Breakthrough Trading S.C ®
Photo
click to show
click to show
የቡድን ማማከር ስልጠና
ለተከታታይ ሶስት ቀናት የቡድን ማማከር (Group Coaching) ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን ይህ የማማከር አገልግሎት የሚጀምረው መስከረም 28 /2019 በቦሌ እና በሰንጋተራ ቅርንጫፍ ሲሆን፣መርሃ ግብሩ በመጀመሪያ ቀን ሙሉ ቀን የሚሰጥ ሲሆን ቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ደግሞ ግማሽ ቀን የሚሰጥ ይሆናል።
ከዚህ በፊት የኃያል ሂደት የስልጠና ጥቅል የወሰዱ ሰልጣኝ ከሆኑና ከስልጠናው ጋር ብቻ የተያያዘ ጥያቄ ወይም ስልጠናውን በግልፅ ለመረዳት እገዛ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ ይህንን የቡድን የማጠናከሪያ ክፍለ ጊዜ በመጠቀም ስልጠናውን ከቀረጹት ዕውቅ አሰልጣኞች ጋር በመጠያየቅ፣ በመመካከርና የህይወት ልምዳቸውን በመካፈል ለጥያቄዎ መልስ እና እገዛ ያገኛሉ። ቦታ ቀድሞ ያልያዘ ማንኛውም የቀድሞ ሰልጣኝ እንደማይስተናገድ በአጽንኦት እናሳውቃለን። ስለዚህም ቦታ ካሁኑ ቀድመው በቴሌግራም ዩዘር ኔም @BTSCinfo ደንበኞች አገልግሎት በማሳወቅ፤ የቡድን ማማከር አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉበትን ቅርንጫፍ፣ ስምዎን፣ ስልክ ቁጥርዎን እና መለያ ቁጥርዎን (ሲሪያል ቁጥር) በመጥቀስ ቦታ ማስያዝ እንዳይዘነጉ ከወዲሁ በትህትና እናሳውቃለን!
ማሳሰቢያ
👉 ከዚህ ቀደም ስልጠና ሲወስዱ የነበሩበትን የተግባር ደብተር እና ከስልጠናው ጋር የተያያዘ ጥያቄዎትን ይዘው መምጣትዎን እንዳይረሱ!
👉 ለቡድን ማማከር አገልግሎት ምንም አይነት ክፍያ የለውም!
👉 እባክዎን በተጨማሪም የቡድን ማማከር አገልግሎት የሚጀምርበትን ቀን በአትኩሮት ይመልከቱ። ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው ሰልጣኞች ፈጥነው ይመዝገቡ!
=== አልፋ ለስኬትዎ ጉልህ ድርሻ! ===
📍አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 3 ሽልም ህንፃ 4ተኛ ፎቅ
49 · 8.6K ·