ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

EHPM - Ethiopian Health Professionals' Movement

сообщение · 2026-07-22 10:09 UTC
E
EHPM - Ethiopian Health Professionals' Movement
Фотография
click to show
​ፍርድ ቤቱ በዋስትና ቢያስፈታውም ፖሊስ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም! ​የዶክተር ሀብታሙ አለሙን ጉዳይ ለመመልከት ትናንት ማክሰኞ ተቀጥሮ የነበረው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ በ40,000 (አርባ ሺህ) ብር ዋስትና እና በሁለት ቅድመ ሁኔታዎች (ከድሬዳዋ ከተማም ሆነ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እንዲሁም ክሱ እስኪዘጋ ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀም) ከእስር እንዲለቀቅ ወስኗል። ​ነገር ግን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላላ ወንጀል ምርመራ ክፍል "በጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ወቅት በነበረህ ተሳትፎ እንፈልግሃለን" በሚል እሱንም ሆነ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አክብሮ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም። ​ከፖሊስ መኮንን ከተገኘው መረጃ እንደተረጋገጠው፣ በዶክተሩ ላይ የሚቀርብበት አንዳች ህጋዊ የክስ ምክንያት ባይኖርም፣ መሪያ ክፍሉ በማንአለብኝነት በልጁ ላይ ተጨማሪ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ እንግልት ለማድረስ እንደሚፈልግ ተገልጿል። ​ህግ ማስከበር ያለበት አካል የፍርድ ቤት ውሳኔን አለማከበሩ ፍጹም አሳዛኝና ህግ አልበኝነት ነው። ስልጣንም ሆነ ጊዜ ተለዋዋጭ ናቸው፤ ነገ እንደዛሬው እንደማይቀጥል ከታሪክ ተምሮ ያወጡትን ህግ ማከበር የብልህነት መለኪያ ነው። ህግ ይከበር፤ ዶ/ር ሀብታሙ በአስቸኳይ ይፈታ! ​#FreeDrHabtamu #JusticeForHabtamu #HumanRightsViolation #ProtectHealthWorkers #Ethiopia #RuleOfLaw

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog