Web appOpen in Telegram
AAddis Learning Center

Addis Learning Center

@Addislearningcenter · group · Education · indexed since 2026-08-19
477members−2 in a week
1writing in 30 days
9messages in 30 days
80messages in the index
👉
Photo
click to show
ደጉ ሳምራዊ በጥቂት ልበለው ደግነት የቱ ነው?? በወንበዴዎች እጅ ደቅቄና ወድቄ ሳለው ሚያነሳኝ ሚጥልኝ እንደው ሚያዝንልኝ ይኖራል በማለት በመንገድ ያለሁኝ እርዳታን የምሻ አንድ ደካማ ነኝ አላፊው አግዳሚው አይቶ ተመልክቶኝ እያለፈ ይሄዳል እንደታዛቢ ሰው ልደሰት መሰለኝ ካህን ሲመጣ አየው አይጨክንብኝም ያነሳኛል እሱ አያልፈኝም ብዬ ሳስብ ሳለው ፊቱን አላዞረም እውነቴን እኮ ነው ገለል ብሎ አለፈኝ ከማዘን በስተቀር ምን አማራጭ አለኝ ይታያል አንድ ሰው ለካ ሌዋዊ ነው ይረዳኛል ብዬ አይን አይኑን እያየው እሱም ገለል አለ አይቶኝም አለፈ የኔም ተስፋ በቃ ወደላይ ከነፈ በህይወትናሞት መካከል ሳለሁኝ እኔ በወንበዴዎች እጅ ደቅቄና ወድቄነበር ያኔ ካህን ሲመጣ ሳይ ተስፋዬ ሊሆነኝ ገለል ብሎ አለፈ እኔ ለሱ ማነኝ???? ጥሎ ማይጥል አምላክ አቃለው እንዳለኝ እንዲም ሆኜ አልቀረው እ/ር ሰው ላከልኝ ካህኑም ያለፈኝ ሌዋዊ ያገለለኝ አንድ ሰው መጣና በጣም አዘነልኝ አይቶኝ ማለፍ ከብዶት ከልቡ ተጠጋኝ ቁስሌን ጠራርጎ ወደህይወት መለሰኝ ተስፋም እየሆነኝ የፊቱን አሳየኝ ገለል ባልኩበት በዛ የውድቀት ስፍራ መዳኒቴ ሆነ ከበሽታ ሁሉ ጋራ ይሄ ሁሉ ማነውካላችሁኝ ደጉሳምራዊነው ታዲያ አንተ ልዑል በዙፋንህ ያለኸው አንተ ባትረዳን ባትቤዠን ኖሮ እውነት አይመረንም ነበር የአለም ኑሮ ዛሬ እኔ አንተ አንቺ እኛ ያለነው በሱ ነው ጠባቂ መከታ ረዳት ከለላ በሆነው ያ ደጉ ሳምራዊ ማነው ካላችሁኝ ተረድቶት ለገባው የእግዜር ምሳሌ ነው ሉቃ 10፥20 by Dave @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber
17 · 3.8K ·
👉
Photo
click to show
‎አንተ ቅደም እኔ አልውጣ!! ‎ ብሮጥ በራሴው መንገድ ቢሄድ እርቄ ‎ጠብቅ ስትል እምቢ ብዬ አንተን ንቄ ‎መታገስህን ቆጥሬ እንደ መቅረት ‎ችኮላዬ በልጦ አሸንፎ ትዕግስት ‎ ‎ብዙ ቢሄድ ብቀድም ከሰው ሁሉ ‎እሱ እርቋል ተሳካለት ሰዎች ቢሉ ‎ከሌለህበት አንተ ቀርተህ እኔ ቢቀድም ‎ምን ሊጠቅመኝ ያለአነንተ ለኔ አይሆንም ‎ ‎የኔ ስኬት ጎልቶ ወጥቶ ‎ሀገር ምድር ስሜን ጠርቶ ‎ሁሉም ቆሞ ቢያጨበጭብ ለስኬቴ ‎ምን ሊረባ ምን መጠቅም ቀርተህ አንተ ‎ ‎ብቻ ስኬት አይሁንልኝ ከአንተ ርቆ ‎እውቀት ብልጽግና አይሁንልኝ አንተን ለቆ ‎ተሳካለት ቢባል ቢጠራልኝ ስሜ ጎልቶ ‎እኔ አላቅም እኔነቴን ካንተ ወጥቶ ‎ ‎ስመስልብኝ የዘገየህ እንዳልወጣ በችኮላ ‎ትዕግሥት ስጠኝ እንድከርም በአንተ ጥላ ‎አቻኩሎኝ የሚያሮጤኝ ይህ ስሜቴ ‎አንተ ወጣ ትመራኝ ዘንድ ቸሩ አባቴ ‎ ‎ቀድመህ ውጣ አንተ ቅደም እኔ አልውጣ ‎አንተ ቀርተህ እኔ ወጥቼ ምን ላመጣ ‎ከዘገየህ እንዲዘገይ ልቤም ይገራ ‎አንተ ካልወጣህ አታውጣኝ አደራ ✍️ አማኑኤል ነጋሽ (አቡ) ‎ ‎ @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber
12 · 3.4K ·
👉
Photo
click to show
ይቅር አንተን አደብዝዞ ራስን ማሳየቱ የሚገባህን ክብር ለሌላ መስጠቱ ይቅርብኝ አባቴ በማትገኝበት በዛ ውሎ ማደር አንተን ችላ ብሎ ከንቱ ኑሮ መኖር. የዚህ ዓለም ክብር ሀብት እውቀት ዝና ካንተ ጋር ካልሆነ መባከን ነውና ምን ዋጋ አለው ጌታ ሁሉን የኔ ባደርግ አንተ ካልተደሰትክ ካልሆንከኝ ወግ ማረግ. ክብሬ ሞገሴ ውበት ማንነቴ የሕይወቴ ድምቀት የመኖር ምክንያቴ የሳቄ ሚስጥር የደስታዬ ምንጩ ኢየሱስ አንተ ነህ ሕይወቴን ለዋጩ. ሺ አደባባይ አንተ የሌለህበት መንፈስህ እርቆ ባዶ ከሆነበት ምን ያረግልኛል በሰዎች መታወቅ አንተ በሌለህበት በዛ ራስን ማድመቅ. ሁሉ ነገር ሞልቶ አንተን ግን አጥቼ ከቶ አልችልምና ልኖር ተደስቼ ይቅርብኝ ብያለሁ ይቅር ሁሉም ነገር ያለኝ ነገር ሁሉ ይሁን ላንተ ክብር.        ✍️ ሃና መኮንን ‎ ‎ @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber
14 · 3.4K ·
👉
Photo
click to show
ዓለም ያላወቀው ፍቅር ፍቅር በሰው ሃሳብ በብዙ ይገለፃል አንድ ሁለት ተብሎ በብዙ ይብራራል ሰው ሁሉ ቢመስለው ፍቅርን ያወቀ በቃላት ብዛት ፅፎ ያጠናቀቀ አንድ ፍቅር አለ ዓለም የማያውቀው ለመፃፍ ቢሞከር ቃላት የማይገልፀው. ከሰዎች አይምሮ እጅጉን የላቀ የዓለምን ትኩረት ሃሳብ የሰረቀ በቃላት ክምችት ከቶ ያልተብራራ በተግባር የታየ በመስቀል ላይ ስራ. አለ አንድ ፍቅር እጅግ የከበረ በአንደበት ሳይሆን የእውነት የተኖረ ርዝመቱ ጥልቀቱ ስፋቱ የማይገመት ዓለምን ያዳነ ከዘላለም ጥፋት ጠቢባን ኃያላን እጅ የሰጡለት በኃይል ሳይሆን ወደው የተገዙለት. የዓለምን ጥበብ በከንቱ ያስቀረ የፍቅርን ምንነት ትርጉም የቀየረ ለዓለም ሁሉ ኃጢያት በመስቀል የሞተ ፍቃዱን ፈፅሞ አብን ያስደሰተ አየው አንድ ፍቅር ዓለም ላይ የሌለ ከሰማይ የመጣ ሰውን ጉድ ያስባለ. ይሄ ፍቅር አጋፔ ይባላል ገደብ አልባ ፍቅር የዓለም ጠቢባን ያልገባቸው ሚስጥር በመስቀል ላይ ሞቶ ሰዎችን ሊታደግ የዓለምን ጌታ ሰው እስከማድረግ ክብሩን እስከመጣል ድረስ ያደረሰው አጋፔ የሆነው ጥልቅ ፍቅሩ ነው. አዎ ይሄ ነው እንግዲህ ዓለም ያላወቀው የጠቢባንን ጥበብ ከንቱ ያደረገው መለኪያ በሌለው የክርስቶስ ፍቅር ነፍሳት እንዲያመልጡ ከያዛቸው ቀንበር አብ ልጁን ሰጥቶ ወልድ የሞተበት በመንፈሱ አትሞ ወራሽ የሆንበት ዓለም እስከዛሬ ልታቀው ያልቻለችው አጋፔ ነው ፍቅሩ ያልተረዳችው. ✍️ሃና መኮንን @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber
37 · 3.5K ·
👉
Audio
🎵 🎶 በአዲሱ አቁማዳ 🎵🎶.ogg · 369 KB · click to show
🎵 🎶 በአዲሱ አቁማዳ 🎵🎶 🎤🎵 mole ከዘመን ዘመን አሸጋግሮ አመታቶችን አሳልፎ ቀኖችን በመልካም ለውጦ እዚህ ደረስኩኝ በጌታ ምህረቱ በዝቶ እዚህ ደረስኩኝ በኢየሱስ ምህረቱ በዝቶ በአዲሱ አመት በአዲስ አቁማዳ አዲስ ወይን ጠጅ ሞልቶ ይፈሳል ከእኔ ወደ ደጅ ያረካል እሱ እኔ ረክቻለው ግቡ እና ጠጡ ጋብዣችኋለው(4×) 🌼 🌼 🌼 🌼 መልካም 🌼 🌼 አዲስ 🌼 🌼አመት🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼@yegetamianmahiber🌻🌻 🌼🌼@yegetamianmahiber🌻🌻
10 · 3K ·
👉
Photo
click to show
ርዕስ: ምን ልከፍል ችላለሁ? ገጣሚ:- መክሊት አዳኝ እፈልጋለሁ ለሞት በተሰጠ ሰዉነት ተይዣለሁ ሀጢያትም ገዛኝ ባሪያዉ ሆኛለሁ መቆሚያ አርጎት ሰይጣን በኔ ላይ ህጉን ሰምቼ እንዳላረግ ከልካይ ተጥሎ ሳለ ከምድር በታች እኔን ሊወስደኝ ሊገለኝ ሲያመቻች ኩነኔም የለ የሞት ፍርሀት አዳኝ ተገኝቶ ለኔ የሚሞት ሀጢያቴን ወስዶ ፅድቅ አለበሰኝ ሞቱ ትንሳኤዉ ህያዉ አረገኝ ለመፅደቅ ሚሆን ባጣ ክፍያ ለክብሩ ሚሆን ፅድቁን ማሳያ ነፍሴ ተጣልቶ ከስጋዬ ጋር መንፈሴም ሆኖ የህግ አገልጋይ አዳኝ ተገኘ ከላይ ከሰማይ እኔን የሚያፀድቅ በአብ ዘንድ ሚታይ ታዲያ እላለሁ በክርስቶስ ላሉ! በአንድያ ልጅ አምነዉ ለዳኑ! ሞት የለም ኩነኔ በእርሱ ነፃ ሁኑ በሞቱ ተባብረን ለሀጢያት ሞተናል! ትንሳኤም ተካፍለን ለእርሱ ቀድሶናል! @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
4 · 1.4K ·
👉
Photo
click to show
አያልቅብህ ትህትናህ ትሻው ነፍሴን ... እንዴት ልግለጥ፤ ከምቀዳው  ....  እንዴት ልብለጥ። ከምኔ ላይ ምኔን ጥዬ ላቅርብልህ ውሃ ብዬ። የለመንከኝ ፍጥረትህን ..  የለመንከኝ የጋን ውሃ፤ ማቅረቢያዬ አዳፋ ልብ ..     ያልታጠበ በንስሐ። ታውቀው የለ..ታሪክ ግብሬን ያልኖርኩትን ቡሩክ ኑሮ ..                 በአደባባይ መናገሬን። ታውቀኝ የለ እድፍ እንዳልኩ ..      ምን እንዳጣሁ ምን እንዳለኝ፤ በኃጢአት ነትባ ያለች ነፍሴን ..              የምሰጥህ እኔ ማን ነኝ። አንካሳ ነኝ ልበ ስንኩል..       ዛሬ ነገ የምቃጠር ..        ለማፍቀርህ መልስ የማጣ፤ ና ስትለኝ ልብ የለኝም ..       በምን ጽድቄስ ችዬ ልምጣ። ዳሩ አንተ ግን መናፈቅህ፤ የጠማህን የነፍሴን ማይ .. እስካጠጣህ  መጠበቅህ አያልቅብህ ትህትናህ ዮሐንስ 4:10 ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት። ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
5 · 1.3K ·
👉
Photo
click to show
#መኖርና-ኑሮ ኮልታፋ ሆኜ ስረግጥ ኮሬብን ቃላቴ ሲያምር አልሻም ግብፅን ባገኝም እንኳን የኔን ሳሙኤል ሴሎን አልፌ ቤቴን አልረግጥም የልቤ ሚዛን ሁለት አይዝም አንዱን ካንተ ጋር አይመዛ'ዝንም ማር አፍልቆ ወተት ቢያዘንብም ከነዓን ለኔ መኖሪያ አደለም መፈለጌ የእዉነት ቢሆን በጌን ትቼ ባግድ ሰዉን ታላቅ ብሆን በተራራ ክብር ባገኝ ክብር ተራ እሺ ብለዉ ቢታዘዙኝ ደሞ አልፈዉም ቢቃወሙኝ ከመራሁት አርባ አመታት ሲጨመቁ አርባ ቀናት ያደርኩበት ባይኖችህ ፊት ኖርከዉ ካሉኝ መቶ አመታት እኔ ያመንኩት ያቺን ቀናት ኦሪት ዘጸአት 24፤18 24፤18 ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ፤ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀን አርባ ሌሊትም ቆየ። ✍️እንደዚህ አይነት special timeዎች ከትክክለኛ መኖር ዉስጥ ይመደባሉ። @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
2 · 1.3K ·
👉
Photo
click to show
አሁን ግን! እስከ ዛሬ በራሴ ሞክሬ ብዙ ወድቄያለሁ ፤ አሁን ግን ከአንተ ቀርቤ ብዙ ላተርፍ እወዳለሁ ። ረጅሙን ጎዳና በራሴ ተመርቼ ብዙ አጥፍቻለሁ ፤ አሁን ግን አንተን እያማከርኩ መቀጠል እመርጣለሁ ። ብዙ ዘመን በቤትህ ጀምሬ በአለም ቀጥያለሁ ፤ አሁን ግን ዘመኔን በፊትህ መፈጸም እሻለሁ ። ብዙ ጊዜ የፈለግሁበት ገብቼ መውጣት ተስኖኝ አይቻለሁ ፤ አሁን ግን በሌለህበት ላልገኝ ራሴን አስገዛለሁ ። ብዙ ወዳጅነቶችን ራሴ ገንብቼ እኔው አፍርሻለሁ ፤ አሁን ግን ወዳጄን እንድለይ እርዳኝ ብዬ እጸልያለሁ ። አያሌ አመታት ለራሴ ስሰበስብ ከርምያለሁ ፤ አሁን ግን በወንጌልህ እርሻ ላይ መሰማራትን እሻለሁ ። ሰፊውን ዘመን ሰሜንን ስታሳየኝ ደቡብን መርጫለሁ ፤ አሁን ግን ወደ ላከኝ ብቻ ልጓዝ ፈቅጃለሁ ። ብዙ ወቅቶች የሚወደኝን በመውደድ ኖርያለሁ ፤ አሁን ግን ጠላቴን ልወድ ቆርጫለሁ ። ብዙ ዘመን 'ለእኔ' ብዬ ኖርያለሁ ፤ አሁን ግን ለወንድሜ እያልኩ መኖር እሻለሁ ። የዕድሜዬን እኩሌታ በስሜት በመኖር አሳልፍያለሁ ፤ አሁን ግን ለቃልህ እውነት መገዛትን መርጫለሁ ። ብዙ ዘመን ስትሰጠኝ እያመሰገንኩ ስትነሳኝ አማርሬያለሁ ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እያልኩ መኖር እሻለሁ ። ትላንቴ ኪሳራና ውድቅት የሞላው መሆኑን አይቻለሁ ፤ አሁን ግን ዘመኔን በድል መፈጸም እናፍቃለሁ ። ከዚህ ቀደም ምድር ቤቴ ብዬ ኖርያለሁ ፤ አሁን ግን ሰማይ መኖሪያዬ ብዬ ማራናታ እላለሁ ። ተፃፈ በቦዔዝ ታምሬ አዳማ , ኢትዮጵያ @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
11 · 1.7K ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count