በፊትና (ፈተናና ግርግር) ጊዜ ሙስሊም ሊከተለው የሚገባ ጠቃሚ ሸሪዐዊ ምክር፦
1.አላህን መፍራትና በእርሱ መጠጋት
በፊትና ጊዜ የልብ መጠጊያ አላህ ነው። ሶላትን፣ ዱዓን፣ ዚክርንና ኢስቲግፋርን ማብዛት ይገባል።
2.ከማያረጋግጡ ወሬዎች መራቅ
አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا﴾
“የሆነ ፋሲቅ ወሬ ቢያመጣላችሁ አረጋግጡ።” — ሱረቱል ሁጁራት 49፥6
3.አንደበትን መጠበቅ
ያልተረጋገጠ ነገር አለማስተላለፍ፣ ሰዎችን አለመሳደብና ክብራቸውን አለመንካት። ፊትና ብዙ ጊዜ በአንደበት ይባባሳል።
4.ከጥርጣሬና ከግል ፍርድ መጠንቀቅ
ማንንም በቀላሉ ካፊር፣ ፋሲቅ ወይም የተሳሳተ ብሎ መፍረድ አይገባም። የዑለማዎችን መመሪያ መከተል ይገባል።
5.ለትዕግሥት መጣር
አላህ ይላል፦
﴿وَاصْبِرُوا إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ﴾
“ታገሱ፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው።” — ሱረቱል አንፋል 8፥46
6.ከግርግር መራቅ
ራስን በግጭትና በጠብ ውስጥ መጣል አይገባም። ሰላምን ማስቀደምና ጉዳዩን ወደ እውቀት ባላቸው ዑለማዎች መመለስ ይገባል።
7.ዱዓ ማብዛት
ከሚመከሩት ዱዓዎች አንዱ፦
اللهم إني أعوذ بك من الفتن ما ظهر منها وما بطن
“አላህ ሆይ! ከታዩትም ከተደበቁትም ፊትናዎች በአንተ እጠበቃለሁ።”
አጭር ምክር: በፊትና ጊዜ የሚያድነን ብዙ መናገር ሳይሆን እውነትን ማረጋገጥ፣ አንደበትን መጠበቅ፣ ወደ አሏህ መጠጋት እና ከግርግር መራቅ ነው።
2 · 273 · በፊትና ጊዜ የሚጠቅሙ ተጨማሪ ሸሪዐዊ ምክሮች፦
8. በቁርኣንና በሱና መጣበቅ
አላህ ይላል፦
﴿وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا﴾
“ሁላችሁም በአላህ ገመድ በጥብቅ ያዙ፤ አትለያዩም።”
[አሊ ዒምራን 3፥103]
9. ስሜትን ከእውነት በላይ አለማስቀደም
በፊትና ጊዜ ቁጣና ስሜት የሰውን ፍርድ ሊያዛባ ይችላል። ስለዚህ ከመናገር ወይም ከመወሰን በፊት ማሰብ ይገባል።
10. የሰዎችን ስህተት ሁሉ አለመከተል
አንድ ሰው ስህተት ሠራ ማለት ሁሉንም ንግግሩን መቀበል ወይም ሁሉንም መካድ አይደለም። እውነትን በማስረጃ መመዘን ይገባል።
11. የማይመለከተንን ነገር መተው
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«مِنْ حُسْنِ إِسْلَامِ الْمَرْءِ تَرْكُهُ مَا لَا يَعْنِيهِ»
“የሰው እስልምና ጥሩነት ከማይመለከተው ነገር መራቁ ነው።”
12. የወሬ ማሰራጨትን መቆም
በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚመጡ ወሬዎችን ሳናረጋግጥ ማስተላለፍ አይገባም። አንድ የተሳሳተ መልእክት ትልቅ ፊትናን ሊያባብስ ይችላል።
13. ከጥላቻና ከበቀል መጠንቀቅ
አላህ ይላል፦
﴿وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ﴾
“የሕዝብ ጥላቻ ፍትሕን እንዳትተዉ አያድርጋችሁ፤ ፍትሕን አድርጉ፤ ይህ ለተቅዋ ይበልጥ ቅርብ ነው።”
[አል-ማኢዳህ 5፥8]
14. ወደ ዑለማዎች መመለስ
የሚያስቸግር የዲን ጉዳይ ሲከሰት በራስ ግምት ፍርድ ከመስጠት ይልቅ በዕውቀት ወደ ታወቁ የዲን ሊቃውንት መመለስ ይገባል።
15. አላህን ብዙ ማስታወስ
﴿أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ﴾
“ንቁ! ልቦች የሚረጋጉት በአላህ ዝክር ነው።”
[አር-ረዕድ 13፥28]
በአጭሩ፦ ፊትና ሲመጣ አረጋግጥ፣ ተረጋጋ፣ አትቸኩል፣ አትከራከር፣ አትስደብ፣ አትበቀል፣ ወደ ቁርኣንና ሱና ተመለስ፣ አላህን ጠይቅ።
2 · 307 · Audio
በእድር_ያለውን_ሸር፣ብልሽትና_ቢድዐህ_ከ30_.MP3 · 76.3 MB · click to show
በእድር_ያለውን_ሸር፣ብልሽትና_ቢድዐህ_ከ30_.MP3 · 76.3 MB · click to show
Photo
click to show
click to show
🔶#በእድር ያለውን ሸር፣ብልሽትና ቢድዐህ ከ30 በላይ በሆነ አቅጣጫ ግልፅ ማድረግና "ባህል ነው እንጂ ቢድዐህ አይደለም" ብሎ በሞገተ ሰው ላይም ምላሽ ተሰጥቷል
🔶 በአዲስ አበባ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተደረገ ሙሐደራ።
🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)
📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan
302 · 8.8K · Photo
click to show
click to show
📌 "ልጆቼን አደራ." ዛሬ የተቀበረው የወንድማችን አብዱልጀዋድ የመጨረሻ ቃል እና የተጣለብን ትልቅ አደራ!
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ዛሬ በካቲማው አምረን፣ በዱዓ አጅበን ሽኝት ያደረግንለት ውዱ ወንድማችን (አብዱልጀዋድ) ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየቱ በፊት የተናገረውና የተወልን ትልቅ የአደራ ቃል ነበረው፡ "ልጆቼን አደራ! ልጆቼን አደራ!"
ወንድማችን አብዱልጀዋድ 5 ታናናሽ የሆኑ የሌሎችን እጅ የሚጠብቁ ህፃናት ልጆቹን ነው ጥሎ ያለፈው። እነዚህን ጨቅላ ህፃናት የቀን ስራ እየሰራ በላቡ (በሙያው) በጉልበት ሰርቶ የሚያስተዳድር ታታሪ አባት ነበር። ዛሬ ግን ሞት ቀደመው፤ ልጆቹንም ለሙሉው ሰለፊያ ጀማዓ እና ለሁላችንም አደራ ብሎ ጥሎብን አልፏል።
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዳሉት፡ "እኔና የየቲም ተንከባካቢ በጀነት ውስጥ እንደዚህ አብረን ነን" ብለው ጠቋሚና መካከለኛ ጣታቸውን አያይዘው አሳይተዋል።
ዛሬ የእኛ ተራ ነው! የዛሬው የእሱ ልጆች ተራ፤ ነገ ደግሞ የእኛ ወይም የልጆቻችን ተራ ሊሆን ይችላል። አደራውን ለመወጣት፣ ህፃናቱን ከጎናቸው ለመቆም እና ከጎናቸው አንለይም ለማለት ሁላችንም አቅማችን የፈቀደውን እናድርግ።
👉የአካውንት ቁጥር፡
1000716206533
👉 የአካውንቱ ስም፡
አብዱል ጀሊል ኡስማን፣
ኸይሩ ሙሐመድ እና
አብዲ ጀማል
🤲 ዱዓ አንርሳ!
ወንድማችንን በዱዓችን አንርሳው፤ አላህ ቀብሩን ሰፊና ብሩህ ያድርግለት፣ ጀነተል ፊርደውስንም ይወፍቀው። ለቤተሰቦቹ እና ለልጆቹም መፅናናትን ይስጥልን።
🔄 አደራ ሼር ሼር በማድረግ ለሌሎችም አድርሱ!
የአንዱ መልካም ስራ የሌላውን ህይወት ይለውጣል!
📢 ተጨማሪ መረጃዎችን እና የልጆቹን ሁኔታ ለመከታተል ይህንን ግሩፕ ይቀላቀሉ፡
👉 https://t.me/abduljewadlijoch
27 · 1.4K · Link
click to show
click to show
ድንገተኛ ሙሃዶራ አሁን
በዳር አስ-ሱንና
🎙በአንጋፋው ሸይኽ ሐሰን ገላው (ሀፊዘሁላህ)
ስለ መውሊድ ቢድዓነት
ይሳተፉ ↘️↘️↘️
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=
19 · 1.7K · Audio
በመውሊድ_ቀን_ከሚጠቀሱ_ሺርክን_ቢድዐህ_.mp3 · 5.0 MB · click to show
በመውሊድ_ቀን_ከሚጠቀሱ_ሺርክን_ቢድዐህ_.mp3 · 5.0 MB · click to show
አዲስ ሙሃዶራ
ርእስ:- በመውሊድ ቀን ከሚጠቀሱ ሺርክን ቢድዐህ!!
🎙በሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)
👉 ይደመጥ!!
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
ነሓሴ 8/2018 ከጁምዐህ ሶላት በኋላ የተሰጠ ሙሃዶራ
የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
71 · 2.9K · Photo
click to show
click to show
🔊ተጀምሯል
🎙በኡስታዝ አቡ መርዋን (ሀፊዘሁሏህ)
🎀ርዕስ ፦የጎረቤት ሀቅን መጠበቅ
"🔊ገባ ገባ በሉ
. 🥀ገባ ገባ በሉ 🔊
🔊ሊንኩን ሼር ሼር አድርጉት ባረከሏሁ ፊኩም
•━════✿🍃🌺🍃✿════━•
👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuMerwanAselefy
32 · 1.7K · ❌️❌️ ‘ደዩስ’ እንዳታስብ ❌️❌️
ሻንጣዋን በመኪና ጭነህ
እስከ ኤርፖርት ሄደህ
ስመህ የሸኘሀት - ከስብሰባ እንዳትቀር
ሚስትህ ደህና ናት - እንዳይልህ ቅር ቅር፡፡
በሰው አገር - ብቸኝነት - ሰርቶባት ድንኳኑን
ያንተ፣ የልጆቿ - ድርቡ ናፍቆት - ዘርግቶ መረቡን
“ይፈጫታል” ብለህ - በሀሳቡ መጅ
“ይደቁሳታል” ብለህ - በትካዜው እጅ፣
‘ደዩስ’ እንዳታስብ - ሚስትህ ደህና ናት
“ደህና ሰንብች” ብለህ - ስብሰባ የላካት፡፡
ሞልተዋል - የ’ሷ ቢጤ ሴቶች - “አይዞሽ! አይዞሽ!” የሚሏት
ሞልተዋል - ያንተ ቢጤ ወንዶች - እያሳሳቁ የሚያጫውቷት
የበቁ-የነቁ - ናፍቆት ለማስረሳት፡፡
ከሴቶችም-ከወንዶችም
ከትልቆችም-ከትንሾችም
ከጎረምሳም-ከጎልማሳም
ሞልተዋል፡-
እንደ እናት - እቅፍ አድርገው - በደስታ የሚዘይሩ
“እንዴት ነው? - ተመቸሽ?” - እያሉ እሚያዋሩ
እሚያጨዋውቱ - ስቀው የሚያስቁ
የተጫጫናትን - ድብርት የሚያርቁ፡፡
እናም፡-
ሀሳብ እንዳይገባህ
ጭንቀት እንዳይነካህ፤
‘ደዩስ’ እንዳታስብ - ሚስትህ ደህና ናት
“ደህና ሰንብች” ብለህ - ስብሰባ የላካት፡፡
በመሆኗ - ላገሩ እንግዳ
- ለሰውም ባዳ
ወርዶባት - የብቸኝነት ናዳ
ሰፍሮባት - የእንግድነት እዳ
እንዳይመስልህ - የምትናጥ በጭንቀት
- ባንተ-በልጆቿ ናፍቆት፡፡
አደራ! ሀሳብ እንዳይገባህ
አደራ! ጭንቀት እንዳይነካህ፡፡
‘ደዩስ’ እንዳታስብ - ሚስትህ ደህና ናት
“ደህና ሰንብች” ብለህ - ስብሰባ የላካት፡፡
ከስብሰባው ቦታ - ከጎኗ ተቆልሎ
ከሻይ-ቡናው ቦታ - ከፊቷ ቁጭ ብሎ
ውበቷን እያደነቀ
ፈግገታዋን እየሞቀ
“እንዴት ነው ቆይታሽ?”
“አይዞሽ አይደብርሽ?”
“እኛ አለን ከጎንሽ”
እያለ እሚያጫውታት
እያመጣ ምሳሌና ተረት
ጥርስ እማያስገጥም
የወሬ ግጥምጥም
ሁሉን አስረስቶ - ባሳብ የሚያዝናናት
- ሞልቷል የወንድ አይነት፡፡
እና - “እንዴት ትሆን?” ብለህ
- ጭንቀት እንዳይነካህ
‘ደዩስ’ እንዳታስብ - ሚስትህ ደህና ናት
“ደህና ሰንብች” ብለህ - ስብሰባ የላካት፡፡
ዝግጅት/በዶክተር ጀማል ሙሐመድ
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
21 · 1.8K · Video
5.8 MB · click to show
5.8 MB · click to show
متى نسينا النبي ﷺ حتى نحتفل بمولده !!
الشيخ د. محمد أمان الجامي رحمه الله تعالى
8 · 320 ·