ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app

የኢስላሚክ ጥያቄዎች እና ሐዲሶች የዉይይት መድረክ™

6 577 members
11 August 2026
I
መመካከረ!🖋 አላህ በሱረቱ አሊ ዒምራን እንዲህ ይላል፦ ﴿فَاعْفُ عَنْهُمْ وَاسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِي الْأَمْرِ ۖ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ﴾ “እነሱን ይቅር በላቸው፣ ለእነሱም ምሕረትን ለምንላቸው፣ በጉዳዮችም አማክራቸው። ከወሰንክ በኋላ በአላህ ላይ ተመካ።” (3:159)📖 ቀታዳ (ረሒመሁላህ) ይህን አንቀጽ ሲያብራራ እንዲህ አለ፦ 🔁“አላህ ለነቢዩ (🩷) ከሰሓቦቹ ጋር በጉዳዮች እንዲመካከሩ አዘዛቸው። ምንም እንኳን ለነብዩ(🤎) ከአላህ ዘንድ ወሕይ የሚወርድላቸዉ ቢሆንም።” 🔁“ሰዎች አላህን ብቻ ለመፈለግ በመመካር ላይ ሲሰበሰቡ አላህ ወደ ትክክለኛውና ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸዋል። Share ➕ 💻@islamic_picture_wallpaper🤩
982 ·
M
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
Фотография
click to show
🔖የዛሬው የመፀሀፍ ግብዣችን ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🎙በሙሀመድ ሰዒድ(ማሒ) የተዘጋጀውን 📌 ያስተነትኑምዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው የተሰኘውን መፅሀፍ ነው። ➖➖➖➖➖🤍➖➖➖➖➖ አንድ ባልንጀራዬ “የወለሉን ሥር መፈተሽ እንዳለብኝ ይሰማኛል አንዳች ምስጢር እንዳለበት  ደመነፍሴ ነግሮኛል” በማለት ፈቃድ ጠየቀኝ።ካህናቱ ይህን ሲሰሙ የመደናገጥ የመረበሽ ስሜት ዓይኖቻቸው ላይ አነበብኩ። ፍተሻው እንዲቀጥል  አዘዝኩ። የገዳሙ እጅግ የተዋበ ምንጣፍ ከነወለሉ ተነሳ። በየክፍሎቹ ወለል ላይ ውሃ በብዛት እንዲያፈሱ አዘዝኳቸው።ከአንደኛው ክፍል የፈሰሰው ውሃ ወደ ውስጥ ሰረገ። ወደታች የሚወስድ በር ነበረው። በስልት  ተዘግቷል። የወለሉ አካል ይመስላል። ከገዳሙ አለቃ ቢሮ አጠገብ በተቀመጠ ቀጭን ሠንሰለት አማካኝነት በስልት ይከፈታል። ወታደሮቹ በሩን መስበር ጀመሩ። ካህናቱ በድንጋጤ ገፅታቸው ገረጣ።  በሩ ተከፍቶ የሚወስደውን መሰላል እየረገጥን ወደታች ዘለቅን። አንድ ጧፍ አገኘሁ።...... ➖➖➖➖➖🤍➖➖➖➖➖ 📖ከመፅሃፉ የተወሰደ ❤ኢስላሚክ ጥያቄዎች እና ሐዲሶች
1K ·
I
Файл
ታሪኮችን ተርክላቸው.pdf · 23.9 MB · click to show
📱ቻናላችን፦  ኢስላሚክ ጥያቄዎች እና ሐዲሶች 📱ግሩፓችን፦ @Islamic_picture_wallpaper_Gp
1K ·
12 August 2026
Видео
1.7 MB · click to show
E
የቀኑ መልእክት 💬 قال ابن تيمية رحمه الله : وَكَمَائِنُ الْقُلُوبِ تَظْهَرُ عِنْدَ الْمِحَنِ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ ፦​"የልብ ውስጥ የተሸሸጉ ነገሮች (ምስጢሮችና እውነተኛ ባህሪያት) የሚገለጡት በፈተናና በመከራ ጊዜ ነው።"
.
