በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
መስከረም (12) ቀን።
🥀🥀 እንኳን በኤፌሶን_አገር በ_431 ዓ.ም (ሦስተኛው ጉባኤ) ሁለት መቶ ኤጲስ ቆጶሳት በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ_አባ_ቄርሎስ ሊቀ መንበርነት ንስጥሮስ ለማውገዝ ለተሰበሰቡበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል እግዚአብሔር ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ነቢዩ_ቅዱስ_ኢሳይያስ_ለንጉሡ_ሕዝቅያስ ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜው ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደተጨመረለት ንገረው ብሎ ለተላከበት ለወራዊ መታሰብያ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት ቅዱስ_አፍላሆስ ከመታሰቢያውና ከሥጋው ፍልሰት፣ ከእስክድርያ አገር ከሆኑ ከባልንጀሮቹ ሰማዕታትም ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕታት_ከቅዱሳን_ከሉዩራስና_ባሌኒኮስ፣ ከቅዱስ_ኢያቄምና_ከቅድስት_ሐናም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
በዚችም ቀን ደግሞ በኤፌሶን_ከተማ የቅዱሳን_የሁለት_መቶ_ኤጲስቆጶሳት_ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው።
ስብሰባቸውም የተደረገው የታላቁ ቴዎዶስዮስ ልጅ አርቃድዮስ የወለደው ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በሃያ ዓመት ነው። የስብሰባቸውም ምክንያት የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በንስጡር ነው። እርሱ ስቶ እንዲህ ብሏልና "እመቤታችን ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ አልወለደችውም እርሷ ዕሩቅ ሰውን ወልዳ ከዚህ በኋላ በውስጡ የእግዚአብሔር ልጅ አደረበት ከሥጋ ጋር በመዋሐድ አንድ አልሆነም በፈቃድ አደረበት እንጂ። ስለዚህም ክርስቶስ ሁለት ጠባይ ሁለት ባህርይ አሉት" የተረገመ የ*ከ*ሐ*ዲ ንስጡር የከፋች ሃይማኖቱ ይቺ ናት።
ስለ እርሱም የተሰበሰቡ እሊህ አባቶች ከእርሱ ጋር ተከራከሩ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አምላክ እንደሆነ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ በአበሠራት ጊዜ ከተናገረው ቃል ምስክር አመጡ። እንዲህ የሚል "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው ከአንቺ የሚወለደውም ጽኑዕ ከሀሊ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል"። ዳግመኛም "እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች" ብሎ በትንቢቱ ከተናገረው ከኢሳይያስ ቃል ሁለተኛም "ከእሴይ ዘር ይተካል ከእርሱም ለአሕዛብ ተስፋቸው ይሆናል"።
ዳግመኛም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ ገሠጸው መከረው ስለዚህም እንዲህ ሲል አስረዳው "ክብር ይግባውና የክርስቶስ የመለኮቱና የትስብእቱ ባሕርያት በመዋሐድ አንድ ከሆኑ በኋላ አይለያዩም አንድ ባሕርይ በመሆን ጸንተው ይኖራሉ እንዲህም አምነን ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንዲት ባሕርይ ነው እንላለን"።
ከሀዲ ንስጥሮስ ግን ከክፉ ሐሳቡ አልተመለሰም ከሹመቱም ሽረው እንደሚአሳድዱትም ነገሩት። እርሱ ግን የጉባኤውን አንድነት አልሰማም ስለዚህም ከሹመቱ ሽረው ረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለይተው አሳደዱት ወደ ላይኛውም ግብጽ ሒዶ በዚያ ምላሱ ተጎልጒሎ እንደ ውሻ እያለከለከ በክፉ አሟሟት ሞተ።
እሊህም ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት አባቶች ሃይማኖትን አጸኑዋት በዚህም ጉባኤ ውስጥ እንዲህ ብለው ጻፉ "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእርሷ ሰው የሆነውን የእግዚአብሔርን አካላዊ ቃል በሥጋ ወለደችው"።
ከዚህም በኋላ ሥርዓትን ሠርተው ሕግንም አግገው በእጆቻቸው ጽፈው ለምእመናን ሰጡ። እኛም የሕይወትንና የድኅነትን መንገድ ይመራን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ለእርሱም ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
በዚች ቀን የመላእክት_አ
22 September 2026
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
ከ 18 ዓመት በላይ የኾኑ ኦርቶዶክሳዊ ወጣትን ቤተ ክርስቲያን ትፈልጋለች። የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት ደግሞ ኑልኝ እና ቅዱስ እና ህያው ቃሉን ላስተምራችኹ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችኹን እንድታዩአት ፣ እንድታውቋት ፣ እንድትወድዷት ላድርጋችኹ ትላለች!!!
