EHPM - Ethiopian Health Professionals' Movement
Фотография
click to show
click to show
ድሬዳዋ ላይ በግሉ ለፓርላማ ሊወዳደር እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረው ዶ/ር ሀብታሙ አለሙ በምስሉ ላይ በሚታየው መልኩ የስም ማጥፋት፣ ዛቻ እንዲሁም ማስፈራርያዎች ከደረሱት በኋላ ራሱን ከምርጫው አገለለ። ለምርጫ ቦርድ በተከታታይ አቤቱታ ቢያስገባም ምንም ሊፈይዱ አልቻሉም፣ አሁን ደግሞ ከምርጫው እንዲወጣ ያስገደዱት የከተማው አመራሮች ለስራ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ሲያመራ አፍነው ወስደውታል።
ፖሊሶቹ ምንም አይነት የፍርድ ቤት የፍተሻም ሆነ የመያዣ ማዘዣ ሳይኖራቸው "በስልክ የተሰጠን የበላይ አመራር ትዕዛዝ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከሶስት ቀን በፊት ፍርድ ቤት አቅርበውት ዳኞቹ "አንተን ብሎ ዶክተር..." በማለት ሲያንቋሽሹት ነበር።
እንኳን ሰው ምርጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ ለመወዳደር በማሰቡ ብቻ ስቃይ የሚያይበት የድሬዳዋ አመራር አቶ ከድር ጁሀር ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል።
በስምሉ ላይ የሚታዩትን ቅንብሮች በመስራት ሲለቁ የነበሩት ከተማው ያደራጃቸው የቀን እና የለሊት የታክሲ ማህበራት አባላት የሆኑ ካድሬዎች ናቸው።
Via Elias Meseret