English
Open in Telegram
AAMOUS Technology° 🇪🇹

AMOUS Technology° 🇪🇹

@AmousTechnology ¡ channel ¡ Tech ¡ indexed since 2026-07-11
1 570subscribers
101posts in the index
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
File
namida_AMOSTECHNOLOGY.apk ¡ 42.8 MB ¡ click to show
ውድ የAMOSTECHNOLOGY ቤተሰቦች እንደተለመደው ለእናንተ የሚጠቅም፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂ አቅም በአንድ ላይ የያዘ ድንቅ አፕሊኬሽን ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ። ይሄ አፕሊኬሽን የምን spotify የሚያስብል ሲሆን ስሙ Namida ይባላል መቼም ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ጽድት ያለ እና እጅግ ቀልጣፋ አፕሊኬሽን አይተው አያውቁም፤ እመኑኝ! ኣታካብድ ባክህ 😒 Namida ምን ልዩ ያደርገዋል ለምትሉ💎 🔗የዩቲዩብ የጀርባ አጫዋች (Background Player) ስልካችሁ ላይ ሌላ ስራ እየሰራችሁ ወይም ስልኩን ዘግታችሁ (Screen off) የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን ማዳመጥ ያስችላችኋል። ✅የማውረድ አቅም (Seamless Downloader)የምትወዷቸውን ቪዲዮዎችና ኦዲዮዎች በፈለጋችሁት ጥራት በቀጥታ ወደ ስልካችሁ ማውረድ ትችላላችሁ። ✅ የዓይናችሁን ማረፊያ፣ የልባችሁን መረጋጋት የሚሰጥ እጅግ ውብ እና ምንም አይነት የተወሳሰበ ነገር የሌለው ዲዛይን አለው። ✅ነጻ እና ንጹህ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ተመራጭ አድርጎታል በሌሎች አፕሊኬሽኖች ውስጥ በክፍያ የምታገኟቸውን አገልግሎቶች፣ እዚህ በነጻ በተጨማሪም ያለምንም ማስታወቂያ ታገኙታላችሁ። ⚠️ Youtube account Login ባታደርጉ ይመረጣል። (In app browser ስለሚጠቀም Passwordችሁ በቀላሉ ለDeveloper ሊደርሰው ይችላል) ይህንን የቴክኖሎጂ ድንቅ ስራ አሁኑኑ ተጠቅማችሁበት ትደሰቱበት ዘንድ እጋብዛችኋለሁ። ራሳችሁ ሞክሩት፣ ጉድ ትላላችሁ! ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅ ዘመዶዎ፣ ለጓደኞቻችሁ ማካፈል (Share) እንዲሁም ሪአክት አርጉበት Click👇👇👇🔗 To find the English translation And I would like to welcome new audiences.🙌
9 ¡ 276 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
ትንሽ ነገር ነው፣ ግን እመኑኝ... ጠቃሚ ከሚባሉት ተርታ ይመደባል የስልኬ የጎን ቁልፎች (side buttons) መቸገር ጀምረው ነበር😄 ስክሪንሻት ለማንሳት ሁለቱንም ቁልፎች በአንድ ሰአት መጫን ያስፈልግ ነበር፣ አንዳንድ ጊዜ ይሳካል፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ያስቸግራል! ዛሬ ምነግራችሁ ሰለ Action Note የሚባል አፕ ሲሆን አፑ ከዚህ አይነቱ የ (side buttons) እድሜን ከሚያሳጥረው ችግር ልታደጋችሁ እያለ ይመስላል ✅ስክሪንሻት ያነሳል፣ ✅መብራት (flashlight) ያበራል፣ ✅የፈለጉትን Permanent አፕ ይከፍታል። ከእንግዲህ ተጨማሪ ቁልፎችን መጫን የለም ዳይ ወደ አፑ 👇 ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ አፑን ለማውረድ ፅሁፉን ይጫኑት 👈🔗 Click the link for English translation. 👉🔗Link 🔗 👈 Нажмите на ссылку, чтобы найти русский перевод. 👉🔗Связь🔗👈
3 ¡ 387 ¡
AMOUS Technology° 🇪🇹
Guys Once I heard everything is not easy🧭 Why not sleep is easy *¿🤩
2 ¡ 259 ¡
A
