ከላይቻው የቀጠለ👇
🍽️ ፩. የጸሎት ሕይወታችን የተቆራረጠና የጥቅም ብቻ ነው!
⛅️እስኪ ራስህን በደንብ ፈትሽ፦ምግብ ላይ ብቻ የምንጸልይ አስመሳይ ክርስቲያኖች ነን! ትልቅ የሣህን ምግብ ወይም እንጀራ ሲቀርብልን አማትበን እንበላለን። ነገር ግን መንገድ ላይ ማስቲካ ስንቆረጥም፣ ቸኮሌት ስንበላ፣ ቡና ወይም ውሃ ስንጠጣ፣ መክሰስ ስንቀምስ እንጸልያለን? በፍጹም አንጸልይም!
⛅️ጸሎት ማለት እኮ ለእያንዳንዱ ወደ አፋችን ለሚገባ ነገር ሁሉ የእግዚአብሔርን ቡራኬ መጠየቂያና የመርዝ ማክሸፊያ መድኃኒት ነው!ጌታችን «የሚያምኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል... የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም» ያለው በጸሎትና በእምነት አማትበው ሲጠጡ ነው (ማር. ፲፮፥፲፯-፲፰)።
⛅️ጸሎት ሳታደርግ የምትበላው ማስቲካና የምትጠጣው ውሃ በጠላት ሰይጣን ወይም በክፉ ሰዎች አበሳጭነት ሕመም፣ ደዌና መከራ ሊያመጣብህ እንደሚችል አታውቅምን?ለእነሱስ በር እየከፈትክ እንደሆነ አታውቅ? ሰይጣን በምን ላጥቃው ድክመቱ የቱጋ ነው እንደሚል እወቅ? መቼ ጠላት ሊያጠቃህ መጥቶ መርዙን በምታከሽፍበት በኩል አያጠቃህ።
⛅️የምንጸልየው ሆዳችንን የሚሞላ ትልቅ ምግብ ሲቀርብ ብቻ ከሆነ፣ አምልኮታችን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለሆዳችን ነው ማለት ነው! ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አምላካቸው ሆዳቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው» ያላቸው እንደ እነዚህ ያሉትን ነው (ፊል. ፫፥፲፱)።
💔 ፪. በስም «የክርስቶስ» — በሕይወት «የዓለም»!
😶🌫ክርስቶስ ሲሰድቡት አልተሳደበም፤ ሲመቱት አልመለሰም፤ ለገዳዮቹ እንኳ "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ብሎ ጸለየ (ሉቃ. ፳፫፥፴፬)። አንተ ግን በትንሽ ነገር ትበቀላለህ፣ ትሳደባለህ፣ ትረግማለህ!
😶🌫ክርስቶስ በከንቱ አልተናገረም፤ አንተ ግን አንደበትህ በሐሜት፣ በውሸት፣ በዘረኝነትና በከንቱ ጨዋታ የተሞላ ነው።
😶🌫በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ቆመህ ክርስቲያን ትመስላለህ፤ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ግን አኗኗርህ፣ ንግድህ፣ ፍቅርህና ግብርህ ከማያምኑት ሰዎች በምንም አይለይም!
💥 የትዝብትና የተግሣጽ ቃል
በሕይወታችን ያልጸለይንበትን ውሃ፣ ቡናና ማስቲካ ጠጥተንና በልተን ስንታመም፦
"እግዚአብሔር ለምን ፈተነኝ? ለምን አከበደብኝ?" እያልን አምላካችንን እንከሳለን። እግዚአብሔርን የምናስበው ችግርና ሕመም ሲመጣብን ብቻ ነው!
በስም «ክርስቲያን ነኝ» እያልን አምላካችንን የምናዋርድ፣ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ የምንጠራ፣ እና ሕይወታችን ፍሬ የሌለው የበለስ ዛፍ የሆነ አመፀኞች ነን! ጌታችን በወንጌል «በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ... በሰማያት ያለው የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ ወደ ሰማያት መንግሥት የሚገባ አይደለም» ብሏል (ማቴ. ፯፥፲፮-፳፩)።
🕊️ የሁልጊዜና የየትኛውም ቦታ ክርስቲያን ሁን!
«በቤተ ክርስቲያን ቅዱስ፣ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ግን ዓለማዊ መሆን የለም!»
አንዳንዶች ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ፊታቸውን አስገብተው፣ ድምፃቸውን አሳንሰው፣ መልካም ሰው መስለው ይታዩና፤ ከቤተ ክርስቲያን ደጅ ሲወጡ ግን ቀድሞውንም የነበሩትን ማንነት ይላበሳሉ። ይህ ግን እውነተኛ የክርስትና ሕይወት አይደለም።
ሁለት ዓይነት ማንነት የለም፦ እውነተኛ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲገባ ብቻ «ቅዱስ» የሚሆን፣ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ (በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት፣ በመንገድ ላይ) ሲወጣ ግን የባህርይ ለውጥ አድርጎ ርኩስ የሚሆን አይደለም።
የሕይወት ወጥነት ፦ የክርስቶስ ተከታይ መሆን ማለት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ውጪ ዓለም ላይ ሳለህ ሕይወትህ፣ ንግግርህ፣ አቋምህ እና ሞራልህ፣አለባበስህ፣አነጋገርህ፣አረማመድህ፣አመጋገብህ ሁልጊዜም አንድ ዓይነትና ወጥ መሆን አለበት። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው አምላክ ውጪም ያለው አምላክ ነውና ምሉዕ በኲለሄ(በሁሉ የመላ) ነው እረሳኸው።
ስለዚህ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለህ መንፈሳዊ ማንነት፣ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉት የዕለት ተዕለት ውሎዎችህም ሁሉ ሊገለጥ ይገባል። ክርስቲያን መሆን ማለት በየትኛውም ቦታና ሰዓት ክርስቶስን ማንጸባረቅ ማለት ነው እንጂ፣ በቦታና በሰዓት የሚለዋወጥ ጭንብል ማጥለቅ አይደለም!
🌿 ከዚህ በኋላ ግን... እውነተኛ ክርስቲያን መሆን አለብን!
ወንድሜ/እህቴ ሆይ! ይህንን ጽሑፍ ካነበብክ በኋላ ራስህን አታልል! እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ እንጂ በስም ብቻ የሚታለል አይደለም።ዛሬ ቆም ብለህ ንስሐ ግባ! ከዚህች ሰዓት ጀምሮ፦
☕ ለእያንዳንዱ ነገር ጸልይ፦ ውሃ ስትጠጣ፣ ማስቲካ ስትቆረጥ፣ ቡና ስትጠጣ፣ የትኛውንም ትንሽ ነገር ወደ አፍህ ስታስገባ አማትበህና አምላክህን አመስግነህ ተመገብ።
🕊️ አኗኗርህ ክርስቶስን ይመስል፦ ንግግርህ፣ አሳብህ፣ ውሎህና አዳርህ ፣አለባበስህ ፣አመጋገብህ ፣አረማመድህ ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ መንፈስ ይመራ። በሥራ ቦታህ፣ በትምህርት ቤትህና በቤትህ ክርስቶስን ግለጽ ።
⛪ በቤተ ክርስቲያን መከራና ደስታ ውስጥ ሁልጊዜ ተገኝ፦ በዓመት ጥቂት ቀን ወይም በሦስቱ አጋጣሚዎች ብቻ የምትመጣ የባህል/የሬሳ ክርስቲያን አትሁን፤ ዘወትር በጸሎት፣በምጽዋት፣በጾም፣በስግደት፣በአስራት በቅዳሴና በቅድስና ሕይወት ጸንተህ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ሁን!
📖 «በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ በእንደ እናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ ራሳችሁ አታውቁምን?» (፪ኛ ቆሮ ፲፫፥፭)
🪴🥀🪴🥀🪴🥀🪴🥀🪴🥀🪴🪵🌺🪵🌺
ዘወትር በጸሎትና በምስጋና እንኑር!
⚡️✨ዲ/ን ሚኪያስ 5&12✨⚡️
👉👉 @Mik_5_12 👈👈
✨ ቃሉ ሕያው ✨
🌐//𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮
https://t.me/kaluhiyawi27
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯
2.3K ·