ETHIO Code&Soft Select🫧💻
ፀሐይ በየቀኑ ትወጣለች... እስከ አንድ ቀን ድረስ። ☀️
እናንተ ግን "loop ናት" ብላችሁ ትንቋታላችሁ።
ትኩረት አትሰጧትም፣ እንደ ተራ ነገር ትቆጥሯታላችሁ።
"ልክ ነው" ብላችሁ ታምናላችሁ -
አሁን ያለው ነገር ዘላቂ ይመስላችኋል።
ነገር ግን ይጠፋባችኋል፣
ማንንም ሳይጠይቅ፣ ማንንም ሳያስጠነቅቅ።
የጠፋችበትን ቀን ስትደርሱ ግን -
ያንን ባዶነት የሚገልጽ ቃል እንኳ ታጣላችሁ።
ቋንቋችሁ ራሱ ዝም ይላል።
እናንተም እንደዚያው ናችሁ ከሰዎች ጋር።
በየቀኑ "ሰላም ነህ" የምትባባሉት ድምፅ፣
ዛሬም የምታዩት ፊት -
ነገ ላይኖር እንደሚችል ሳታስቡ፣
እንደ routine ቆጥራችሁ ታልፉታላችሁ።
እሱ ሲጠፋ ግን፣
ያ ክፍተት ስም የለውም።
ልባችሁ ብቻ ያውቀዋል - ቃል ግን ያጣዋል። 💔
ይህን ስታነቡ "ትክክል ነው" ትላላችሁ።
ነገ ግን ትረሱታላችሁ።
ልክ ትናንት እንደረሳችሁት።
ፀሐይ ዛሬ ወጥታለች።
ድምፁም አለ፣ ፊቱም አለ።
ግን ይህ ቅጽበት አይደገምም።
ከምሽት በፊት -
"አላችሁ" በሉ።
ዛሬውኑ በሉ፣ ነገ ሳይረፍድ። 🕊️
እኔ እናንተን motivate ለማድረግ አስቤ አይደለም። በሂወቴ ውስጥ ለእኔ ምርጡን ነገር ያደረግልኝ ሰው ዛሬ ሰላጣሁት ነው። ለእናንተም ላጣችሁት ሰው I'm worry። ሌላ ምንም አልላችሁም። መልካም ቀን ለሁላችሁም 🙏
145 ·