Photo
📚መጽሐፍትን ማንበብ ከሌሎች ዘዴዎች በተሻለ እራስን ዘና አድርጎ ጭንቀትን ለመቀነስ ፍቱን መፍትሄ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
📚በሀገረ ብሪታንያ ባሉ ተመራማሪዎች በተገኘው ጥናት ቢያንስ ለስድስት
ደቂቃ በፀጥታ ማንኛውንም መጽሐፍ ማንበብ 68% የሚሆነውን የጭንቀት ደረጃ ለመቀነስ እንደሚያስችል ተረጋግጧል፡፡
እንደ ጥናቱ ግኝት ከሆነ፦
#ሙዚቃ ማዳመጥ በ61%
#አንድሲኒ ቡና መጠጣት በ54%
#መራመድ በ42% ጭንቀትን
የመቀነስ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
14 · 3.1K · አምባ መፅሐፍ
Photo
🟡 ከፍ ያለ ቦታ ላይ ስትሆን ኩራት (PRIDE) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ኩራት አንተ የደረስክበት የስኬት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ሰዎችን በንቀት እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡
🔴 ታችኛው ክፍል ላይ ስትሆን ፣ ምሬት (BITTERNESS) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ምሬት ቅናት እንዲሰማህ እና አንተ ያልተሳካልህ በሌሎች ሰዎች ምክንያት እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል፡፡
🟡 ወደ ላይኛው መንገድ ስትጓዝ ስግብግብነት (GREED) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ስግብግብነት ትዕግሥት ያሳጣሃል እናም እንድትሰርቅ ወይም አቋራጮችን እንድትፈልግ ያደርግሃል።
🔵ወደ ታች በምትወርድበት ጊዜ ፣ ተስፋ መቁረጥ (DESPAIR) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ፣ ሁሉም ነገር ተጠናቋል ብለህ እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።
✍️ኔልሰን ማንዴላ
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
26 · 3K · Reply✨✨ፍቅር ቅብ✨✨
የመጨረሻው ክፍል✨
"አንድ አንዴ ይቅር የምንለው እንዲሁ ነው....እንዲሁ.....ለምን እንደተተውን ሳናውቅ.....ለምን እንደሄዱ ሳናውቅ.....ለምን እንዳስለቀሱን ሳናውቅ እንዲሁ".....ያለኝ መክብብ ነበር.....በነጋታው ካፌ ተገናኝተን ስለሆነው ሁሉ ሳጫውተው ነበር....እውነቱን ነው....አንድ አንዴ እንዲህ ነው....ሳናውቅ ይቅር ማለት ያለብን ይበዛል.....ሁሉን ካወቅንማ ይቅር አንልምም ይሆናል....
ቢሆንም ግን እናቴን ይቅር ማለት
ሰላም ቤተሰብ❕
ከዚህ በፊት ስንለቅ የነበረው <<ፍቅር ቅብ>> የተሰኘው ተከታይ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ድርሰት በእናንተ ተሳትፎ ተወዳጅ እንደነበር ተመልክተናል ።📖
እናም በዚህ መሰረት <<የልብ እዳ>> የተሰኘ አዲስ ተከታይ ድርሰት ይዘንላችሁ ልንመጣ አስበናል ። 📖
እስኪ ቤተሰብ አድሱን ድርሰት ለማንበብ ጓጉታችኋል ?👀
ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት በ react ❤️ እና በ comment💬 አሳውቁን 👇👇👇
2.7K · 📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ብላችሁ ታስባላችሁ ❓
2.3K · አምባ መፅሐፍ
Photo
...አየህ_ልጄ!
🔴የፈለከውን ነገር ብታገኝም የሚቀር ነገር መኖሩ እሙን ነው።
ምስጢራትን ሁሉ ያወቅክ ቢመስልህም በዚህ አለም ከአንተ ህሊና የተደበቀ ብዙ ነገር ይኖራል። እናም የሚሻለው፦
➡️የምትጠቀምበት ያክል ብቻ እወቅ፣
➡️የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፣
➡️የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ።
ሁሉንም ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም
ሁሉንም ነገር ማግኘትም እዳ ይሆናል፤
ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም
ሁሉንም ማወቅ ደግሞ ሸክም ይሆናል።
👌 #ሁሉ_በልክ_ሁሉ_በመጠን_ሲሆን_ይሆናል_መልካሙን_የሚሰጠን።
ሰናይ ቀን ተመኘው!!!
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
8 · 1.6K · 🔥 የልብ እዳ 🔥
አባተ ከሰርግ ሳይሆን ከልቅሶ ቤት የተመለሰ ያህል ተክዞአል፤ እኒያ በራሱ ተነግረው ራሱን የሚያስቁ ቀልዶቹም የሉም፤ብቻ ዝምብሎ ከሰርግ ቤት ይዞት የተመለሰውን የሙሽሮች ፎቶግራፍ ይዞ ይተክዛል። ጩኸት ያስለመደ ሰው ዝምታው ለደቂቃም ቢሆን ስለሚከብድ፤ የወሬ መነሻው የጠፋው ይመስል ለወሬ መንደርደሪያ ለመስጠት ያህል
" ሰርግ እንዴት ነበር" ስለው፤ቀና ብሎ አየኝና
"እእ አሪፍ ነበር" ካለ በሁዋላ ከመሬቱ ላይ መርፌ ይፈልግ ይመስል አይኑን መሬት ላይ አፍጥጦ እግሩንም እጁንም አጣምሮ ዳግም ይተክዝ ያዘ። የዚህ ልጅ ነገር አልጣመኝም፤እኔ እንደሁ እንደሱ ጨዋታ ፈጥሮ ማሳሳቅ አይሆንልኝም፤ቤቱ መቃብር መሰለ፤ላነብበው የያዝኩት መጽሐፍ አስጠላኝ፤ይሄኔ የቴሌቪዥኑን ሪሞት ኮንትሮል አንስቼ ፊልም ማሰሴን ጀመርኩ፤አባተ አይኑን ከመሬት አንስቶ ከቴሌቪዥኑ አኖረና ከቻናል ቻናል ስዘል ይመለከታል። አይኑ ወደቴሌቪዥኑ መመለሱን አይቼ በብሽቀት ካናገርኩት ብዬ የቴሌቪዥኑን ጣቢያ የችግር ቋት ብሎ ወደሚጠራቸው ወደ ዜና ጣቢያዎች አዙሬ የተመቸኝ ያህል እመለከት ያዝኩ፤ ምንም አላለኝ። አሁንም አይኑ ቴሌቪዥኑ ላይ እንደተሰካ ነው። ጭንቅ ያዘኝ ከዚያም ዳር ዳር ከመሄድ እንቅጩን የሆነውን ለምን አልጠይቀውም ስል አሰብኩና፤ አጠያየቄን ቀልድ ለማላበስ በማሰብ
"ምነው የምታፈቅራት ልጅ ናት እንዴ የተዳረችው ?" እንዳልኩ ከተቀመጠበት የመስፈንጠር ያህል ቀና ብሎ
"በምን አወቅክ ?" እንዲህ ተጨንቆም ጨዋታ አለማጣቱ አስገርሞኝ ከወሬው በሳቅ ተባበርኩ፤አይኑ ከቴሌቭዥኑ ነቅሎ እኔ ላይ አፈጠጠና
"ምን አባህ ያስገለፍጥሃል ?"
"አይ አቤ ከስንቷ ጋር እንዳልነበርክ ሙሽራ ላይ ይጣልህ !?"
"ምን አይነት ወሬ ነው የምታወራው...ቆይ ማነው እንደዚህ ብሎ የነገረህ ?"
"ቅድም በሰመመን ስታወራ ሰምቼ ነው"
"ቡዳ ነህ !" በሽቆ ነበር ይሄኔ የምሬን ሳቅ አንገላታኝ። አባተን ማብሸቅ ቀላል አልነበረም አብረን መኖር ከጀመርን አንስቶ እሱን ለማናደድ ጨዋታ አንስቼ፤ነገሩን ወደራሴ አዙሮ እኔ ነበርኩ የምነድደው። ዛሬ ግዳዬን የጣልኩ ያህል ጀግንነት ስለተሰማኝ፤የቀልድ ጅራፌን ማጮሄን ቀጠልኩ
"ታውቃለህ ይሄኔ እሷ ከባሏ ጋር...ትንፋሽ አጥሯት፤በፍቅር ረጥባ የፍቅርን ዜማ ለባሏ እያንጎራጎረች ነው" አባተ ከተቀመጠበት ተነሳና ፊልም ላይ እንደሚታዩት አፍቃሪ ወንዶች ከፍሪጁ መጠጥ አወጣና መጠጣት ጀመረ። ሆኖም ይጠጣ የነበረው ለስላሳ ነበር፤ አባተ ከባለስልጣኑ ልጅ ጋር መውጣት ከጀመረ ወዲህ እቤት ውስጥ ቅምቀማ ትተናል፤ከፍሪጁ የቀሩትን የተውሶ የቢራ ጠርሙሶች ብቸኝነት ሲያንገላታኝ አንድ ሁለት ስል እኔ ነኝ የጨርስኳቸው። አባተ ፍለጋው መሻቱን ባይሞላለትም ያገኘውን የኮካ ጠርሙስ በአንድ ትንፋሽ ተጋተና በሙሉ አካሉ እየተውለበለበ ያጋሳ ጀመር። ከመሳቅ ውጭ ምርጫ አልነበረኝም፤ይሄኔ የግዱን ሳቀና
"ዛሬ ጥርስ በጥርስ ሆነሃል...ምን የሚያስገጥጥ ነገር ተገኘ" ነገረኛነቱ ጀመረው
"ለማግጠጥ ዛሬ ካንተ በላይ ምን ምክንያት ያስፈልጋል ?" ላለመረታት መለስኩ፤እሱ መች ይረታል በሹፈት አይን እያየኝ
"እርሟን ብታፈላ አተላ በዛባት" አለኝና፤
"ዛሬን ብታገኘኝ አሳሬን ታበላኝ !?" ንግግሩ አናደደኝ፤ የሆነ ነገር ብዬ ላስቀይመው ፈለግኩ፤ለጊዜው የመጣልኝ መላ የጀመርኩትን ማብሸቂያ ቀዳዳ ማስፋት ነበረና
"ቆይ አንተ ምን ስትል ሙሽራ ላይ አንጠለጠለህ" የሚመጣውን መልስ ለመቀበል ቆፍጠን ብዬ። አባተ አልሰደበኝም፤እዛው በቆመበት ፍሪጁን ተደግፎ
"የመጀመሪያ ፍቅረኛዬ ነበረች እኮ ያኔ ሴት ልጅን እንዴት መያዝ እንደምችል ባለማወቄ … Read in full →
❤50👍9🥰5🔥1
11 · 5.2K · አምባ መፅሐፍ
Photo
#3ቱ_የፍቅር_ሕይወቶች
💎 የፍቅር ህይወትህ የደስታህ መሰረት ነው። ፍቅር የተለያዩ ሰዎች የሚተሳሰቡበት የስሜት ትስስር አለው። ፍቅር በግፊት ሊሆን አይችልም። ብዙዎች ለዚህ ሰዋዊ ስሜት ትኩረት አይሰጡም ይህ ከባድ አደጋ አለው።
የፍቅር ህይወትህ የተሻለና የምትወደው እንዲሆን እኒህን ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ተለማመድ።
#1_ጠባቂ_አለመሆንን።
➡️ በሰጠኸው ልክ ለመቀበል አትጓጓ። ያ ውስጥህን የሚያከስም ሊሆን ይችላል። ማድረግ ያለብህን በፍቅር ስታደርግ ምላሽ ለማግኘት አይሁን። ደስታህ ከመስጠትህ ላይ ብቻ ይሁን።
#2_ሙጥኝ_አለማለትን።
➡️ ይህን እውነት ተቀበል። የወደድከው ሁሉ ሊወድህ... ያከበርከው ሁሉ ሊያከብርህ... የፈለከው ሁሉ ሊፈልግህ ግዴታው አይደለም። አንተ ያለህን ያህል ሁሉም ሰው የራሱ ፍላጎትና ምርጫ አለው። ሰዎች ምርጫቸው ካላደረጉህ ያ ያንተ ችግር ሊሆን አይገባም። አቅጣጫህን ቀይር እንጂ ሙጥኝ በማለት ራስህን የሌሎች ፈተና አታድርግ።
#3_ራስህን_መውደድ።
➡️ ራስህን መውደድ አለብህ። ይህ ሀጢአት አይደለም። ራስህን ስትወድ ለሌሎች የምትሰጠው ቦታ ልክ ይኖረዋል። ሰዎችም ሊወዱህ ይገደዳሉ ምክንያቱም በልካቸው ስለምትወዳቸው። ራስህን መውደድ ስትጀምር ሌሎች ባይወዱህ ብቸኝነት አይሰማህም ምክንያቱም መቼም የማይጠላህ ትክክለኛ ወዳጅ እንዳለህ አውቀሃልና።
📚የሕይወት_ኬሚስትሪ
©ምንጭ ተክሉ ጥላሁን
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
❤35👍9💯2🔥2
36 · 5.7K · አምባ መፅሐፍ
Replyቤተሰብ 👨👩👧👦 አስደሳች ነገር ላሳያችሁ እያሰብኩ ነው ...! 👀📚ከእንግዲህ በኋላ ቋንቋ አልችል ብሎ ነገር የለም ❕
ወድ የአምባ ቤተሰቦች ❕
የፈለጋችሁትን መፅሐፍ ወደ መረጣችሁት ቋንቋ ተርጉማችሁ በPDF መልክ ማውረድ ወይንም በቀጥታ በድረ ገፅ ላይ ማንበብ የምትችሉበትን መድረግ በቅርቡ እናስተዋውቃለን ።
ከዚህ በኋላ በቋንቋ ምክኒያት ማንበብ የፈለጋችሁትን መጽሐፍ እንዳያመልጣቸው አድስ አማራጭ ይዘንላችሁ መጥተናል ።
በቅርቡ በአምባ መፅሐፍ ❕
እስኪ ለዚህ አዲስ ስራችን ያላችሁን ድጋፍ
ሀሳብ በ React እና comment ላይ አጋሩን ።
👇👇👇
❤79👍26👏4😘3💯1
2 · 4.6K · Reply📚ከእንግዲህ በኋላ ቋንቋ አልችል ብሎ ነገር የለም ❕
ወድ የአምባ ቤተሰቦች ❕
የፈለጋችሁትን መፅሐፍ ወደ መረጣችሁት ቋንቋ ተርጉማችሁ በPDF መልክ ማውረድ ወይንም በቀጥታ በድረ ገፅ ላይ ማንበብ የምትችሉበትን መድረግ በቅርቡ እናስተዋውቃለን ።
ከዚህ በኋላ በቋንቋ ምክኒያት ማንበብ የፈለጋችሁትን መጽሐፍ እንዳያመልጣቸው አድስ አማራጭ ይዘንላችሁ መጥተናል ።
በቅርቡ በአምባ መፅሐፍ ❕
እስኪ ለዚህ አዲስ ስራችን ያላችሁን ድጋፍ
ሀሳብ በ React እና comment
📖 እዚህ ላይ አንድ ግልፅ የማደርግላችሁ !👀
ወድ የአምባ ቤተሰቦች ❕
በቅርቡ የምናጋራችሁ ድረ ገፅ ከሌሎች የመጽሀፍ ትርጉም ድረ ገጾች ና እንደ AI ያሉ የትርጉም መሳራያወች የሚለየው ምንድ ነው ?🤔
ይሄ ጥያቄ ትጠይቃላችሁ ብየ እገምታለሁ ። እኔም ይሄን ጥያቄ አስፈላጊ ስለሆነ ራሴ ጠይቄዋለሁ ።
✅ስለዚህ ድረ ገጹ የሚሰጠውን ጥቅምና ልዩ ባህሪያት በተለይም ለመጽሐፍ አፍቃሪዎች የሚኖረውን ጥቅም ወደ እናተ እጋራለሁ ።
አብራችሁን ቆዩ ❤️
መልካም ምሽት 🌃
❤27🔥3
4.2K · Reply📖 እዚህ ላይ አንድ ግልፅ የማደርግላችሁ !👀
ወድ የአምባ ቤተሰቦች ❕
በቅርቡ የምናጋራችሁ ድረ ገፅ ከሌሎች የመጽሀፍ ትርጉም ድረ ገጾች ና እንደ AI ያሉ የትርጉም መሳራያወች የሚለየው ምንድ ነው ?🤔
ይሄ ጥያቄ ትጠይቃላችሁ ብየ እገምታለሁ ። እኔም ይሄን ጥያቄ አስፈላጊ ስለሆነ ራሴ ጠይቄዋለሁ ።
✅ስለዚህ ድረ ገጹ የሚሰጠውን ጥቅምና ልዩ ባህሪያት በተለይም ለመጽሐፍ አፍቃሪዎች የሚኖረውን ጥቅም ወደ እናተ እጋራለሁ ።
አብራችሁን ቆዩ ❤️
መልካም ምሽት 🌃
1️⃣፣ 📚 የረጅም ጽሑፎች ትርጉም
እጅግ ረጅም ጽሑፎችንና የተለያዩ ውስብስብ ቅርጸቶች ያሏቸውን ፋይሎች መተርጎም ይደግፋል። ሙሉ ልቦለዶችንና ረጅም መጻሕፍትን ለማስተርጎም የሚመች ሲሆን፣ ጽሑፉን በእጅ የመከፋፈል፣ ደጋግሞ የመቅዳትና የመለጠፍ፣ እንዲሁም የተተረጎመውን ጽሑፍ የማደራጀት ሥራን ይቀንሳል።
2️⃣፣✍️ የላቁ የትርጉም ቅንብሮች
የቃላት መዝገብ (Glossary) እና የትርጉም ዘይቤ ቅንብሮችን ያቀርባል። እነዚህም የገጸ ባህሪያት ስሞች፣ የቦታ ስሞችና ልዩ ቃላት ወጥ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም ከመጽሐፉ ባህሪ ጋር የሚስማማ አገላለጽ ለመምረጥ ይረዳሉ።
❤10
4.1K · አምባ መፅሐፍ
Photo
📖 እያንዳንዱ ሰው አንድን ነገር በጥሩ ሁኔታ መሥራት ይችላል። በአንዴ ብዙ ቢሞክር ግን በየትኛውም ልዩነት መፍጠር አይችልም።
✍️ ፦ ፖላቶ
✅ትልቁ ቁብነገር ብዙ ነገርን በአንዴ ማድረጉ ሳይሆን፣ አንድን ተግባር በሙሉ ትኩረትና ጥሞና በተመጠነ ሰዓት መከወን መቻል ነው። የጅምር ብዛት ለውጥ አያመጣም፤ ለፍፃሜምም አያደርስም። የትኩረት ሃይል እምቅ አቅም ነው። የሚባክነው ሲበታተንና በተገቢው ስፍራ ሳይውል ሲቀር ነው። ያተኮርክበት ሁሉ ፍሬያማ ሲሆን፣ ችላ ያልከውም በምትኩ ፊቱን ሲያዞርብህና ከውጤት ሲያርቅህ ትመለከታለህ። ትኩረትና ጊዜ የሰጠሀው ማንኛው ነገር የውስጥ ፍላጎትና ውጤትህን የሚወስን ነው።
✅በአንዴ አንድን ብቻ ተግብር፣ መሰረታዊ ልዩነት ባላቸው የተለያዩ ሃሳቦችህ አዕምሮህን አታስጨንቀው፤ ፋታ አታሳጣው፤ እርጋታ አትንሳው። አንድን ተግባር ብቻ በተወሰነ ሰዓት መፈፀም የሚኖርብህ ዋነኛው ምክንያት የትኩረት አቅምህን፣ እምቅ ሃይልህን በሚገባ ለመጠቀም እንዲያስችልህ ነው። ተግባርህ ምንም ይሁን የውጤታማነቱ ሚስጥር ብዛቱ ወይም መደራረቡ ሳይሆን የተሰጠው ትኩረትና በቂ ጊዜ ነው። ከመዳረሻህ የሚያደርስህ ብዙ መንገድ ቢኖርም አንዱንና በይበልጥ ያመንክበትን ጠንቅቀህ ያዝ፤ በዛው መንገድ እስከጥግ ተጓዝ፤ በሙሉ ትኩረትም አቅጣጫህን ወደ አንደኛውና አዋጭ ወዳልከው አዙር።
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
❤30🔥5
10 · 4.1K · 📖ምን መፅሐፍ እያነበባችሁ ነው?✍️
ደራሲውስ ማነው?
3.5K · አምባ መፅሐፍ
📚ምርጥ አሥር (10) የአማርኛ ልቦለዶች
1️⃣.ፍቅር እስከ መቃብር፤ ክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡‹‹አባይን ያላየ ››አለ ያገሬ ሰው፡፡ ዓለም ፍቅር እስከ መቃብርን አንብቦ ቢሆን ሮምዮና ጂሊየት የልጆች ጨዋታ ይሆን ነበር፡፡
2️⃣. 5ቱ የዴርቶጋዳ ክፍሎች (ዴርቶጋዳ :ራሕማቶሃራ: ዣንቶዣን: ዩራቶራድ: ዮቶድ) በ ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ ::
3️⃣. የደራሲ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ ድንቅ ሶስት+1 ተከታታይ መፅሐፍቶች:: እመጎ:ዝጎራ እና መርበብት +ሜተራልዮን :: አገር በቀል እውቀትን መሰረት ያደረጉ መፅሐቶች ናቸው:'
⚪️. የታንጉት ምስጢር፤ ብርሃኑ ዘርይሁን ፡፡ታሪከዊ ልቦለድመፃፍ ካማረህ ብልሃቱን የታንጉት ምስጢር ውስጠ ታገኘዋለህ፡፡
5️⃣. ኦሮማይ፤ በዓሉ ግርማ፡፡የኖርክበትንና የምትኖርበትን ሕይወት ትንሽ ቅመም ጣል አድርገህ በከባድ መስዋዕትነት ለመጻፍ ወኔው ካለህ አዲዮስ-ኦሮማይ!
6⃣. አልወለድም፤ አቤ ጉበኛ፤ ማሕበራዊ ኢፍታሀዊነትን የምትዋጋ ከሆነ ‹‹አልወለድም!›› በል፡፡
7️⃣. ጉንጉን፤ ሀይለመለኮት መዋዕል፤ ለኔ ከሀይለመለኮት ድርሰቶች ከወዲያነሽ ይልቅ ጉንጉን ይበልጣል፡፡ በተለይ የቋንቋው ዘይቤው፡፡
🤩. ሰመመን ፤ሲሳይ ንጉሱ፡፡ የማይረሱ ገጸ-ባሕሪያት እንዴት እንደሚሳሉ ማወቅ ከፈለግህ በሰመመን ተጓዝ፡፡
🤩. ሀሽማል : ከርታታ ኮከቦች....በ ቅኔ ቤቶች መሰረታቸውን የጣሉት ሁለቱ ተያያዥነት ያላቸው መፅሐፍቶች ሲሆኑ በተደራሲያንም ተወዳጅነትን አትርፈዋል:: የደራሲና ባለቅኔ ማዕበል ፈጠነ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው
🔟. ሜሎሪና :ቴሎስ...... ከወጣት ደራሲዎች መካከል አንዱ የሆነው ናሁሰናይ ፀዳሉ::
📏እጅግ ብዙ ተወዳጅና ማራኪ መፅሐፍቶች ቢቀሩም ሚፈለጉት ግን 10 ብቻ ናቸው🙏
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
❤21💯11👎3🔥1
31 · 3.6K · አምባ መፅሐፍ
Reply📖ስንቶቻችሁ ይህንን መፅሐፍ አንብባችሁታል❓
አንብቤዋለሁ ❤️ ፣ አላነበብኩትም 🤝 ፣ ጀምሬው ነበር 👍📚ራማቶሓራ 📚
📝ደራሲ:- ይስማዕከ ወርቁ
📜ዘውግ:- ልቦለድ
🗓ዓ.ም:- 200ው
📜የገፅ ብዛት :- 288
💰ልጥፋ ዋጋ:- ..
🪝Type :- #pdf #ልቦለድ
🔔 ቻናል :- @AmbaBooks|📚
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
❤11
2 · 3.2K · File
ራማቶሓራAmbaBooks.pdf · 112.1 MB · click to show
ራማቶሓራAmbaBooks.pdf · 112.1 MB · click to show
📚ራማቶሓራ 📚
📝ደራሲ:- ይስማዕከ ወርቁ
📜ዘውግ:- ልቦለድ
🗓ዓ.ም:- 200ው
📜የገፅ ብዛት :- 288
💰ልጥፋ ዋጋ:- ..
🪝Type :- #pdf #ልቦለድ
🔔 ቻናል :- @AmbaBooks|📚
📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅
❤6👍2🔥2
9 · 3K · Reply📚ከእንግዲህ በኋላ ቋንቋ አልችል ብሎ ነገር የለም ❕
ወድ የአምባ ቤተሰቦች ❕
የፈለጋችሁትን መፅሐፍ ወደ መረጣችሁት ቋንቋ ተርጉማችሁ በPDF መልክ ማውረድ ወይንም በቀጥታ በድረ ገፅ ላይ ማንበብ የምትችሉበትን መድረግ በቅርቡ እናስተዋውቃለን ።
ከዚህ በኋላ በቋንቋ ምክኒያት ማንበብ የፈለጋችሁትን መጽሐፍ እንዳያመልጣቸው አድስ አማራጭ ይዘንላችሁ መጥተናል ።
በቅርቡ በአምባ መፅሐፍ ❕
እስኪ ለዚህ አዲስ ስራችን ያላችሁን ድጋፍ
ሀሳብ በ React እና comment
Photo
1 · 2.8K · Link
click to show
click to show
📚 Amba Books ከSEKA ጋር በመተባበር አዲስ የንባብ አማራጭ አቅርቧል!
