አባ አባ ተክለሃይማኖት አቡዬ /2/
በለኒ በለኒ ወልድየ /2/
አዝ----------------//
አባ አባ እንኳን ሰው ምድሪቱን
አባ አባ ጦም አያሳድርም
አባ አባ አምላከ ተክልዬ
አባ አባ ብዬ አፍሬ አላውቅም
አባ አባ ምድራዊ መልዓክ ነህ
አባ አባ የእቲሳ አምበሳ
አባ አባ ለደብረ ሊባኖስ
አባ አባ አንተ ነህ ሞገሷ
አዝ-------------//
አባ አባ ስማኒ ብያለው
አባ አባ ሳለ በሰማይ
አባ አባ ከኪሩቤል ተርታ
አባ አባ ሆነህ ስትታይ
አባ አባ ስምህም ሲጠራ
አባ አባ ገድልህ ሲነገር
አባ አባ እፁብ ድንቅ ያሰኛል
አባ አባ የተሰጠህ ክብር
አዝ------------//
አባ አባ አባቴ እልሃለው
አባ አባ ልጄ ሆይ በለኝ
አባ አባ የአባትና የልጅ
አባ አባ ፍቅርህ ይጽናልኝ
አባ አባ ንፍሮ ውሃ ጠጥቼ
አባ አባ ታምር አይቻለሁ
አባ አባ እባብና ጊንጡን
አባ አባ ተረማምጃለሁ
አዝ-----------------//
አባ አባ እለት በለት ሄጄ
አባ አባ ደጅ ስጠናው
አባ አባ ይሰማል ተክልዬ
አባ አባ ዛሬም ህያው ነው
አባ አባ እንቆቅልሽ ፈቶ
አባ አባ ደስ አሰኝቶኛል
አባ አባ የተክለሃይማኖት
አባ አባ ቡራኬው ደርሶኛል