ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
B

Bible Reporters

66 members
3 August 2026
S
⭕️ ኤልሮኢ የመልአኩ ስም ነው ‼️ ♨️ "ኤልሮኢ" የሚለውን ቃል ሁላችንም ከልጅነታችን ጀምሮ ስንሰማ ስላደግን በደንብ እናውቀዋለን ፤ ነገር ግን በዚህ ስም የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ሳናስተውል ቀርተናል ። 📜 “እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።” — ዘፍጥረት 16፥13 🔰 አጋር "ኤልሮኢ" ብላ የጠራችው ይናገራት የነበረውን ማንነት ነው ፤ ያ ማንነት ደግሞ የእግዚአብሔር መልአክ እንደሆነ ከላይ ያሉትን ቁጥሮች በማየት መረዳት እንችላለን ። 📜 “የእግዚአብሔር መልአክም፦ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት።” — ዘፍጥረት 16፥10 🔰 መልአኩ ለአጋር ዘሯን እንደሚያበዛ እየነገራት ነው ፤ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ባዩ መልአኩ እራሱ ነው ። መልአኩ የሌላን ማንነት ንግግር በ reported speech እያቀረበ አይደለም ፤ ከዛ ይልቅ የዘፍጥረት መፅሐፍ ፀሐፊ የመልአኩን ንግግር በ direct reported speech እያቀረበ ነው ። ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እስኪ ከ direct ወደ indirect ቢቀየር ምን እንደሚል እንመልከት ። የእግዚአብሔር መልአክም "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም" አላት ። ይሄ 👆👆 የዘፍጥረት ፀሐፊ የመልኩን ንግግር በ direct reported speech ያቀረበበት ነው ፤ ወደ indirect reported speech ሲቀየር እንደዚህ የሚል ይሆናል 👇👇👇 የእግዚአብሔር መልአክም ዘሯን እጅግ እንደሚያበዛውና ከብዛቱም የተነሳ እንደማይቆጠር ነገራት ። 🧱 መልአኩ ዘሯን የሚያበዛ ከሆነ እንዴት ፍጡር ሊሆን ይችላል ?? ዘርን የሚያበዛ ፈጣሪ ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ፤ እየፈጠረ ነው ዘርን የሚያበዛው ። 📜 “ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤” — ዘፍጥረት 12፥2 🔰 አብርሃምን "ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ" ያለውን ፈጣሪ ነው ብለን አጋርን "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ያላትን ፍጡር ነው ማለት አንችልም ። መልአኩ ዋሽቷል ካልተባለ በስተቀር ፈጣሪነቱን እየተናገረ እንዳለ መካድ አንችልም ። ♨️ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ማለት "ፈጣሪ ነኝ" እንደማለት ነው ፤ እንደዚህ አይነቱን ንግግር ፍጡር ሊናገር አይችልም ፤ ስለዚህ መልአኩ ፈጣሪ ነው ። አጋር ኤልሮኢ ብላ የጠራችሁ ይሄንን ንግግር የተናገረውን መልአክ ነው ። የጌታ ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🙏🙏🙏
4.6K ·
4 August 2026
8 August 2026
10 August 2026
11 August 2026
13 August 2026
15 August 2026
16 August 2026
17 August 2026
21 August 2026
S
💢 ለኩ የሚደረገው ዲቤት ይዘትና ቅርፅ ♨️ የጠዋቱ ፈረቃ = ከ 3:00 እስከ 7:00 ♨️ የከሰዓቱ ፈረቃ = ከ 8:00 እስከ 12:00 ♨️ ርዕስ = የእግዚአብሔር መልአክ (ዘፀ 3:2) ፍጡር ነው ወይንስ ፈጣሪ ነው ??" በጠዋቱ ፈረቃ የአንድ ለአንድ ዲቤት ይደረጋል ። 🔰 መግቢያ = 20 ደቂቃ 🔰 cross examination = 10 ደቂቃ 🔰 ጥያቄና መልስ = 25 ደቂቃ 🔰 ለሌሎች ጠያቂዎች = 20 ደቂቃ 🔰 ማጠቃለያ = 5 ደቂቃ (ጊዜ ካልበቃ) የከሰዓቱ ላይ 🔰 10 ደቂቃ የመግቢያ ንግግር 🔰 ከአወያዩ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች = 1 ሰዓት (ለእያንዳንዱ መልስ 90 ሰኮንድ) 🔰 እርስ በእርስ መጠያየቅ = 30 ደቂቃ (back and forth) አንድ ለአንድ 👆 🔰 የመጨረሻ ንግግር (ግምገማ) = 20 ደቂቃ አወያዩ (ዳኛው) ከዲቤቱ አስቀድሞ ከተለያዩ ሰዎች (ከሁለቱም ወገን) የሰበሰባቸውን ጥያቄዎች ተራ በተራ በሁለቱም ወገን ላሉት ዲቤተሮች ያቀርባል ። ለሐዋርያት ቤተእምነት ለቀረበ ጥያቄ ቀድሞ ከሐዋርያት ቤተእምነት ለዲቤት የቀረቡ ወገኖች በ 90 ሰኮንዶች ውስጥ መልስ ይሰጡና ቀጥሎ ደግሞ ከ Evangelical የተወከለው ዲቤተር ደግሞ ቀጥሎ የመልስ ምት ይሰጣል ። ከ Evangelical ተወክለው ለቀረቡ ዲቤተሮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም አሠራሩ እንዲሁ ይሆናል ። በዚህ ጊዜ የሚቀርቡት ሦስት ሰዎች ሲሆኑ ፤ ከሦስቱ አንዱ እየተነሳ በ 90 ሰከንድ ውስጥ መልስ ሰጥቶ ይቀመጣል ። የጥያቄና መልስ ሰዓት ላይ ሁለት ሰዎች እርስ በእርስ የሚጠያየቁ ይሆናል (ልክ እንደ ጠዋቱ ፈረቃ) ፤ ጠያቂው ደቂቃውን ካልጨረሰ የቀረውን ደቂቃ ለሌላ ጠያቂ መስጠት ይችላል (የጠዋቱም ላይ እንዲሁ) ። መጨረሻ ላይ ከሁለቱም ወገን አንድ አንድ ሰው ቀርቦ በሁለቱም ፈረቃ የተነሱ ሀሳቦችን በተመለከተ በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ የማጠቃለያ ሀሳብ ያቀርባል ፣ ለታዳሚው የተነሱ ሀሳቦችን summerize ያደርጋል ። የማጠቃለያ ንግግር የሚያደርገው ሰው ደቂቃው ሳያልቅ ሀሳቡን ከጨረሰ የቀረውን ደቂቃ ለሌሎቹ (አብረውት ላሉ) መስጠት ይችላል ። ዲቤቱ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ነው ፤ የቪዲዮ ቀረፃም ይኖራል (ዲቤት የሚያደርጉ ወገኖችን በማይረብሽ መልኩ) ። ይሄንን ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ቦታው ላይ መገኘት የማይችሉ ሰዎች ዲቤቱን መከታተል እንዲችሉ ነው ። ከዚህም በተጨማሪ ዲቤቱ (ክርክሩ) ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲደረግ ሁሉም ነገር በካሜራ ዕይታ ውስጥ መግባቱ የተሻለ ነው ። ♨️ ይሄ መረጃ ለሁሉም ሰው እንዲደርስ share አድርጉ 🙏🙏🙏
3.1K ·
26 August 2026
28 August 2026
1 September 2026
2 September 2026
E
የሚረዳችሁ ሰው የተገቸገረ ሠው ነው። ✍️ብዙ ጊዜ ሰዎች አይናቸውን ወደ ከፍታዎች ፣ ባለሥልጣን ፣ሀብታም እና የተማሩ ደግሞም ትልልቅ ብለው ወደሚያስቡ ሰዎች እንደሚያደርጉ እሙን ነው። ሰው ገንዘብ ስኖረው በመስጠት ፣እውቀት ስኖረው በምክር ፣ጥሩ ዘመድ ስኖረው አንዳች ጥሩ ነገር ማድረግ የገሃድ እውነት ነው። ሥጋ ለባሽን ተስፋ የሚያደርግ ግን ብዙ ጊዜ ጉዳት ፣ሐዘን ፣አላስፈላጊ መጎዳት ፣በመጨረሻ ለውስጥ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ይዳርገናል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰው የሚታመን፣ በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው(ት. ኤርም 17:5 (NASV))። ብዙ ጊዜ የሚረዳንን ሰው ከእኛ ከፍ ካለ ቦታ መጠበቅ የተለመደ ነው። አንድ አንድ ጊዜ ግን የሚረዳን ሰው ከታች ሊሆን ይችላል። ✍️ዛሬ ከሥራ ቦታ ስመለስ አንድ ነገር ገጠመኝ። በአርባ ምንጭ ከተማ ከሴቻ ወደ ታች ቁልቁለት እየፈጠንኩ ስመጣ ፣አንድ በእድሜ ገፋ ያለ አባት ወደ ታች ፣ለጸሐይ ጀርባውን ሰጥቶ እየወረደ ነበር። ይዠው ብኸድስ ቢዬ ሞተሬን አቆምኩኝና አባ ወዴት ኖት ? የእኔ ልጅ ወደታች ነኝ ፣አሉና እኔጋ መጡ። ሞተር ላይ እንደተቀመጡ የእኔ ልጅ እግዚአብሔር ይባርክህ እያሉኝ ጀርባዬ ላይ ሳሙኝ። አሜን አሜን... እያልኩኝ አባ ከየት ኖት አልኩኝ ? ልጄ ከመሥሪያ ቤት ወጥቼ ወደቤተ እየኸድኩኝ ነው። እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ አሉኝና ፣ እየጸለይኩ ነበር አሉኝ። ምንድነው አባ የሚጸልዩት ? ልጄ መንቀሳቀሻ(Transport) ያስቸግረኛል ፣እግዚአብሔር ሆይ ወደ ቤት የሚያደርሰኝን ሰው ስጠኝ እያልኩ እየጸለይኩ ነበር አሉኝና ጌታ ይባርክኽ አሉኝ አሁንም። አባ እኔ አገልጋይ ኢሳይያስ እባላለሁ ስል እልልል እሰይ የእኔ ልጅ አሉና ፣ልጄ እኔ የሚሠራው ክልል ላይ ነው ፣የዛሬ ሶስት ዓመት ወደ አርባምንጭ መጥቻለሁ ፣ሐዋሳ ረጅም ዓመት ሰርቻለው ፣ከ2004 ጀምሮ ከትልልቅ አገልጋዮች ጋር እያገለገልኩኝ ቆይቼ አሁን ወደ አርባምንጭ መጥቻለሁ ፣አሉና እኔ ሚዲያ ላይ ብቻ የማውቃቸውን አገልጋዮች ፣እሳቸው አብሮአቸው አገልግለዋል። እየገረመኝ እየሰማው እኔ ወደ ቤቴ ከሚመለስ ፣እሳቸው ወደ ሚሄዱበት ቦታ ድረስ አደርሳቸዋለሁ አልኩና ለራሴ በውስጤ ወሰንኩኝ። ታዲያስ በዚህች አጋጣሚ በሚትመስል ግኑኝነት ውስጥ እኔ አንዳች ነገር አደርግልሃለሁ አሉኝና ፣ሁለት ነገር ከእኔ ወሰዱ። ራእዬና የሕይወቴ ግብ ከሆኑ ነገሮች መሐል አንዱን በቀላሉ አደርግልሃለሁ አሉና ስልክህን ሰጠኝ አሉኝ እየገረመኝ ፣ስልክ ተለዋውጠን አድርሻቸው ወደ ቤቴ ተመለስኩ። እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቍራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፣ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች። ዳዊትም፣ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብፃዊ ስሆን፣ የአንድ አማሌቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ። የከሊታውያንን ደቡብ፣ የይሁዳን ግዛትና የካሌብን ደቡብ ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።”ዳዊትም፣ “ታዲያ ወራሪው ሰራዊት ወዳለበት መርተህ ታደርሰኛለህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እንደማትገድለኝ ወይም ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ እነዚህ ወራሪዎች ወዳሉበት አደርስሃለሁ” አለው(ሳሙ ቀዳማዊ 30:12-15 (NASV))። ✍️ዳዊትን ወደ ተማረኩ ሚስቶቹና ወደ ተወሰዱ ንብረቶች መርቶ ያደረሰው ሰው ፣በረሃብ ምክንያት መንገድ ላይ የወደቀ ፣በሞት አፋፍ ላይ የሚገኝ ፣ጉልበት የሌለው ፣አቅሙም የከዳው ሰው
282 ·
3 September 2026
9 September 2026
11 September 2026
14 September 2026
15 September 2026
16 September 2026
S
✝️ ኢየሱስን ከብሉይ ኪዳን 📜 ✅ ታላቅ የወንጌል ዘመቻ 🗓 ሕዳር 5 ቅዳሜ ♨️ መሪ ጥቅስ = ዘፀዓት 3:14 “ ... «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ ... ” ዘጸአት 3፥14 " ... I AM THAT I AM ... " Exodus 3:14 🔰 ሁላችንም በዚህ ቀን ባለንበት ከተማ ስለ ኢየሱስ ከኮሬብ ጀምረን እስከ ቀራንዮ እንስበክ ። በዚህ መንገድ መስበክ አስፈላጊ የሆነው ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ኢየሱስን አለመግለጥ ውጤታማ ስለማያደርገን ነው ። በተለይ በክርስቶስ ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት ለማፅናት መፅሐፍ ቅዱስን የሚያጣምሙ ሰዎችን (ሙስሊሞችን እና ኦንሊ ጂሰሶችን) ለመድረስ ይሄንን መንገድ መከተል ግዴታ ነው ። ♨️ ይሄ መረጃ ለሁሉም ሰው እንዲደርስ share አድርጉ 🙏🙏🙏
609 ·
Archive by month
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog