Web appOpen in Telegram
NNessim Mahaba 📚 نسيم المحبة 🛖

Nessim Mahaba 📚 نسيم المحبة 🛖

@MuhammedNessim · channel · Education · indexed since 2026-07-14
5 211subscribers+1 in a week
1 215average post reach
23.3%ER — reach to subscribers
39posts in 30 days
N
«የአላህ መልእክተኛ [ﷺ] ሶሓባው ሳኢብ ኢብኑ የዚድን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከህጻናት ጋር ሲጫወት አግኝተውት ስሙን ጠየቁት። ከዚያም ጭንቅላቱን አብሰውት 'ባረከላሁ ፊክ (አላህ በረካ ያድርህ)' አሉት። ከዚያም በመላ ጠጉሩም ሆነ ጺሙ ላይ ሽበት ሲታይበት እርሳቸው የዳበሷት ቦታ ግን ጥቁር ሆና ቀረች።» 📚 በይሀቂይ ዘግበውታል : ሰይዲ አለምላሚ ናቸው። የደረቀን የሚያረጥቡ፣ ያረጀን የሚያድሱ፣ የታመመን የሚያሽሩ፣ የበረካ ከዝና!… #ፊዳሁ #አቢ #ወኡሚ
1.5K ·
N
«ሰጪ አንበሳ እንጂ፣ ተቀባይ ተኩላ አትሁን!» : አንድ ባለጸጋ አባት ነበር። ልጁን ከልክ በላይ በቅንጦት አሳድጎት ነበር። ምንም እንዳይጎድለው ሁሉንም ያሟላለት ነበር። ያልደከመበትን ሀብት በጭካኔ እንዲያወድም ሰልጦት፣ ነዋይ ይበትን ነበር።… ወደ ኋላ ይህ ነገር ያሳስበው ጀመር።… እኔ ከሞትኩ ይህ ልጄ ሀብቴን ማስተዳደር ስለማይችል የተውኩለትን ንብረት ያጠፋዋል የሚል ስጋት ገባው። ስለዚህ ልጁ ራሱን እንዲችል፣ ሥራን እንዲያውቅና የአባቱን ሀብት በትክክል እንዲጠብቅ ንግድ እንዲሞክር ወደ ሩቅ አገር ከሚሄድ ቅፍለት ጋር ላከው። ወጣቱም ሊሸጥ፣ ሊገዛ፣ ሊገበያይ ጉዞውን ጀመረ። ነገርግን በመንገድ ላይ ግን አንድ አስገራሚ ክስተት ተመለከተ። አንድ አንበሳ ጥንቸል አደነ፤ ከዚያም ምግብ ለማግኘት መንቀሳቀስ የማይችል ዕውር ተኩላ የሚገኝበት ዋሻ አጠገብ ወስዶ ጣለውና ሄደ። ወዲያው ዕውሩ ተኩላ እያነፈነፈ መጣና የተጣለለትን ትኩስ አደን ተመገበ።… ወጣቱም ይህን ትእይንት ሲመለከት እንዲህ አለ፦ «አላህ በጉድጓዱ ውስጥ የተሸሸገ ይህን ዕውር ተኩላ እንኳን አልረሳውም፤ ሲሳዩን ደጃፉ ላይ ጣለለት። ለተራው አውሬ ይህንን ያደረገ ጌታ እኔንማ አይተወኝም።» ከዚያም ንግዱን ትቶ ወደ አባቱ ተመለሰ። አባቱም፦ «ለምን ተመለስክ?» ብሎ ጠየቀው። ወጣቱም ያየውን ነገረውና፦ «አላህ ለዚህ ዕውር ተኩላ ሲሳይ ከላከለት፣ እኔን እንዴት ይተወኛል!?… ስለዚህ ሥራ መሥራት አያስፈልገኝም።» አለው። አባቱ ግን ፈገግ ብሎ እየተመለከተው፣ እድሜ ልኩን ሰምቶት የማያውቀውን ነገር ነገረው፦ «ልክ ነህ፣ ልጄ! አላህ ሪዝቅን ከፍጥረቱ አይነፍግም። ነገር ግን እኔ የምፈልገው ሰጪው አንበሳ እንድትሆን እንጂ፣ ተቀባዩን ተኩላ እንድትሆን አይደለም!» ወዳጄ ሆይ! እውነት ነው! ሲሳይህ ከአላህ ነው። ነገር ግን በሲሳይ መተማመን ሥራን መተው ማለት አይደለም። በአላህ ተመካ፤ ነገር ግን ጥረትህን አትተው። 📚 ተማር። 💪 ራስህን ገንባ። 🔨 ሥራ ጀምር። 🚀 ደፍረህ ሞክር። 🌱 ከወደቅክበት ተነሳ። 🤲 ካገኘህ ለሌሎችም አካፍል። ዛሬ «ማን ይረዳኛል?» ብለህ አትጠይቅ። «ነገ ማንን ልረዳ እችላለሁ?» ብለህ አስብ። ሥራ ፈላጊ አትሁን፤ ሥራህን ራስህ ፍጠር። እገዛ የሚጠብቅ ደካማ አትሁን፤ ይልቁንስ ለሌሎች ድጋፍ ሁን። ሀብት የሚፈልግ ስግብግብ አትሁን፤ ሀብት ፍጠርና ለሌሎች አጋራ። አላህ ሲሳይህን ይሰጥሃል፤ አንተ ግን ለሌሎች ሲሳይ አከፋፋይ ለመሆን ጥረት አድርግ። ሰጪ አንበሳ ሁን፤ ተቀባይ ተኩላ አትሁን! የወጣትነት ክብር የሚቀለሰው በምትቀበለው ሳይሆን፣ በቸርነት በምትለግሰው አበርክቶህ ነው። 💚 መልካም ጁሙዐ ይሁንልን!
2 · 1K ·
Photo
click to show
ታማኝ የእማኝነት የታሪክ ሰነድ! ሸህ ሐቢብ ሐሰን በደቡብ ኢትዮጵያ የገደባኖ ዓሊም ናቸው። የቀዳማዊ ሸህ ዒሣ ቃጥባሬ ተማሪ፣ በቅርበት ለሦስት ዐስርት ዓመታት አብሮ ኗሪ ነበሩ። ለመምሕራቸው ጥልቅ ፍቅር እና ዕምቅ ክትትል ነበራቸው። የመምሕራቸውን መዋዕለ ታሪክ በመሰነድ እረገድም ቀዳሚ ናቸው። የታሪክ ድርሳን ለማዘጋጀት የተነሳሱት ግን ከመምሕራቸው ኅልፈት በኋላ ነበር። ይኽም ኾኖ በቀጥታ የድርሳን ዝግጅቱን አልጀመሩም። ለዝግጅቱ “ማለፊያ ፈቃድ” ለማግኘት ለአንድ ዓመት ሙሉ ተከታታይ እስቲጝፋር(ስባሔ) እና ዱዓ(ጸሎት) አከናውነዋል። በመጨረሻም ተሳካላቸው። “ነፍሐቱል ዓንበሪያ ፊ ዚክሪ መናቂቢ ሸይኹና አል-ቀጥበሪያ” የተሰኘውን አስተማማኝ የታሪክ መዝገብ አዘጋጁ። የታሪክ ስነዳው የተጀመረበትን ኹነኛ ጊዜ ባይገልጹም (መምሕራቸው በ1366 ዓመተ-ሒጅራ ከአለፉ በኋላ) በ1371 ዓ.ሒ. ነበር ያጠናቀቁት።(ከዛሬ 77 ዓመታት በፊት።) ድርሳኑ ስድስት ምዕራፎች፣ ከሓያ በላይ ንዑስ ክፍሎች፣ አንድ መቶ ሓምሳ-ስድስት ገጾች የተዋቀሩበት ሲኾን ከሦስት ዓመታት በላይ የዝግጅት ጊዜ ወስዶባቸዋል። በተሟላ የዓረብኛ ቋንቋ አቅም፣ በአስተማማኝ የታሪክ ስነዳ እና ገለጻ ችሎታ፣ ጥንቃቄ በበዛበት አተራረክ፣ በጥዑም አቀራረብ - ርቱዕ የታሪክ መረጃ አበርክተዋል። እንዲህ ዓይነት አስተማማኝ የታሪክ ጽሕፈት ሥነ ዘዴ፣ ታማኝ የእማኝነት የታሪክ ሰነድ ብርካቴ እምብዛም በቀላሉ አይገኝም። በብሔራዊው የታሪክ ክምችታችንም በቀላሉ ታዝበን የምናገኘው አይመስልም። ክብር ኹሉ ለአበው ይኹንና!!! (ማበሪያ ምስል፦ የሸህ ሐቢብ የታሪክ ድግ የፊት ገጽ፣ ከግል ማኅደር) ከድር ታጁ
2 · 976 ·
Nessim Mahaba#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ሰይዱና ጫሌ ለዘምዘሙ ደግስ ተጠሩና መዲና ሐረም ተጥደው ተጋቱት። ጣም ጣም ቢላቸው ሐውዱን ከጀሉ። ዳሩ የእርሳቸው ዕጣ በመውጁ መስከር ሆነና በሐያት ወደ ሐገራቸው መለሳቸው። እነ አሕመደል ሐዲ ግን ፉት ያሉት የሸውቁን መርዝ ኖሮ ሩኃቸውን ነጥቆ ወደዚያኛው ሐገር ደበለቃቸው። እነ ሸህ ዳንግላ ዘምዘሙን ለጥም መቁረጫ ነይተው ቢጎነጩትም ዕድያቸው ለሐውዱ ድግስ ነውና እስትንፋሳቸውን ቆርጦ እዛው አጋደማቸው። ሰይድ ጫሌ "የኛማ ሙሐባ ምንድን አለው ለዛ እንደ አሕመደል ሐዲ ፍግም ታንል እዛ!" ብለው በትካዜ ያንጎራጎሩት ለዚሁ ነው። የካውካሶች ኸሊፋ፣ የነቅሸበንዲዮች ጌጥ ኢማም ሻሚል መዲና ሲገቡ ሰብሰብ ያሉ ሰዎች አግኝተው ተቀላቀሉ። ይህን ያዬ አንድ የአካባቢው ታላቅ ሰው ተጠጋቸውና ብስራት ሹክ አላቸው። ረሱሉሏህን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በዒሻራ አይቶ ነው። ሰይዳችን በመናሙ እንዲህ ነበር ያሉት። "ሻሚል የክብር እንግዳችን ነው። ሽር ጉድ ሊባልለት፣ ታላቅ መስተንግዶ ሊደረግለት ይገባል!" ኢማሙ ይህን ቡሽራ በሰሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ እዛው መዲና ሞተው ጀነቱል በቂዕ ተቀበሩ። የሶሪያው ሸይኽ ዓብዱላህ ሲራጁዲን አል ሑሰይኒ በሰይዳችን ሙሐባ ክፉኛ የተነደፉ ነበሩ። ከኑራቸው ቀብቷቸዋል። በዚህም የተነሳ ሰዎች "ኑረል ሃላብ!" ይሏቸው ነበር። የአሌፖው ኑር። ስለ ነቢ ሲያወሩ ውለው ቢያድሩ አይጠገቡም። ስለ ትልቁ ሰው ሲፅፉ ልክ ሰይዳችን ከፊታቸው የተቀመጡ ይመስል ነበር። አንድ ጊዜ ሩቅ አገር የሚኖር ሰው ነቢን በህልም አይቶ ስለሳቸው እንዴት በደንብ ማወቅ እንደሚችል ሲጠይቃቸው "ሰይዱና ሙሐመድ ረሱሉሏህ የሚለውን የዓብደላህን መጽሐፍ አንብብ!" ብለው መልሰውለታል። ሸይኹን ነቢ ብዙ ጊዜ በመናም ዘይረዋቸዋል። በአንደኛው መናምማ "አንተ የኛ የምር አሽከር ነህ!" ብለው መሰከሩላቸው። በኺታማቸው መቃረቢያ ስለ ሶለዋት ፈዋኢዶች የሚያትት መጽሐፍ እያዘጋጁ ነበር። ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ እንደደረሱ ነቢን አዩ። ክፍላቸውን የሚስክና አምበር መዓዛ አጠነው። የመጡት እንግዳ ኑር ናቸውና ሊገልፁት የሚቸግር ብርሃን የሸይኹን ማረፊያ ሞልቶ የጀነት ጨፌ አደረገው። ጎረቤቶቻቸው እነ ሸይኽ ኢማዱዲን ወደ ክፍላቸው ገብተው የሆነውን ሲጠይቋቸው የኑሩ መገኛ፣ የሚስኩ መፍለቂያ፣ ጀነቱል ዑልያው ሰይዳችን መሆናቸውን ነገሯቸው። መቸስ ሶሪያ የሙሐባ ምድር ነበር። ይሄው ቀዬ ያበቀላቸው ሌላው ሸይኽ ኢሳ አል በይኑኒ ወዳጆቻቸውን ሰብስበው መውሊድ ማውጣት ጀመሩ። ሰኞ ለይሉን በአንዱ ተረኛ ቤት ይሀድራሉ። ታድያ አንዴ በዚህ መውሊድ ላይ አልፎ አልፎ በእንግድነት ይሳተፍ የነበረ ሰው ነቢን በመናም አዬ። በሺሩ "ለመውሊዱ ሰዎች ጥላ ከለላ እሆናለሁ!" ብለው አበሰሩት። ሰውዬው ከእንቅልፉ እንደነቃ ወደ ሸይኽ ኢሳ ሄዶ የመውሊዱ ቋሚ አባል እንዲያደርጉት ጠየቀ። እስከ እለተ ሞቱም ሲታደም ኖረ። ይህን መውሊድ ካወጡት ሙሒቦች አብዛኞቹ ነቢን በመናም አይተዋል። የሰርጉ ደጋሽ ሸይኽ ኢሳም ሐጅ ሲያደርጉ ነቢ በመናማቸው "በመዲና ቦታ ተይዞልሃል!" ብለዋቸው ነበር። ጉድ አትልም!? ቀኑ ሲደርስ ሞታቸው መዲና፣ ማረፊያቸው ጀነቱል በቂዕ ሆነ! ነቢ ሹመቴ ክብረት ማ’ረጌ ለዚሁ ብዬ ነው ሰርክ ማደግደጌ! #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
8 · 1.3K ·
N
ሰብዓዊ ተልዕኮ የሚያስቀድም! ሡልጣን ሐሰን በወሎ የቦረና ገዥ ነበር። በዘመነ መሣፍንት። በቸርነት፣ በፍትሐዊነት፣ በዠግንነት ይታወቃል። “አሕያ ፈጅ” የተባለውን የሸዋ ጦር ምሽግ በመስበር ይዎሳል። ለሠይፈል-ሐቅ(ሸህ ጃዕፈር ሲዲቅ 1778-1848) ቅርብ ወዳጅ ነው። ለማኅበረሰብ በመኖር፣ ወረትና ጥሪታቸውን ለተቸገረ በመቸር የሚታወቁት ሠይፈል-ሐቅ - በቅርበት ይገስጹትና ያንጹት ነበር። በአንድ ወቅት ፈረስ፣ በቅሎ፣ ላምና ልብስ በስጦታ መልክ አበረከተላቸው። ሠይፈል-ሐቅ፦ ‹‹ከጫፍ እስከ ጫፍ ግዛ!›› በማለት መረቁት። ሡልጣን ሐሰን የአካባቢው ንጉሥና ሹም ነው። ፖለቲከኛ፣ ጦር አስከትሎ ዘማች ነው። ለዙፋኑ ተቀናቃኝ አለው። ወዲህም የሠይፈል-ሐቅ ዱዓ ምድር-ለምድር እንደማይንከራተት ያምናል። የለገሱት ዱዓ ብስራቱ ሊኾን ይገባ ነበር። ይኽን ተቃርኖ ‹‹አሚን›› ሳይል በዝምታ ቀረ። ለተለገሰው ዱዓ ቁብ እንደሌለው አሳበቀ። ሠይፈል-ሐቅ ወትሮም የሡልጣን ሐሰንን ልቡና አላጡትም፣ የዱዓቸውን ፈለግ ለወጡት። ‹‹ሶፍህ ከአሽረፈል-ኸልቅﷺ ጋር ይኹንልህ!›› አሉት። ‹በሰማይ ዓለም ሠልፍህ ከነቢ ሙሐመድﷺ ተርታ ይኹንልህ!› ብለው መረቁት። ሡልጣን ሐሰን በደስታ ፋመ። በአሚንታ ወድቆ የሠይፈል-ሐቅን ጉልበቶች ሳመ። ምድራዊ ሹመት ከመደራረብ ይልቅ፣ ምድራዊ ሃላፊነቱን በሥርዓት ተዎጥቶ በሰማይ ቤት የዓለማት ዕዝነትን መወዳጀትን አስበለጠ። የነገ ውጥኑ ይስመርለትና! ቀደምት ዓሊሞች(ሊቀ ሊቃውንት)፣ “ዓሊም” ብቻ አልነበረም የሚያፈሩት። አካባቢና ወገንን በፍትሕ የሚያገለግል፣ በሥጋዊ እሾት የማይደለል፣ ከሥጋው ይልቅ የመንፈሡን ሰብዓዊ ተልዕኮ የሚያስቀድም “የታነጸ ሹማምንት”ም ያመርቱ ነበር!!! ማበሪያ ምስል፦ የታሪኩም ምንጭ ድርሳነ "ሚስኩል አዝፈር"(በሸህ ሙሐመድ-ፈቂሕ እንደተጻፈ፡ 1876) ገጽ-102፣ ከግል ማኅደር። ከድር ታጁ
2 · 1.5K ·
N
Video
530 KB · click to show
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ዐላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ። ወዓላ ኧሊ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ
2 · 1.3K ·
N
​"አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ። እንዴት ናቹህ። ለስራዬ በጣም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ የእርዳታህ ፍላጎት ነበረኝ። 'DE RECUPERAÇÃO DE DISPLAY, COF ESQUEMAS E PROCEDIMENTOS' የተሰኘ በጣም የሚያስፈልገኝ PDF ፋይል አለ። የፋይሉ ዋጋ 5 ዶላር ብቻ ሲሆን በቪዛ ካርድ (Visa Card) ወይም በፔይፓል (PayPal) ክፍያ ይጠይቃል። እኔ ኢትዮጵያ ስላለሁ በኢንተርኔት ክፍያ ፈጽሜ ለማውረድ ተቸግሬአለሁ። ይህንን pdf ፋይል 5 💵 💲 ገዝቶ ካወረደልኝ በኋላ በዚህ Telegram username @Nessim_muhaba ልትልኩልኝ ትችላላቹ? የሚከፈለውን 5 ዶላሩን ክፍያ በኢትዬጲያ ብር እከፍላለሁ። ለምታደርጉልኝ ትብብር በጣም አመሰግናለሁ። በዚህ ይላኩልኝ @Nessim_muhaba
3 · 1.5K ·
N
ሰይዲና አቡ ዘር [ረዲየላሁ ዐንሁ]፦ …«አንድም መልካም ሥራን ለመፈጸም አቅም ቢያንሰኝስ?» በማለት የአላህን ነቢይ [ﷺ] ጠየቁ። እርሳቸውም እንዲህ መለሱላቸው፦ «ክፋትህን ከሰዎች አርቅ፤ ይህ ከአንተ ለራስህ የምትሰጠው ሰደቃ ነው» ሙስሊም ዘግበውታል። : ከክፋቶች መካከል ደግሞ፦ መልካም ሥራ የሚሰሩትን ማስቆም፣ ተግተው የሚሰሩ ሰዎችን ማሳነስና ተስፋ ማስቆረጥ አንዱ ነው። እንግዲህ ክፉ ተግባርን መተው እንኳን ትልቅ ዋጋ ያስገኛል። ራስህ ከመልካም ሰሪዎች ስትሆን ወይም መልካም የሚሰሩትን ስትደግፍስ ምንኛ የላቀ ደረጃ ታገኝ ይሆን!?…
3 · 1.4K ·
N
የትዳር ነገር ትዳር አንዱ ብቻ ሐቅ የሚጠይቅበት ሳይሆን፣ ሁለቱም ኃላፊነታቸውን በፍቅርና በመከባበር የሚወጡበት ነው። ባልም ሆነ ሚስት፣ ከሌላው የሚፈልገውንና የሚጠብቀውን ክብር፣ ርህራሄና ታማኝነት ራሱም ለጥንዱ ይስጥ። የትዳር ሰላም የሚጀምረው «ሐቄ ምንድነው?» ከማለት ሳይሆን፣ «በእኔ ላይ የእርሱ/የእርሷ ሐቅ ምንድነው?» ብሎ ከመጠየቅ ነው።
8 · 683 ·
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል፦ «እያንዳንዱ የአደም ልጅ ኃላፊ ነው፤ ወንድ የቤተሰቡ ኃላፊ ነው፤ ሴትም የቤቷ ኃላፊ ናት!» 📚 ኢብኑ ሱንኒይ ዘግበውታል : በኢስላም የትዳር ጥንዶች መብትና ግዴታ በዝርዝር ተቀምጧል። በሦስት ነጥቦች ላይ ማሳረፍ እንችላለን: ‐ 🔹 የባል ኃላፊነት፦ ለቤተሰቡ መንፈሳዊና ቁሳዊ ፍላጎት (ቀለብ፣ ልብስ፣ መጠለያና ጥበቃ) የማሟላት ግዴታ ነው። 🔹 የሚስት ኃላፊነት፦ የቤቷንና የልጆቿን እንክብካቤ ማስተካከል፣ ለባሏ ታማኝ መሆንና የቤተሰቡን ክብር መጠበቅ። 🔹 ሚዛናዊነት፦ መብትና ግዴታቸው በተፈጥሯቸው ልክ በፍቅርና በመከባበር የተቃኘ ነው። ሁሉም ግዴታውን ከመወጣት ጋር ለትዳሩ እርጋታ ኃላፊነት ይወስዳል። የጾታዎች ግጭትና ፉክክር ቤትን አያፀናም! : አላህ ቤተሰቦቻችንን የፍቅርና የሰኪና መኖሪያ ያድርግልን!
❤9
3 · 799 ·
N
ለሚመለከተው… ============ የጁሙዐ ኹጥባ በዐረብኛ ስለመሆን የጁሙዐ ኹጥባ በዐረብኛ መሆኑ ግዴታ (ሸርጥ) መሆኑን የሚበይነው የፊቅህ አቋም በልሂቃን ዘንድ የታወቀና የተደገፈ ነው። በዚህ ጉዳይ ኺላፍ ቢኖርም፣ የአብዝሃኞቹ ዑለማዎች አቋም ኹጥባው በዐረብኛ መሆኑን ይጠይቃል። ደግሞም ደጋግ ከሆኑና በእውቀት የመጠቁ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያቶቻችን የወሰድነው መንገድም ይኸው ነው። ታላቁ፣ ሸይኹል ኢስላም፣ ሙሕዪዲን፣ ኢማም የሕያ ኢብኑ ሸረፍ አን‐ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] «አል‐መጅሙዕ» በተሰኘው ድንቅ መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፦ «هل يشترط كون الخطبة بالعربية؟ فيه طريقان، أصحهما وبه قطع الجمهور: يشترط؛ لأنه ذكر مفروض فشرط فيه العربية كالتشهد وتكبيرة الإحرام...» «ኹጥባው በዐረብኛ መሆኑ ግዴታ ነው ወይ? በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት አቋሞች አሉ። ትክክለኛውና አብዝሃኞቹ ዑለማዎች የወሰኑበት አቋም በዐረብኛ የግድ መሆኑን ነው። ምክንያቱም ግዴታ የሆነ ዚክር ስለሆነ ተሸሁድና የመጀመሪያው ተክቢራ (ተክቢረቱል ኢሕራም) ዐረብኛ መሆን እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ እዚህም ያስፈልጋል።» : ስለዚህ በልሂቃን መካከል ያለውን ኺላፍ ሳንክድ፣ የአብዝሃኞቹን እና ከድሮ ጀምሮ መዝሀብ ሳይለይ ይሰራበት በነበረበት አቋም መሠረት ኹጥባ ቢደረግ መልካም ነው። ለሕዝቡ የኹጥባው መልእክት እንዲገባ ከተፈለገ ግን ትርጉሙን ከኹጥባው በፊት ወይም በኋላ በአማርኛ ማብራራት ይቻላል። ስለዚህ ጁሙዐችንን እየተጠራጠርን ለምንሰግድ ወንድሞቻችሁ እዘኑልን! አላህ ህዝባችንን ከፍ ያድርግልን። ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን። ኡመቱንም ከክፋት ሁሉ ይጠብቅልን። መልካም ጁሙዐ!
❤14🥰1
2 · 845 ·
N
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد وعلى آل سيدنا ومولانا محمد አልላሁምመ ሶልሊ ወሰልሊም ወባሪክ ዐላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ዐላ ሰይዲና ወመላና ሙሐመዲን፡፡
❤11
665 ·
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد وعلى آل سيدنا ومولانا محمد አልላሁምመ ሶልሊ ወሰልሊም ወባሪክ ዐላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ዐላ ሰይዲና ወመላና ሙሐመዲን፡፡
❤9
539 ·
Photo
click to show
File
كِتَابُ رَوْضَةُ الْأَسْرَار -1.pdf · 240 KB · click to show
📚 የጀማሉዲን አኒይ "ረውዶቱል አስራር" pdf ኪታብ
❤6
8 · 534 ·
N
Photo
click to show
File
روضة_الأسرار_لشيخ_محمد_الأني_ረውዶቱል_አስራር_የጀማሉዲን_አንይ_ኪታብ_روضة_ · 50.6 MB · click to show
📚 የጀማሉዲን አኒይ "ረውዶቱል አስራር" pdf ኪታብ
❤6
12 · 600 ·
N
ኢላሂ! እስትንፋሴ ስትቋረጥ፤ ፊቴ ሲገረጣ፤ ሩሔ ስትወጣ፤ ከፊትህ ስደፋ እዘንልኝ። ኢላሂ! መንገዴን አብራልኝ፤ ነገሬን አግራልኝ፤ ማረፊያዬን ጀነት አድርግልኝ። አሚን!
❤15🙏1
2 · 325 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count