English
Open in Telegram
BBirhan Ber School 2026 GC

Birhan Ber School 2026 GC

@Berhan · channel · Education · indexed since 2026-10-01
925subscribers
142average post reach
1posts in 30 days
10 745posts in the index
B
Birhan Ber School 2026 GC
💎💎 ወርቃማ የህይወት መርሆዎች 💎💎 ፩) ቸኩለህ ቃል አትግባ። ስትቸኩል የገባኸውን ቃል ልታጥፍ ትችላለህ። ብታከብረው እንኳን ባልገባሁ ብለህ የምትጸጸትበት ሊሆን ይችላል። ማንኛውንም ውሳኔ ከመወሰንህ በፊት አስተውል። ፪) በሌላቸው ሰዎች መሃል ስለሌላቸው ነገር አብዝተህ አታውራ። በማጣቴ ያላግጣል ሊሉህ ይችላሉና። ፫) በሰዎች ንግግር እና የግል ህይወት ላይ ጣልቃ     አትግባ። ባያከብረኝ፣ ቢንቀኝ ነው ይሉሃልና። ፬) ከሰው ምንም አትጠብቅ፤ በሰው ላይም ተስፋ አታድርግ። የሚቻልህን አድርገህ ሌላውን ለፈጣሪህ ንገር። ፭) ለሁሉም ሰው ያለአድልዎ መልካም ሰው ሁን፤ መልካም ስትሆን እውነተኛ ደስታ ታገኛለህ። ፮) የሰው እንባ፣ ላብ እና ደም ፈፅሞ አይኑርብህ። በምድር ስትኖር ስጋህ፣ ስትሞት ደግሞ ነፍስህ ስትደነግጥ እና ስትሸማቀቅ ትኖራለችና። ፯) የራስህን ክብር እወቅ። ለሰው ክብርም ተጠንቀቅ። ስታከብር የበለጠ ትከበራለህና። ፰) አስተሳሰብህ ህይወትህ ነውና አስተሳሰብህን ቀና ለማድረግ ጣር። ቀና ስትሆን ሌላ ቀና ትፈጥራለህ። በቀልን፣ ቂምና ጥላቻን አስወግድ። ይቅር ባይ እንጅ በቀለኛ አትሁን። ፱) ከፍቅር ጋር ኑር፣ የህይወት መርህህ ፍቅር ይሁን። ፍቅር ሲኖርህ ሰብዓዊነትህ ይጠነክራል፤ የበለጠ ፈጣሪን ትፈራለህ። እውነተኛ፣ ሀቀኛም ትሆናለህ። ፲) አጥፍተህ ከሆነ ይቅርታ ጠይቅ። ይቅር ስትል ያንተንም፣ የሌላውንም ልብ ትጠግናለህ። ይቅር ማለት ትልቅነት እንጅ ሽንፈት አይደለምና። ፲፩) አምላክህን አመስጋኝ ሁን። የምትኖረው በፈቃዱ ነውና ምስጋናህ በሁኔታ ላይ ሳይመሰረት፣ ብታገኝም ብታጣም ተመስገን ማለትን ልመድ። ፲፪) ፈጽሞ አትዋሽ። እውነተኛ ሁን። ህይወት አጭር ናትና ዋሽተህ የምትኖረው በእውነት ከምትኖረው አይበልጥም። በዋሸህ ቁጥር ከራስህ፣ ከሰውና ከፈጣሪህ ጋር ትጣለህ። ፲፫) በክፉ አትቅና። በጎ ነገር ለመስራት ካልሆነ በስተቀር ቅናት ጥፋትን ያመጣል፤ ብዙ ቤተሰቦችን በትኗዋል። ፲፬) አታመንዝር። ራስህን ግዛ። ይህን ስታደርግ ስሜትህን ትቆጣጠራለህ፤ ራስህንና ቤተሰብህን ታድናለህ። ⏩ ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ @addisTDPoffice 
3 · 1.1K ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
Photo
የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ! (ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
667 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
Photo
ቢሮ ለ1884 መምህራን የማስተማር ስነ-ዘዴ /PGDT/ ስልጠና በክረምት መርሀ ግብር ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስራ ውል ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ተፈራረመ፡፡ (ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ1884 መምህራን የPGDT/የማስተማር ስነ-ዘዴ/ ስልጠና በክረምት መርሀ ግብር ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስራ ውል ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ተፈራርሟል፡፡ በፊርማ መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ያደረገው የጋራ ስራ ውል ስምምነት ለ1884 መምህራን በክረምት በርሀ ግብር የPGDT ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማረገገጥ እና የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማጎልበት ትልቅ ሚና እንዳለው የጠቀሱት ሀላፊው ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በሚያወጣው የስልጠና መስጫ መርሀ ግብር መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ቢሮ ያመቻቸዉን ይህንን የ PGDT ስልጠና እድል መምህራን በመጠቀም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል ያሉት ሀላፊው ስምምነቱ በ2019 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰጠው ትምህርት የቅድመ ዝግጅት ስራ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
930 ·
Birhan Ber School 2026 GC
ሰላም እንዴት ናችሁ   ለ2019 አ.ም  በአዳሪ ት/ቤቶችና  እና ሳይንስ ሸርድ   ትቤት  ለመማር  የተመዘገቡ  ተማሪዎችን  በበይነ መረብ  ፈተናውን ለመስጠት ድላችን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመፈተኛ  ጣቢያ መሆኑን አውቃችሁ  ፡-   1. የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እሮብ በ22/11/2018   2.  የ6ኛ ክፍል  ተማሪዎች ደግሞ ሀሙስ በ23/11/2018 ፈተናው እንደሚሰጥ ይታወቃል ፡፡  በመሆኑም በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እንዲገኙ ጥሪ እንድታስተላልፉላቸው በጥብቅ እናሳስባለን !!! የተፈታኝ ተማሪዎች ሊስት ከዚህ በታች ባለው Excel ይመልከቱ ማሳሰቢያ ፡- በመረጃ ክፍተት ተማሪዎቻችን እድሉ እንዳያመልጣቸው ሁላችንም የድርሻችን እንወጣ !!!        መልካም ጊዜ
1 · 886 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
Photo
የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ! (ሀምሌ 21/2018 ዓ.ም) መመዝገቢያ ሊንኮች 1. ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች https://docs.google.com/forms/d/1RRFzFMb2HEoCyRp_ye5E-joooyGYzpAMfEvFBQdbJJs/edit 2. ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ትምህርት ቤቶች https://docs.google.com/forms/d/1exSs8OJs3UzYpyzcqQ8e13-JiczbyGR1ohmYFpdHJOY/edit 3. Barnoota Sadarkaa 1ffaan duraa hanga kutaa 8ffaa isa jala jiraniif Bara Barnootaa https://docs.google.com/forms/d/1UXIAIH736rY4YoENoRNSmNsYkZsOJFrh6o7-G3qz53E/edit ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
2 · 766 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
