ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app

ብሔረ መፃሕፍት መወያያ ግሩፕ

сообщение · 2026-07-23 09:23 UTC
I
Фотография
click to show
ዴል ካርኒጌ ‹‹ጠብታ ማር›› ለምሳሌ ልጅህ ሲጋራ እንዳያጨስ ብትፈልግ ስለ ሲጋራ መጥፎነት አትስበክለት፡፡ ሆኖም ሲጋራ ማጨስ የአንድ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች እንዳይሆን ወይም በሩጫ ውድድር እንዲሸነፍ የሚያደርገው መሆኑን ንገረው፡፡ የሌላውን ፍላጎት የመጠበቅ ነገር ከማንኛውም ነገር ጋር ማለትም ከሕጻናት ወይም ከጥጃ ወይም ከዝንጀሮ ጋር በምናደርገው ግንኙነት ሁሉ ሊታሰብበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰንና ልጁ አንድ ቀን አንድ ጥጃ ወደ ጋጥ ለማስገባት ሞከሩ፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው የሚፈፅመውን ስህተት ፈፀሙ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን እንጂ ጥጃው የሚፈልገውን አላደረጉም፡፡ ኤመርሰን ከኋላ ወድሮ እምቢ አለ፡፡ ይህን ከንቱ ጥረቱ ታይ የነበረችው ሠራተኛ ጥጃው ምን እንደፈለገ ገባት፡፡ ጠጋ አለችና ጣቷን በዘዴ ለጥጃው አጎረሰችው፡፡ ጥጃው ጣቷን መጥባት ሲጀምር ቀስ ብላ ወደ ጋጡ እየተራመደች ይዛው ገባች፡፡ ሠራተኛው ምንም እንኳን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ባይኖራትም በዚያች ወቅት ከኤመርሰን የበለጠ ማስተዋል ችላ ነበር፡፡ ከተወለድክ ጀምሮ ያደረግካቸውን ለምሳሌ ለቀይ መስቀል ማኅበር 100 ብር የሰጠህበት ጊዜ ቢኖር እንኳን ሌላውን ከመውደድ የመነጨ በጎ ሥራ ለመሥራት ስለፈለግህ ነው፡፡ ከመርዳት ፍላጎትህ ይልቅ የብር ፍላጎትህ ቢያይልብህ መቶ ብሩን ባልሰጠህ ነበር፡፡ እርግጥ አስተዋጽኦው እንድታደርግ የጠየቀህ ሰው እምቢ የማትለው ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ እውነት አለ፡፡ ብሩን የሰጠኸው ምናልባት ከሰውየው አንድ የፈለግከው ነገር ስለነበረ ነው፡፡ ዴል ካርኒጌ “ጠብታ ማር” (1989) ጠብታ ማር ለወዳጅዎ ይጋብዙ፡፡ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን ቆየት ላሉ መፅሐፍቶች↘️ @ETHIO_PDF_BOOKS1 @BIHRE_MUSIC @BHERE_TREKA @YETMHRTPDF
5.5K ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog