🌼
7 September 2026
🌼 የአዲስ ዓመት መዝሙሮች 🌼
Аудио
ጋሜል_ዘ_ኦርቶዶክስ_ናልኝ_ሩፋኤል_አባቴ.mp3 · 9.0 MB · click to show Аудио
ጋሜል_ዘ_ኦርቶዶክስ_ሩፋኤል_ብዬ_ስጠራው.mp3 · 6.6 MB · click to show Аудио
ጋሜል_ዘ_ኦርቶዶክስ_እግዚአብሔር_ፈዋሽ.mp3 · 6.1 MB · click to show ✥ ናልኝ ሩፋኤል አባቴ ✥
እኔ ያንተ ልጅ ዝማሬን ላንሳ
ለኔ ያረከውን ፍጹም ሳልረሳ
''ትገርመኛለህ ሩፋኤል ትደንቀኛለህ
በደረስኩበት ሳትለየኝ ታከብረኛለህ''/2/
ዓይኔን አብርተህ ሩፋኤል ሠው ልታደርገኝ
በእናቴ ማህጸን ጠብቀህ ዛሬን አየሁኝ
አስማንድዮስን አስረኸው ተረፍኩኝ ከሞት
እዘምራለው ለክብርህ ቀን እና ሌሊት
ናልኝ ሩፋኤል አባቴ ና መድኃኒቴ
ናልኝ መልዐኩ በሳህል የአምላክ ባለሟል
ቤትህ ተጥዬ ማደጌ ክብሬ የሆነው
አሳ አንበሪውን ገስጸኸው ተርፌልህ ነው
ያንሳል ብዘምር ሩፋኤል ስላንተ ስራ
ልሳኔ ያውጅ ስራህን ጸጋህን ያውራ
ስንቱ ታበሰ ከዓይኖቹ የሐዘን ዕንባ
የራጉኤል ልጅ ዘመረች ቤቷ ስትገባ
ምስክር ቢያሻ ኑሮዬን የኔን ቤት እዩ
ሩፋኤል ላለ ይበዛል ጽውዓ ሲሳዩ
ዜማው መስጦኝ አነቃኝ ደብሩ በደስታ
ተጥዬ አልቀረሁ መክሊት ነኝ እኔ ለጌታ
ቃል እያስጠና የአምላኩን ከአትሮንሱ ስር
ታሪኬ እርሱ ነው ሩፋኤል የልቤ ምስጢር
ሰማይ ተከፍቶ በቀንህ ምሕረት ፈሰሰ
እኔም ተጠመኩ በእምነት ውስጤ ታደሰ
ከልጅነቴ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ
አስታዋሼ ነህ ሩፋኤል የነፍሴ ሞገስ
🌼 መዝሙር 🌼
ዘማሪ ዲያቆን በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
12.2K · 🌼
🌼 እንኳን ለርኅወተ ሰማይ: ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
•➢ ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት፦ ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው። በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች።
•➢ በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ (መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል። በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት።
•➢ አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት:: ጌታም ሦስቱን ሊቃናት (ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው።
•➢ ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው::" አለው:: እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው። በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ።
•➢ በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል። በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል።
•➢ ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው። በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል።
•➢ ቅዱስ ሩፋኤል
¤መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
¤አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
¤መዝገበ ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
¤ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ)
¤ፈታሔ ማኅጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ)
¤መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል።
✝ በምልጃው አይለየን።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
13.4K · 9 September 2026
🌼 የአዲስ ዓመት መዝሙሮች 🌼
Аудио
6082726593_1.mp3 · 3.8 MB · click to show 🌼 አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን 🌼
አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/
ባርክልን ኧኸ በዓሉን
ለዛሬ ዓመት ኧኸ አድርሰን
ሠላም ፍቅር ኧኸ አድለን
በዕምነታችን ኧኸ አበርታን
በአንድነት ኧኸ አቁመን
አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/
ጽኑ ሠላም ኧኸ ለሐገሪቱ
እንዲጦሩ ኧኸ አዛውንቱ
ወጣቱ እና ኧኸ ሕጻናቱ
ያለ ጊዜ ኧኸ እንዳይሞቱ
አንድም ሳይጎድል ኧኸ በመሃላችን
ለዓመት ያብቃን ኧኸ አምላካችን
አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/
አገልጋዩን ኧኸ ከመቅደሱ
እንዲኖሩ ኧኸ ሲያወድሱ
ታቦቱንም ኧኸ ከመንበሩ
አታናውጠው ኧኸ ከደብሩ
ወታደሩን ኧኸ በድንበሩ
ጠብቅልን ኧኸ በበረከት
ቸሩ ጌታ ኧኸ የፍቅር አባት
ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/
ለባርኮ ኧኸ አውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ኧኸ በምሕረት
ያዘነው ኧኸ እንዲጽናና
የተከዘው ኧኸ እንዲል ቀና
በሐገር ውስጥ ኧኸ ውጭም ላለው
በበረከት ኧኸ አትለይው
ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን
የናቁሽም ኧኸ ጽዮን ብለው
ይሠግዳሉ ኧኸ ፊትሽ ወድቀው
ካኅናቱ ኧኸ በማሕሌቱ
በቅዳሴው ኧኸ በሠዓታቱ
ከልጅሽ ጋር ኧኸ ከዓለም ጌታ
ዘመሩልሽ ኧኸ በዕልልታ
ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን
ባርኪልን ኧኸ /4/
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
12.3K · Аудио
6082726593_1.mp3 · 5.2 MB · click to show 🌼 እነሆ አበባ 🌼
ጽኑ በተዋህዶ በእምነታችሁ በርቱ
በንስሀ እንጀምር ቀርባለች መንግስቱ
እነሆ አበባ ይበቃናል እንባ(2)
እነሆ ለምለም ይግባልን ሰላም (2)
Tewaahidoon cimaa Amantaa jabeessaa
Gaabbiin haa jalqabnu dhiyaatt e Mootummaansaa
Kunoo Abaaboo(n)... Nu haa gahu boo'ichi
Kunoo Laliseera...Nagaan ol seeneera
ጠብ መንጃው ይውደቅ እነሆ አበባ
ይነሳ ፍቅር እንሆ አበባ
አልባሽ አጉራሽ ይብዛ እነሆ አበባ
ይባረክ ሀገር እነሆ አበባ
ሰላም አይጓደል እነሆ አበባ
ከአብሮነት ማጀት እነሆ አበባ
ወንጌል እንጫማ እነሆ አበባ
እናብዛ ስብሃት እነሆ አበባ
Tewahdon kenyi... Kuno ababoni
Leliste haa sabbontu
Atronsin ol bahet
Goftaan haa mullatu
Gitee kadhannadhaan
Rakkinaaf dhiphinaa
Gammadee ha simatu
Bara haraa kanaa
እምነት ተስፋ ፍቅር
ፍሞ እንደ ችቦ
እንደ መስኩ አደይ
እንፍካ በደቦ
ጎተራው ይትረፍረፍ
ለምለም ይቆረስ
ህፃናት ይደጉ
ይጦር አዛውንት
እንደ ጸናን በተዋህዶ
ተሰብስበን ለአምልኮ
ከርሞ ያድርሰን እንደገና
እየበዛን ለምስጋና
Tawaahidoon jabaanne
Waaqeffannaan dhaabbannee
Nuun haa ga'u kan dhufuunii
Nu baay'isee galaataanii
🌼 ዘማሪ ዲ/ን ምትክ ሲሳይ 🌼
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox 14.4K · 🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?
ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡
በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡
ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡
ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡
አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🌼
@maedot_ze_orthodox 🌼
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
18.7K · 🌼
🌻🌼 ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ አመጣጥና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል።👇
10 September 2026
I
ድንግል ሆይ ባርኪልን በአሉን የሚለው በአውዲዮ እና በፅሁፍ ላኩልኝ
I
Аудио
dc4ab779.mp3 · 3.1 MB · click to show ሩፋኤል ብዬ ስጠራው
ሩፋኤል ብዬ ስጠራው ሚስጥሬን ሁሉ ሳወራው
ትላንት የረዳኝ ጸሎትህ ዛሬም ይድረሰኝ ለልጅህ
ሩፋኤል ብዬ አንደበቴ ለምዶት ስምህን
ሩፋኤል ብዬ ልጅነቴ ቀምሶት ፍቅርህን
ሩፋኤል ብዬ የህይወቴ ቅጥር ሲላላ
ነፍሴ ትጮሀለች ሩፋኤል ሩፋኤል ብላ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት
ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት
ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ
ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ህመሜ እንዳይጸና ክፋቱ
ሩፋኤል ብዬ መድሐኒት እንዲሆን ሀሞቱ
ሩፋኤል ብዬ ካጠገቤ እንዳትርቅ ከጎኔ
ትዳሬ እንዲጸና ሩፋኤል እንዲበራ አይኔ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት
ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት
ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ
ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ
https://t.me/mezmur19211229 426 · I
Please ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታሳብኝ አድስ ዘመን ለኔ ያሳየኽኝ የሚለውን መዝሙር በፁሁፍ ላኩልኝ 🤲🤲🤲
I
Аудио
1476790306_final_1788725526.mp3 · 10.6 MB · click to show 🌼 ምን ብትወደኝነው 🌼
ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ
አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ
ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ ከተሻገርኩኝ
ኦ ጌታዬ እዘምራለሁ ስቡህ እያልኩኝ/2/
ጠዋትም የለኝ ካንተ በቀር ማለዳዬ ነህ
ማምሻዬም አንተ አልሻገርም አንተ ካልፈቀድህ
ማዕበል ወጀቡን አሳልፈህ ጨለማውን አብርተህ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/
አዝ 🌼 🌼 🌼 ?
አልፍ እንድትሆን አንተ የባረካት ከመሬት ወድቃ
ትላንትናዬን ወዜን ባርከኸው ለዚህ ብበቃ
ባጌጠችው የምድር መሀል ሆኜ
እቀኛለሁ ስለአዳኜ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/
አዝ 🌼 🌼
ፍሬ ፈልገህ መጣህ ወደኔ በብርሀን ጸዳል
ፀሐይ አውጥተህ ልትባርከው ጌታ ፈቅደሀል
ያንተ ወንዞች ውሃ ከተሞሉ
ተራራዎችም ምስጋናህን ያመጣሉ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/
አዝ 🌼 🌼
ማለፍ በክንድህ አዲስ ዘመንን ላንተ መዋጀት
ግዛው ዘመኔን ውረስ አምላኬ የኔን ማንነት
አዝማናቱ ስራህን እያሳየ
ልሁንልህ ከዓለም የተለየ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/
አዝ 🌼 🌼
ቀንን ብቆጥር ዘመን ባሰላ ካልተለወጥኩኝ
ከጸጋህ ዙፋን በዕምነት ቀርቤ ካልተፈወስኩኝ
ምን ሊረባኝ ካንተ ጋር ካላረጀሁ
ያለቃልህ በዘመን እንዲያው ባውጀው
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/
መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE
👇👇👇
@yemezmur_getimoche
@yemezmur_getimoche
@yemezmur_getimoche 6.1K · ኪ
I
𝑆𝑒𝑙𝑎𝑚 𝑒𝑑𝑎𝑡 𝑛𝑎𝑐ℎ𝑤𝑒 𝑒𝑘𝑜𝑘𝑒𝑙𝑠𝑒 𝑦𝑒𝑠𝑎𝑏𝑎 𝑙𝑎𝑘𝑢𝑙𝑒𝑔𝑔𝑔𝑔
I
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
★
@zemariian ★
#እሰይ_ደስ_ደስ_ይበላችሁ
እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ፪
ዘመነ ሉቃስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን ፪
ጌቶች አሉ ብለን ደስ ብሎን መጣን
እሜቴ አሉ ብለ " " "
አበባዮሽ ፪ ቅድስት
እንቆቅልሹን "
ልትፈትን ሔዳ "
ንግስተ አዜብ "
እናት ማክዳ "
በልቧ ያለውን "
አጫወተችው "
አሰቀምጣ አበባ "
እያሳየችው "
መዓዛው የሚሸት ከሁለቱ
የቱ ነው አለችው "
ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ክብር አለሽ (፪) ለሀገር አግባብ የሚሆነውን ከልብ
ሽተሽ
እንቆቅልሹ የሳባ
ከበድ ቢለው "
ጥበብ ስላለው ንጉሱ
ሚስጥሩን ሊያውቀው "
ክፈት መስኮቱን ሰለሞን
አለው ለሎሌው "
ገቡ ንቦቹ ሊቀስሙ
ከአበባው አልፈው "
ብልህ ጠቢቡ መለሰ
ለተጠየቀው በእውነት
ንጉሥ ሰለሞን አንዳች
አልተሰወረው በእውነት
አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (፪)
ኢትዮጵያ የዝናሽ ግርማ በአለም ተሰማ
ለፈጣሪዋ ንግስት
ምስጋና አቅርባ "
ኢትዮጵያዊቷ "
ንግስተ ሳባ "
ጥበቡን አይታ "
ላደነቀችው "
ወርቅ ሽቶውን "
እንቁ ሰጠችው "
ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)
የአምላክን የፈጣሪሽ ስሙን ጠርተሽ(፪)
የኢትዮጵያ ሰዎች ለንግስት
ቆሙ በተራ "
ስንዱ ሆነው "
ለዙፋን ክብሯ "
በመስከረም ወር "
ሀገር ስትገባ "
ይዘው ስጦታ "
የፈካ አበባ "
አደይ የብርሀን ጮራ በኢትዮጵያ በራ(፪)
ኢትዮጵያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ/፪/
እየሩሳሌም ቅድስት
ደርሰሽ መጣሽ "
እንኳን ለክብር "
ለዚህ አበቃሽ "
ከአምላክ በረከት "
ፍሬ አግኝተሽ "
ይዘሽ ስጦታ "
እንቁ ለጣትሽ "
ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር ያለሽ
ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናጫውትሽ ፪
የአባቶች ተስፋ ለፃድቃን
የነቢያት ትንቢት ለፅናት
የሙሴ ፅላት ለፀሎት
የአሮን ክህነት ለፍትሀት
የዳዊት መንግሥት ለፀጋ
ይዘሽ የመጣሽ
አምስቱን ሀብታት
ለሀገር መሠረት
አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ
ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ/፪/
በህገ ልቦና ጥንቱን
ፈጣሪ አውቀሽ "
ህገ ነቢያትን ከአለም
ቀድመሽ ተቀበልሽ "
በብሉይ ኪዳን ለጌታ
መስዋዕት አቅርበሽ "
ተስፋ ከአደረጉት ከአይሁድ
ከእስራኤል ቀድመሽ "
ህገ ወንጌልን በፊት
ይዘሽ ተገኘሽ "
ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ
ስለፈፀምሽ
2.1K · I
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼
🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼
🌼
🌼
🌼🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼🌼 🌼 🌼🌼
🌼
🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼 🌼 🌼🌼 🌼
🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼
🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻
🌻
🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻
🌻
🌻
🌻
🌻
🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻
🌻
🌼
🌼 የአዲስ ዓመት መዝሙሮች 🌼
🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?
ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡
በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡
ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡
ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡
አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🌼
@maedot_ze_orthodox 🌼
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
18.7K · 12 September 2026
I
17 September 2026
D
18 September 2026
I
D
I
D
20 September 2026
A
A snapshot of an open public feed from the search index
ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled.
Times are UTC.
Public content only, official Telegram API.
About ·
FAQ ·
What we do not do ·
Remove a page ·
Catalog