🍃 ነገሮችን ባላየ ማለፍን ልመጂ...... የማይጠቅሙሽን ነገሮች ህይወትሽ ላይ ምንም የማይጨምርና ...የማይቀንሱን ነገሮች በመዝለል ላይ በርቺ .....ትተሽ ያለፍሻቸውን ነገሮች ዞረሽ ባለማየት ላይ ጀግኚ ......ላልሆንሻቸው ስያሜዎችሽ መልስ በመስጠት ላይ አትገኚ .......በቀኖችሽ ውስጥ የሚጠቅምሽን ብቻ ዝገኚ!!!!! #እህቴ ትኩረት አልባ ሁኚ ማለቴ አይደለም ነገር ግን መርጠሽ ትኩረት ስጪ የማይጠቅምሽን እያሰብሽ እንቅልፍ አተሽ አትደሪ ነቃ በይ።
H
ሴት ልጅ ፊቷን ገልጣ የምትወጣ ቢሆን ኖሮ ሊያጫት ለሚፈልግ ሰው ሂድና ተመልከታት የሚል ፍቃድ ባላስፈለገ ነበር። ሸይኸ ሷሊህ አልፈውዛን 📓اتحاف الطلاب | ٣٨٥
И
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ለሁለት ለሚዎደዱ" ጥንዶች (ትዳርን) የመሰለ (መልካም ነገርን) አልታየላቸውም።🌹           📜ሲልሲለቱ ሶሂሀህ (624)
.
🍃 ምንም አልረባም ብለህ በተደጋጋሚ በራስህ ተስፋ የቆረጥክበት ጊዜ አለ፡፡ አላስፈልግም ከንቱ ነኝ ብለህ ራስህን የረገምክበት ጊዜም ብዙ ነው፡፡ ከባድ ችግር አግኝቶህ ሞትን በራስህ ላይ የጠራህበት ጊዜም አንድ ሁለት አይባልም፡፡ እናታችን መርየም፣ ያች ቅድስቲቷ እመቤት ... ምጥ ላይ በሆነች ጊዜ ጭንቅ ተደራረበባትና “ ዋ ምነዋ ከዚህ ፊት ሞቼ ተረስቼ በሆነ ኖሮ!” አለች፡፡ በሆዷ ምን እንደያዘች ሳትገነዘብ። ከባዱ ምጥ የያዘው ከባዱን ሰው ነበር፡፡ ነብዩ ዒሳን (ዐለይሂ ሰላም)፡፡ ዱንያ መላ አካለዋ ምጥ ነው ወዳጆቼ፡፡ ከተፈጠርንበት ጊዜ ጀምሮ ምጧ አልተፋታንም ይሆናል፡፡ ግና ቀናት ምን እንዳረገዙም አናውቅም። ፈተናና ችግሮቻችን ነገ መልካም ነገር ይወልዱ ይሆናል ማን ያውቃል። አብሽሩልኝ ውዶችየ ✋
🥰
እንዴት ናችሁ እስኪ ቁርአን ወይም ፅሁፍ ጋብዙን
.
ቢያውቁ ኖሮ ይህች የዱኒያ ህይወት በውስጧ ከያዘቻቸው ሃብትና አጓጊ ጌጣ-ጌጦች ጋር በሙሉ መታለያና ከጊዜ በኋላ የሚያበቃ ጨዋታ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አይደለችም። እውነተኛ እና የዘላለም ህይወት ማለት የኣኺራህ ሃገር ህይወት ነው። ሰዎች ይህን ቢያውቁ ኖሮ የዚችህን ጠፊና አላቂ ዓለም ህይወት ከኣኺራህ ባላስበለጡ፤ በርሷም ተታለው ኣኺራቸውን የሚያበላሽ ስራ ባልሰሩ ነበር።
I
اصبر يا عبدَ اللَّه، المنازل العالِية لا تُنال إلا بالبلاء. ابـن تيمية ኢስላሚክ ጥያቄዎች እና ሐዲሶች
169 ·
Архив по месяцам
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog