መከራከሪያ አለ። በዚህም መሠረት መጽሐፉ ለግል ስብስብ ከመሸጡ በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል። ቅርሱ ከኢትዮጵያ መወሰዱና አሁን ለሽያጭ መቅረቡ በሚዲያና በዲፕሎማሲ በኩል ጫና ከተፈጠረ፣ ግለሰቦችም ሆኑ ሙዚየሞች መጽሐፉን ለመግዛት እንደማይደፍሩ ተመራማሪው ገልጸዋል። የሽያጩን ሂደት ለማስቆም ከኦስትሪያና ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር በዲፕሎማሲ በኩል መነጋገር እንደሚያስፈልግም ዶ/ር አሉላ አመልክተዋል። “ዘመኑ ተለውጧል፤ ስለ ቅርሶች መመለስ ያለው እይታም ተቀይሯል” ያሉት ዶ/ር አሉላ፣ ኢንሊብሪስ ሽያጩን በማቆም ይህ ድንቅ የብራና ጽሑፍ ወደ ሌላ የግል ስብስብ ገብቶ ከሕዝብ ዕይታ ከመሰወሩ በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለሕዝብ እይታ እንዲበቃ ጥረት መደረግ እንዳለበት ጠይቀዋል። ለመጽሐፉ መመለስ የሚደረገው ጥረት አንድ ሳምንት ብቻ የጊዜ ገደብ እንዳለው የገለጹት ዶ/ር አሉላ፣ ቅርሱ ከተቻለ በነፃ፣ ካልሆነም ለሽያጭ ከቀረበበት ዝቅተኛ ዋጋ ተገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ሁሉም የሚችለውን ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። https://share.google/vNjXzJPAx9Hghu0rT
1.1K ·
15 September 2026
I
ሰላም እንዴት ናችሁ? ቅዱሳን ስዕላትን የመስራት ፍላጎት አለኝ። እናም እንዴት መጀመር እንዳለብኝ መንፈሳዊ አስተምህሮ ብትለግሱኝ ደስ ይለኛል
16 September 2026
17 September 2026
እ
ቅድስት ስላሴ በመንበረ ክብራቸው እና 12ቱ ሐዋርያት በ12ቱ ነገደ እስራኤል ላይ እንደሚፈርዱ የማያሳይ ይመስላል ...
18 September 2026
I
Фотография
click to show
እንኳን ለነቢያት አለቃ ቅዱስ ሙሴ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ። ከቅዱሳን ወገን በጣም የምወደው እና ሥዕሉን በሣልንበት ወቅት ከፍተኛ ሀሴት የተሰማኝ ነቢይ በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን። በተለይ ይኸኛውን ሥዕል በሁለተኛ ደረጃ ልገልጸው የማልችል ትልቅ ደስታ ይሰማኝ ነበር ከጅማሮ ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ስንሥለው። እስቲ ከስር በዚህ ሥዕል ላይ የምትመለከቱት ከቅዱስ ሙሴ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ምን እንደሆነ አስተያየት ላይ አስቀምጡ።
432 ·
E
K
B
19 September 2026
H
id 1399055988እንኳን ለነቢያት አለቃ ቅዱስ ሙሴ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ። ከቅዱሳን ወገን በጣም የምወደው እና ሥዕሉን በሣልንበት ወቅት ከፍተኛ ሀሴት የተሰማኝ ነቢይ በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን። በተለይ ይኸኛውን ሥዕል በሁለተኛ ደረጃ ልገልጸው የማልችል ትልቅ ደስታ ይሰማኝ ነበር ከጅማሮ ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ስንሥለው። እስቲ ከስር በዚህ ሥዕል ላይ የምትመለከቱት ከቅዱስ ሙሴ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ምን እንደሆነ አስተያየት ላይ አስቀምጡ።
ወንድሞቼ ካልጠቀሷቸው ውስጥ 👉 አንደኛወ ደግሞ ህዝበ እራኤል ውሃን በተጠሙ ጊዜ ሊቀ ነብያት ቅዱስ ሙሴ አለቱን በበትሩ ቢመታው ውሃ እንደፈለቀላቸው የሚያሳይ ነው። 👉 ሁለተኛው ደግሞ ለረጅም ዘመን ደርቃ የነበረችው ቅዱስ አሮን ከአባቶቹ የተቀበላት በትር ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማመልከት ከብዙ ሰዎች በትር ተለይታ አብባ መገኝቷን። አንድም ነገረ ስጋዌን ይናገራል። ድንግል ያለዘር ክርስቶስን ጸንሳ መገኝቷን ያስተምረናል።
A
አንድ ጥያቄ ግን አለኝ በአሮእን ልብስ ደረት ላይ ያለው 4 መአዘኖች የልብሱ ጌጥ ናቸው ወይስ ትርጉም አላቸው?
Архив по месяцам
Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog