English
Open in Telegram
𝐄𝐄𝐳𝐮 𝐓𝐞𝐜𝐡 𝐭𝐢𝐩𝐬

𝐄𝐳𝐮 𝐓𝐞𝐜𝐡 𝐭𝐢𝐩𝐬

@EzuTech_tips · channel · indexed since 2026-08-25
3 239subscribers
43average post reach
1.3%ER — reach to subscribers
9posts in 30 days
ᴇ
ᴇᴢᴇᴅɪɴ
Photo
🚀ቴሌግራማቹ ባን ከተደረገ ለመመለስ ! ➡️የቴሌግራም አካዉንታቹ በተለያየ ምክንያት ባን ቢደረግና ቢዘጋ የምትመልሱበትን አንድ አማራጭ ልጦቅማቹ። ወደ ምትጠቀሙት ብሮዉዘር ጎግል or ክሮም ግቡና Telegram Support ብላቹ ሰርች አርጉ። ➡️ከዛ አንደኛ ላይ ሚመጣላቹን ነክታቹ ግቡ። ከዛ Please describe your problem የሚለዉ ላይ ምክንያታቹን በ English አስገቡ ለምሳሌ :- 'Dear Telegram Support Team, my number +2519444444444 has been banned but i have done noting to be happen please help me unbann my account, i will appriciate if you unbann my account' ብላቹ ማስገባት። ከዛ  ከታች ሙሉ ስም Emailና ስልክ ቁጥራቹን አስገብታቹ Submit በሉት። ➡️ለቀናት Review ካደረጉ በዋላ አካዉንታቹን ሊመልሱላቹ ይችለል እንደየክብደቱ አይተዉ ማለት ነዉ 𝐑𝐄𝐀𝐂𝐓 አርጉ አንጂ
1 · 231 ·
𝐄
𝐄𝐳𝐮....ᴡᴀᴠᴇʀ
Photo
#ተሸፋኟ የተሰኘውን እጅግ አስተማሪ እና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ በእኛ #ኢስላሚክ_ቻናል ተዘጋጅቶ ይቀርባል በውስጥ ብዙ ነገሮችን ለማስተማር ሞክረናል። ለማንበብ ዝግጁ ናቹ??
257 ·
​عــــــز الــــــديــــــن👳
Photo
Google Assistant ሊዘጋ ነው! ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት Google በብዙ ሚሊዮን አንድሮይድ ተጠቃሚዎች ለዓመታት ስንጠቀምበት የነበረውን Google Assistant ሙሉ በሙሉ ሊዘጋው መሆኑን ይፋ አድርጓል። በአዲሱ የGenerative AI Gemini እንደሚተካ ተገልጿል። አሁን ላይ በአንድሮይድ ስልኮች እና ስማርት device ላይ ዋናው የድምፅ ረዳት (Default Voice Assistant) ሆኖ የሚሰራው Gemini ነው። የGoogle Assistant ሞዴል አሁን ካለው የGenerative AI ቴክኖሎጂ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ ወደ Gemini እንዲሸጋገሩ ጉግል ግፊት እያደረገ ይገኛል። ኩባንያው አገልግሎቱን September 2026 ከአገልግሎት ውጪ እንደሚያደርገው 9to5Google ዘግቧል።
1 · 300 ·
​
መንግሥት 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውን ዛሬ በይፋ አሳውቋል። መተግበሪያዎቹ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ እንደነበር አመልክቷል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የክሪፕቶ ከረንሲ መተገበሪያዎች የኢትዮጵያን ብር ከP2P መድረክ ላይ ማስወጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል። በሌላ በኩል፤ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን አሳውቋል። በተጨማሪ በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓልም ብሏል። ከዚህ ባለፈ፣ ከቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች ጋር በተገናኘ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ መታገዱን መንግሥት አሳውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
327 ·
𝐁
𝐁𝐌°°𝚌𝚛𝚎𝚊𝚝𝚒𝚟𝚎
Photo
ሰበር ዜና!! የYouTube የMonitization መስፈርት ጭማሪ ተደረገበት። YouTube የዩትዩብ ክሬተሮች ከቻናላቸው ገንዘብ ለማግኘት (Monetized) ለመሆን የሚያስፈልገውን የWatch Hours መስፈርት በእጥፍ ማሳደጉን ይፋ አደረገ። ከዚህ ቀደም አንድ ቻናል Monetize ለመሆን ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 4,000 Watch Hoursና 1,000 Subscribers እንዲሁም በshorts በ90 ቀናት ውስጥ 10 Million እይታ ማሟላት ይጠበቅበት ነበር። አሁን በተሻሻለው ህግ መሰረት ግን የMonetization ማመልከቻ ለማስገባት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 8,000 Watch Hoursና 20 Million የshorts ዕይታ ማሟላት ይኖርባቸዋል። የSubscribers መስፈርት ከ1,000 Subscribers ጭማሪ አልተደረገበትም። ይህም ተግባራዊ የሚሆነው ከFebruary 1 ጀምሮ ነው። ይህ አዲስ መመሪያ በተለይም ገና በማደግ ላይ ላሉ Small Creators ትልቅ መሰናክል የሚፈጥር ሲሆን Monetized ለመሆን የሚወስደውን ጊዜ በእጥፍ ያራዝመዋል። ሆኖም ግን አስቀድመው Monetized የሆኑ ቻናሎች ላይ ተግባራዊ አይደሩግም ተብሏል። ✍️YouTube መስራት የጀመራችሁ ወይም ለመጀመር ያሰባችሁ ምን ተሰማችሁ?
364 ·
​عــــــز الــــــديــــــن👳
Photo
Elon musk በራሪ መኪናዎች ይኖሩናል ብሏል✈️🚓
335 ·
​
Photo
የGemini ዕለታዊ የተጠቃሚ ቁጥር 1 Billion መድረሱን የGoogle CEO Sundar Pichai አስታወቀ። ይህም 1B የተጠቃሚ ቁጥር የደረሰ 14ኛው የGoogle product መሆን ችሏል። ✍️እናንተ በብዛት የምትጠቀሙት AI chatbot ምንድን ነው? @bighabesha_softwares
415 ·
​
​عــــــز الــــــديــــــن👳
Photo
Samsung ቀጣይ በሚወጣው One UI 9.5 ያለምንም ተጨማሪ መተግበሪያ App lock (መቆለፍ ) የሚያስችል አዲስ አማራጭ አምጥቷል። በስተመጨረሻም Samsung 👏
384 ·
𝐄
𝐄𝐳𝐮....ᴡᴀᴠᴇʀ
Modes and Routines Android ስልካችን ላይ በብዛት ከማንጠቀምባቸው ነገር ግን እጅግ ጠቃሚ ከሆኑ ፊቸሮች መካከል አንዱ Modes and routines ነው። Modes and routines በSamsung Galaxy ስልኮች ላይ Built-in Automation Feature ሲሆን በርካታ ነገሮች እንደየሁኔታው እንድናስተካክል ይረዳናል። Modes እንደምናደርገው እንቅስቃሴ ወይም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ የስልክችንን ድምፅ፣ የNotifications ሁኔታና የስክሪን ገጽታ የአጠቃላይ የስልካችንን ሁኔታ automatically እንዲቀይር የምናደርግበት አሰራር ነው። ለምሳሌ ⚫Sleep Mode: ማታ ስትተኙ ስልኩ በራሱ mute እንዲሆን፣ የብርሃን መጠኑ እንዲቀንስ እና አስቸኳይ ካልሆኑ ጥሪዎች ውጭ ጥሪ እንዳይቀበል ያደርጋል። ⚫Work Mode: ስራ ቦታ ሲደርሱ ጌሞችና የሶሻል ሚዲያ አፖችን notification እንዳይመጡ በማገድ ትኩረታችን ስራ ላይ እንዲያደርጉ ይረዳል። ⚫Driving Mode (የመኪና ማሽከርከር): መኪና ውስጥ ስንገባ ስልካችን mute ወይም Don't disturb mode ላይ እንዲሆን ብሉቱዝ በራሱ እንዲበራና notification በድምፅ እንዲነበቡ ያደርጋል። Routines: "ይህ ከሆነ (IF)" -> "ይህ ይደረግ (THEN)" በሚል መመሪያ የሚሰሩ አውቶማቲክ ትዕዛዞች ናቸው። ስልካችን የተወሰነ ሁኔታ ሲፈጠር በራሱ ምን ማድረግ እንዳለበት አስቀድመን ትዕዛዝ እንሰጠዋለን። ከዚያ በኋላ If ብለን የሞላነው condition ፡ከተሟላ then ብለን የሰጠነውን በራሱ ይከውነዋል። ለምሳሌ: IF: ቤት ስደርስ እና ከቤት Wi-Fi ጋር ስገናኝ… THEN: የሞባይል ዳታ ይዘጋ፣ የስልክ ድምፅ ይክፈት፣ ስክሪን መቆለፊያ (Lock Screen) ይከፈት። Modes and Routines እንዴት ማስተካከል ይቻላል? የስልካችሁን Settings ክፈቱና Modes and Routines የሚለውን አማራጭ ምረጡ። Modes ውስጥ ከሚዘረዘሩት (Sleep, Theater, Work, Driving) ውስጥ የምትፈልጉትን መርጣችሁ በሰዓት ወይም በቦታ automatically እንዲበራ ማድረግ ትችላላችሁ። Routines tab: Routines የሚለውን ስትጫኑ ከላይ በቀኝ በኩል ያለውን (+) ምልክት ትጫናላችሁ። If (ይህ ሲሆን): የሚለውን በመጫን መሟላት ያለበትን condition ትመርጣላችሁ። ለምሳሌ፡ ባትሪ 20% ሲደርስ፣ ዩቲዩብ ሲከፈት፣ ወይም earphone ሲሰካ Then (ይህ ይደረግ): የሚለውን በመጫን የሚፈጸመውን ድርጊት ምረጡ (ለምሳሌ፡ Power saving ይበራ፣ Auto-rotate ይበራ ወዘተ) ጥቅሞቹ ⚫የባትሪ ዕድሜን ያራዝማል: ማታ ማታ የማያስፈልጉ አገልግሎቶችን በራሱ በመዝጋት ባትሪ ይቆጥባል። ⚫ጊዜን ይቆጥባል: በየቀኑ አውቶማቲክ የምናደርጋቸውን ማስተካከያዎች ስልኩ በራሱ ያከናውናቸዋል። ⚫ትኩረትን ያጠናክራል: በስራ እና በጥናት ሰዓት የሚረብሹ ነገሮችን ያስወግዳል።
1 · 454 ·
​
​عــــــز الــــــديــــــن👳
Photo
Apple ካሜራ የተገጠመለት AirPods ሊያወጣ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። ይሄ ከባድ ነዉ በጣም ለPrivacy👀 2027 🟧
479 ·
𝐄
𝐄𝐳𝐮....ᴡᴀᴠᴇʀ
Photo
📷በጉግል መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ለየት ያሉ መቀመጫዎች🤩
324 ·
𝐄
𝐄𝐳𝐮....ᴡᴀᴠᴇʀ
Photo
​🖤 «የጨለማ ብርሃን» ⚪️ (እውነተኛ ህይወትን መሰረት ያደረገ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ) ከቤተሰቦቼ ፍቅርና ሰላም ተከብቤ አድጌአለሁ...አሚሬ ላይ ትልቅ ተስፋ አለኝ... ግን ዘመኑ ያስፈራኛል! ነገር ግን የካምፓስ ህይወት ደግሞ የራሱ የሆነ የጨለማ መንገድ አለው..." አንብበው የማይጨርሱት፣ በደስታና በሀዘን የተሞላ ውብ ታሪክ!
155 ·
​عــــــز الــــــديــــــن👳
Photo
በአዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ John Ternus መሪነት በተካሄደው የApple ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ከiPhone 18 Pro በተጨማሪ በርካታ አዳዲስ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ይፋ ሆነዋል። 1️⃣ iPhone Ultra / Duo — የአፕል የመጀመሪያው ተጣጣፊ (Foldable) ስልክ! አፕል ታሪካዊ የሆነውን የመጀመሪያውን ተጣጣፊ ስልክ ይፋ አድርጓል። ⚫ሲታጠፍ 5.5 ኢንችnormal ስልክ ሲሆን ሲከፈት ወደ 7.8 ኢንች ግዙፍ OLED ታብሌትነት ይለወጣል። ⚫ሲከፈት የ4.5mm ቅጥነት ያለው ሲሆን የዕጥፋት መስመሩ እንዳይታይ በLiquid Metal ማጠፊያ የተሰራ ነው። ባህሪያት፦ በA20 Pro ቺፕሰት የሚሰራ፣ 48MP ሁለት ካሜራዎች ያሉት፣ ከApple Pencil ጋር የሚሰራና የጣት አሻራ በጎን በኩል የተገጠመለት ነው። 2️⃣ iPhone 18 Pro እና 18 Pro Max ⚫Variable Aperture ካሜራ ⚫2nm A20 Pro ቺፕ ⚫ረጅም የባትሪ ዕድሜ ⚫ተጨማሪ Glacier (በረዶ መሰል)ና Burgundy ቀለማት። 3️⃣ Apple Watch Series 12ና Ultra 4 ⚫Apple Watch Series 12 በአዲስ S12 ቺፕ የተገጠመለት ሲሆን ከሴራሚክ የተሰራ አዲስ አማራጭና የጤና መከታተያ አፕሊኬሽን ይዞ መጥቷል። ⚫Apple Watch Ultra 4 ደግሞ የባትሪ ዕድሜው የበለጠ የተሻሻለና ለስፖርተኞች ተጨማሪ የላቁ የጤናና የጉዞ መከታተያ (GPS) ባህሪያትን ያካተተ ነው። 4️⃣ AirPods 5 (አዲሱ የጆሮ ማዳመጫ) አዲስ H3 ቺፕ፦ የድምፅ ጥራቱን የላቀ የሚያደርግና የድምፅ መዘግየትን (Latency) በእጅጉ የሚቀንስ ይሆናል። የልብ ምት መለኪያ፦ ለመጀመሪያ ጊዜ በኤርፖድ ላይ Heart-rate sensor ተገጥሞለታል። ሁለት የውጪ ድምፅ አማራጮች፦ Active Noise Cancellation ቴክኖሎጂ ባለውና በሌለው ሁለት አይነት ምርቶች ይቀርባል። 5️⃣ HomePad — አዲሱ የስማርት ሆም ማዕከል አፕል የቤት ውስጥ ስማርት መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል የ7-ኢንች ስክሪንና ስፒከር ያለው አዲስ Smart Home Hub ይፋ አድርጓል። @bighabesha_softwares
169 ·
Photo
Apple በከፍተኛ የካሜራ እና የፕሮሰሰር ማሻሻያዎች የታጀቡትን iPhone 18 Pro እና iPhone 18 Pro Max ስልኮችን ይፋ አድርጓል። 🔹 ዋና ዋና የአዲሱ iPhone 18 Pro ባህሪያት፦ 📷 ትልቅ የካሜራ ማሻሻያ፦ የካሜራው ሌንስ ወደ ውስጥ የሚገባውን የብርሃን መጠን በራሱ ወይም በተጠቃሚው ፍላጎት ማስተካከል የሚያስችል 48MP Variable-Aperture ዋና ካሜራ ተገጥሞለታል። በቂ ብርሃን በሌለበት ወይም ማታ በሚነሱ ፎቶዎች ላይ ሌንሱ ሰፋ በማለት (Aperture በመክፈት) ጥራታቸው የላቀና ግልጽ የሆኑ ምስሎችን ያነሳል። ለቪዲዮ ቀረጻ የሚረዱ አዳዲስ Pro Controlsና በDolby Vision HDR የተቀረጹ 4K Time-lapse ቪዲዮዎችን handle ያደርጋል። ⚡️ የመጀመሪያው 2nm A20 Pro ቺፕሰት፦ ስልኩ በ2nm ቴክኖሎጂ የተሰራውን A20 Pro ፕሮሰሰር የሚጠቀም ሲሆን ግራፊክሱን እስከ 40% ያፈጥነዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Apple Intelligence) ስራዎችን በ2 እጥፍ በፍጥነት የማስላት አቅም አለው። 🔋የባትሪ ዕድሜ በችፕሴቱ ቀልጣፋነት ምክንያት የባትሪው ዕድሜ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። iPhone 18 Pro እስከ 36 ሰዓታት Pro Max ደግሞ እስከ 45 ሰዓታት የቪዲዮ እይታ (Video Playback) መስጠት ይችላሉ። በ15 ደቂቃ Wired ቻርጅ በማድረግ ብቻ እስከ 6 ሰዓት መጠቀም ይቻላል። ✨ ዲዛይን እና ቀለማት፦ ስክሪን ላይ የሚገኘው Dynamic Island መጠኑ በትንሹ የቀነሰ ሲሆን ተጨማሪ የስክሪን ቦታ ይሰጣል። ስልኮቹ ቀደም ከነበራቸው ቀለማት በተጨማሪ በአዳዲስ Glacierና Burgundy ቀለማት ይቀርባሉ። 📌 ዋጋ፦ የiPhone 18 Pro ዋጋ ከ$1,199 ጀምሮ ሲሆን የiPhone 18 Pro Max መነሻ ዋጋ ደግሞ ከ1,299 ዶላር እንደሚጀምር ታውቋል።
225 ·
​
Photo
Apple አዲሱን iPhone 18 Pro እና 18 Pro Max ይፋ አደረገ። Apple በዛሬው ዕለት የተለያዩ አዳዲስ ስልኮችን፣ smart watch እንዲሁም AirPods 5 እያስተዋወቀ ይገኛል። ዝግጅቱ ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቲም ኩክ ምትክ በአዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆን ተርነስ የተመራ ሲሆን በርካታ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይፋ እያደረገ ይገኛል። አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት በዓለም ላይ ከተሰሩት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያዎች ሁሉ iPhone አሁንም ቢሆን ወደር የሌለው ምርጡ መሳሪያ እንደሆነ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው የገለጿቸው ዋና ዋና ነጥቦች ⚫አፕል ለአርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ስራዎች የሚጠቀመው On-device processingና የግል መረጃ ደህንነትን የሚጠብቁ ቴክኖሎጂዎችን (Private Cloud Compute) በመሆኑ ከሌሎች የተለየ ያደርገዋል። ⚫ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ሌላ የAI መሳሪያ መያዝ ሳያስፈልጋቸው በለመዱት አይፎን ስልካቸው አማካኝነት የላቁ የ AI አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ። ⚫በአዲሶቹ አይፎኖች ላይ የተገጠመው A20 Pro ፕሮሰሰር የAI ስራዎችን በ2 እጥፍ በፍጥነትና ያለ ምንም መዘግየት ለማከናወን የሚያስችል አቅም ሰጥቶታል ብለዋል። ዝርዝር መረጃ እየተከታተልሁ አቀርብላችኋለሁ።
2 · 306 ·
𝐄𝐳𝐮....ᴡᴀᴠᴇʀ
➡️2 VERY USEFUL PC TIPS ✔️ ⚡️የPC አችሁ Graphics card እየዛገ🙀 ከተቸገራችሁ (intel'ም ቢሆን) ➡️Ctrl+Shift+Win+B በመንካት Refreshማድረግ ትችላላችሁ ⚡️ኮምፒተራችሁ በጣም እየዛገ🚬 ከተቸገራችሁ ➡️Win+R ንኩ እና %temp% ብላችሁ ፃፉ ከዛ Enter ነክታችሁ እዛ ውስጥ ያሉትን ፋይል ሁሉንም አጥፋት👍 ምንም ፋይል አይጠፋም Cache ነው ሚጠፋው ❤️‍🔥በሉ ሪአክት እና ሼር አድርጉ ከጠቀማችሁ 🔥
44 ·
Photo
✅Chat gpt Accurate and relevant የሆነ output እንዲሰጠን clear የሆነ personalization rules ይፈልጋል። ይህ prompt ደሞ የተለያየ ሰው በተለያየ መንገድ ስለሚፅፈው  ማሽኑ ግራ ይጋባል። በዚ ምክንያት chat gpt 7 ready made personalization rules setting ውስጥ ካካተተ ቆይቷል። 👉የሚመቻቹን ለመምረጥChatgpt------settings----- personalizations👍 ከዛ ይሄን ፅሁፍ አስገብታችሁ save 👇 Write in natural, human-sounding English. Avoid the AI tone: overly formal, polished, or generic phrasing.Do not use long dashes, excessive quotation marks, corporate jargon, or bureaucratic language.Choose simple, clear wording. Conversational style is fine if it helps convey the idea.Don’t repeat the same phrases or overcomplicate sentences without need.Vary sentence length and rhythm so the text feels alive. The priority is clarity of meaning, individual style, and practical value in every line.Each sentence should feel intentional, not mechanically generated.  ከጠቀማችሁ 👍
53 ·
𝐄
𝐄𝐳𝐮....ᴡᴀᴠᴇʀ
USDT ወይም ዶላር ያላችሁ መሸጥ የምትፈልጉ ካላችሁ አናግሩኝ @ezedinm1 👈
😘7❤4👍3😍2🥰2
57 ·
​عــــــز الــــــديــــــن👳
በዚህ ቦት አማካኝኘት Gemini pro version በነፃ ማግኘት ትችላላችሁ 15 ሰው በመጋበዝ ወይም $1 በመግዛት https://t.me/hubxshop_bot?start=aekb6ra0
👍6🥰4😘3😍2❤2
36 ·
Photo
​🖤 «የጨለማ ብርሃን» ⚪️ (እውነተኛ ህይወትን መሰረት ያደረገ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ) ከቤተሰቦቼ ፍቅርና ሰላም ተከብቤ አድጌአለሁ...! ነገር ግን የካምፓስ ህይወት ደግሞ የራሱ የሆነ የጨለማ መንገድ አለው..." አንብበው የማይጨርሱት፣ በደስታና በሀዘን የተሞላ ውብ ታሪክ!
🥰6❤4😍4😘2👍1
29 ·
𝐄
. ከስር ያለውን ፅሁፍ Copy የሚለውን ተጭናችሁ ለ Chat Gpt ስጡት የሚላችሁን እዩ፤ ከፈለጋችሁ ያላችሁን Copy አድርጋችሁ በጥቂቱ በ Comment ፃፉልን 😂 ℹ️ Based on everything you know about me, roast me and do not hold back, use Amharic language.
😍5😘5❤3🥰2👍2
41 ·
​عــــــز الــــــديــــــن👳
Photo
Tesla የሚበር መኪና አስተዋወቀ። የኤለን መስክ ድርጅት የሆነው Tesla በሳይንቲፊክ ፊልሞች ላይ ያየነው ቴክኖሎጂ እውን አድርጎታል። Roadster የተሰኘ የኤሌክትሪክ Sport car ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም መኪና በሚያወጣው የአየር ግፊት ምክንያት መብረር ወይም አየር ላይ መንሳፈፍ ይችላል። ይህ መኪና በSpace X በተበለፀገ ቴክኖሎጂ አማካኝነት መኪኖችን መዝለል እና አየር ላይ ማንሳፈፍ እነደሚችል ተገልጿል። ይህም መኪና ከ0 እስከ 60 ማይል በሰዓት በአንድ ሴኮንድ መድረስ ይችላልም ተብሏል። Teslaም ይህንን መኪና በተለያዩ በራሱ የመኪና ሞዴሎች ላይ ሲዘል አሳይቷል። ይህንንም ለማድረግ ከፍተኛ አቅም ያላቸው Fans እና thrusters/ ግፊት ሰጪ መሳሪያዎችን እንደሚጠቀም ተመላክቷል። ምንጭ፡ TechCrunch
❤6🥰4😍3👍3😘3
37 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count