ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

EHPM - Ethiopian Health Professionals' Movement

сообщение · 2026-06-28 16:58 UTC
E
EHPM - Ethiopian Health Professionals' Movement
Фотография
click to show
አመኖ መከዳት! ዶክተር Habtamu Alemu ወደ ምርጫ ብዙ ሰዎች እንዳይገባ ለምነውታል:: እርሱ ለመግባት የወሰነው ከሁሉም በላይ "በመንግስት ስርዓት (System)” እምነትና ተስፋ ስለነበረው ነው:: ለዚህ ምስክሩ ምርጫው ሊጀምር ሁለት ሳምንት ቀርቶት እንኳን ነገሮች እንደሚስተካከሉ ተስፋ ስለነበረው ለከተማው ፖሊስ ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ፣ ለአቃቤ ህግ ፣እንዲሁም ለከተማና ለዋናው ምርጫ ቦርድ ነገሮች እንዲስተካከሉ ሲማጸን ነበር:: ሰሚ ግን አልነበረም:: እንዴውም ይባስ ብሎ "የከተማው ተከፋይ የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት" ስሙን በማጥፋትና የተለያዩ ምስሎችን በማቀነባበር ይለቁበት ነበር:: መታሰር የነበርባቸው ሳይታሰሩ መንግስትና የመንግስት ስርዓትን ተማምኖና ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ወደ ምርጫ የገባው ሰላማዊ የህዝብ አገልጋይ መታሰሩ ወደ ፊት ዜጎች በመንግስት ምንም እምነት እንዳይኖራቸው ያደርጋል:: #FreeDrHabtamuAlemu #freedom #diredawapolice #DireDawa #Ethiopia #diredawamayer #EthiopiaMinistiryOfJustice #followers https://www.facebook.com/100001300540779/posts/27363580016601981/?app=fbl

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog