💢 ለኩ የሚደረገው ዲቤት ይዘትና ቅርፅ
♨️ የጠዋቱ ፈረቃ = ከ 3:00 እስከ 7:00
♨️ የከሰዓቱ ፈረቃ = ከ 8:00 እስከ 12:00
♨️ ርዕስ = የእግዚአብሔር መልአክ (ዘፀ 3:2)
ፍጡር ነው ወይንስ ፈጣሪ ነው ??"
በጠዋቱ ፈረቃ የአንድ ለአንድ ዲቤት ይደረጋል ።
🔰 መግቢያ = 20 ደቂቃ
🔰 cross examination = 10 ደቂቃ
🔰 ጥያቄና መልስ = 25 ደቂቃ
🔰 ለሌሎች ጠያቂዎች = 20 ደቂቃ
🔰 ማጠቃለያ = 5 ደቂቃ (ጊዜ ካልበቃ)
የከሰዓቱ ላይ
🔰 10 ደቂቃ የመግቢያ ንግግር
🔰 ከአወያዩ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች = 1 ሰዓት
(ለእያንዳንዱ መልስ 90 ሰኮንድ)
🔰 እርስ በእርስ መጠያየቅ = 30 ደቂቃ
(back and forth) አንድ ለአንድ 👆
🔰 የመጨረሻ ንግግር (ግምገማ) = 20 ደቂቃ
አወያዩ (ዳኛው) ከዲቤቱ አስቀድሞ ከተለያዩ ሰዎች (ከሁለቱም ወገን) የሰበሰባቸውን ጥያቄዎች ተራ በተራ በሁለቱም ወገን ላሉት ዲቤተሮች ያቀርባል ።
ለሐዋርያት ቤተእምነት ለቀረበ ጥያቄ ቀድሞ ከሐዋርያት ቤተእምነት ለዲቤት የቀረቡ ወገኖች በ 90 ሰኮንዶች ውስጥ መልስ ይሰጡና ቀጥሎ ደግሞ ከ Evangelical የተወከለው ዲቤተር ደግሞ ቀጥሎ የመልስ ምት ይሰጣል ። ከ Evangelical ተወክለው ለቀረቡ ዲቤተሮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም አሠራሩ እንዲሁ ይሆናል ። በዚህ ጊዜ የሚቀርቡት ሦስት ሰዎች ሲሆኑ ፤ ከሦስቱ አንዱ እየተነሳ በ 90 ሰከንድ ውስጥ መልስ ሰጥቶ ይቀመጣል ።
የጥያቄና መልስ ሰዓት ላይ ሁለት ሰዎች እርስ በእርስ የሚጠያየቁ ይሆናል (ልክ እንደ ጠዋቱ ፈረቃ) ፤ ጠያቂው ደቂቃውን ካልጨረሰ የቀረውን ደቂቃ ለሌላ ጠያቂ መስጠት ይችላል (የጠዋቱም ላይ እንዲሁ) ።
መጨረሻ ላይ ከሁለቱም ወገን አንድ አንድ ሰው ቀርቦ በሁለቱም ፈረቃ የተነሱ ሀሳቦችን በተመለከተ በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ የማጠቃለያ ሀሳብ ያቀርባል ፣ ለታዳሚው የተነሱ ሀሳቦችን summerize ያደርጋል ። የማጠቃለያ ንግግር የሚያደርገው ሰው ደቂቃው ሳያልቅ ሀሳቡን ከጨረሰ የቀረውን ደቂቃ ለሌሎቹ (አብረውት ላሉ) መስጠት ይችላል ።
ዲቤቱ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ነው ፤ የቪዲዮ ቀረፃም ይኖራል (ዲቤት የሚያደርጉ ወገኖችን በማይረብሽ መልኩ) ። ይሄንን ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ቦታው ላይ መገኘት የማይችሉ ሰዎች ዲቤቱን መከታተል እንዲችሉ ነው ። ከዚህም በተጨማሪ ዲቤቱ (ክርክሩ) ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲደረግ ሁሉም ነገር በካሜራ ዕይታ ውስጥ መግባቱ የተሻለ ነው ።
♨️ ይሄ መረጃ ለሁሉም ሰው እንዲደርስ
share አድርጉ 🙏🙏🙏
3.1K ·