የውጭ ቋንቋ ልቦለድ ወይም መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ? በSEKA መጽሐፍዎን ይስቀሉና በሚፈልጉት ቋንቋ ለመተርጎም የሚሰጡትን ነፃ ክሬዲቶች ይጠቀሙ።
በቻናላችን የመጽሐፍ ፖስቶች ላይ ያለውን የSEKA የንባብ ሊንክ ሲያዩ፣ በአንድ ጠቅታ ወደ መጽሐፉ ገብተው ፋይሉን ሳያወርዱ በነፃ በመስመር ላይ ማንበብ ይችላሉ። ጥቂት ካነበቡ በኋላ ለመቀጠል ነፃ ምዝገባ ሊጠየቁ ይችላሉ።
👉 የSEKAን ትርጉምና ንባብ ይሞክሩ
🔥3
1 · 2.7K · Reply📚 Amba Books ከSEKA ጋር በመተባበር አዲስ የንባብ አማራጭ አቅርቧል!
የውጭ ቋንቋ ልቦለድ ወይም መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ? በSEKA መጽሐፍዎን ይስቀሉና በሚፈልጉት ቋንቋ ለመተርጎም የሚሰጡትን ነፃ ክሬዲቶች ይጠቀሙ።
በቻናላችን የመጽሐፍ ፖስቶች ላይ ያለውን የSEKA የንባብ ሊንክ ሲያዩ፣ በአንድ ጠቅታ ወደ መጽሐፉ ገብተው ፋይሉን ሳያወርዱ በነፃ በመስመር ላይ ማንበብ ይችላሉ። ጥቂት ካነበቡ በኋላ ለመቀጠል ነፃ ምዝገባ ሊጠየቁ ይችላሉ።
👉 የSEKAን ትርጉምና ን
ስለ ድረ ገጹ ከምዝገባ ጀምሮ አጠቃላይ ዝርዝር መረጃ guide video አሁን post አደርጋለሁ !
react እያደረጋችሁ ቤተሰብ 🙏
👍8
2.6K · አምባ መፅሐፍ
Reply🔥 የልብ እዳ 🔥
አባተ ከሰርግ ሳይሆን ከልቅሶ ቤት የተመለሰ ያህል ተክዞአል፤ እኒያ በራሱ ተነግረው ራሱን የሚያስቁ ቀልዶቹም የሉም፤ብቻ ዝምብሎ ከሰርግ ቤት ይዞት የተመለሰውን የሙሽሮች ፎቶግራፍ ይዞ ይተክዛል። ጩኸት ያስለመደ ሰው ዝምታው ለደቂቃም ቢሆን ስለሚከብድ፤ የወሬ መነሻው የጠፋው ይመስል ለወሬ መንደርደሪያ ለመስጠት ያህል
" ሰርግ እንዴት ነበር" ስለው፤ቀና ብሎ አየኝና
"እእ አሪፍ ነበር" ካለ በሁዋላ ከመሬቱ ላይ መርፌ ይፈልግ ይመስል አይኑን መሬትPhoto
🔥15❤8😘1
1 · 2K · 🔥የልብ ዕዳ -2🔥
ከቴሌ በነጻ ወስደን ካርድ ለጉድ እየሞለን የምንጠቀምበት ስልክ ቀኑን ሙሉ ሲያላዝንብኝ ዋለ፤ስልኩን አንስቼ ወሬ እንደጀመርኩ
"ኤቢን ፈልጌ ነበር !" የሚል ተደጋጋሚ የሴቶች ዘፈን ነበር የማደምጠው፤ከደዋዮቹ መሃል አንድም እኔን ፈላጊ ባለመኖሩ መናደዴ ሳያንስ፤ቀኑን ሙሉ አባተን በሚፈልጉት ሴቶች ድምጽ ስደናቆር መዋሌ ይብሱን አንድዶኛል።በዛ ላይ የጥያቄአቸው መብዛት፤ሁሉንም ጥያቄ እንደአመጣጡ ጓደኛዬን ላለማስጠቆር እየጣርኩ መለስኩ፤የቸገረኝ ነገር ቢኖር የስማቸው ብዛት ነበር።እውነቱን ለመናገር በዛሬ ውሎዬ ብቻ ስድስት ሴቶችን አውርቻለሁ፤ደግነቱ አባተ ስለእያንዳንዷ ሴት ቀድሞ ስላጫወተኝ ብዙዎቹን ሳናግር የማውቃቸው ያህል ይሰማኝ ነበር። የአንዳንዶቹ ሴቶች ድምጽ አባተ ከነገረኝ ጸባይ እና መልክ ጋር ባዕድ ይሆንብኛል።
አሁን ሜሮን ስለምትባለው ልጅ የነገረኝ በጣም አይናፋር እና ዝምተኛ እንደሆነች ነበር። ሆኖም ከሁሉም ሴቶች የተሻለ ለሰባት ደቂቃ ከምናምን ያህል ማውራት የቻልኩት ከእሷ ጋር ብቻ ነበር።አባተ እቤት እንደሌለ ስነግራት፤ማን እንደሆንኩ ጠየቀችኝ
"ወንድሙ ነኝ!" ስል መለስኩለት፤ወዲያው ከት ብላ ሳቀችና
"አሃ እንደወንድሜ ነው የማየው የሚለው አንተን ነበር ?"አስከትላም
"ቆይ የት አባቱ ሄዶ ነው እሱ ስልኩን አጥፍቶ"
"እኔንጃ ከእኔ ጋር እራሱ ከተገናኘን ቆየን...አልፎ አልፎ ነው የምንገናኘው"
"ውይ ምነው ምን ዋጠው ባክህ !?"
"የስራው ጉዳይ ነዋ !"
"ለምን ከውሸቱ ጋር ትተባበራለህ ? ምን እንዳደረገኝ ታውቃለህ" አባተ ከእሷ ጋር ስለነበረው ነገር ሁሉ የነገረኝ ቢሆንም ምናልባት ሳልሰማው የቀረ ጉድ ካለ ስል የጓደኛዬን ምስጢር ልሰማ ጆሮዬን አሾልኩ፤ምንም አዲስ ነገር አልነበረም።ባልሰማት ይሻለኝ ነበር።
አባተ ከሳራ ጋብቻ በሁዋላ አምሽቶ የመግባቱን ነገር እርም ብሎ በጊዜ መግባት ጀምሮአል፤ ገና ከቤት እንደገባ
"ዛሬ የፈለገነኝ ሰው ነበር" አለኝ ወደስልኩ እየተመለከተ
"ቆይ አንተ ስታየኝ የሆነ ኦፕሬተርህ መስልሃለው እንዴ !?" ተናድጄ ነበር
"አግኝተህ ነው ?" አባተ መልሶ አለገጠብኝ
"ደግሞ የቤቱን ስልክ ለጆንጀና ላለመጠቀም አልተስማማንም ነበር !?"
"ኡፋ አንተ ደግሞ...ሜሮን ደውላ ነበር ?"
"በምን አወቅክ ?"
"ዛሬ መስሪያ ቤት መጥታ ነበር"
"ቆይ ምን ብታደርጋት ነው እንዲህ በእግር በፈረስ የምትፈልግህ ?"
"ያ የምታውቀውን ነው"
"እኔ ግን ከእሱ ውጪ ነገር እንዳለ በስልክ አጫውታኛለች" አባተ ከት ብሎ ሳቀና
"ኧረ ባክህ ጫወታም ጀምራችኋላ !?" አለና
"ለመሆኑ ምን አለችህ እሷ እንደው ወሬ አያልቅባት...ፍቅረኛ በነበርን ጊዜ እንደፍቅረኛሞች መዝናናት እና መጫወት ስለማይመቻት ደነዘዘችብኝ...ሁሉ ነገር ስንጋባ ይደርሳል በማለት እጮኝነትን የሆነ የጉጉት እስር ቤት አደረገችው...የተለያየነው በዚህ ምክንያት ነው"
"እውነቷን እኮ ነው ፍቅር አድጎ በጋብቻ ካልተቋጨ ምን ትርጉም ይኖረዋል ?"
"ከሴት ጋር በአንድም በሁለት ትገናኛለህ...እና ሁሉንም በትዳር ካልቋጨሁ ማለት እብደት ነው"
"ስለዚህ ?"
"ስለዚህማ በህብረት የደስታን እሳት አንድዶ መሞቅ"
"እና ለዚህ ነዋ አርፋ አግብታ የምትኖርን ሴት እየደወልክ የምትበጠብጠው ?" ከዚያ መከረኛ ሰርግ ወዲህ አባተ ደጋግሞ ወደሳራ ስለሚደውል።፤ሳራን ማለቴ ነበር። አባተ ስለሳራ በክፉ ሳወራ ደስ አይለውም፤ንግግሬን እንዳቆም ሙሉ መዳፉን ከክንዱ ዘረጋብኝ።መልእክቱን ተቀብዬ በዝምታ ሀሳቡን ያብረራልኝ እንደሁ እጠብቅ ጀመር፤አባተ ምንም አላለኝ። የወሬውን አርእስት ለወጠና እራት ካልበላህ ብዬ ይሄን አምጥቼልሃ… Read in full →
❤25🥰4🔥2
1 · 1.3K ·