🔐🔐  ገልብጠህ አንብበው  🔐🔐 🔐 አንድ ቀን፣ አንድ ትንሽ ልጅ ከትምህርት ቤት ደብዳቤ ይዞ ወደ ቤት መጣ፣ ለእናቱም "መምህሬ ይህንን ደብዳቤ ለአንቺ ብቻ እንድሰጥሽ ላከኝ" አላት። እናቱም ከፈተችው፣ በቅድሚያ በፀጥታ አነበበችው... ከዚያም አይኖቿ በእንባ ተሞሉ። እናትም በጥልቀት ካሰላሰለች በኋላ ትንሽ ትንፋሽ ወስዳ ደብዳቤውን ለልጇ ጮክ ብላ አነበበችለት፤ እንዲህም ስትል፡- "ልጅሽ በጣም ሊቅ ነው፣ ትምህርት ቤታችን ለእሱ እውቀት የሚመጥን አይደለም፣ እና የሚገባውን ትምህርት ስለማንሠጠው እባክሽ እራስሽ አስተምሪው።" በልጇ ላይ የተደረገው ነገር እሷንም፣ ልጁንም ቢያሳዝንም እርሷ ግን ልጇን በቤት ውስጥ ለማስተማር ወሰነች። 🔐 ዓመታት አለፉ ...። ልጁም አደገ... እና በክፍለ ዘመኑ ውስጥ ካሉት እጅግ ጎበዝ የፈጠራ ሰዎች መካከል አንዱ ሆነ። በመሆኑም፦ ለዓለም መብራት፣ ለፎኖግራፍ፣ ለቴሌግራፍ፣ ለካሜራ እና ለሌሎችም ፈጠራዎች የመፍትሔ ሠው ነበር። ልጁም እናቱ ከሞተች ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ በቤቱ ውስጥ በማስታወሻዎች የተሞላ አሮጌ ሣጥን አገኘ። በሳጥኑ ውስጥም በጥንቃቄ የተጣጠፈ አንድ ደብዳቤ ተመለከተ። ያኔ በልጅነቱ መምህሩ ለእናቱ ብቻ እንዲሠጥ የሰጠው ደብዳቤ ነበር። አነበበው እንዲህ ይላል “ልጅሽ አቅም የለውም፣ የአዕምሮ ችግር አለበት፣ ወደ እኛም ትምህርት ቤት እንዲመለስ ፈፅሞ አንፈቅድለትም።” የሚል ነበረ። 🔐 ለካንስ እናቱ ደብዳቤውን ገልብጣ ነበር ያነበበችለት። ያ ልጅ የአሁኑ "ቶማስ ኤዲሰን" ነበር። ደብዳቤውን አንብቦ ሲጨርስ ለረጅም ሰዓት አለቀሰ። ከዚያም በማስታወሻው ላይ እንዲህ ሲል ፃፈ፡- “ቶማስ ኤዲሰን ጉድለት እንዳለበት የሚታሰብ ልጅ ነበር… ለልዩ እናቴ ምስጋና ይግባትና ያ ልጅ ዛሬ ሊቅ ሆነ።” 🔐 የሰው ልጅን (በተለይ ልጆችን) የምንመለከትበት መንገድ ዕጣ ፈንታቸውን ሊለውጥ ይችላል። እናቱ ደብዳቤውን ገልብጣ ባታነብለት፣ በቤቷ ውስጥ አቅሟን አሟጣ ባታስጠናው ኖሮ፤ አንተ አትችል፣ አቅም የለህም፣ ጉድለት አለብህ፣ አርፈህ ቁጭ በል እያለች ብታሳድገው ኖሮ፤ "ቶማስ ኤዲሰን" ዛሬ ማንም፣ ምንም፣ ባልነበረ ነበር። ከ"ምክረ ትምህርት" 💎 ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ @addisTDPoffice  በጣም የሚገርም አስተማሪ ስንፀ ሀሳብ ይዟል።
3 · 780 ·
Birhan Ber School 2026 GC
Link
click to show
✔️ተማሪዎች ሆይ የ2019 የት/ት ዘመን ጥናት አሁኑኑ ጀምሩ መጽሀፍት ለማግኘት :- ✅የቅድመ 1ኛ መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3693?single ✅የቅድመ አንደኛ የእንግሊዘኛ መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/4609?single ✅የ1ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3716?single ✅የ2ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3709?single ✅የ3ኛ ክፍል  መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3702?single ✅የ4ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3685?single ✅የ5ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3678?single ✅የ6ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3670?single ✅የ7ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3659?single ➡️የ8ኛ ክፍል መጽሀፍ ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3641?single ✅Afan Oromo Grade 3-8 text books ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3099?single ✅ከ9ኛ-12ኛ ክፍል መጽሀፍ ለማግኘት ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76/3720
8 · 1.1K ·
B
ተፈጥሮ በተለያየ መንገድ ታስተምረናለች; እኛም በጥበብ እንኑርባት። ከንስር አኗኗር የምንወስደውን በጥንቃቄ እንመልከት። 🦅🦅 ንስሩ እና አዲሱ ክንፍ 🦅🦅 🦅 በአንድ ረጅም ተራራ ጫፍ ላይ የሚኖር አንድ ታላቅ ንስር ነበር። ይህ ንስር ለብዙ ዓመታት በሰማይ ላይ በነፃነት እየበረረ፣ ማዕበሎችንና ኃይለኛ ነፋሳትን እያሸነፈ የሰማዩ ንጉሥ ሆኖ ኖሯል። ነገር ግን ዕድሜው እየገፋ ሲሄድ አንድ ትልቅ ፈተና ገጠመው። ምንቃሩ በጣም ስለረዘመና ስለታጠፈ ምግብ ማደን አቀተው፤ ጥፍሮቹ ስለደነዘዙ ማናቸውንም ነገር መጨበጥ አልቻለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ ክንፎቹ በላባዎች ብዛት ስለከበዱት እንደ ድሮው ወደ ሰማይ መጥቀስ አቅቶት ዝቅ ብሎ መብረር ጀመረ። በዚህ ጊዜ ንስሩ በሕይወቱ ትልቅ ምርጫ ፊት ቆመ፦ ወይ ተስፋ ቆርጦ ሞቱን መጠበቅ፣ ወይም ደግሞ በጣም ከባድና አሳማሚ የሆነውን የምንጭ ማደስ ጉዞ መጀመር። ንስሩ ሁለተኛውን መረጠ! ወደ ተራራው ጫፍ በመውጣት ማንም በማያየው ዋሻ ውስጥ ተሸሸገ። መጀመሪያ ምንቃሩን በኃይል ከአለቱ ጋር በመምታት ሰበረው። አዲሱና ስለታሙ ምንቃሩ እስኪበቅል ድረስ ለብዙ ቀናት በራብና በሕመም ታገሠ። አዲሱ ምንቃሩ ሲበቅልለት፣ ያንን በመጠቀም የደነዘዙ ጥፍሮቹን አንድ በአንድ ነቃቅሎ ጣላቸው። አዳዲስ ጥፍሮች በቀሉለት። በመጨረሻም፣ በሰውነቱ ላይ የከበዱትንና ያረጁትን የክንፍ ላባዎቹን በሙሉ በምንቃሩ እየነጨ አረገፋቸው። ይህ አሳማሚ ሂደት አምስት ወራትን ፈጀ። ነገር ግን ከአምስት ወራት ከባድ ትግልና ሕመም በኋላ፣ ንስሩ ሙሉ በሙሉ አዲስ ጥፍር፣ አዲስ ምንቃርና ቀላል የሆኑ አዳዲስ ክንፎችን አገኘ! ከዋሻው ውስጥ በታላቅ ኩራት ወጥቶ ክንፎቹን ዘረጋ። ከዚያም ካለፈው በበለጠ ፍጥነትና ኃይል ወደ ሰማይ ጥቆ በመብረር ለተጨማሪ 30 ዓመታት በክብር መኖር ቻለ። 🦅 የታሪኩ መልእክት (Moral of the Story)፦ ሕይወታችን እንዲቀየርና ወደ ላቀ ስኬት ለመድረስ ካለን፣ አሮጌውንና የማይጠቅመንን አስተሳሰብ፣ ተስፋ መቁረጥንና የድሮ ስንፍናችንን አውልቀን መጣል አለብን። ያ አሮጌውን የመቀየር ሂደት ልክ እንደ ንስሩ ሊያምም ወይም መስዋዕትነት ሊጠይቅ ይችላል፤ ነገር ግን ያንን ጊዜ በትዕግሥት ካለፍነው በኋላ በታላቅ ኃይልና በአዲስ ስኬት ወደ ሰማይ እንጠቅሳለን! 🔄 💎 ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ @addisTDPoffice 
1 · 957 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
Link
click to show
✅በህይወታችን ልንማርባቸው የሚገቡ ጠቃሚ #️⃣አባባሎች 1️⃣. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ! 2️⃣. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ! 3️⃣. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ! 4️⃣. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ! 5️⃣ .ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ! 6️⃣. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ 7️⃣. ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ! 8️⃣. ወሬኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ! 9️⃣ .ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ! 1️⃣0️⃣. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ! 1️⃣1️⃣.አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ! 🔤🔤🔤🅰️ 🔤🔤🔤 ✅የተማሪዎች አለኝታ! ⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76
2 · 1.3K ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
#NGAT   አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡     ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket ለማግኘት የኢሜይል አድራሻችሁን መጎብኘት አትዘንጉ። @tikvahuniversity
902 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
ሐሰተኛ ገንዘብ መሥራት፣ መያዝ እና ማዘዋወር የሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት መግቢያ ሐሰተኛ ገንዘብ መሥራት፣ መያዝ እና ማዘዋወር በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ድርጊት ነው፡፡ ይህንንም ለመከላከል ድርጊቱ በወንጀል የሚያስጠይቅ እንዲሆን ተደንግጓል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ሐሰተኛ ገንዘብ መሥራት፣ መያዝ፣ ማስቀመጥ እና ማዘዋወር የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት በአጭሩ እንመለከታለን። የገንዘብ ምንነት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ሥነ-ጽሑፍ ጥናት ምርምር ማዕከል መዝገበ ቃላት (1993፣ ገጽ 505) መሠረት ገንዘብ በመግዛትና በመሸጥ ሂደት ውስጥ በሻጭና በገዥ መካከል ተቀባይነት ያለው ለመገበያያ የሚያገለግል ነገር፣ የተወሰነ ልኩ ላዩ ላይ የታተመበት የሳንቲም ወይም የወረቀት መገበያያ ነው፡፡ የሐሰተኛ ገንዘብ ምንነት ሐሰተኛ ገንዘብ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ላይ ትርጉም ያልተሰጠው ቢሆንም ሐሰተኛ ገንዘብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል ድንጋጌዎች ይዘት በመነሳት ሐሰተኛ ገንዘብ ማለት ሕጋዊ የመገበያያ ገንዘብ ሆነው እንዲያገለግሉ በሕግ የመገበያያ ገንዘቦችን የመሥራት ወይም የማሠራት ሥልጣን ባለው አካል አማካኝነት ወይም ፍቃድ ሰጪነት ከተሠሩት የመገበያያ ገንዘቦች ጋር ተመሳስለው የተሠሩ የብር ኖቶች መሆናቸውን መረዳት ይቻላል፡፡ የአንድ አገር ገንዘብ ሊሠራ የሚችለው በአገሩ መንግሥት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በአገራችን በብሔራዊ ባንክ አዋጅ ቁጥር 1359/2017 አንቀጽ 6(15) መሠረት ገንዘብ የማተም፣ የመቅረጽ፣ የማሰራጨት ወይም የማሳተም፣ የማስቀረጽ እና የማሰራጨት ሥልጣን የተሰጠው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው፡፡ የወንጀል ተጠያቂነት ሐሰተኛ ገንዘቦችን የመሥራት፣ መያዝ፣ ማስቀመጥ እና የማዘዋወር ድርጊት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ከአንቀጽ 356 እስከ አንቀፅ 362 ባሉት ድንጋጌዎች መሠረት የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት ነው፡፡ በመሆኑም  በኢትዮጵያ ወይም በውጪ አገር እንደእውነተኛ አድርጎ ለማዘዋወር በማሰብ ሕጋዊ መገበያያ የሆኑትን ገንዘቦች ያለ ፈቃድ መሥራት ወይ አስመስሎ መሥራት ከ5 (አምስት) ዓመት በማያንስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 356 ተደንግጎ ይገኛል፡፡  ሕጋዊ መገበያያ የሆኑትን ገንዘቦች ከትክክለኛ ዋጋቸው በላይ በሆነ ዋጋ እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰብ መልካቸውን መለወጥ፣ እውነተኛ መልካቸው ላይ ሌላ ነገርን መጨመር፣ ቀለማቸውን መለዋወጥ ወይም በሌላ ዓይነት ዘዴ በኢትዮጵያ ወይም በውጭ አገር ወደ ሐሰተኛነት መለወጥ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 357 መሠረት ከ15 (አስራ አምስት) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡ በተመሳሳይ በሜካኒካል፣ በፊዚካል ወይም በኬሚካል ወይም በማንኛውም ሌላ ዘዴ ተጠቅሞ የሕጋዊ ገንዘቦችን ዋጋ ዝቅ ማድረግም ከ10 (አስር) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ነው (አንቀጽ 358)፡፡  በወንጀል ሕግ አንቀጽ 359 መሠረት ማንም ሰው ሐሰተኛ የሆኑ ወይም ዋጋቸው ዝቅ እንዲል የተደረጉ ገንዘቦችን እውነተኛ ወይም ሙሉ ዋጋቸውን እንደያዙ አስመስሎ ራሱ እንዲገበያይባቸው ወይም እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰብ ወደ አገር ማስገባት፣ ከአገር ማስወጣት፣ መያዝ ወይም ማስቀመጥ ወይም ማቅረብ ከ15 (አስራ አምስት) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ ከላይ ከአንቀጽ 356 እስከ አንቀጽ 359 የተገለጹት የወንጀሎች ድርጊቶቹ የተፈፀሙት ለማዘዋወር በማሰብ እንደሆነ ግምት እንደሚወሰድ ተደንግጓል (አንቀጽ 360)፡፡  ሐሰተኛ የሆኑትን… Read in full →
629 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
Link
click to show
💪💪  አይዞህ በርታ፣ ተነስ 💪💪 💪 አፈር ልሰህም ቢሆን ተነስ፦ 'ዓለም' ለደካሞች ቦታ የላትም! ሕይወት አንዳንዴ ትበረታለች፤ ካልጠበቅነው አቅጣጫ መጥታ ዘርራ ትጥለናለች፡፡ ጉልበታችን ይዝላል፣ ተስፋችን ይጨልማል፣ ምድሩም ይከብደናል። ነገር ግን ትልቁ ውድቀት መውደቁ ሳይሆን፣ ወድቆ መቅረቱ ነው፡፡ "አፈር ልሰህም ቢሆን ተነስ" የሚለው ጥሪ፣ የሽንፈትን መራራነት ቀምሰህም ቢሆን መልሰህ እንድትቆም የሚገፋፋ የነፍስ ጩኸት ነው፡፡ መሬት መላስ ማለት የመጨረሻው የውርደትና የስቃይ ጥግ ላይ መድረስ ማለት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አፈር የነካ ሰው ወደ ታች ዝቅ ሊል አይችልም፤ የቀረው አንድ መንገድ ብቻ ነው። እሱም፦ 🧗🏽‍♂️ ወደ ላይ መውጣት! ውድቀትህ የጉዞህ ማብቂያ ሳይሆን፣ ይበልጥ ጠንክረህ እንድትነሳ የሚረዳህ መነሻህ ነው፡፡ ትቢያህን አራግፈህ ስትቆም፣ ካንተ በላይ ብርቱ የለም፡፡ እውነቱ መራራ ቢሆንም፣ ዓለም ለሚያለቅሱና እጅ ለሰጡ ሰዎች የራራችበት ጊዜ የለም። ቆመህ ስትታይ ሁሉም አብሮህ ከጎንህ ይቆማል፤ ወድቀህ ስትቀር ግን