Mention 👈 ሰላም የ Amos technology ቤተሰቦች ባለፈው ጊዜ የጀመርነው ርእስ ነበር አስታወሳችሁ ያላነበባችሁት mention የተደረገውን ፅሁፍ ተጫኑት 👆 ዛሬ ደግሞ አንስታይን ስለ ስበት (Gravity) ያለውን 🌌 እይታ የምናይ ይሆናል እሺ፣ ስለ ኒውተን ቀደም ብለን ተነጋግረናል — እሱ ስበትን "force" (ኃይል) ነው ብሎ ነበር የጠራው። ይህ ሀሳብ ለዘመናት በስራ ላይ የዋለ ድንቅ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ነበር ነገር ግን አንስታይን ሲመጣ ነገሩን ቀየረው."አይ እንደዛ አይደለም የሚለውንም አፅደቀ እዚህ ጋር ነው ነገሩ በጣም አስገራሚ የሆነው 🤯 አንስታይን እንዳለው ስበት "force" ሳይሆን /spacetime bending/(የዘመን እና የቦታ መታጠፍ) ነው። እስቲ እንዲህ ብላችሁ አስቡ፦ አንድ የተወጠረ "blanket" (ብርድ ልብስ) ላይ በጣም ክብደት ያለው ኳስ ብታስቀምጡ፣ ምን ይፈጠራል? ቦታው ይጎረጉዳል አሁን ደግሞ አንድ ትንሽዬ ሎሚ 🍋 አጠገቡ ብታሽከረክሩት፣ ወደ ትልቁ ኳስ ይሳባል። ይህ የሆነው የሆነ ነገር ስላሳበው ሳይሆን፣ የመሬቱ (surface) ቅርጽ ስለተጠመዘዘ ነው። አንተ ሰውዬ ናላችንን አዞርከው በቪድዩ አሳየን ትሉኛላችሁ ብዬ ስላሰብኩ የዚህን ሂደት ሚያስይ ከ 1 minutes ያልበለጠ ቪድዩ ከዚሁ ከ telegram ከቻናላችን ሳትወጡ ሊንኩን በመጫን ቪድዩውን መመልከት ትችላላችሁ ሊንክ 👇 👇 👇 🔗 ፅሁፉን ተጫን 👈 👆👆👆👆👆 እናም ከ video መልስ አንስታይን አጽናፈ ዓለማችንን ያየው በዚህ መንገድ ነበር። ማለትም ከ ኒውተን በተለየ መልኩ ፀሐይ ምድርን "አትይዝም" (doesn't grab)። ይልቁንም በዙሪያዋ ያለውን space ታጠፍዋለች፣ ምድርም🌍☀️ ያንኑ ጥምዝ መንገድ ትከተላለች። ማለትም ማቆሚያ የሌለው ጥምዝ ማለት ነው በጣም አስገራሚ ይመስላል ፎርሙላውን ለማግኘት ሊንክ 👇 🔗 ፅሁፉን ተጫን 👈 በሌላ በኩል ደግሞ ይህንን የ አንስታይን ንድፈ ሐሳብ ኒውተን ሊያብራራቸው ያልቻላቸውን ነገሮች ይፈታል 👇 ለምሳሌ ✅ ⚫ Black holes (ጥቁር ጉድጓዶች) እንግዲህ በአማረኛ ከዚህ የተሻለ ስም አጣሁለት😄 ✅* 💫 Gravitational waves (የስበት ሞገዶች - በ1915 የተነበዩ፣ ከ100 ዓመታት በኋላ የተረጋገጡ!) ✅ 🌠 የብርሃን መታጠፍ በከዋክብት ዙሪያ ✅ 🛰️ በስልክሽ ላይ ያለው GPS— አዎ፣ የምንጠቀምባቸው ካርታዎች በትክክል እንዲሰሩ አንስታይን የዘረጋው መርህ ነው ዋነኛው ምክንያት።  እኔ በበኩሌ እንደማየው — ኒውተን "ምን" እንደሚፈጠር ነግሮናል፣ አንስታይን ደግሞ "ለምን" እንደሚፈጠር አብራራልን ብዬ አምናለሁ እናም አልጨረስንም ምንቀጥል ይሆናል እንደተለመደው ፅሁፉ ጠቅሞናል ብላችሁ የምታስቡ ያክል Sher & react ማድረግ እንዳይረሳ Click the link for English translation. 👉🔗Link 🔗 👈 Нажмите на ссылку, чтобы найти русский перевод. 👉🔗Связь🔗👈
4 ¡ 445 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
Volume Scroll 😯 በድምፅ መጨመሪያ እና መቀነሻ ቁልፎች Scroll የሚያደርግላችሁ ጽድት ያለ አፕ  ከፕሌይ ስቶር ለማውረድ ሊንክ👇 👉🔗 VOLUME Scroll🔗👈 ይመቻችሁ ✌🏾
3 ¡ 247 ¡
AMOUS Technology° 🇪🇹
Photo
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ! 🚨 ​ሰሞኑን በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ድርጊት እየተፈጸመ ይገኛል። ​በጣም ፀያፍ የሆኑ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ ከስራቸው ሊንክ (Link) ያያይዛሉ።ሊንኩ የሚላክላችሁ ከማታውቁት ሰው ብቻ ሳይሆን፣ አካውንታቸው በተጠለፈ የቅርብ ጓደኞቻችሁ ወይም ዘመዶቻችሁ ስም ሊሆን ይችላል። 🛑🔗link አትንኩ! https://t.me/stem_with_kha
2 ¡ 174 ¡
ሰላም ውድ የ AMOS TECHNOLOGY ቤተሰቦች እነዚህ የቴክኖሎጂ አህጽሮተ ቃላት ምን ማለት እንደሆኑ ታውቁ ነበር? በየቀኑ የምንጠቀምባቸው ግን ሙሉ ትርጉማቸውን የማናውቃቸው ዋና ዋና ቃላት ናቸው እነሱም 1,🔹 OTP: One-Time Password 2,🔹 PIN: Personal Identification Number 3,🔹 SMS: Short Message Service 4,🔹 GIF: Graphic Interchange Format 5,🔹 GPS: Global Positioning System 6,🔹 PDF: Portable Document Format 7,🔹 PNG: Portable Network Graphics 8,🔹 WWW: World Wide Web 9🔹 Wi-Fi: Wireless Fidelity ይህን አስመልክቶ አጭር Video ውን ከዚሁ ከ telegram ሳትወጡ ለመመልከት ሊንክ 👇 👉🔗{ፅሁፉን ይጫኑ }🔗👈 ይህን ጠቃሚ መረጃ ለጓደኞቻችሁ ማጋራት እንዳትረሱ! 🚀🔥
3 ¡ 237 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ጅማሮ ትልቅ ራዕይ ያለውና የሚያስደስት ነበር። ነገር ግን፣ ከምዝገባና ከተፈጠሩት የሰርተፍኬት ብዛት ባለፈ «ስንቱ የእውነት እውቀቱን ተማረ? ስንቱስ አዲስ ነገር መፍጠር ቻለ? እና ትክክለኛ ችግሮችን መፍታት ይችላል?» የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው። በተጨባጭ የታየው አንዳንዶች በግዴታ፣ ሌሎች ደግሞ ሰርተፍኬት ብቻ ለማግኘት ሲሉ ትምህርቱን በችኮላ Next Next እያሉ ሲያልፉት አስተውለናል፤ አልፎ ተርፎም ለሌላ ሰው ገንዘብ ከፍለው ሰርተፍኬት ያወጡም አሉ። ይህ የሚያሳየው መማር በግዴታ ወይም በወረቀት ብቻ ሲለካ፣ የሰዎች ትኩረት ከዕውቀት ይልቅ ወደ ሰርተፍኬት ማጋደሉን ነው። ለኔ ቀጣዩ የዚህ ፕሮግራም ምዕራፍ ጥራትና ተግባር ላይ ሊያተኩር ይገባል ብዬ አምናለሁ። ስልጠናዎቹ በሀገርኛ ቋንቋዎች ቢሰጡ፣ ከተጨባጭ የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚሄዱ ፕሮጀክቶች (ለምሳሌ የትምህርት ቤት አቴንዳንስ መቆጣጠሪያ፣ የገበያ ዋጋ መረጃ መተግበሪያ ወዘተ) ቢሰሩበት፣ እንዲሁም ምዘናው በተግባራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ቢመሰረት እውነተኛ የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት እንችላለን። ስኬት መለካት ያለበት በተማሪዎች የፈጠራ ስራና በተፈቱ የሀገር ችግሮች መሆን አለበት። ዋናው ቁምነገር ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የምትሆነው በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰርተፍኬቶች ሳይሆን፣ የህብረተሰቡን ችግር በሚፈቱ እውነተኛ ኢንጂነሮችና ኢኖቬተሮች ነው! 👉🔗{ ሊንክ}🔗👈
165 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
ባለፈ ልጆቻችሁን ለክረምት ኮርስ አስመዝግቡ ካልኳችሁ መካከል አንዱ ኢንሳ ነበር። ምናልባት የተመዘገባችሁ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ግቡና ማለፋችሁን ቸክ አድርጉ። https://ctc.insa.gov.et መቼም በየጊዜው ስመክር አልኖርም።
142 ¡
AMOUS Technology° 🇪🇹
ሰላም ቤተሰቦች! 👋 ዛሬ ከ technology ብንወጣም በጣም ያስገረመኝን ነገር ልንገራችሁ ስለ ሩሲያ ስፋት አንድ የሚገርም እውነታ እንዳለ ታውቃላችሁ። በተለይ በግሩፓችን ውስጥ ብዙ የሩሲያ ኦድየንሶች ስላላችሁ ይህንን ለኛ ማወቅ መልካም ይሆናል! 🌍 እስኪ አስቡት፤ ሩሲያ በጣም ሰፊ ከመሆኗ የተነሳ 11 የተለያዩ የሰዓት ቀጠናዎች እንዳሏት ታውቁ ነበር። ነገሩን ቀለል ለማድረግ፡ በሩቅ ምስራቅ (ለምሳሌ ካምቻትካ) የሚኖር ሰው ቀኑን ጨርሶ ማታ 2 ሰዓት ላይ ሊተኛ ሲዘጋጅ፣ በዚያው እኩል ሰከንድ በሩቅ ምዕራብ (ካሊኒንግራድ) የሚገኝ ሰው ገና ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ ከእንቅልፉ ተነስቶ የጠዋት ቡናውን ይጠጣል። ☕️☀️ ይህ ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ ፀሐይ በአንድ ጊዜ እየጠለቀችም እየወጣችም ነው ማለት ነው! ይሄ በእውነት አስገራሚ አይደለምን? በሀገራችን ሰዓት አቆጣጠር እንኳን ስናስበው ፅሀይ ለ 1/ 10 ጉዳይ ምትገባበት ጊዜ ያስገርመናል ታዲያ የነሱን ደግሞ አስቡት። የሩሲያ ቤተሰቦቻችን እስኪ ንገሩን፤ አሁን እናንተ ጋር ሰዓቱ ስንት ነው? ሩሲያ ያላችሁበትን ቦታ ኮሜንት አድርጉልን! 🇷🇺✨ (ጽሑፉ ከተመቻችሁ ሪአክት ማድረጉን እንዳትረሱ! 👍) Ребят, привет! 👋 Сегодня хочу поделиться с вами одним невероятным фактом о масштабах России. Особенно круто это осознавать, так как большинство из вас как раз оттуда! 🌍 Только вдумайтесь: страна настолько огромная, что охватывает 11 часовых поясов. Чтобы вы понимали масштаб: когда на Камчатке человек уже заканчивает свой день и ложится спать в 8 вечера, в ту же самую секунду в Калининграде кто-то только просыпается и пьет утренний кофе в 9 утра! ☕️☀️ Получается, в одной и той же стране солнце одновременно и заходит, и встает. Разве это не поразительно? Наши ребята из России, расскажите в комментариях, из какого вы города и сколько у вас сейчас времени? 🇷🇺✨ (Если пост вам понравился, не забудьте поставить лайк! 👍)
1 ¡ 217 ¡
A
ጥቆማ‼ ነጻ የክረምት ስልጠና ይከታተሉ! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ1ኛ-12ኛ ክፍል ለሆነ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና አዘጋጅቷል። የክረምት ስልጠና መስኮች፦ ● ፋንዳሜንታልስ ኦፍ ኤ.አይ. ● ፕሮግራሚንግ ● ማሽን ለርኒንግ ● ሮቦቲክስ እና IOT ● ዳታ ሳይንስ የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇 ሰኔ 30/2018 ዓ.ም በተከታዩ የጉግል ፎርም ይመዝገቡ 👇 https://forms.gle/uDGPmQsiZcWWeNuRA
1 ¡ 181 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች! 👋 ዛሬ የዩቲዩብን አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ የሚቀይረውን NewPipe የተሰኘውን ምርጥ አፕሊኬሽን ይዤላችሁ መጥቻለሁ። እና appፑ አጭር መረጃው እነሆ፦ 🔥 ዋና ዋና ጥቅሞች ያለ ማስታወቂያ (No Ads): አንድም አሰልቺ ማስታወቂያ ሳይረብሻችሁ መመልከት መቻላችሁ ♨️ከበስተጀርባ ማጫወት: ስልካችሁን ዘግታችሁት ወይም ሌላ አፕ እየተጠቀማችሁ ኦድዩና ፖድካስት ማዳመጥ። ♨️ ተንሳፋፊ መስኮት (Popup): ቪዲዮውን በትንሽ መስኮት እያያችሁ ቻት ማድረግ ወይም ስራችሁን መስራት። ♨️ ቀጥታ ማውረድ (Download): ቪዲዮ ወይም ኦዲዮ (Audio) በፈለጋችሁት ጥራት በቀጥታ ወደ ስልካችሁ መጫን። ♨️ደህንነት (Privacy): የጉግል አካውንት (Sign-in) አይጠይቅም፤ መረጃችሁ ፍጹም የተጠበቀ ነው ስለዚህም ምንም ሚያሰጋ ነገር ኣለመኖሩ ተመራጭ ያደርገዋል። 🌐 ይፋዊ የማውረጃ ሊንኮች ይህ አፕ በፕሌይ ስቶር ላይ ስለማይገኝ በየትኛውም ጊዜ ትክክለኛውን ስሪት ከእነዚህ ታማኝ ሊንኮች ማግኘት ትችላላችሁ፦ ሊንክ👇 > 🔗 ዋናው ድረ-ገጽ: NewPipe Official Website > 🔗 የፕሮጀክቱ ጊትሃብ: NewPipe GitHub Repository > አፑን አውርዳችሁ ሞክሩትና ይመቻችሁ! ለመሆኑ ከእነዚህ ጥቅሞች ውስጥ እናንተን ይበልጥ የሳባችሁ የትኛው ነው?
1 ¡ 193 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
Photo
ሰላምታ ለወዳጆቼ👋 ዛሬ "Guys, here is a real game-changer" ላስተዋውቃችሁ፤ እሱም Dala Studio ይባላል! ይህ በታዋቂው "Gebeya" የተደገፈ እጅግ የሚደንቅ የ-AI ፕላትፎርም ነው። እስቲ አስቡት፣ ምንም ዓይነት "coding" ወይም የፕሮግራም እውቀት ሳይኖራችሁ፣ "without any complex coding," በቀላሉ በማውራት ብቻ የራስዎን ዌብሳይት እና አፕሊኬሽን መገንባት፣ አልፎም "amazing digital images" እና ታሪኮችን መፍጠር ትችላላችሁ! ለአጠቃቀም በጣም ቀላል ከመሆኑም በላይ፣ ተጨማሪ "features" ለመግዛት ወይም የራስዎን "custom domain" ለመያዝ ክፍያውን እንደ M-Pesa ባሉ የአፍሪካ የክፍያ መንገዶች በቀላሉ መፈፀም ይቻላል። ይህ "smart platform" እንደ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ስዋሂሊ እና ፈረንሳይኛ ያሉ ቋንቋዎችን በደንብ ይደግፋል፤ ስለዚህ "your creativity will reach your audience in their own native language." ዋናው ነገር ደግሞ "it’s totally free!" በየቀኑ ነፃ ክሬዲት ይሰጣችኋል። 👉🔗{Link}🔗 👈 በDala Studio አስደሳች እና "amazing creative journey" እመኛለሁ!
3 ¡ 200 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
ሰላም ጓዶች 👋 ዛሬ ያመጣነው 🔈 Voice Remover ይሰኛል— የማንኛውንም ድምፅ እና (ዜማ) በየብቻ መለያ። ምን ምን ነገሮች አሉት? 🎤 የ background ድምፅ ብቻ ነጥሎ ማውጣት ያስችላል 🎵 የተለያዩ ድምጾችን ወይም ዜማ ብቻ ለይቶ ያስቀራል ወዘተ... 🤖 በዘመናዊ የ-AI ቴክኖሎጂ የተሰራ ስለሆነ ጥራቱን አይቀንስም 💬 ተራ የድምፅ ፋይሎችንም ሆነ በቮይስ (Voice Message) የተላኩትን ይሰራል 🔀 አንድን ዜማ ወደ 2፣ 4 ወይም 6 የተለያዩ የኦድዩ ክፍሎችን መከፋፈል ይችላል 📥 የፈለግከውን ፋይል በ WAV ወይም በ MP3 ፎርማት በቀላሉ ወደ ስልካችሁ ማውረድ ያስችላችኋል 🔎 በውስጥ መስመር (Inline) ፈጣን መፈለጊያ አለው 👉🔗@voice_remover_bot 🔗👈
2 ¡ 187 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
የ 'File Converter' ቦትን ይተዋወቁ! ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች! ዛሬ ስራችሁን እጅግ የሚያቀል፣ ፍጹም amazing የሆነ አዲስ ቦት ይዤላችሁ መጥቻለሁ። ይህ ቦት በሌሎች ቦታዎች በቀላሉ የማይገኙ በርካታ ልዩ ጥቅሞችን (features) በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ነው ✨ ዋና ዋና ጥቅሞች (Key Features)፦ Multi-Format Conversion 🎬፦ ማንኛውንም ቪዲዮ ያለምንም እንግልት ወደ AVI፣ MKV፣ MP4 ወይም ወደፈለጉት ፎርማት በሰከንዶች ውስጥ ይቀይራል። Audio Extraction (Video to MP3) ከማንኛውም ቪዲዮ ላይ ድምፁን ብቻ ነጥሎ በማውጣት ወደ ከፍተኛ ጥራት ባለው MP3 ፋይል መቀየር ያስችላል። Video to GIF 🔄፦ ረጅም ቪዲዮዎችን ወደ ፈጣን እና ቀላል የ GIF ምስሎች መቀየር። Super Fast & Efficient ⚡፦ ምንም አይነት መዘግየት (lag) የሌለው፣ እጅግ ፈጣን (lightning-fast) የሆነ አሰራር። Privacy & Convenience 🔒፦ ሌላ ተጨማሪ ሶፍትዌር ስልክዎ ላይ መጫን ሳይጠበቅብዎት፣ በቴሌግራምዎ ብቻ ፋይሎችዎን በምስጢር እና በደህንነት ይለውጡ። በአጭሩ፦ ፈጣን፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ፍጹም ውጤታማ! አሁኑኑ ሊንኩን ተጭነው ሞክሩት ይመቻችሁ 👇 @newfileconverterbot
3 ¡ 324 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
​ሰላም ጓዶቼ 👋 ​የኮዲንግ ዓለምን ለመቀላቀል እና አሁን ላይ በጣም ተፈላጊ የሆነውን የ Python ቋንቋን በቀላሉ መማር ትፈልጋላችሁ ብዬ አስባለሁ ይህ ድረ-ገጽ የሚጠቅማችሁን ሁሉንም በአንድ ቦታ ይዟል፣ በዚያ ላይ ሙሉ በሙሉ በነፃ ነው! ​🚀 FreeCodeCamp ከዜሮ ተነስታችሁ በተግባር እንድትለማመዱ የሚያደርግ እጅግ ድንቅ website ነው ​ጉዟችሁን አሁኑኑ እዚህ ጀምሩ ፡ 🔗 freecodecamp.org
1 ¡ 250 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
✅ዛሬ ሁላችንም ስልካችን ላይ ብንጠቀምበት በጣም የሚጠቅም አንድ ምርጥ አፕ ላሳያችሁ፤ እሱም Google Files ነው። አፑ ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፣ ደግሞ ምንም አይነት ማስታወቂያ (Ads) የለበትም። በየቀኑ የሚጠቅሙን ነገሮችን በውስጡ ይዟል ለምሳሌ ቦታ መቆጠብ (Storage)፦ ስልካችን Full እየሆነ ሲያስቸግረን፣ የእኛን የግል ፎቶዎች ሳይነካ እነዚያን አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻ ፋይሎች (Junk Files) በአንድ ክሊክ ያጠፋልናል። ተደጋጋሚ ፎቶዎችን ማጥፋት (Duplicates)፦ በስህተት ሁለት ሶስት ጊዜ የመጡ ተደጋጋሚ ፎቶዎችን ወይም ቪዲዮዎችን ፈልጎ በማውጣት ቦታ እንድንቆጥብ ይረዳናል። በፍጥነት ፋይል መላክ (File Transfer)፦ ምንም ኢንተርኔት ሳይኖረን ፎቶ እና ቪዲዮ በከፍተኛ ፍጥነት ለመላላክ ይጠቅማል። በቃ ያንን ማስታወቂያ የሚበዛበትን SHAREit ያስረሳናል። የግል መቆለፊያ (Safe Folder)፦ ማንም ሰው እንዲያይብን የማንፈልገውን ፎቶ ወይም ዶክመንት በፓስወርድ (Password) ወይም በፊንገር ፕሪንት ቆልፈን የምናስቀምጥበት ልዩ ቦታ አለው። በጣም ቀላል እና ማንኛውም ሰው ስልኩ ላይ ሊኖረው የሚገባ አፕ ነው። ሞክሩትና ትወዱታላችሁ! [Download Link]
4 ¡ 488 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
👉Mention 👈 LINK 🔗 👇 ♨️Messenger abeto.com🕸️
95 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
Photo
This perfectly sums up startups before & after AI.
1 ¡ 76 ¡
F
Father bot
በስራችን ወቅት፣ በተለይም በዲጂታል አለም ውስጥ፣ በተደጋጋሚ የሚጻፉ ጽሑፎች (repetitive texts) ወይም ረጅም ኮዶች (long codes) ማስገባት ግድ የሚሆንባቸው ጊዜያት ብዙ ናቸው። ይህን በእጅ ማድረግ ጊዜ የሚወስድ ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ስህተቶች ያጋልጠናል። ዛሬ ላስተዋውቃችሁ የፈለግኩት Utility Application espanso ይባላል። ይህ ድንቅ Tool የ Productivity-ያችንን (ምርታማነትን) በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል እውነተኛ Hidden Gem ነው። 🎯 espanso ምንድነው? ይህ Application በምታስገቡት አጭር Keyword (ለምሳሌ አድራሻ ወይም ፊርማ) ላይ ተመስርቶ ሙሉ ዓረፍተ ነገሮችን፣ ረጅም Paragraph-ዎችን አልፎ ተርፎም ኮዶችን በቅጽበት (instantly) እንድንጽፍ ያስችለናል። 🛠️ ለምሳሌ: `ኢሜልዬ` ብላችሁ ስትጽፉ፣ የራሳችሁ ሙሉ የኢሜል Address በራስ-ሰር እንዲመጣ ማዘጋጀት ትችላላችሁ። አድራሻ ብላችሁ ስትጽፉ፣ የኩባንያችሁን ሙሉ Address እና የስራ ሰዓት በአንድ ጊዜ እንዲገባ ማድረግ ትችላላችሁ። ይህ Tool Cross-platform በመሆኑ በ Windows፣ macOS እና Linux Operating Systems ላይ ያለ ምንም ችግር ይሰራል። 🌐 ኮድ ለሚጽፉ Developer-ዎችም ሆነ ብዙ ጽሑፎችን ለሚያስገቡ Content Creator-ዎች፣ ለ Customer Support Agents እና ለማንኛውም ተደጋጋሚ የጽሑፍ ግብዓት ለሚያስፈልገው ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። 📱 espanso Open Source Project በመሆኑም፣ በየጊዜው በአድናቂዎቹ እየተሻሻለ እና አዳዲስ Feature-ዎች እየተጨመሩለት ይገኛል። ለዚህ ድንቅ Tool Creator (አዘጋጅ) ከልብ እናመሰግናለን፤ እንዲህ ያሉ Project-ዎች እውነትም የቴክኖሎጂውን አለም ለሁሉም የበለጠ ተደራሽ እና ጠቃሚ ያደርጉታል። ሞክሩት! ይህን አፕሊኬሽን አንዴ ከተጠቀማችሁ በኋላ ያለሱ መስራት እንደማትችሉ እርግጠኛ ነኝ።
1 ¡ 93 ¡
G
በየዕለቱ ከምንጠቀምባቸው 📱 Softwareዎች መካከል፣ አንዳንዶቹ እንደ ድብቅ ሀብት (hidden gem) ሆነው የኛን የሥራ ሂደት (workflow) በእጅጉ የሚያቀሉ Utility applications ይኖራሉ። ዛሬ ላስተዋውቃችሁ የምፈልገው የproductivity አቅማችሁን በአስገራሚ ሁኔታ ሊያሳድግ የሚችል አንድ ድንቅ 'text expander' ነው። ስሙም Espanso ይባላል። ይሄ Application በተደጋጋሚ የምንጠቀማቸውን ቃላት፣ ሀረጎች፣ አልፎ ተርፎም code snippets በቀላሉ እንድናስገባቸው ያስችላል። ለምሳሌ፣ 'eml' ብለው ሲጽፉ ሙሉ የኢሜል አድራሻዎን በቅጽበት ማስገባት ይችላሉ። ወይም 'addr' ሲሉ ሙሉ አድራሻዎ፣ 'codejs' ሲሉ ደግሞ በተደጋጋሚ የሚጠቀሙበት የJavaScript ኮድ snippet እንዲመጣ ማድረግ ይችላሉ። ይህ ለDevelopers, writers እና ለማንኛውም በተደጋጋሚ text ለሚጠቀሙ ሰዎች ትልቅ የጊዜና የድካም ቁጠባ ነው። የEspanso ዋነኛ ጥንካሬዎች አንዱ 'cross-platform' 🌐 መሆኑ ነው። Linux፣ macOS እና Windows Operating Systems ላይ ያለምንም ችግር ይሰራል፣ ይህም አንድ አይነት 'configurations' በየትኛውም መሳሪያዎ ላይ መጠቀም እንዲችሉ ያደርጋል። ከዚህም በላይ 'open-source' 🛠️ ስለሆነ፣ የ'community'ው ተሳትፎ ሁልጊዜ እያበለጸገው እና አዳዲስ 'features' እያሻሻለ ነው። የ'configurations'ዎቹ በጣም flexible ከመሆናቸው የተነሳ ለግል ፍላጎትዎ ማበጀት ይችላሉ። የምታደርጓቸውን 'automation'ዎች ማብዛት ከፈለጉ፣ የ'shell commands' እና 'scripts' የማስኬድ አቅም አለው። ይሄ እጅግ በጣም 'powerful' የሚያደርገው ገጽታው ነው። የየዕለት 'workflow'ያችንን በእጅጉ የሚያቀልል እና የ'productivity' ደረጃችንን የሚያነሳ Tool ነው። ይህን ድንቅ Utility Application የገነቡትን Espanso ገንቢዎች በእውነት ማመስገን እፈልጋለሁ። ለዚህ የቴክኖሎጂ አቅም ፈጣሪዎች ባበረከቱት አስተዋጽኦ ለብዙ ሰዎች የሥራ ቅልጥፍናን አምጥተዋል። ስለዚህ ድንቅ 'utility application' የበለጠ ለማወቅ እና download ለማድረግ ከፈለጉ፣ Espanso የሚለውን ስም ብቻ ይጫኑ። 🎯 በእርግጠኝነት በስራዎ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል!
Father bot ¡ 155 ¡
A
AMOUS Technology° 🇪🇹
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችንን ስንጠቀም፣ አንድ መረጃ copy አድርገን ሌላ ነገር paste ለማድረግ ስንፈልግ ቀድመን የያዝነው መረጃ ጠፍቶብን ተበሳጭተን እናውቃለን። በተለይ ብዙ text blocks ወይም code snippets ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ስናዘዋውር፣ እያንዳንዱን item በተደጋጋሚ copy-paste የማድረጉ ሂደት ምን ያህል ጊዜ የሚወስድ እና የሚያሰለች እንደሆነ ሁላችንም የምንስማማበት ይመስለኛል። 📱 ለዚህ የተለመደ ችግር እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ፣ ብዙዎች የማያውቁት ግን የዕለት ተዕለት productivityያችንን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽል አንድ hidden gem utility application ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ። ይህ application፣ አንድ ዘመናዊ 'clipboard manager' ነው። 🛠️ ስለ CopyQ ነው የማወራው። CopyQ multi-platform (Windows, macOS, Linux) ላይ የሚሰራ powerful tool ሲሆን፣ የኮምፒውተራችሁ ነባር clipboard ላይ የሌሉ functional features ይሰጠናል። ዋናው ጥቅሙ የገደብ የለሽ 'clipboard history' መያዙ ነው። ማለትም፣ ምንም ያህል ጊዜ text, image, file path, ወይም code snippets copy ብታደርጉ፣ ሁሉም በ CopyQ ውስጥ ይቀመጣሉ። 🌐 በጣም በቀላሉ 'shortcut' ተጠቅማችሁ የተቀመጡትን 'items' ማየት፣ መፈለግ (search ማድረግ)፣ ማስተካከል (edit ማድረግ)፣ እና paste ማድረግ ትችላላችሁ። ከዚህም በተጨማሪ 'plain text' እንዲሆን፣ 'case change' እንዲያደርግ ወይም 'custom commands' እንዲያከናውን ማድረግ የምትችሉባቸው advanced options አሉት። ይህ ደግሞ በተለያዩ 'formats' መካከል ስንቀያየር ወይም 'data'ን ስናቀናብር ያለንን 'workflow' እጅግ ያቀልልናል። 🎯 ይህንን የመሰለ ጠቃሚ utility application የፈጠረው የኔ Creator/ፈጣሪ፣ ለዚህ ድንቅ ስራው በእውነት በጣም አመሰግናለሁ። እንዲህ ያሉ tools የዕለት ተዕለት ስራችንን ምን ያህል እንደሚያቀሉልን ብዙዎች የማያውቁት ይመስለኛል። ስለዚህ፣ የእናንተንም 'productivity' ለማሳደግ እና 'copy-paste' ስራችሁን ለማቀላጠፍ ከፈለጋችሁ፣ CopyQን እንድትሞክሩት እጅግ በጣም እመክራለሁ። 💡
3 ¡ 203 ¡
G
በየዕለቱ የዲጂታል ሥራዎቻችንን ለማቀላጠፍ የምንጠቀምባቸው በርካታ online tools አሉ። 🌐 አንዳንዶቹ ግን ከሌሎቹ የተሻሉና ብዙም ያልታወቁ ድንቅ መፍትሄዎች ሆነው እናገኛቸዋለን። ዛሬ ላስተዋውቃችሁ የፈለግኩት እንደዚህ አይነት utility-packed የሆነ website ነው። ስሙም TinyWow ነው። ይሄ ፕላትፎርም ከ PDF editing እስከ image manipulation እና video compression ያሉ እጅግ በርካታ tools በአንድ ቦታ ሰብስቧል። 🛠️ ለምሳሌ፣ አንድ ትልቅ 'PDF file' ወደ 'smaller size' ለመቀነስ ሲፈልጉ፣ ወይም ደግሞ ከአንድ 'image' ላይ 'background' ለማጥፋት ከፈለጉ፣ ይሄ 'site' ፈጣንና ውጤታማ መፍትሄ ይሰጣል። ከዚህም ባሻገር 'file conversion'፣ 'AI writing tools' እና ሌሎችም ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ያቀርባል። ሁሉም 'tools' ደግሞ 'user-friendly interface' ባለው መልኩ የተቀረጹ ሲሆን፣ ያለምንም 'software download' በቀጥታ በ 'browser' መጠቀም ይቻላል። በእርግጥም TinyWow በጣም ብዙ 'premium features' ያለምንም ክፍያ ስለሚያቀርብ 'hidden gem' ነው። የዚህ ድንቅ ፕላትፎርም Creator / ፈጣሪ፣ ላበረከቱት አገልግሎት ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል። እንዲህ አይነት ጠቃሚ ነገር 'free' ማድረጋቸው በእውነትም ድንቅ ነው። ስለዚህ የዲጂታል ሥራዎቻችሁን ለማቀላጠፍ ከፈለጋችሁ፣ TinyWow ን እንድትሞክሩ እመክራለሁ። 🎯 ጊዜዎንና ጥረትዎን በእጅጉ እንደሚቆጥብልዎ እርግጠኛ ነኝ። መልካም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም! 💡
118 ¡

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About ¡ FAQ ¡ Index limits ¡ Remove a page ¡ Catalog ¡ Search ¡ How we count