👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !
ክፍል ሰባት
ሰይድ ቁጥብ ቁርኣን መኽሉቅ ነው የሚል ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ በመረጃ ማረጋገጥ !
ውድ ሰለፍዮች ቁርኣን የአላህ ቃል መሆኑ የራሱ የቁርኣን ፣ የነብዩና የሶሓቦች አስተምሮ ነው ። ቁርኣን ፊደሎቹም ንግግሩም መልእክቱም ባጠቃላይ የአላህ ቃል ነው ። አላህ በቀጥታ ተናግሮበት ጅብሪል ሰምቶት ወደ ነብዩ ያደረሰው መለኮታዊ የህይወት መመሪያ ነው ። ንግግር የአላህ ሲፋ ነው ። የአላህ ሲፋ መኽሉቅ (የተፈጠረ) ነው የሚል ይከፍራል ።
ይህ ነጥብ የነብዩን ሱና በተከተሉና በዲን ላይ አዳዲስ ፈጠራ ባመጡ የጥመት አንጃዎች መካከል መሰረታዊ የልዩነት ነጥብ ነው ። ከእነዚህ የጥመት አንጃዎች ዋና ዋናዎቹ ጀህምዮችና ሙዕተዚላዎች ፣ እንዲሁም አሻዒራዎች ይገኙበታል ። በመካከላቸው የአገላለፅ ልዩነት ቢኖርም የአላህ ቃል አይደለም መኽሉቅ ነው የሚለው ያገናኛቸዋል ። በመሆኑም የዚህ አይነት ዐቂዳ ባለቤት የሆነ ሰው እንኳን የዲን መሪ ሊሆን ጉዳዩ ዑለሞች ዘንድ ይከፍራል ወይስ አይከፍርም ነው ።
ሰይድ ቁጥብ ቁርኣን መኽሉቅ ነው የሚል ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ እንመልከት : –
" إن القرآن ظاهرة كونية كالأرض والسماوات"
الظلال: (4/2328
" ቁርኣን ግልፅ የሆነ ሁን በሚለው የአላህ ትእዛዝ እንደ ሰማይና ምድር የተፈጠረ ነው "።
"والشأن في هذا الإعجاز هو الشأن في خلق الله جميعاً وهو مثل صنع الله في كل شيء وصنع الناس".
الظلال (1/38)
" የዚህ ማሳኛ ( ቁርኣን) ጉዳይ እንዳጠቃላይ የአላህ መፍጠር ነው ። ምሳሌው በሁሉ ነገር ላይ የአላህ መፍጠር አይነት ነው… " ።
وقال عن الحروف المقطعة :
" ولكنهم لا يملكون أن يؤلفوا منها مثل هذا الكتاب, لأنه من صنع الله لا من صنع إنسان".
الظلاله (5/2719)
ሆሄያቶችን ( ምህፃረ ቃላቶችን) አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል : –
" ከሀዲያኖች እንደዚህ አይነት (ቁርኣን) መፃፍ አይችሉም ። ምክንያቱም የሰው ስራ ሳይሆን የአላህ ስራ (መፍር) ስለሆነ ነው " ።
وهذا الحرف "صاد " يقسم به الله سبحانه, كما يقسم بالقرآن ذي الذكر, وهذا الحرف من صُنعة الله فهو موجده, موجده صوتاً في حناجر البشر".
الظلال (5/3006)
የሷድን ምእራፍ ሲያብራራ እንዲህ ይላል : –
" በ" ሷድ " አላህ ጥራት የተገባው ጌታ ይምላል ። በቁርኣን እንደሚምለው ሁሉ ። ይህ ፊደል የአላህ ስራ ነው ። እሱ ነው ያስገኘው (የፈጠረው) በሰዎች ጉሮሮ ውስጥ ድምፅ አድርጎ ያስገኘው ነው "።
የአላህ ቃል ሳይሆን በሰዎች ጉሮሮ ውስጥ ድምፅ ሆኖ የተፈጠረ ነው ይለናል !!!።
ይህ ነው ኢኽዋኖች ከነብያቶችና ከሶሓቦች በላይ ንግግሩን የሚቀበሉትና ለክብሩና ለዝናው ጥብቅና የሚቆሙለት የኢኽዋኖቹ መሪ !!!
ሰይድ ቁጥብ ማለት በአለም ላይ አጥፍቶ የመጥፋትን ሽብር በእስልምና ስም ያሰራጨ የሱን አስተሳሰብ ያልተቀበሉ የሙስሊም መሪዮችና ዑለሞችን እያከፈረ እነርሱን አጥፍቶ መጥፋት ፅድቅ ነው የሚል ትውልድ እየተተካ እንዲሄድ የሚያደርግ መርህ ትቶ የሄደ ግለሰብ ነው ። ንግግሮቹና ተግባሮቹ የሚያከፍሩ ከመሆናቸውም ጋር ንግግሩንና ተግባሩን የሚመዝንበት የሸሪዓ እውቀት ስላልነበረው በወቅ
11.8K ·