ብዙዎች ይረግጡሃል። ዓለም የምታከብረውና ቦታ የምትሰጠው ለታጋዮች፣ ለጽኑዎችና ለማይበገሩ ሰዎች ነው፡፡ "ደካማ ነኝ' ብለህ ራስህን አትልቀቅ፤ በውስጥህ ያለው አንበሳ እንዲነቃ አድርገው። ከወደቅህበት ስትነሳ የምታገኘው ጠባሳ የውርደት ሳይሆን የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ ያ ጠባሳ ምን ያህል ፈተናን እንዳለፍክና ምን ያህል ብርቱ እንደሆንክ ለዓለም የሚናገር ሕያው ምስክር ነው። አፈር የላሰ ሰው የድልን ጣዕም ከማንም በላይ ያውቀዋል። ዛሬ ላይ ያለህበት ሁኔታ ነገህ አይደለም፤ ተነስና ታሪክህን በራስህ እጅ ጻፈው፡፡ እዚህላይ ለናተ አንድ ጥያቄ  ሕይወት መሬት ላይ ዘርራ ጥላችሁ ታውቃለች፣ "ተስፋ የለም" ስትላችሁስ ምን አደረጋችሁ? አፈር ልሳችሁ የተነሳችሁበትን ያንን የድል ቀን ታስታውሳላችሁ? ዛሬ ደክሞኛል ለምትሉ ሁሉ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው፦ ተነሱ! ዓለም የእናንተን ዳግም መቆም እየጠበቀች ነው! "ወድቆ መቅረት ሞት ነው፤ አፈር ልሶ መነሳት ግን ዳግም መወለድ ነው!" 💪 ታላቁ መፅሐፍ ሲናገር፦ "ፃድቅ ሠባቴ ወድቆ፣ ሠባቴ ይነሳል"። ይላልና፦ አይዞህ ቢደክምህም ተስፋ አትቁረጥ፣ ተነስ፣ አይዞህ በርታ !!!። 💎 ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ https://t.me/Sourceofwisdom2024http
5 · 1.2K ·
Birhan Ber School 2026 GC
File
በፌዴራል_ትምህርት_ሚኒስቴር_የወጣ_የተማሪዎች_አለባበስ_ስነስርዓት_መመሪያ_ሕዳር_2000ዓ:ም_p · 469 KB · click to show
9 · 565 ·
File
የአዲስ_አበባ_ከተማ_ት_ቢሮ_የወ_ተ_መ_ህ_መመሪያ_2012_1.pdf · 366 KB · click to show
9 · 702 ·
File
የመምህራን_የዲሲፕሊን_መመሪያ_2016_ዓም።_1.pdf · 279 KB · click to show
13 · 788 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
Photo
በሀገር ደረጃ የሚገኝ ሰላም እንደግለሰብ እና በትምህርት ላይ ያለው ጠቀሜታ በአጭሩ፡ 1. እንደ ግለሰብ (ለተማሪዎች፣ መምህራን እና ወላጆች)፦ የአእምሮ ሰላም፦ ከፍርሃትና ስጋት ነፃ ሆኖ ሙሉ ትኩረትን በትምህርትና ማስተማር ላይ ማድረግ ያስችላል። የማይቋረጥ ትምህርት፦ ትምህርት ሳይቋረጥ በጊዜው አጠናቆ ለተሻለ ደረጃ ለመድረስ ይረዳል። የወላጆች እረፍት፦ ወላጆች የልጆቻቸውን ደህንነት ሳይሰጉ በስራቸው ላይ እንዲያተኩሩ ያደርጋል። 2. በትምህርት ሥርዓቱ ላይ፦ የመሠረተ ልማት ደህንነት፦ ትምህርት ቤቶች እና ቁሳቁሶች ሳይወድሙና ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል። የትምህርት ጥራት፦ የትምህርት ጊዜና ካሪኩለም ሳይስተጎል በትክክል እንዲፈጸም ያስችላል። ሀብትን ለትምህርት ጥራት ማዋል፦ ለመልሶ ማቋቋም የሚወጣው ወጪ ቀጥታ ለትምህርት መሳሪያዎችና ስልጠናዎች እንዲወል ያደርጋል። ዛሬ ካነበብኩት👍👍👍👍 From We Best👍ለነገው ትውልድ ይድረስ! ✨ካነበብኩት አካፈልኩላችሁ! tiktok.com/@webest.19 
1 · 633 ·
B
Birhan Ber School 2026 GC
File
1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም.pdf · 332 KB · click to show
1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም.pdf
1 · 440 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count