English
Open in Telegram
አአለ ሕግ

አለ ሕግ

@AleHig · channel · Education · indexed since 2026-07-31
16 354subscribers
2 979average post reach
18.2%ER — reach to subscribers
29posts in 30 days
አ
አለ ሕግ
File
HOTEL OCCUPANCY DECLARATION FORM.xlsx · 72 KB · click to show
4 · 1K ·
አ
አለ ሕግ
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን፣ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ ----------------------- (ዜና ፓርላማ) መስከረም 27፣ 2019 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባው ነው ያፀደቀው፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የመንግሥት ተወካይ የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ግልጽና ውጤታማ የሆነ የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት በመፍጠር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና የተጠሪ ተቋማት የውልና የተናጠል ተግባር በግልጽ በማስቀመጥ ረገድ ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት እና ዓላማ በተመለከተ አስረጂ ሆነው የቀረቡት የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የተከበሩ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እና ክብርት ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ በዝርዝር ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ በመንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት መስሪያ ቤቶች በአለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የታዩትን ውስንነቶች ለመቅረፍ ረቂቅ አዋጁ እንደሚያግዝ እና የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲአዊ መብቶች እንዲከበሩና የህዝቡ የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል እና የአገልግሎት ዘርፉን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ሰፊ ጥናት የተደረገበት እና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር ውይይት በማድረግ በቂ ግብአት ማግኘት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ የተቋማትን አደረጃጀት በግልጽ ማስቀመጥ የመንግስትና የህዝብ ሃብት የስራ ኃላፊዎች በአግባብ እንዲጠቀሙ ለማስቻል ረቂቅ አዋጁ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡ የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ አንዳንድ የተጠሪ ተቋማት ለወጥ በደንብ የስራ ባህሪያቸውን እና ያላቸውን ፋይዳ ያገናዘበ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ቀልጣፋና ውጤታማ አደረጃጀት በመፍጠር የተቋማትን የማስፈጸም አቅምን ለማሳደግ ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን የምክር ቤት አባላቱ አያይዘውም ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ ባካሄደው ልዩ ስብሰባው፤ የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት ፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1440/2019 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ (በ መኩሪያ ፈንታ) FDREHOPR www.hopr.gov.et
6 · 4.8K ·
አ
አለ ሕግ
Photo
“ፍትሕ ለሃገሬ” ላለፉት አምስት ዓመታት ገደማ አቅሜ በፈቀደና በገባኝ ልክ ከብዙ ውጣ ውረድና ጫናዎችጋ እየሰራሁ እዚህ ደርሷል። በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም. ጠዋት 2:30 ተኩል ላይ ደግሞ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ቫምዳስ ሲኒማ ፕሮግራሙን ለማስቀጠልና ለማሻሻል በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ከእናንተ ጋር ለመወያየት ፕሮግራም ይዘናል። ፍትሕ ለሃገሬን በሀሳብ፣ እንግዳ ሆኖ በመቅረብ፣ ይጠቅማታል ድካሟን ያቀልላታል ብላችሁ ባሰባችሁት ያገዛችሁኝ እና ፕሮግራሙ ጥቅም አለው ብላችሁ የምታምኑ የሕግ ባለሙያ ባልደረቦቼ ሁሉ በእለቱ ተገኝታችሁ የማሻሽለውን፣ “ቢሆን ጥሩ ነው”፣ “ይሄ ቢቀር ይሄ ቢጨመር” የምትሉትን እንድታካፍሉኝ በአክብሮት ጋብዣችኋለሁ። #ፍትሕለሃገሬ @Alehig
4 · 2.9K ·
📌 ያለ ሰላም ይኖራል❓⁉️ አንዳንዶች "ሕግ ነፃነቴን ይገድባል" ይላሉ፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ቦታ እውነተኛ ሰላም ሊኖር አይችልም‼️ ሕግ የሌለበት ሰላም🔽ጊዜያዊ ወይም በኃይለኞች ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የውሸት እፎይታ ነው። ሕግና ፍትሕ ሲኖሩ ✏️የሁሉም ሰው መብት ይከበራል፤ የሕግ የበላይነት ባለበት ቦታ ደግሞ ዘላቂ ሰላም ይነግሣል። ሕግ ሰላምን የሚጠብቅ አጥር እንጂ ነፃነትን የሚያስር እሰር አይደለም። ያለ ሕግ አክባሪ እና አስከባሪ ያለ ሕግ የበላይነት ዘላቂ ሰላምን ማሰብ አይቻልም‼️ 💬 እርስዎ ምን ያሰባሉ? ሰላም ከሕግ ይመነጫል ወይስ ሕግ ከሰላም? አስተያየትዎን በኮመንት ያጋሩን! 👇 🌍 Different voices. Different views. One shared humanity. #ሕግ #ሰላም #የሕግበላይነት #ፍትሕ #PeaceAndLaw #RuleOfLaw #Justice #Ileadpeace #PeaceStartsWithMe #YouthForPeace #PeacefulCommunities #AyreseTechShow #DignityForLife #GNRC #Arigatou
13 · 3.7K ·
Photo
የተሻሻለው አዲሱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ እና የማስረጃ ሕግ 1410/2018ዓ.ም የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ዓ/ም #Click Ethiopian Laws 👇👇👇👇👇👇👇
❤5
7 · 3K ·
File
የተሻሻለው_የወንጀል_ስነ_ስርዓትና_የማስረጃ_ህግ_የታተመ.pdf · 24.7 MB · click to show
🙏11
63 · 3.2K ·
አ
File
1051_ከተሽከርካሪ_የሚወጣ_በካይ_ጋዝ_ልቀት_ቁጥጥር_መመሪያ_ቁጥር_1051_2017.pdf · 474 KB · click to show
File
Article on Torture .pdf · 194 KB · click to show
ከተሽከርካሪ የሚወጣ በካይ ጋዝ ልቀት ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1051-2017
❤1
12 · 3K ·
አለ ሕግ
ሕግ ሰላምን ይጠብቃል፣ ሰላም ደግሞ ሕግ እንዲፈጠርና እንዲጸና ያደርጋል✍️‼️
❤1
2.6K ·
ሰላም ሚኪ ዳግም እባላለሁ የህግ ባለሙያ ነኝ ይህ ቪዲዮ INSA ባዘጋጀው የሶስት ደቂቃ የቪዲዮ ውድድር  ስለ ህፃናት የኦንላይን ደህንነት ከህጉ አንፃር  የሰራሁት ቪዲዮ ነው። እንዲታይልኝ  አለ ሕግ ግሩፕ ላይ share ብታደርግልኝ አመሰግናለሁ።
❤7
2.3K ·
አ
አለ ሕግ
Photo
ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነ ✍️🙏 @AleHig ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነCapital EthiopiaOct 16, 20263 min readTelegramLinkedInCopy linkኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነለያፒ መርከዚ ኩባንያ እንዲከፈለው ከተወሰነለት ውስጥ 89 ሚሊዮን ዶላር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ለደረሱ ጉዳቶች የሚከፈል ነው ተብሏል።በአዋሽ ኮምቦልቻ ወልደያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ክርክር ጉዳይ በኢትዮጵያ እና በስራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ መካከል ሲካሄድ የቆየው የክስ ሂደት ተጠናቋል፡፡ለንደን በሚገኘው የዓለም አቀፍ ግልግል ዳኝነት የተካሄደው ክርክር 392 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን ፕሮጀክት በ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በተደረገው የስራ ውል አፈጻጸም ላይ አለመግባባት መነሳቱን ተከትሎ ነበር፡፡ስራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግስት ለደረሰበት ጉዳት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፈለው መጠየቁን ተከትሎ ክርክሩ ሲካሄድ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ኢትዮጵያ የያፒ መርከዚ ክስን ተከትሎ 400 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ጥያቄ አቅርባ እንደነበር ካፒታል ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሰምታለች፡፡ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራር እንዳሉት ላለፉት አራት ዓመታት በለንደን ሲካሄድ የቆየው ክርክር ባሳለፍነው መስከረም 23 ቀን 2026 ተጠናቋል፡፡በዚህ ውሳኔ መሰረትም ኢትዮጵያ ለያፒ መርከዚ የዘጠኝ በመቶ ወለድን ጨምሮ 242 ሚሊዮን ዶላር የጉዳት ካሳ እንድትከፍል ተወስኗል።ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ለያፒ መርከዚ ኩባንያ በቅድመ ክፍያ መልኩ ለኩባንያው ከፍላው የነበረው 29 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር እንዲመለስላትም ተወስኗል፡፡ Read More Source: Capital Ethiopia via #Ethiopianbusinessdaily
❤4👍3💔2
6 · 2K ·
አ
አለ ሕግ
File
የIMF አዲስ የ2026 የኢኮኖሚ ትንበያ.pdf · 7.8 MB · click to show
#ለመረጃ፡ የIMF አዲስ የ2026 የኢኮኖሚ ትንበያ ሰነድ ማንበብ ለምትፈልጉ ከላይ ሙሉ ሰነዱን ታገኛላችሁ!
👏6❤1
11 · 1.8K ·
አለ ሕግ
Photo
#ለመረጃ: ለአትክልት እና ፍራፍሬ ማቀናበር እና ማቆየት የሥራ ዘርፍ የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ደብዳቤ አውጥቷል! መመሪያ ቁጥር 1064/2017 የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ተቀምጧል!
❤3👏1
3 · 1.3K ·
አ
File
ኢንቨስትመንትት_ማበረታቻን_ለማስፈጸም_የወጣ_መመሪያ_3.pdf · 546 KB · click to show
👏2
13 · 1.4K ·
አ
አለ ሕግ
Photo
Photo
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ቀን ሊከበር ነው! ⚖️💎 በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ጠበቆች አምረው፣ ደምቀው እና ተውበው በሚታዩበት ልዩ ቀን‼️ ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበው ታላቅ "የጠበቆች ቀን" (Lawyers' Day) በቅርብ ቀናት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ መሆኑን በዝግጅት ኮሚቴው ይፋ ሆነ! ✔️💎 ጠበቆች በሀገር ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በፍትህ ማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና የማይተካ በመሆኑ፤ የሙያዊ ህብረት እና አወንታዊ ተፎካካሪነትን ማሳደግ፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍትሔ መስጠት እና የሙያ ትስስራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጠበቆች ቀን ተዘጋጅቷል‼️ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታሪካዊ መርሃ-ግብር የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በፌዴራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅነት ሁሉም ጠበቆች የሚታደሙበት የማይረሳ ምሽት ይሆናል! 🍷ይህ ደማቅ ፕሮግራም ምን ምን ያካተተ ነው?⁉️ 🍽 የራት ግብዣ (Gala Dinner) 🎶 የተለያዩ ማራኪ የመዝናኛ ፕሮግራሞች 🤝 የኔትወርኪንግና የእርስ በእርስ ትውውቅ መድረክ 📺 የሀገር ውስጥና የውጭ ትልልቅ ሚዲያዎች ሽፋን ⚖️ የፍትሃዊነትና የጠበቆችን ማህበራዊ ሚና ማጎልበቻ ውይይቶች ቀን እና ቦታው በጥቂት ቀናት ልዩነት ይፋ ይደረጋል!💡 #የኢትዮጵያፌዴራልጠበቆች #የጠበቆችቀን #FirstLawyersDay #EthiopianLawyers #Networking #GalaDinner #LegalExcellence
❤2
1 · 584 ·
አ
አለ ሕግ
Photo
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ውስጥ ግብይት እንዴት እንደሚከናወን፣ ስርዓቶቹና ሂደቶቹስ ምንድናቸው? የሚሉትን ቁልፍ ሀሳቦች በዛሬው የኢንቨስትመንት ትምህርት ክፍላችን የምንዳስሰው ይሆናል። በዚህ የትምህርት ክፍል፤ በገበያው ላይ የግብይት ዑደት (Trading Cycle) ክንውኖችን እና ዋና ዋና ደረጃዎችን በዝርዝር የምናይ ሲሆን፤ የግዢ እና የሽያጭ ትዕዛዞች በስርዓቱ ውስጥ እንዴት እንደሚዛመዱ፣ የግብይት አገናኝ አባላትን (Trading Members) ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ግብይት ስፈጸም (Trade Execution) እና በኋላ ባሉት ሂደቶች (Post-trade Settlement and Clearing) መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ እንመለከታለን። Read More Source: Ethiopian Securities Exchange Telegram #Ethiopianbusinessdaily https://t.me/AleHig 🙏 https://t.me/AleHig ✍️ https://t.me/AleHig ✅
❤2
5 · 1.2K ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count