English
Open in Telegram
AAL-BURHAN 𖣐

AL-BURHAN 𖣐

@Apologetics_Channel · channel · indexed since 2026-09-28
131subscribers
42average post reach
2posts in 30 days
35posts in the index
A
AL-BURHAN 𖣐
👉🏽መጠኑ ይለያያል እንጂ ሁሉም ሰው የየራሱ የሆነ ድካም ፣ ጭንቀት ፣ ሃሳብ አለበት! "አንቺ ምን አለብሽ!" "አንተ ምን አለብህ!" •••አይባልም•••!🗣
2 · 927 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
السلام_عليكم_ورحمة_الله_وبركاته🌐 😎 በ ቅርቡ ኢንሻ አላህ :ሴት ልጅ በ አይሁድ እምነት የሚል ቀለል ያለ አርቲክል እየተዘጋጀ ነው! እስከዛው ከላይ የለቀቅናቸውን articles እያነበባቹ ጠብቁን 😜 💬ሃሳብ አስተያየት ካለ በ direct message አስቀምጡልን 💬🌟
2 · 736 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم 📖 ​✍️ የዛሬው ርዕሳችን ፦ "ሴት ልጅ በአይሁድ እምነት (Judaism) አስተምህሮ እና በታልሙድ እይታ" የሚል ይሆናል። Let's see🔸 ​1️⃣ "ሴት አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግናለሁ" — በየቀኑ የሚደረግ ጸሎት! ​በእስልምና ወንድና ሴት እኩል የአላህ ባሪያዎች መሆናቸውና እርስ በእርስ መደጋገፋቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ በአይሁድ እምነት ግን አንድ አይሁዳዊ ወንድ በየቀኑ ጠዋት ሴት ሆኖ ባለመፈጠሩ አምላኩን (ሃሼምን) ያመሰግናል። ​📖 የታልሙድ ቀጥተኛ ህግ፦ በአይሁድ እምነት ውስጥ ከፍተኛው የህግ ስልጣን ባለው ታልሙድ ላይ እያንዳንዱ አይሁዳዊ ወንድ በየቀኑ ጠዋት ሲነሳ ሊላቸው ከሚገቡት ሶስት ምስጋናዎች አንዱ ይህ ነው፦ ​"ሃሼም' ሆይ አረመኔ (Gentile) አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግናለሁ፤ ባሪያ አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግናለሁ፤ ሴት አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግናለሁ።" (Talmud, Menachot 43b) 📜 ​💬፦ ምንም እንኳ ዘመናዊ የአይሁድ ምሁራን "ይህ ጸሎት ሴትን ዝቅ ለማድረግ ሳይሆን ወንዶች ብዙ ትዕዛዛትን (Mitzvot) ስለሚፈጽሙ ነው" የሚል ሰበብ ቢደረድሩም፣ የጸሎቱ ይዘት ግን ሴትን ከ"ባሪያ" እና ከ"አረመኔ" ጎን ለጎን አስቀምጦ ማመስገኑ እውነታውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። 2️⃣ ወንድ ልጅ ባለበት ቤት ሴት ልጅ ፈጽሞ አትወርስም! ​እስልምና ሴት ልጅን ገና ከመነሻው ራሷን የቻለች የንብረት ባለቤትና በማንኛውም ሁኔታ ወራሽ ሲያደርጋት፣ በአይሁድ እምነት ግን ሴት ልጅ በአባቷ ወይም በባሏ ጥላ ስር ካልሆነች በስተቀር የራሷ የኢኮኖሚ ህልውና የላትም። ​📖 የBIBLE (ብሉይ ኪዳን) ቀጥተኛ ህግ፦ ​"ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ሰው ቢሞት ወንድ ልጅም ባይኖረው ርስቱ ለሴት ልጁ ይለፍ" (ኦሪት ዘኍልቍ 27:8) ​💬 ፦ ታዋቂው የአይሁድ ተንታኝ Rashi ራሱ ይህንን ጥቅስ ሲያብራራ "ወንድ ልጅ ወይም የእሱ ተባዕት ዘር (ወንድ የልጅ ልጅ) ካለ ሴት ልጅ ፈጽሞ አትወርስም" ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል። ህጉ "ወንድ ልጅ ከሌለ ብቻ" የሚል ግልጽ ቅድመ-ሁኔታ ያስቀመጠ በመሆኑ፣ ወንድ ልጅ ባለበት ሁኔታ ሴት ልጅ በቅንጣት ታክል እንኳን የመውረስ መብት እንደማይኖራት ጥርጥር የሌለው ግልጽ ህግ ነው። ​3️⃣ ሴት ልጅን ለአገልጋይነት (ለባርነት) መሸጥ! ​በእስልምና ሴት ልጅን መሸጥ ቀርቶ የገዛ ልጁን በጥሩ ስነ-ምግባር ያሳደገ ሰው ጀነት እንደሚገባ ሲያስቀምጥ፣ በአይሁድ እምነት ግን አባት ልጁን መሸጥ የሚችልበት ህግ በሃሼም ሃይማኖታዊ ህግጋት ውስጥ ተደንግጓል። ​📖 የBIBLE (ብሉይ ኪዳን) ቀጥተኛ ጥቅስ፦ ​"ሰውም ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ ባሪያዎች እንደሚወጡ ርሷ አትውጣ።" (ኦሪት ዘጸአት 21:7) ​💬፦ የአይሁድ ሊቃውንት ይህ ሽያጭ "የመጨረሻው አማራጭ ድህነት ሲገጥም ብቻ ነው" ወይም "ለጋብቻ ታስቦ ነው" የሚል ማስተባበያ ያቀርባሉ። ሆኖም ግን፡- ​ድህነት ቢኖር እንኳ ወንድ ልጅን መሸጥ ፍጹም ክልክል ሲሆን፣ ይህንን የባርነት ቀንበር በገዛ ሴት ልጅ ላይ ብቻ መጫኑ፣ ​ገዢው ሰውዬ እሷን ወይም ልጁን እንዲያገባ ቢታዘዝም፣ እርሱ ያንን ማድረግ ባይፈልግና ጥሏት ቢሄድ እንኳ ለደረሰባት ስብራት የሚሆን ካሳ ሳይኖራት፣ መዳኛዋ "መልሰው ከገዟት" (ከዋጇት) ብቻ መሆኑ ህጉ ሴቷን እንደ ግዑዝ የንግድ እቃ እንደሚመለከታት ያረጋግጣል።  4️⃣በወር አበባ ጊዜ እንደ ተላላፊ በሽታ መገለሏ! ​እስልምና በወር አበባ ወቅት ሴቶች ከባሎቻቸው ጋር አብረው እንዲበሉ፣ እንዲጠጡና ምንም ዓይነት ማ… Read in full →
4 · 796 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
السلام_عليكم_ورحمة_الله_وبركاته🌐 📖 በ ቅርቡ ኢንሻ አላህ :ሴት ልጅ በ "Western Feminism" የሚል ቀለል ያለ አርቲክል እየተዘጋጀ ነው! 🖋️እስከዛው ከላይ የለቀቅናቸውን articles እያነበባቹ ጠብቁን ✍️ ሃሳብ አስተያየት ካለ በ direct message አስቀምጡልን 💬🌟
3 · 901 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
Video
9.0 MB
Listen Carefully!!🔺 Haram relationship🔵 📣በደንብ share አድርጉት ⛓
6 · 660 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
Link
click to show
📖 ​☪☪☪☪☪️ ​🪶 የዛሬው ርዕሳችን ፦ "ሴት ልጅ በምዕራባውያን ፌሚኒዝም (Western Feminism) እይታ " የሚል ይሆናል። Let's see🔸 ​1️⃣ "ሴት ልጅ ነፃ ለመውጣት ወንድን መምሰል አለባት!"( ተፈጥሮን የመካድ ፍልስፍና ) ​የምዕራባውያን ፌሚኒዝም ትልቁ ውድቀት ሴት ልጅን በራሷ ተፈጥሮና ማንነት ከማክበር ይልቅ፣ "ሴት ልጅ ስኬታማ የምትሆነው ወንድ የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ስታደርግና ወንድን ስትመስል ብቻ ነው" የሚል የተሳሳተ ሚዛን ማስቀመጧ ነው። 🔹ታዋቂዋ የፌሚኒዝም እና የፍልስፍና እናት በመባል ምትጠራው Simone de Beauvoir "The Second Sex" በተሰኘው ታዋቂ መጽሐፏ ላይ እንዲህ ብላለች፦ ​"ሴት ሆኖ አይወለድም፤ ይልቁኑ ሴት ይኮናል... እናትነትና የቤት ሕይወት ሴቷን ባሪያ የሚያደርጉ ወጥመዶች ናቸው።" (Simone de Beauvoir, The Second Sex, 1949) 📖 ​🪶 እውነታው፦ ፌሚኒዝም የሴቷን ተፈጥሯዊ የእናትነት፣ የቤት እና የቤተሰብ እሴት እንደ ተጨቆኑበት/ባርነት ሲቆጥር፣ ከቤቷ ወጥታ ለካፒታሊስት ድርጅቶች መሥራቷን ደግሞ እንደ "ነፃነት" ይስላል። ይህ ደሞ ሴቷን ከራሷ ተፈጥሮ ጋር በማጋጨት ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ ይከታታል ።  ​2️⃣ የሴት ልጅ አካል ለንግድና ለማስታወቂያ መጠቀሚያ መደረጉ! ​ምዕራባውያን "ሴትን ነፃ አወጣናት" ቢሉም፣ በተግባር ግን ሴት ልጅን የንግድ ዕቃ (Commodity) አድርገዋታል። 🕶​OnlyFans እና Pornography፦ የሴትን ልጅ አካል በገንዘብ መሸጥን እንደ "የሰውነት ነፃነት" በመስበክ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያፈሱበት የባርነት ዘመን ንግድ አድርገውታል። ሴቷን ከሰብአዊነቷ ይልቅ በአካሏ ብቻ እንድትመዘን አድርገዋታል። ​ 🔹ታዋቂዋ ምዕራባዊት ደራሲ Naomi Wolf "The Beauty Myth" በተሰኘው መጽሐፏ ላይ የምዕራቡን ዓለም ግብዝነት እንዲህ ታጋልጣለች፦ ​"ካፒታሊዝም ሴቶችን ከቤት ያስወጣቸው ለነፃነታቸው ሳይሆን፣ አዲስ የኢኮኖሚ ገበያ ለመፍጠር ነው። ሴቶች አካላቸውን እንዲጠሉና አካላቸውን ለመሸጥ ወይም ለማስዋብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዲያወጡ በሚደረግ የንግድ ማሽነሪ ውስጥ ተይዘዋል።" (Naomi Wolf, The Beauty Myth, 1990) 📖 ​🪶 እውነታው፦ ዛሬ በምዕራቡ ዓለም ከሽቶ እስከ መኪና ድረስ ማንኛውም ምርት እንዲሸጥ የሴቷ አካል እርቃኑን ተስሎ ማስታወቂያ መደረግ አለበት። ​3️⃣ የቤተሰብ መፍረስና የእናትነት ክብር መሬት መውደቅ! ​ፌሚኒዝም ትዳርንና ቤተሰብን እንደ "የወንዶች ጭቆና ሥርዓት (Patriarchy)" ስለሚመለከት፣ ሴቶች እንዳያገቡና ልጆችን እንዳያሳድጉ ቅስቀሳ ያደርጋል። 🔹አክራሪዋ የፌሚኒስት ደራሲ Shulamith Firestone "The Dialectic of Sex" በተሰኘው መጽሐፏ ላይ አደገኛውን ዓላማቸውን እንዲህ ገልጻዋለች፦ ​"የመጨረሻው የፌሚኒዝም አብዮት ግብ የፆታ ልዩነትን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን፣ የቤተሰብ መዋቅርን Nuclear Family ሙሉ በሙሉ ማፍረስና እናትነትን ማስወገድ ነው።" (Shulamith Firestone, The Dialectic of Sex, 1970)📖 ​🪶 እውነታው፦ በዚህ ፍልስፍና ምክንያት በምዕራቡ ዓለም የፍቺ መጠን ከ50% በላይ ደርሷል። በርካታ ሴቶች የእናትነትን ታላቅ ጸጋና ደስታ አጥተው፣ በዕድሜያቸው ማጠቃለያ ላይ ብቸኝነትና ጭንቀት (Depression) ሰለባ ሆነዋል። ሴት ልጅ ቤት ውስጥ ልጆቿን ማሳደጓ እንደ ዝቅተኛነት ሲቆጠር፣ የሌላ ሰውን ኩባንያ ማገልገሏ ግን እንደ ትልቅ ስኬት ይቆጠራል! ​4️⃣… Read in full →
3 · 608 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
🤲ሰላትን አድራ🤲 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል 🪶፦ ﴿إنّ الصلَواتِ الخمْسَ، يُذْهِبْنَ بِالذُّنوبِ كَما يُذهِبُ الماءُ الدَّرَنَ.﴾ 🕋 “አምስቱ ሰላቶች ወንጀልን ያስወግዳሉ (ያሰርዛሉ) ልክ ውሃ ቆሻሻን እንደሚያስወግደው።” ሶሂህ አልጃሚ: 1668 📒
3 · 658 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
☁️የማይረሳንን እናስታውስ🌙 ✍️ከአቡ ሁረይራ 💚 ተይዞ: ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أكثِروا ذكرَ هاذمِ اللَّذّاتِ: الموتِ﴾ “ጥፍጥና ቆራጭ የሆነውን (ሞት) ማስታወስ አብዙ።” 📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 2307
2 · 586 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
✍️ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إذا قال العبدُ الحمدُ للهِ كثيرًا قال اللهُ تعالى اكتُبُوا لعبدي رحمتي كثيرًا﴾ “ባሪያው፦ ‘የበዛ ምስጋና ለአላህ ይሁን’ ሲል የላቀው 🙏 ደግሞ እንዲህ ይላል፦ ‘የበዛ ራህመትን’ ለባሪያዬ መዝግቡለት።” 📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 7/1335
1 · 338 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
💡ደስ የሚለው ነገር የ ፍርዱ ቀን ዳኛ 🙏 መሆኑ ነው 💔 ✨
231 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
✍️ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَا تَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّى تُؤْمِنُوا، وَلَا تُؤْمِنُوا حَتَّى تَحَابُّوا﴾ “ጀነትን አትገቡም እስካላመናችሁ ድረስ። አማኝ አትሆኑም እስካልተዋደዳችሁ ድረሰ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 54🖋 ለ🙏 ብለው ከተዋደዱት እና ነገ በአርሽ ጥላ ስር ከሚጠለሉት ያድርገን 🤲
185 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
💭 ወላሂ እያየናቸው ያሉ ነገራቶች ከምንም በላይ ልብ የሚሰብሩ እና ከሰውኛ አስተሳሰብ የወጡ ናቸው🙁! የሰው ልጅ ደም የረከሰበት ዘመን ይሄ ነው! የ ሰው ልጅ ደም ከእንስሳ ደም የበታች የሆነበት ዘመን, ማንም ተነስቶ የሰውን በግ አያርድም እንዴት ነው የሰው ልጅ ሰው ላይ ካራ የሚመዘው! ነብዩና ሙሀመድ 🤎 የሰው ልጅ ደም ሚረክስበት ጊዜ ይመጣል ብለው ነበር ይሄው እያየነው ነው! አላህ ከ እንዲህ አይነቱ ፊትና ይጠብቀን, ፍትህ ለ ተበዳዮች ደም ያረብ🤲
152 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
📖ኢቅራ ኦላይን የቂርአት ማዓከል🕌 🌎በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጭ በአሜሪካ:በአውሮፓ:በአረብ ሀገራት: እንዲሁም በመላው አለም ለምትገኙ ለሙስሊም ቤተሰቦች የቀረበ🎓        🎙️ሚሰጡት ትምህርቶች📄 ✅ቁርአን መቅራት📖 ✅ሐዲስ መማማር📒 ✅ኢስላማዊ ተርቢያ 🧔 ✅ሙክተሰር ኪታቦች📚 🌐 https://t.me/iqra74 📍@Iqraquran11 📞+251948193520 📞+251970725874
1 · 536 ·
AL-BURHAN 𖣐
🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ዛሬ አጠር ያለች ፅሁፍ ትኖረናለች የአላህ ፍቃድ ከሆነ! ተዘጋጁ 📚
1 · 123 ·
📖 ☪☪☪☪☪️ ✍️የተወኩልና የየቂን ጥበብ💡 🙏በተከበረው ቃሉ📖 ስለ እውነተኛ ምእመናን አቋም እና በእርሱ ላይ ስለመደገፍ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ ❇️وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ ۚ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ ۚ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا ❇️ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡✳️ሱረቱ አጥ-ጠላቅ፡3📖✳️ ✍️ይህ አንቀጽ የልባችንን እረፍትና ሰላም የሚወስን ታላቅ መርህ ነው። ሰው በዚህ ምድር ላይ ሲኖር የሚጨነቅባቸው፣ የሚፈራቸውና የሚያሳስቡት ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። 🫀ነገር ግን ሙሉ ልቡንና ጉዳዩን ወደ 🙏ያስጠጋና በእርሱ ላይ የተመካ ሰው፣ 🙏 ለነገሮቹ ሁሉ በቂው እንደሚሆን ያረጋግጥለታል። 🎙ኢብኑል ቀይም رحمه الله፣ ስለ ተወኩል ሲያብራሩ፦ 💬ተወኩል ማለት በምክንያቶች መጠቀምና ጥረት ማድረግ፣ ነገር ግን በልብ ሙሉ በሙሉ በምክንያቶቹ ሳይሆን በምክንያቱ ፈጣሪ (በ🙏) ላይ ብቻ መደገፍ ነው💬 ይላሉ። 💡ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ሥራ ይሠራል፣ ያጠናል፣ ወይም ሕክምና ያደርጋል። ነገር ግን፦ ⭕️ «ውጤቱን የሚያመጣው ጥረቴ ነው» ብሎ ከተመካ፣ ከራሱ ድክመት ጋር ይተዋታል። ☑️«እኔ ምክንያቱን አደርጋለሁ፤ ስኬቴና ውጤቴ ግን በ🙏 እጅ ነው» ብሎ ከተመካ፣ 🙏 በቂው ይሆናል። ❓የሚጨነቅ፣ የሚፈራ፣ ወይም ነገው የሚያስፈራው ሰው እውነተኛውን የተወኩል ጣዕም ሲቀምስ ልቡ ሰላም ያገኛል። ምክንያቱም ሙሉ የቂን ያለው ሰው የሚያስበው፦ ✳️🙏የጻፈልኝ ነገር በፍጹም አያልፈኝም፤ 🙏 የከለከለኝንም ነገር ማንም ሊሰጠኝ አይችልም✳️ ብሎ ነው። 🤍ሰዎች ቢቃወሙትም፣ ሁኔታዎች ቢከብዱትም፣ የያዘው 🙏 ሁሉን ቻይ መሆኑን ያውቃል። 🖋እውነተኛ ተወኩል፦ “እውነተኛ ተወኩል ማለት እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ሳይሆን፣ በችሎታህና በስራህ ሙሉ ጥረት እያደረግክ፣ የልብህን መደገፊያ ግን ለ 🙏 ብቻ ማድረግ ነው። 📝“ስለዚህ ለወደፊት ህይወትህ ስታቅድ፣ ለትምህርትህ ወይም ለስራህ ስትደክም፣ የምትተማመንበት ነገር የራስህ አእምሮ ወይም የሰዎች እርዳታ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። አንተ ምክንያቱን አድርግ፤ውጤቱን ደግሞ ለ🙏 አስረክብ። ነገሮች እንደጠበቅከው ቢሄዱ 🙏ን አመስግን፤ እንደፈለግከው ባይሄዱ ደግሞ «🙏 ለኔ የተሸለውን ያውቃል» ብለህ ሰከን በል። 🙏 ዘንድ የተከማቸልህ ጥበብና ኸይር በፍጹም አይባክንም። 🙏 ልባችንን በእርሱ ብቻ ከሚመኩት፣ ነገራቸውን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ከሚሰጡትና እውነተኛውን የየቂን ጣዕም ከሚያገኙት ባሮቹ ያድርገን። “اللهم اجعلنا ممن توكل عليك فكفيته، واستهداك فهديته، واستنصرك فنصرته. آمين”🤲 🌐https://t.me/Apologetics_Channel
4 · 235 ·
A
A
AL-BURHAN 𖣐
የዚህ Generation ነገር ግርም የሚለኝ እኔን ብቻ ነው!? Haram Relationship ላይ ሆነው restaurant ይገቡና "ስጋው halal ነው?!" ብለው ይጠይቃሉ። አጂብ •••°
1 · 221 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إن لكلِّ أمةٍ فتنةً، وإن فتنةَ أمتي المالُ.﴾ “ለሁሉም ህዝብ የራሱ የሆነ ፈተና አለው። የኔ ህዝቦች ፈተና ደግሞ ገንዘብ ነው።” 📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 2148
3 · 176 ·
A
AL-BURHAN 𖣐
📖☪☪☪☪☪️ 📝የሪዳ (الرضا) ውበት🏮 🎤አላህ ﷻ በተከበረው ቃሉ ስለ ባሮቹ ሁኔታና ስለ ውሳኔው ሲናገር እንዲህ ይላል፦ ❇️كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ وَهُوَ كُرْهٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ❇️ ❇️መጋደል እርሱ ለእናንተ የተጠላ ሲሆን በእናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡ ❇️ (ሱረቱል በቀራህ፡ 216) 🔂ይህ አንቀጽ በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙንን ውጣ ውረዶች የምንመለከትበትን መነፅር ሙሉ በሙሉ የሚቀይር መመሪያ ነው። ሰው በፍጡርነቱ አጭር እይታ ስላለው፣ አሁን የሚታየውን ደስታ ወይም ችግር ብቻ ያያል። አላህ ግን የቀደመውንም፣ የወደፊቱንም፣ የነገሮችን ጥቡቅ አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ያውቃል። 📖ኢብኑ ዐጣእላህ አል-እስከንደሪ 🇧🇬፣ ስለ «ሪዳ» (በአላህ ውሳኔ መውደድ/መርካት) ሲያብራሩ፦ 🎵 «እውነተኛ እረፍት የሚገኘው ነገሮች አንተ በፈለግከው መንገድ ሲሄዱ ሳይሆን፣ አላህ በወሰነልህ መንገድ ሲሄዱ በልብህ ሙሉ በሙሉ ስትቀበላቸውና ስትወደው ነው» ይላሉ። ☑️ለምሳሌ፦ አንድ ሰው የፈለገውን ነገር አጥቶ ሊሆን ይችላል — የሚወደው ሥራ አልተሳካለትም፣ ወይም ያቀደው መንገድ ተዘጋበት። በዚህ ጊዜ፦ ✍️በአላህ ውሳኔ ካልረካ፣ ልቡ ሁልጊዜ በቁጭት፣ በጭንቀትና በምሬት ይቃጠላል። ->«አላህ አውቆና አዝኖልኝ ነው የከለከለኝ» ብሎ በሪዳ ከተቀበለው ግን፣ አላህ በልቡ ውስጥ ሰላምና እረፍት ያሰፍንበታል። ✅የሪዳ ባለቤት የሆነ ሰው አላህ የሰጠውንም ሆነ የከለከለውን በጸጋ ይቀበላል። ❓«አላህአንድን ነገር ከከለከለህ፤ የከለከለህ በስህተት ወይም በስስት ሳይሆን፣ የተሻለውን ሊሰጥህ ወይም ከትልቅ አደጋ ሊጠብቅህ ነው።» ነገሮች ቢጠቡም፣ በሩ ቢዘጋም፣ የአላህ እዝነትና ጥበብ ከሁሉ በላይ መሆኑን ማወቅ አለብህ። ☑️እውነተኛ ሪዳ፦ “እውነተኛ ሪዳ ማለት ችግር አይንካኝ ወይም ሕመም አይሰማኝ ማለት ሳይሆን፣ ምንም ዓይነት ፈተና ቢመጣ «አላህ ያደረገው ሁሉ መልካም ነው» ብሎ ልብን ለአላህ ውሳኔ ማስረከብ ነው። “ስለዚህ በሕይወትህ ውስጥ ያቀድከው ነገር ሳይሳካ ሲቀር፣ ወይም የጠላኸው ነገር ሲገጥምህ፣ አላህን ከማማረርና በቁጭት ከመቃጠል ተጠንቀቅ⚠️። 🤍አላህ ላንተ ያሰበውን ጥበብ አምነህ ተቀበል። ✨ነገሮች እንደፈለከው ሲሆኑ <<አልሐምዱ ሊላህ>> በል፤ እንደፈለግከው ባልሆኑ ጊዜ ደግሞ <<አልሐምዱሊላህ አላ ኩሊ ሃል>> ብለህ ይበልጥ አመስግን። ምክንያቱም የአላህ ምርጫ ሁልጊዜም ከራስህ ምርጫ የላቀ ነው። 🫀አላህ ﷻ ልባችንን በውሳኔው ከሚረኩት፣ በሰጠው ከሚያመሰግኑት፣ በከለከለውም ላይ ጥበቡን አምነው በሰላም ከሚኖሩት ባሮቹ ያድርገን። “اللهم أرضنا بقضائك، وبارك لنا فيما قُدّر لنا، حتى لا نحب تعجيل ما أخرت ولا تأخير ما عجلت. آمين"🤲 🌐https://t.me/Apologetics_Channel
12 · 651 ·
A
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما كرهتَ أن يراهُ الناسُ فلا تفعلهُ إذا خلوتَ﴾ “ሰዎች ቢያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህን ስትሆን አትስራው።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ: 5659 https://t.me/Apologetics_Channel
23 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count