ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
B

Bible Reporters

сообщение · 2026-08-03 17:44 UTC
E
⭕️ ኤልሮኢ የመልአኩ ስም ነው ‼️ ♨️ "ኤልሮኢ" የሚለውን ቃል ሁላችንም ከልጅነታችን ጀምሮ ስንሰማ ስላደግን በደንብ እናውቀዋለን ፤ ነገር ግን በዚህ ስም የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ሳናስተውል ቀርተናል ። 📜 “እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።” — ዘፍጥረት 16፥13 🔰 አጋር "ኤልሮኢ" ብላ የጠራችው ይናገራት የነበረውን ማንነት ነው ፤ ያ ማንነት ደግሞ የእግዚአብሔር መልአክ እንደሆነ ከላይ ያሉትን ቁጥሮች በማየት መረዳት እንችላለን ። 📜 “የእግዚአብሔር መልአክም፦ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት።” — ዘፍጥረት 16፥10 🔰 መልአኩ ለአጋር ዘሯን እንደሚያበዛ እየነገራት ነው ፤ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ባዩ መልአኩ እራሱ ነው ። መልአኩ የሌላን ማንነት ንግግር በ reported speech እያቀረበ አይደለም ፤ ከዛ ይልቅ የዘፍጥረት መፅሐፍ ፀሐፊ የመልአኩን ንግግር በ direct reported speech እያቀረበ ነው ። ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እስኪ ከ direct ወደ indirect ቢቀየር ምን እንደሚል እንመልከት ። የእግዚአብሔር መልአክም "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም" አላት ። ይሄ 👆👆 የዘፍጥረት ፀሐፊ የመልኩን ንግግር በ direct reported speech ያቀረበበት ነው ፤ ወደ indirect reported speech ሲቀየር እንደዚህ የሚል ይሆናል 👇👇👇 የእግዚአብሔር መልአክም ዘሯን እጅግ እንደሚያበዛውና ከብዛቱም የተነሳ እንደማይቆጠር ነገራት ። 🧱 መልአኩ ዘሯን የሚያበዛ ከሆነ እንዴት ፍጡር ሊሆን ይችላል ?? ዘርን የሚያበዛ ፈጣሪ ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ፤ እየፈጠረ ነው ዘርን የሚያበዛው ። 📜 “ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤” — ዘፍጥረት 12፥2 🔰 አብርሃምን "ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ" ያለውን ፈጣሪ ነው ብለን አጋርን "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ያላትን ፍጡር ነው ማለት አንችልም ። መልአኩ ዋሽቷል ካልተባለ በስተቀር ፈጣሪነቱን እየተናገረ እንዳለ መካድ አንችልም ። ♨️ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ማለት "ፈጣሪ ነኝ" እንደማለት ነው ፤ እንደዚህ አይነቱን ንግግር ፍጡር ሊናገር አይችልም ፤ ስለዚህ መልአኩ ፈጣሪ ነው ። አጋር ኤልሮኢ ብላ የጠራችሁ ይሄንን ንግግር የተናገረውን መልአክ ነው ። የጌታ ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🙏🙏🙏
4.6K ·

All messages on 3 August 2026 · Whole feed · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog