Web appOpen in Telegram
DDebtera Media

Debtera Media

@DebteraMedia · channel · News · indexed since 2026-05-23
3 572subscribers−15 in a week
174average post reach
4.9%ER — reach to subscribers
317posts in 30 days
D
Debtera Media
Audio
[ ስንክሳር መስከ. ፳፬ ] .mp3 · 7.4 MB · click to show
Photo
click to show
Photo
click to show
Photo
click to show
2 · 147 ·
Debtera Media
Photo
click to show
Audio
10 Track 10.mp3 · 7.1 MB · click to show
🕊                         💛                        🕊    †   [     ክ ብ ር ት    ሰ ን በ ት  !      ]   †  🍒▬▬▬▬▬     †     ▬▬▬▬▬🍒 ❝ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደውን የክርስቶስን መኖር [ አኗኗሩ ] እናምናለን ፤ እሱ በቤተልሔም ተወለደ ፣ በናዝሬት አደገ ፣  ለዕረፍት ትሆን ዘንድም ሰንበትን አዘጋጀ [ ሠራ ፣ ሰጠ ] ። ... ለነገሥታት ፣ ለአሕዛብ እና ለሁሉም ሀገራት ሰላምን ያድል ዘንድ ትንሣኤውን በሰንበት አደረገ። ... ❞ [  ቅዱስ ያሬድ  ] 🕊                      💖                      🕊 ❝ እሷ ሰንበት ናት እሷ ቅድስት ናት ፣ ሰንበት ከሁሉም ዕለታት ትበልጣለች ፥ ሰንበት ግን ስለ ሰው ተፈጥራለች እኮን ! ጽዮን ፣ ቅድስት ፣ ሰላማዊት የሆነች ፣ እንደ መብራት ከሩቅ የምትታይ [ ሰዎች በተስፋ የሚጠብቋት ] እና ለሰው ልጆች መድኃኒት [ ድኅነት ] የሆነች [ የእርሱ የክርስቶስ ]  ሰንበተ ሰንበታት ናት።  ❞ [ ቅዱስ ያሬድ ]                           🕊        [    🕊 ክብርት ሰንበት  🕊     ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊
107 ·
D
Photo
click to show
Audio
[ የእግዚአብሔር ሕግ - ፴፭ - ] .mp3 · 8.9 MB · click to show
Photo
click to show
🕊                        💖                       🕊           [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒                                                    🍒 [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]         [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🌸                         ♱                       🌸 [  ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]           [    ክፍል ሠላሳ አምስት   ]           💛   ድንቅ ትምህርት  💛 [ በመምህራችን ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ማስታወሻ ፦ ትምህርቱ የተሰጠው በአባታችን በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል ዕለት ነው። 🍒                                                    🍒 ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊                              👇
94 ·
Debtera Media
🕊 [  † እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን [ሃገራችን] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] : ሐጋይ [በጋ] : ጸደይ [በልግ] ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል:: ዘመነ መጸው /ወርኀ ጽጌ/ ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም :- ፩. የእመቤታችን የቅድስት ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ :- -  የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን:: -  የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን:: -  የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን:: -  ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን:: -  ዘመኑ የበረከት ነው:: ፪. በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት [የደስታ ወቅት] ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው:: ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው:: በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል:: "ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም : አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም : አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም : ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::" † የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን ወርኀ ትፍስሕት ያድርግልን:: 🕊 🕊  †  ቅዱስ ዮናስ ነቢይ  †  🕊 † ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን ፯ ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: [፩ነገ.፲፯፥፲፯] እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች:: ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ፰፻ ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ:: "ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ [ገራገር] የለምና እንቢ አለ [ሰምቶ ዝም አለ]:: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ:: ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ :- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው:: ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ፫ ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና [ጥፋት] ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ [ምሳሌ] ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው:: "ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወ
15 ·
Audio
[ ስንክሳር መስከ. ፳፭ ] .mp3 · 2.9 MB · click to show
Photo
click to show
18 ·
Photo
click to show
Audio
[ + በአንቺ + ] .mp3 · 6.8 MB · click to show
🌺                                                  🌺 🌷  [   🕊    ወርኃ ጽጌ    🕊   ]  🌷 🌸                                                  🌸 [ 🕊 🌼 ጸአተ ክረምት 🌼 🕊 ] [ ከመስከረም ፳፮ [ 26 ] እስከ ኅዳር ፮ [ 6 ] መስከረም ፳፭ [ 25 ] በሃገራችን [ በቤተ ክርስቲያናችን ] "ጸአተ ክረምት - የክረምት መውጫ" ዕለት ነው:: 🌼 ❝ ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት ፤ ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት ፥ ንግሥታትና ቍባቶችም አመሰገኑአት። ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች ፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት ? የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ ፥ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እመለከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረድሁ። ❞ [ መኃል.፮፥፱ ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊
1 · 131 ·
Photo
click to show
Audio
[ + እንሂድ ተነሺ + ] .mp3 · 7.4 MB · click to show
Photo
click to show
🌺                                                  🌺    🌷  [   🕊    አዘክሪ ድንግል    🕊   ] 🌷 🌸                                                  🌸  ❝ አዘክሪ ድንግል ንግደቶ ዘምስሌኪ እንዘ ትጐይዪ ምስሌሁ እምሀገር ለሀገር በመዋዕለ ሄሮድስ ንጉሥ ፤ አዘክሪ ድንግል ረኀበ ወጽምዐ ምንዳቤ ወሐዘነ ወኲሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ… ❞ [ ድንግል ሆይ ፦ ርጉም በኾነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ [ ከልጅሽ ] ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ረኀቡና ጥሙን ፣ ችግሩንና ጒዳቱን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጸዋትወ መከራ ኹሉ አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዐትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ ፤ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ ] [ 🕊 አባ ሕርያቆስ 🕊 ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊
92 ·
Video
2.2 MB · click to show
🌺                                                  🌺    🌷  [   🕊   ወርኃ ጽጌ   🕊   ]   🌷 🌸                                                  🌸   ❝ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ❞ [ ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን እያቀፍሽው በተአምርና በንጽሕና ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ድንግል ማርያም ሆይ ከልቅሶ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ ፤ መልካማዬ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ]  [ 🕊 አባ ጽጌ ድንግል  🕊 ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊
80 ·
🕊                     [  † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊   †  ተአምረ ማርያም  †   🕊 † ተአምር ማለት "ድንቅ: ምልክት: ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ: በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር [ድርጊት] " ነው:: ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው:: ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን:: ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው:: ነገር ግን :- - ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት:: - ሁሌ ምልክትን [ተአምርን] አለመፈለግ:: - መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል:: - ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም:: ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል:: [ማቴ.፯፥፳፪ , ፲፪፥፴፱] ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም:: እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን:: የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው:: በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል:: ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት: የጸጋው ደጅ ናት:: እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና:: እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር:: በዚህ ዕለት ከ2007 ዓመታት በፊት ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው:: አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [የችግር ዘመን] በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው:: ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው:: "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት" ብሎ ሔደ:: ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ:: "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር [በሥራ] በሃሳብም አላውቅባት" ብሎት ወደ ቤት ገባ:: ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ" አላት:: "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው:: ግራ ገባው: ምሥጢርም ተሠወረበት:: "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ: ያወርድ: ይጨነቅም ገባ:: የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች:: ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት:: በደቂቃም የአረጋዊው ዐይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ: አብቦ አፈራ:: ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ:: "አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው:: "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው" አላት:: እርሷም "በማሕጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል" አለችው:: አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ:: †  🕊 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 🕊  † † ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የ
9 ·
D
Audio
[ ስንክሳር መስከ. ፳፮ ] .mp3 · 5.2 MB · click to show
Photo
click to show
Photo
click to show
Photo
click to show
9 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count