ባሉበት ቦታ ኾነው ለመመዝገብ ከታች ያለውን ጎግል ፎርም ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ!!!
መመዝገቢያ ሊንክ
https://tinyurl.com/ez7aktee
በስልክ ደውለው ለመመዝገብ
0974732450
0947750885
654 · 23 September 2026
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፲፫ (13) ቀን። እንኳን #ለታላቁና_ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ባስልዮስ አንድ ጎልማሳ አገርልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት እርሷንም ከመውደዱ የተነሣ እርሷን ለማግባት ብሎ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔዶ እግዚአብሔር ክዶ በሰይጣን አምኖ በእጁ ፈርሞ ለሰይጣን ሰጠው ይህንን የጽሕፈት ደብዳቤ በእግዚአብሔር ኃይልና በጸሎቱ #ቅዱስ_ባስልዮስ በመደምሰስ ድንቅ ተአምር ላደረገበት ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከከበረ ከባሕታዊ #ከአባ_ይስሐቅ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
የቂሣርያ_ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_ባስልዮስ ያደረገው ተአምር፦ ይህም እንዲህ ነው አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ልቡ እርሷን ወዶ እንደ እሳት እስከ ነደደ ድረስ እርሷንም ከመውደዱ ብዛት የተነሣ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው።
ይህም አገልጋይ ይህን ነገር ተቀብሎ ያ መሠርይ እንዳዘዘው አደረገ። በዚያንም ጊዜ ከሰይጣናት አንዱ መጥቶ ወደ አለቃቸው ወስዶ አደረሰው ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። እንዲህም ብሎ ጠየቀው "ንጉሥህ ክርስቶስን ትክደዋለህን? ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላ ወደእርሱ አትመለስምን?" ይህም ጐስቋላ ባሪያ "አዎን ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው። መስሐቲ ዲያብሎስም "ይህን ልታደርግ በእጅህ ደብዳቤ ጻፍልኝ" አለው። እርሱም በከበረ ደሙ የዋጀውን የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ በደብዳቤ ውስጥ የክህደቱን ቃል ጻፈለት።
በዚያንም ጊዜ ሰይጣን በጌታው ልጅ ልብ ውስጥ የፍትወት እሳትን አነደደ ይህንንም ባሪያ እጅግ ወደደችው ከእርሱም መታገሥ አልተቻላትም። ወደ አባቷ በመጮህ በግልጥ "ከዕገሌ ባሪያህ ጋር ካላጋባኸኝ አለዚያ ራሴን እገድላለሁ" ትለዋለች እንጂ መታገሥ አልተቻላትም። አባትና እናቷም ፈጽሞ አዘኑ በምንም በምን ሊያስታግሥዋት አልቻሉም። የዚያም አገልጋይ ፍቅሩ በየዕለቱ በልቧ ይጨመር ነበር እንጂ። ስለዚህም ራሷን እንዳትገድል አባቷ ፈራ ለዚያ ባሪያ ሰጠው። እርሱም የጌታውን ልጅ ተቀብሎ ወደቤቱ አስገባት። ከርሷ ጋር ያለውን ፍላጎቱንም ፈጸመ። ከእርሱም ጋር ረጅም ጊዜ ከኖረች በኋላ አባትና እናቷም ይቅር ብሎ ኀዘናቸውን ከላያቸው ያርቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኀዘንንና ልቅሶን አብዝተው ነበር።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ጩኸታቸውን ሰማ ልመናቸውንም ተቀብሎ ይህ የወደደችው አገልጋይ ጐልማሳ ክርስቲያን እንዳልሆነ አስገነዘባት ከእርሷ ጋር በነበረበት በዚህ በረጅም ዘመን አንዲት ቀን እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔድ ሥጋውንና ደሙንም ሲቀበል ወይም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት ራሱን ሲአማትብ እርሷ አላየችውም።
ስለእምነቱም ጠየቀችው ግን አልገለጠላትም እርሷም እንዲህ አለችው "አንተ ክርስቲያን ከሆንክ ና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድና በፊቴ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበል"። እንዲህም በአስገደደችው ጊዜ ስለርሷ ያደረገውን ሁሉ ወደ ሥራየኛ እንደሔደም በሰይጣንም አምኖ እምነቱንም በክርታስ ጽፎ ያንን ክርታስ ለሰይጣን እንደ ሰጠው ነገራት።
ይህንንም ነገር ከእርሱ በሰማች ጊዜ ደነገጠች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች ራሷንም በማወዛወዝ እጅግ ተጸጽታ አዘ
24 September 2026
ሰላመ ክርስቶስ ይብዛላቹ ጠፋ ብዬ እንደነበር አውቃለው እናም የጠፋውትም እስኪ ትንሽ ስለ ቤተክርስቲያን ላንብብ ብዬ ነበር ግን አንድ የተረዳውት ነገር ቤተክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ አውቃታለው ብሎ መናገር እንደማይቻል ነው እኛ የማናውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ ያው ድብቅ ሆነው አይደለም የመረዳት አቅሙ ስለሌለን እና ገና የመንፈሳዊነት ህፃናት ስለሆነን ነውንጂ እናም ለማወቅ ሰነፎች ስለሆንን እናም ቤተክርስቲያንን ማወቅ ብዙ እንደሚቀረኝ ተረድቻለው ቤተክርስቲያን ልክ መጨረሻው እንደማይታወቅ ባህር ናት መጨረሻዋን ምናውቀው ከዚህኛው ወደ ሌላኛው ዓለም ስንጓጓዝ ነው ለዚህም ይመስለኛል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደዚህ ያለው
“
ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥12
ወደ እዛኛው ዓለም ስንሸጋገር የሚገለጡልን ብዙ ምስጢራቶች አሉ
ጌታ ትንሳኤን እናይ ዘንድ ያድለን
መልካም ቀን
✍✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15
1.8K · አመሻሹ ላይ ይመጣል❤️🩹❤️🩹
እግዚአብሔር መቼ ወደ ህይወታቹ እንደሚመጣ ታውቃላቹ ልክ ሰው የለኝም በቃ አበቃልኝ በምትሉበት ሰዓትና ዙርያቹ ገደል መስሎ በታያቹ ሰዓት ያንን የማይዝክ እጁን ይዘረጋላችኋል
በዘመዶቼም የእኔ የምላቸው ሰዎች ሸሹኝ እግዚአብሔርም ይሄው እስካሁን አለመጣም ብላቹ አትጨነቁ ማምሻው ላይ አመሻሹ ላይ ይመጣል እግዚአብሔር እግዚአብሔርን በማምሻችን ሰዓት እንጠብቀው እንደ አብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ስር(በቤተክርስቲያን )እንጠብቀው
እንደ ዮሴፍ በእስር ቤት ውስጥ (በዚህ ዓለም መከራ)ውስጥ ሆነን እንጠብቀው
እንደ ዳንኤል በአንባ ጉድጓድ(ሀዘናችን በችግራችን)ውስጥ ሆነን እንጠብቀው
ቢመሽም ይመጣል ወደ ቤታችን ይገባል ከእኛ ዘንድም ያድራል ብቻ ግን ጌታ አይቀርም አዎ ይመጣል ደስታንም ያጎናፅፈናል
መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ
ሞጆ ያላቹና መንፈሳዊ ማህበር መቀላቀል ምትፈልጉ በውስጥ አናግሩኝ
✍✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15
1.9K · በልቡ እግዚአብሔርን የያዘ ሰው ሕግጋቱን መፈፀም ይችላል ነገር ግን በከንፈሩ ብቻ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚል ልቦናው ተጠራጣሪ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ህግ መፈፀም አይችልም
እረኛው ሄርማን
ሰላም እደሩልኝ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ
✍✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15
1.9K · Фотография
click to show
click to show
መንፈሳዊ የፊልም ምሽት በዐውደ ወንጌል ሚዲያ
"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"
(መዝሙር 122፡1)
የተወደዳችሁ የዐውደ ወንጌል ሚዲያ ተከታታዮች ዛሬ ማታ መንፈሳዊ ፊልም የምናይበት ግዚያችን ነው
መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያንጹ እምነታችንን የሚያጠናክሩና ትምህርት የሚሰጡ ድንቅ መልዕክቶችን ከፊልሙ እናገኛለን
#ዛሬ ማታ 3:00 ጀምሮ ይጠብቁን
ሼር ሼር ሼር
https://t.me/awude_wengel_media_21
🛑በዐውደ ወንጌል ሚዲያ 🛑
143 · 25 September 2026
አሁን ይቺ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን አሰብክም ተብላ መወቀስ ይገባታል ስሙማ ቅዳሴዋን
ይስማዕ ሰማይ ወታጽምእ ምድር ወይድንግጹ መሠረታት ሐምዝ
ሰማይ ይስማ ምድርም ታድምጥ የምድር መሠረቶችም ይደንግጡ
አኅዝዎ አይሁድ ወአቅምዎ ውስተ ዐውድ ለዘሎቱ ይቀውሙ ሠራዊተ መላእክት በፍርሃት ወረዓድ ሰቀልዎ ዲበ ዕፀ ወቀነውዎ በቀነዋት ወኰርዕዎ ርእሶ በሕለተ ረገዝዎ ገቦሁ በኵናት አስተይዎ ለጽምዑ ሐሞተ ወከርቤ ቱሱሐ ለዘአሰተዮሙ ለእስራኤል እመ ፩ዱ ዕብን ለሰብአ ዓይን ሞተ ዘኢይመውት ሞተ ከመ ይሥዓሮ ለሞተ ሞተ ከመ ያሕይዎሙ ለሙታን በከመ አሰፈዎሙ በቃለ ኪዳን
አይሁድ ያዙት የመላእክት ሠራዊት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የሚቆሙለትን እርሱን በዓደባባይ አቆሙት በዕንጨት ላይ ሰቅለው በቀኖት ቸነከሩት ራሱንም በዘንግ መቱት ጐኑን በጦር ወጉት ለጉበኞች እስራኤል ካንድ ድንጋይ ያጠጣቸውን ለጥሙ ከከርቤ ጋራ የተቀላቀለ ሐሞትን አጠጡት የማይሞት እርሱ ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ በቃል ኪዳን ተስፋውን እንደ ነገራቸው
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
የቅዳሴው ክፍል የተለያዩ ቦታ ላይ ሚባሉ ቢሆኑም እኔ አንድ ላይ ነው የፃፍኩላቹ
መልካም ዕለተ አርብ የፍቅር ቀን
መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ
ሞጆ ያላቹ ኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ ማህበር መቀላቀል ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ
✍✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15
1.6K · በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
መስከረም ፲፭ (15) ቀን።
🥀እንኳን ለዲያቆናት_አለቃ_ለቀዳሜ_ሰማዕት ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለሥጋው_ፍልሰት ለመታሰብያ በዓል፣ ጠራው ከሚባል አገር ለሆኑ እግራቸው በውኃው ሳይርስ በእግራቸው በባሕር ላይ ሲራመዱ ለነበሩት ለከበረ ለጻድቁ_ለአባ_ጴጥሮስ በዓለ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
የዲያቆናት_አለቃ_ቀዳሜ_ሰማዕት ቅዱስ_እስጢፋኖስ_የሥጋው_ፍልሰት፦ ይህም እንዲህ ነው ከዐረፈበት ጊዜ ብዙ ዓመቶች ከአለፉ በኋላ ሦስት መቶ ዓመት ያህል ከዚያም የሚበዛ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ሲነግሥ የቀናች ሃይማኖትም ተገልጣ የሕያው እግዚአብሔር አምልኮት በሁሉ ሲዘረጋ ያን ጊዜ የቅዱስ እስጢፉኖስ ሥጋ በአለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ "እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ" አለ።
ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራእይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ። "በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ" እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። እንዲህም መላልሰው ሦስት ጊዜ አመሰገኑ ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከሌሎች አምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።
በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።
ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደ ደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም
ወር በገና በ15 የእናታችን ቅድስት ኢየሉጣ ወ ልጃ ቅዱስ ቂርቆስ መታሰቢያቸው ነው በረከት እረድኤታቸው ይደርብን🙏 አሜን
🧎♀➡️ቅድስት ኢየሉጣ ሆይ ሰላም ለአንቺ ይሁን
የደከመች ማርታ ያልደከመችም ማርያም ልጆቿንም ሰማዕትነት የሰጠች ሶፍያ ከአንቺ ጋር አይተካከሉም።
🧎♀➡️ቂርቆስ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን
በምቆምበት ጊዜ በየሰዓቱ በወልድና
በእናቱ ፊት የዚህ ምልጃዬ መልእክተኛ ነኝ በለኝ፡፡ሰላም ለአንተ፡፡
🤲ተከዜን የምትተካከል የሰላማችን ወንዝ
ቂርቆስ ሆይ! ከሕዝባችን ልብ ማጣት ታስወግድ
ዘንድ በየጊዜው ለመባረክና ለማረጋጋት ና ና፡
📚መልክአ ቅዱስ ቂርቆስ
የቅዱስ ቂርቆስ እንዲሁም የእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በረከታቸው ትደርብን በቃልኪዳናቸው ከስጋ ፈተና ይሰውሩን ካልታሰበ አደጋ ወቶ ከመቅረት ይጠብቁን አምላከ ቅዱስ ቂርቆስ አምላከ ቅዱስ ቂርቆስ አምላከ ቅዱስ ቂርቆስ የደነደነውን አይነ ልቦናሄን ግለጥልኝ🙏🙏🙏🙏
የኃጥእን መመለሱን እንጂ ሞቱን የማትወድ ሆይ አቤቱ የሚያገለግልህን ልቦና ስጠኝ
ቅዱስ ባስልዮስ
“በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው?
— ሚክያስ 7፥18
መልካም አዳር
መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ
✍✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15
1.8K · 26 September 2026
Фотография
click to show
click to show
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሠን አደረሳችኹ....❤
🗣 ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ነው፣ እናም መስቀልን እንደ በዓልና መንፈሳዊ ድግስ አድርጋችሁ እንድትመለከቱት እያከበርን ነው።
🗣 ቀደም ሲል መስቀል የጥፋተኝነት ፍርድ ነበር፣ አሁን ግን የአምልኮ ዓላማ ሆኗል። ቀድሞ የሞት ፍርድ ማለት ነበር፣ አሁን ግን የመዳን ምክንያት ነው።
🗣 መስቀል ለእኛ የማይቆጠሩ በረከቶች ምንጭ ሆኗል፦ ከስህተት (ከመታለል) አድኖናል፣ በጨለማ ለተቀመጡ አብርቶላቸዋል፣ እናም ከእግዚአብሔር ጋር ጠላትነት የነበርን ሰዎችን አስታርቋል። ጠላቶች ሳለን ወዳጆች አደረገን፤ ሩቅ ሳለን አቀረበን። የጥል አጥፊ፣ የሰላም ጠባቂ፣ እና የሁሉም በረከቶች ግምጃ ቤት ነው።
🗣 ለመስቀሉ ምስጋና ይግባውና ከእንግዲህ በምድረ በዳ አንንከራተትም፣ ምክንያቱም እውነተኛውን መንገድ አግኝተናልና፤ ከእንግዲህ ከ መንግሥቱ ውጪ አንኖርም፣ ምክንያቱም ደጁን አግኝተናልና፤ የእሳታማ የሰይጣንን ፍላጻ አንፈራም፣ ምክንያቱም የምንጭ መገኛውን አይተናልና።
🗣 በመስቀል ምክንያት:- ከእንግዲህ ወዲያ መበለቶች አይደለንም፣ ምክንያቱም ሙሽራውን ተቀብለናልና፤ ተኩላውን አንፈራም፣ ምክንያቱም መልካሙ እረኛ አለንና። እርሱም፡— “እኔ መልካም እረኛ ነኝ” [ዮሐ. 10:11] ብሏልና።
🗣 በመስቀል ምክንያት፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጨካኙን አንፈራም፣ ምክንያቱም በንጉሡ አጠገብ ነንና። ለእነዚህ ምክንያቶች ነው የምናከብረው፣ እናም መስቀልን የምናስበው።
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: ትምህርት በእንተ መስቀል ወፈያታይ ዘየማን- On the Cross and the Thief)
62 · እኛ ኦርቶዶክሳውያን አቋማችን ይሄ ነው
በመስቀል የተሰቀለውን ኢየሱስን እናመልከዋለን እንገዛለታለን እንንበረክለታለን
ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ደሞ እናከብረዋለን የጌታ እግር ለቆመበትም (መስቀሉ)እንሰግድለታለን:-
እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።”
— መዝሙር 132፥7
መስቀልከ ይኲነነ ቤዛ
መስቀልህ ጥላ ይሁነን
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ
መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ
✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15(ዘሞጆ
1.3K · Фотография
click to show
click to show
እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆች
«የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድነው ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።»
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1:18
#ዛሬ ማታ ስለ ክቡር መስቀሉ በሰፊው የምንማርበት ልዩ መረሃ ግብር ተዘጋጅቷል
#በመስቀል ዙሪያ የተኛውንም ጥያቄ በውስጥ ላኩልን ማታ ምላሽ ይሰጥበታል @Maranatha1921
#በሊቀ ሊቃውንት መምህር ሰለሞን ፈጠነ
#ዛሬ ማታ ከምሽቱ 3:30 ስዓት ጀምሮ
ሼር ሼር ሼር 👇👇👇 https://t.me/awude_wengel_media_21
🛑ዐወደ ወንጌል ሚዲያ🛑
285 · ❤️ኢዮብ ተሰቃየ ግን በእምነቱ ጸና
በህይወታችን መንገድ ላይ የሚያጋጥሙን ከባድ ፈተናዎች በእምነታችን ለመፈተን እንጂ ሊሰብሩን አይመጡም
በካንሰር ተይዛ አልቅሳ ብዙዎችን ያስለቀሰችዋ ህፃን ከካንሰር ነፃ እንደሆነች እንደዳነች በራሷ አንደበት ተናግራለች
ደግፊኝ እናቴ ይሙላልኝ ጉድለቴ እያለች በእንባ እያለቀሰች እመብርሃንን ስትማፀን ነበር
ያመነቻት ድንግል ማርያም አላሳፈረቻትም ዛሬ ተፈውሳ ለቅሶዋ በሳቅ ተቀይሯል።
የደም ካንሰር ብዙ ጊዜ ቀዶ ጥገና ተደርጎ መቅኔ ተቀይሮ የሚድን በሽታ ቢሆንም እሷ ግን ህንድ ድረስ መቅኔ ለማስቀየር ብትሄድም ምንም አይነት ቀዶ ጥገና ሳታደርግ በሽታው ከውስጧ ጠፍቷል።
እልልልልልልልልል👏👏👏👏እንኳንም ድንግል ማርያም ሰማችሽ
እንኳንም እግዚአብሔር ፈወሰሽ 🙏🙏🙏🙏
27 September 2026
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ
ቤተክርስቲያን የመስቀልን በዓል ስናከብር ምን እንድናስብ ታስተምራለች
1ኛ ትዕግስት እንድናስብ ታደርገናለች
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ታላቅ የሆነውን ትዕግስቱን አሳይቶናል ማጥፋት እየቻለ በዝምታ አለፋቸው
መፅሐፍ እግዚአብሔር ትዕግስተኛ ነው ይላልና (ናሆ 1:3) እንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስ ለሌሎች በእርሱ እንዲያምኑ ምስሌ ይሆነ ዘንድ ትዕግስቱን አበዛልኝ ይላል 1ኛ ጢሞ 1:16
2ተኛ ትህትናን ነው :-በመስቀል ላይ በመሆን ፍፁም የሆነ ትህትናውን አሳይቶናል ሀያል ሆኖ እንኳ ተተፋበት እንደሚሸልቱት በግ ዝም ብሎ ተነዳላቸው
ሐዋርያው ለመስቀል ሞት ታዘዘ እንዲል “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።”
— ፊልጵስዩስ 2፥8
3ተኛ ፍቅር ነው :- ክርስቶስ በመስቀል ላን ሆነ ለሰዎች ልጆች ያለውን ፍፁም ፍቅር አሳይቶናል ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ
“በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥9
እንዲሁም ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ይገልፃል
“ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”
— ሮሜ 5፥8
4ተኛ ይቅር ባይነትን:- ክስቶስ በመስቀሉ ካሳየንና ካስተማርን ትልቁ ነገር ይቅር ባይነትን ነው የሚተፉበትን የሚሰድቡትን የሚገድሉትን ይቅርታ የለመነ ታላቅ ጌታ
“ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።
— ሉቃስ 23፥34
ስለዚህ በዓሉን ስናስብ እነዚህን ነገሮች ማሰብ ይጠበቅብናል
“በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤”
— ቆላስይስ 2፥14
✍✍ Esuye(ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15 ዘ-ሞጆ
611 · 🌻🌼🌻🌼 መስቀል፣ የሕይወታችን፣ የኃይላችንና የጽናታችን አርማ🥀🌼🌻🌼🌻🌼🥀🌼🌻🥀🌼🌻🥀🌼
በመስቀሉ ድውይ ከተፈወሰ፣ ሽባው ተተርትሮ ከሄደ፣ ጎባጣው ከቀና፣ እውሩም ዓይኖቹ በርቶለት ብርሃንን ካየ... ዛሬ በአንተ ዘንድ ያለው የነፍስና የሥጋ ድካም፣ የልብ ስብራትና የሕይወት መዛባት በመስቀሉ ኃይል አይፈወስም ብለህ አትጠራጠር። መስቀል የቀደሙትን ብቻ ሳይሆን ዛሬም የታመመውን የሚያድን፣ የታሰረውን የሚፈታ፣ የተሰበረውን የሚጠግን የማይጎድል የጸጋ ምንጭ ነው። በሕይወትህ የተዛባውና የተጠማዘዘው ነገር ሁሉ በመስቀሉ ሥር ተንበርክከህ ስትጸልይ የቀና ይሆናል። በመስቀሉ ጥል ከተገደለ፣ የእግዚአብሔርና የሰው ልጅ እርቅ ከተከናወነ፣ የእውነተኛ ፍቅር ማኅተምም ከተረጋገጠ... በልብህ ውስጥ ያለው የውጥረትና የሁከት ማዕበል መረጋጋት አለበት። መስቀል የወደቀውን ሕይወት የመታደግና ሰላምን የማስፈን ታላቅ የፍቅር ምስክር ነው። የትኛውም የዓለም ሁከትና የውስጥ ጭንቀት በመስቀሉ ላይ በተገለጠው ታላቅ ፍቅር ፊት ይቀልጣል። ፍቅር ያሸንፋል፤ በእርቅ የታተመው ሰላምም ልብህንና አእምሮህን ይጠብቃል።
መስቀል ለእኛ አምባችን፣ ክብራችንና መለያችን ነው። ዓለም መስቀልን የውርደትና የመከራ ምልክት አድርጋ ስታስበው፣ ለእኛ ግን የድል አክሊላችን፣ የጽናታችን መሠረትና የኃይላችን ምንጭ ነው። አቅም አጥተህ በተዋረድክበት፣ የሰው ልጅ ንቆ በተወህና ብቸኛ በሆንክበት ወቅት ሁሉ መስቀልን ተመልከት። በእሱ ላይ የተከፈለው ዋጋ ያንተን ታላቅነትና ክብር ያሳያል። አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ ውድ ነህ፤ ክብሩም በልብህ ላይ ታትሟል። መስቀል ለእኛ ከሞት ማምለጫችን፣ የዲያብሎስንና የጨለማውን ኃይል መምቻ ቀስታችን ነው። የትኛውም ተስፋ የሚያስቆርጥ መንፈስ፣ ፍርሃትና የጨለማ ውጊያ በፊቱ ሊቆም አይችልም። በመስቀል የተሸነፈው ጠላት ዛሬ በዛቻና በፈተና ሊያስፈራህ ቢሞክር እንኳን እንዳትደነግጥ፤ ቀስቱ ተሰብሯል፣ ኃይሉም ተደምስሷል። በሕይወትህ በሚመጣው የትኛውም ማዕበል ውስጥ መስቀልን አጥብቀህ ያዝ፤ እሱ ከውደቅ፣ ከሞትና ከሥጋት የሚያመልጥበት ታላቅ አምባህ ነው።
መስቀል ለእኛ ክርስቶስንና ታላቁን የምሕረት ሥራውን ለዓለም የምናሳይበት ሕያው ምስክርነታችን ነው። በፍቅር፣ በትሕትና፣ በይቅርታና በጽናት ስንኖር የሕያው አምላክን መልክ በሕይወታችን እናሳያለን። በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍቅርህና በጽናትህ ውስጥ የክርስቶስን ብርሃን ያያሉ። መስቀልን መሸከም ማለት ሕይወትን በፍቅር፣ በጽናትና በብርሃን መኖር ማለት ነው። በመስቀሉ ላይ የተፈፀመው ታላቅ የፍቅር ሥራ የዓለምን ሞትና ውድቀት ወደ ሕይወትና ድል እንደለወጠው ሁሉ፣ አሁን ያለህበት የሐዘንና የጨለማ ምዕራፍም ወደ ታላቅ ደስታ ይለወጣል። መስቀል ተስፋ ቢስነት የሚያበቃበት፣ አዲስ ሕይወትና አዲስ ጸጋ የሚበቅልበት የመዳን መድረክ ነው። ዛሬ በዓይኖችህ የሚፈሰው የሐዘን እምባ፣ ነገ በምስጋናና በደስታ በሚፈነዝር አፍህ ይተካል፤ ምክንያቱም የመስቀሉ ኃይል በነፍስህ ላይ አዲስ ተስፋንና ሕይወትን ስለሚዘራ።
መስቀል የኃጢአትንና የዲያብሎስን የባርነት እሰራት የሰበረ ታላቅ የነፃነት ምልክት ነው። በልብህ ውስጥ ያለው የፍርሃት፣ የጭንቀት፣ የሱስ ወይም የድካም እስራት ዘላቂ ሊሆን አይችልም። በመስቀሉ የተሰጠህ ነፃነት ከማንኛውም የምድር እስራት በላይ ነው፤ ስለዚህ በእስራትህ ላይ አትኮርኩር፣ ይልቁንስ በመስቀሉ ኃይል ከእስራትህ ተፈትተህ በነፃነት ተመላለስ። የወደቀበትን ሰንሰለት ሰብሮ ለመነሳት የመስቀሉን ኃይል እመንደር። በሕይወትህ ጉዞ ውስጥ የት መሄድ እንዳለብህ ግራ ሲገባህ፣ አቅጣጫህ ሲጠፋ