ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
R

Rhapsody of Realities Readers Hawassa🇪🇹

943 members
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Saturday 29th, August 2026 ቅዳሜ ፥ ነሀሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. አባታችን አስቀድሞ ያውቃል ▬▬▬▬▬▬▬ “እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ወይም ምን እንጠጣለን? ወይም ምን እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።” (ማቴዎስ 6፥31-32) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ጌታ ኢየሱስ እንዳንጨነቅ የነገረንበት አንዱ ምክንያት ሰማያዊው አባታችን ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅ ነው። በልባችሁ ውስጥ ያለውን ያውቃል። ፍላጎቶቻችሁንና ምኞቶቻችሁን ሁሉ ያውቃል፤ አስቀድሞም ሊሰጣችሁ ተዘጋጅቷል። እሱ ሙሉ በሙሉ ያውቃል፣ በነገሩ ሁሉ ላይ በቂ መረጃ አለው፣ እናም እናንተን ከሚያስጨንቋችሁ ሁኔታዎች ሁሉ ቀድሞ በዚያ ይገኛል። የሚያሳዝነው ግን፣ ብዙዎች አሁንም እግዚአብሔር ምንም እንደማያውቅ አድርገው ይኖራሉ፤ ይጨነቃሉ፣ በውጥረት ውስጥ ይውላሉ፣ እንዲሁም እርግጠኛ ሳይሆኑ ይመላለሳሉ። ምን እንደሚበሉ፣ ምን እንደሚለብሱ እና ነገሮች እንዴት እንደሚሆኑ ዘወትር ያስባሉ። ይህ እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች ሕይወት ነው። ኢየሱስ አሕዛብ እነዚህን ነገሮች እንደሚከተሉ ተናግሯል። የእነሱ ሩጫና ትኩረት እሱ ነው። እናንተ ግን የተለያችሁ ናችሁ። ዳዊት ይህንን ተረድቶ ነበር፤ በምስጋናም እንዲህ ሲል አወጀ፦ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።” (መዝሙር 23፥1)። ይህ በእናንተ መንፈስ ውስጥ ይብራ። በጭንቀት አትመላለሱ፤ በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ኑሩ። ለሕይወት ሁኔታዎች በእምነት ምላሽ ስጡ። ሁልጊዜም ረጋ ያላችሁ፣ በነገሩ እርግጠኞች የሆናችሁ እና የማትናወጡ ሁኑ። ይህ የሚሆነው ፈተናዎች ስለሌሉ ሳይሆን፣ ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ፣ እንዲሁም ያለ ረዳትና ያለ አቅራቢ እንዳልቀራችሁ ስለምታውቁ ነው።  (መዝሙር 68፥19) በእንግሊዝኛ መፅሐፍ ቅድስ እንዲህ ይላል "ሰማያዊው አባታችሁ በየዕለቱ በረከትን ያዘንብላችኋል"። ሊኖራችሁ የሚገባው  ንቃተ-ህሊና ይህ ነው። ፍላጎቶቻችሁ ሁሉ ከእግዚአብሔር የአቅርቦት ሥርዓት ጋር የተያያዙ ናቸው፤ ምንም የሚጎድላችሁ የለም፤ የአብርሃም ዘር ስለሆናችሁ ሁሉ ነገር አላችሁ። ስለዚህ፣ ሁኔታዎች ሲከሰቱ አትደናገጡ፤ “አባቴ ያውቃል!” ብላችሁ ራሳችሁን አስታውሱ። ያ ልባችሁን ያሳርፋል፣ እምነታችሁንም ያጠናክራል። በእሱ ታመኑ፣ በቃሉም ላይ ጸንታችሁ ቁሙ። እናንተ የእግዚአብሔርን ትኩረት ለመሳብ እየታገላችሁ አይደለም፤ አስቀድሞ ትኩረቱ በእናንተ ላይ ነው። እንዲያስብላችሁ ልታሳምኑት እየሞከራችሁ አይደለም፤ እሱ አስቀድሞ ያስብላችኋል። 1 ጴጥሮስ 5፥7 አምፕሊፋይድ ትርጉም ቃል በቃል እንዲህ ይላል፦ “…እሱ በፍቅር ያስብላችኋል፣ በንቃትም ይጠብቃችኋል።” ስለዚህ፣ ሰማያዊው አባታችሁ ስለእናንተ እንደሚያስብ፣ ቸርና ደግ እንደሆነላችሁ፣ መልካም ሊያደርግላችሁም ሁልጊዜ እንደሚጠብቃችሁ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ። ሃሌሉያ!    ጸሎት   ════════ ውድ አባት ሆይ፣ ስለ ፍቅርህና ስለ ፈሰሰው ጸጋህ አመሰግንሃለሁ። ስለ እኔ እንደምታስብ፣ ቸርና ደግ እንደሆንህልኝ፣ እናም መልካም ልታደርግልኝ ሁልጊዜ እንደምትጠብቀኝ ባለ ሙሉ እምነት ነኝ። ልቤ አርፏል፣ በእምነት፣ በእርግጠኝነትና በሰላም እመላለሳለሁ፤ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ማቴዎስ 6፥8 1 ጴጥሮስ 5፥7 (AMPC) ማቴዎስ 6፥31-34 (NIV) 📖 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14)
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Sunday 30th, August 2026 እሁድ ፥ ነሀሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አይዟችሁ — ድል በእርግጥ የእናንተ ነው ▬▬▬▬▬▬▬ "ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ።" (ሮሜ 4:18) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ የምታውቁትን ነገር ሁሉ አድርጋችሁ፣ ሁኔታው ግን አሁንም ምንም ያልተለወጠ የሚመስልበት ጊዜ አለ። ጸልያችኋል፣ በቃሉ ላይ ቆማችኋል፣ የተሰጣችሁንም ምክር ተግብራችኋል፣ ሆኖም ግን ምንም የተለየ ነገር አይታይም። ያ ጊዜ ብዙዎች ለተስፋ መቁረጥ እጃቸውን ለመስጠት የሚፈተኑበት ወቅት ነው። ነገር ግን የእናንተ ምላሽ መሆን ያለበት በፍጹም ይህ አይደለም፤ እምነት መቼም ቢሆን እጅ አይሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ አብርሃም፣ ተስፋ በሌለበት ጊዜ፣ ተስፋ በማድረግ እንዳመነ ይነግረናል። ለውጥን ለመጠበቅ ምንም ዓይነት ተፈጥሯዊ ምክንያት ባልነበረበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በተናገረው ቃል ላይ ጸንቶ ቆመ። የእምነት ሕይወት ማለት ይህ ነው። ሁኔታዎች እንዲያወዛውዟችሁ ወይም እንዲያናውጧችሁ አትፍቀዱ፤ መተማመኛችሁን በቃሉ ላይ እሰሩ። የምትፈልጉት ለውጥ በአንድ ጀምበር ያልሆነ ስለመሰለ ብቻ፣ ባለማመን በእግዚአብሔር ቃል ላይ በፍጹም አትጠራጠሩ። ይልቁኑ የእግዚአብሔር ቃል መቼም እንደማይወድቅ እያወቃችሁ፣ ለእግዚአብሔር ክብርን በመስጠት በእምነት በርቱ። የቆማችሁበትን ቦታ ጠብቁና አሸንፉ። መጽሐፍ ቅዱስ እኛ ወደ ኋላ ከሚያፈገፍጉት ወገን እንዳልሆንን ይነግረናል፤ እኛ እስከ መጨረሻው የምናምን ነን:-"ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።" (ዕብራውያን 10:38-39) እኛ እጅ አንሰጥም፣ አንንበረከክምም። የማይለወጡ ወይም እልኸኛ በሚመስሉ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ወይም እናንተን ለጉዳት አጋልጠው በሚሰጡ ተጽዕኖዎች ውስጥ ራሳችሁን ልታገኙት ትችላላችሁ፤ አትፍሩ። ፊታችሁን ወደ እነርሱ አዙሩና አሸንፉ። በቃሉ ላይ በመቆም የያዛችሁትን ይዛችሁ ጽኑ። እናንተ ለዚህ ዓለም ሁኔታዎችና አካላት የምትማርኩ አይደላችሁም፤ እናንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል ነሺዎች ናችሁ። እርሱ አስቀድሞ " በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።" ብሏል (ሮሜ 8:37)። ይህ የእርሱ ቃል ነው፣ የእርሱ ቃል ደግሞ የሚታመን ነው። ይሰራልም። ነገር ግን የእናንተን ጽናት ይጠይቃል። ስለዚህ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፣ ትከሻችሁንም አስፉ፤ ለተስፋ መቁረጥ እጃችሁን ለመስጠት እምቢ በሉ። አይዟችሁ፤ ድል በእርግጥ የእናንተ ነዉ" ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤" (2 ቆሮንቶስ 2:14)   ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ በሕይወቴ ውስጥ ስላለው ስለ ቃልህ ኃይልና የማይለወጥ ማንነት አመሰግንሃለው። ሁልጊዜም በድል ላይ እንዳለሁ እያወኩኝ፣ በሁኔታዎች ሳልናወጥና ቃልህን አጥብቄ በመያዝ በእምነት ጸንቼ እቆማለሁ። ቃልህ ዛሬ በእኔ ውስጥና በእኔ በኩል ያሸንፋል፣ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ዕብራውያን 10:23 ገላትያ 6:9 ያዕቆብ 1:12 📖 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ አካውንት ዝርዝሮችን
L
👉እምነት መቼም ቢሆን እጅ አይሰጥም 👉 እኔ እስከመጨረሻ የማምን ነኝ 👉 የእግዚአብሔርን ቃል መቼም አይወድቅም 👉 ጠብቃችሁ አሸንፉ 👉 እስከመጨረሻው እናምናለን 👉 ለተሰፋ መቁረጥ እጅ ለመስጠት እምቢ በሉ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Monday 31st, August 2026 ሰኞ ፥ ነሀሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. እናንተ ለሀሳቦቻችሁ ተገዢ አይደላችሁም ▬▬▬▬▬▬▬ "ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።"   (ፊልጵስዩስ 4:6) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ፣ ሀሳቦቻችሁን ማስተዳደር መማር አለባችሁ። በየቀኑ ወደ አእምሯችሁ ለሚመጡት ሀሳቦች ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ማወቅ ይኖርባችኋል። ድላችሁ ወይም ውድቀታችሁ ብዙ ጊዜ የሚጀምረው ለማሰላሰል ከምትመርጧቸው ሀሳቦች ነው። መንፈስ ቅዱስ «በአንዳች አትጨነቁ» የሚለውን መመሪያ የሰጠው ለዚህ ነው። መጨነቅ የሚለው ቃል የመጣው (ሜርማኖ) ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም ሀሳብን መውሰድ(ማስተናገድ) ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ 6:25 ላይ "...ስለ ነፍሳችሁ አትጨነቁ..." ሲል የተጠቀመበት ያንኑ ቃል ነው። ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ይነግራችኋል—ወደ እናንተ የሚመጣውን እያንዳንዱን ሀሳብ መቀበል የለባችሁም። ሀሳቦች ያለማቋረጥ ይመጣሉ። አሁንም እንኳ፣ አእምሯችሁ ንቁ ነው። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የሀሳቦች ጋጋታ አለ። ስለ ስራችሁ፣ ስለ ቤተሰባችሁ፣ ስለሰማችሁት ነገር፣ ስላያችሁት ነገር ወዘተ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነሱን "መውሰድ" (መቀበል) የለባችሁም። አንድን ሀሳብ "በወሰዳችሁበት" ቅጽበት፣ አእምሯችሁን በዚያ ላይ ታተኩራላችሁ። በእሱ ላይ ማሰላሰል ትጀምራላችሁ፣ እናም ይህን ስታደርጉ፣ ስሜታችሁን መቅረጽ እና ድርጊቶቻችሁን መለወጥ ይጀምራል። የተሳሳቱ ሀሳቦች ትኩረትን የሚከፋፍሉ ናቸው። የተነደፉት ትኩረታችሁን ለመስረቅ፣ ጭንቀትን፣ ስጋትን ወይም መረበሽን ለመፍጠር ነው። ለዚህ ነው ቃሉ ልትቀበሏቸው የሚገቡትን የሀሳብ አይነቶች የሚያሳያችሁ፦ " በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤" (ፊልጵስዩስ 4:8)። አስጨናቂ ሀሳቦችን አታስተናግዱ። በእነሱ ላይ አታውጠነጥኑ ወይም ወደ ጸሎት አርእስትነት አትቀይሯቸው። አስታውሱ፣ እናንተ ለሀሳቦቻችሁ ተገዢ አይደላችሁም፤ የትኞቹን ሀሳቦች መፍቀድ እንዳለባችሁ የምትወስኑት እራሳችሁ ናችሁ። አእምሮን ማደስ ያስፈለገበትም ምክንያት ለዚህ ነው፦ "የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።" (ሮሜ 12:2)። አእምሯችሁ በቃሉ ላይ ሲጸና እና፣ በቃሉ ሲታደስ፣ ትክክለኛ የሆኑትን ሀሳቦች ብቻ ለመለየትና ለማሰላሰል የተቀደሰ ይሆናል። ሀሳቦቻችሁ ትክክል ሲሆኑ ደግሞ፣ ቃላቶቻችሁ ትክክል ይሆናሉ፣ ሕይወታችሁም ትክክል፣ ምርጥና በክብር የተሞላ ይሆናል። ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ በእኔ ውስጥ ለሚሠራው የመንፈስ ቅዱስ ሥርዓት አመሰግንሃለሁ ። የተሳሳቱ ሀሳቦችን ማስተናገድ እምቢ እላለሁ፣ ይልቁንም አእምሮዬን ከቃልህ ጋር አሰልፋለሁ። ለእያንዳንዱ ሁኔታ በጸሎት፣ በምልጃና በምስጋና ምላሽ እሰጣለሁ፣ ሁልጊዜም በሰላምና በድል እመላለሳለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን። *ለተጨማሪ ጥናት* ማቴዎስ 6:25-26 ኢሳይያስ 26:3 ቆላስይስ 3:2 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Tuesday 1st, September 2026 ማክሰኞ ፥ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰማይና ምድርን የሚገዛ ስም ▬▬▬▬▬▬▬ “ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ” (ማቴዎስ 28:18)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ጌታ ኢየሱስ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ” ብሎ ሲያውጅ፣ በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ገዥ  በድፍረት ሊናገረው የማይችለውን ነገር ተናገረ። በታሪክ ውስጥ፣ ታላላቅ መንግሥታት እጅግ  በገነነ ተፅዕኖና ሰፊ ግዛትን በመያዝ ተነሥተው ያውቁ ነበር። ፈርዖኖች ግብፅን በሚያስፈራ ሥልጣን አስተዳድረዋል። ናቡከደነፆር የባቢሎንን ታላቅነት በሕገራት ላይ አስፋፍቷል። ፋርሳውያን፣ ግሪኮች፣ እና በኋላም ሮማውያን እያንዳንዳቸው በዘመናቸው ዓለምን ተቆጣጥረው ነበር። ሆኖም ግን፣ እነዚያ ሁሉ መንግሥታት በመጨረሻ ወድቀዋል። ነገር ግን፣ ሮም በትዕቢቷና “በክብሯ” ጫፍ ላይ በነበረችበት ጊዜ፣ ጌታ ኢየሱስ እጅግ ከፍ ባለ ሥልጣን መጣ። ይህም እንዲሁ የፖለቲካ ሥልጣን ወይም የምድራዊ ተፅዕኖ አልነበረም፤ ይልቁንም በሚታየውና በማይታየው፣ በሰማያዊውና በምድራዊው ሁሉ ላይ ያለ ፍጹም ሥልጣን ነበር። ይህንን ሥልጣን አንድም ንጉሠ ኖሮት አያውቅም። አንድም ንጉሥ በሰማይም በምድርም ላይ ገዝቶ አያውቅም። እንዲህ ዓይነቱን ሥልጣን ያወጀው ኢየሱስ ብቻ ነው። ደቀ መዛሙርቱ በጽኑ የተሳደዱት በዚህ ምክንያት ነበር። ቄሣር ንጉሥ በነበረበት ወቅት፣ እነርሱ ሌላ መንግሥት እንደሚያስተዳድር አወጁ። ከሮም ሥልጣን ይልቅ የሚበልጥ ስምን ሰበኩ፣ የዚያ ዘመን ገዥዎችም ይህንን ሊቀበሉ አልቻሉም። ነገር ግን እነርሱ ሁሉ ጠፍተው ሲቀሩ፣ የክርስቶስ ግዛት ግን ያለምንም እንቅፋት እየጨመረ ቀጠለ። ዕብራውያን 13:8 “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘላለምም ያው ነው” ይላል። ሥልጣኑ በጊዜ ሂደት አልቀነሰም። ስሙም በዘመናት ውስጥ አልደከመም። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የታመሙትን የፈወሰው፣ ሙታንን ያስነሳው፣ አጋንንትን ያወጣው እና ሀገራትን ያናወጠው ያው ስም ዛሬም ያንኑ ኃይል ይዟል። ከሁሉም በላይ የሚያስደንቀው ደግሞ፣  በእርሱ ምትክ እንድንሠራ የውክልና ስልጣንን፣ ሕጋዊ መብትንና መለኮታዊ ሥልጣንን ሰጥቶናል። በኢየሱስ ስም ስትናገሩ እንዲሁ ዝም ብላችሁ ቃላትን መናገራችሁ አይደለም፤ በሰማይና በምድር ላይ በሚገዛው በአንዱ ሥልጣን እየተጠቀማችሁ ነው። ስለዚህ፣ በምድራዊ ሥርዓቶች፣ በተቃውሞዎች ወይም በሁኔታዎች በፍጹም አትሸበር። ነገስታት ሊነሡና ሊወድቁ ይችላሉ፣ መንግሥታት ሊለወጡ ይችላሉ፣ የሰው ልጅ ኃይልም ሊጠፋ ይችላል፣ ነገር ግን የኢየሱስ ስም ለዘላለም የበላይ ሆኖ ይኖራል። ያንን ስም በድፍረት ተጠቀሙበት። በዓለማችሁ ውስጥ የእርሱን ፈቃድ ለማስፈጸም ተጠቀሙበት፣ እርሱ አሁንም ለዘላለምም በሁሉ ላይ ይገዛልና። ሃሌሉያ! ጸሎት ════════ ወድ አባቴ ሆይ፣ በኢየሱስ ስም ውስጥ ስለተሰጠው ሥልጣን አመሰግንሃለሁ። ጽድቅህንና ፈቃድህን በምድር ላይ እንዳደርግ በእርሱ ስም እንደተላክሁ በማወቅ ዛሬ በድፍረት፣ በድልና በመግዛት እመላለሳለሁ። አሁን እንኳን ሁኔታዎች ለሕይወቴ ካለህ ፍጹም ዓላማ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን በኢየሱስ ስም አውጃለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:9-10 የሐዋርያት ሥራ 4:12 ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:20-21 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶ
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Wednesday 2nd, September 2026 ረቡዕ ፥ ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ዓላማችሁን ለክብሩ ፈጽም ▬▬▬▬▬▬▬ “እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” (ኤፌሶን 2:10)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ክርስቶስ ሕይወት የሰጠን ለአብ ክብር እንድንኖረው ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ  ለፈጠረው ዓለምና ፍጥረት ሁሉ፣ እጅግ ግልጽ የሆነ አጀንዳ፣ የተወሰነ ዓላማ አለው ፣ እንዲሁም፣ በተለይም ደግሞ፣ ለሕይወታችሁ የመረጠው ዓላማ አለው። መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠኑ፣ በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ አስደናቂ የሆነ ወጥነት እና ስለ ፍጥረቱ እንዲሁም እናንተ በዚያ ውስጥ ስላላችሁ ድርሻ የማያጠራጥር የዓላማ ግልጽነት ታገኛላችሁ። በዚህ ዓለም ያላችሁት ሥነ-ምህዳሩን ለማመጣጠን አይደለም። በዚህ ጊዜ፣ በዚህ ስፍራ፣ የተሰጣችሁን ስጦታዎች፣ ችሎታዎች እና እድሎች ይዛችሁ አንድትወለዱ የተደረገበት ምክንያት አለ። ነገር ግን የሚያሳዝነው፣ ብዙዎች በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይንን ዓላማ ሳይረዱ ማለፋቸው ነው። በልማዶች፣ በጫናዎች፣ በሁኔታዎች እና በሚለዋወጡ ነገሮች እየተነዳችሁ እንዲሁ ዝም ብለላችሁ አትኑሩ። እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው ዓላማ ይህ አይደለም። ጥሩም ሆኑ መጥፎ ሁኔታዎች ሕይወታችሁን አንዲመራ አይፈልግም። በውጫዊ ሁኔታዎች ብቻ የሚመራ ሕይወት፣ ውጫዊ ስኬት ቢኖረው እንኳ በመጨረሻ ባዶነትና ውስጣዊ  ደስታን የሚነጥቅ ይሆናል። ዓለም የእንደዚህ አይነት ሰዎችን ስኬት የሚመስለውን ነገር ሊያደንቅ ይችላል፤ ሆኖም ግን በውስጣቸው ጥልቅ የሆነ የተፈጠሩበትን ዓላማ በእርግጥ አንዳልፈጸሙ የሚነግራቸው የሚጎዳ ስሜት ይኖራቸዋል። በዚህ ዓለም ውስጥ ማንኛውም ሰው ሊያደርገው የሚገባው በጣም አስፈላጊው ነገር እግዚአብሔር ለሕይወቱ ያለውን ዓላማ ማወቅና መፈጸም ነው። ይህም ሊመጣ የሚችለው ከእርሱ ጋር በሚደረግ እውነተኛ ግንኙነት ብቻ ነው። ዓላማ በግምት፣ በሰው ፍልስፍና፣ ወይም በግል ምኞት አይገኝም። ይልቁንም ከጌታ ጋር በሚደረግ ህብረት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይገለጣል። በእውነት ጌታን ወደ ማወቅና ከእርሱ ጋር በህብረት ወደ ማድረግ ስትመጡ፣ በመንፈሳችሁ ውስጥ ለሕይወታችሁ መለኮታዊ መመሪያ እና ሰማያዊ ራዕይ በእርግጠኝነት ታገኛላችሁ። ከዚህም ባሻገር መንፈስ ቅዱስ ያንን ዓላማ እንድትፈጽሙ ይረዳችኀል። እርሱ የእግዚአብሔርን ዕቅድ ለእናንተ ከመግለጥ ባለፈ፤ እንድትመላለሱበት እና እንዲትፈጽሙ ያደረጋችኀል። ስለዚህ በዓላማ ኑሩ፤ ሕይወታችሁ ትርጉም፣ አቅጣጫ፣ እና መለኮታዊ ዓላማ  እንዳለው በሚያውቅ በዚህ ንቃተ ህሊና ተመላለሱ። በመንፈስ ቅዱስ በኩል ዓላማችሁን ለእግዚአብሔር ክብር ፈጽሙ። ጸሎት ════════     ወድ አባቴ ሆይ፣ ለሕይወቴ ትርጉም፣ አቅጣጫ እና መለኮታዊ ዓላማ ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ያለ ዓላማ መኖርን ወይም በሁኔታዎች መነዳትን እንቢ እላለሁ። ከመንፈስህ ጋር በሚደረግ ህብረት እና በቃልህ ብርሃን፣ ዓለም ሳይመሠረት አስቀድመህ ለእኔ ባዘጋጀኸው መንገድ ውስጥ እመላለሳለሁ፤ ዓላማህንም በደስታና በብቃት እፈጽማለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ትንቢተ ኤርምያስ 1:5 መጽሐፈ ምሳሌ 19:21 ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ አካ
💫RHAPSODY OF REALITIES DAILY DEVOTIONAL💫 Wednesday, September 2nd 📜FULFIL YOUR PURPOSE TO HIS GLORY 📖 For we are his workmanship, created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them (Ephesians 2:10). 👤 PASTOR CHRIS OYAKHILOME DSc. DSc. DD. The life Christ has given us to live is to the glory of the Father. God always had a very clear agenda, a definite purpose for the world and universe He created and, in particular, a definite purpose for your life. When you study the Scriptures, you discover a remarkable consistency in God’s plan and an unmistakable clarity of purpose concerning His creation and your place in it. You’re not in this world to balance the ecosystem. There’s a reason you were born at such a time as this, in the place where you are, with the gifts, abilities and opportunities entrusted to you. But it’s unfortunate that many go through life without ever discovering that purpose.  Don’t just exist, driven by trends, pressures, circumstances, and changing conditions. That’s not God’s plan for you. He never intended for your life to be directed by circumstances, whether favourable or unfavourable. A life governed merely by external events eventually produces emptiness and inward frustration, regardless of outward success. The world may admire the seeming accomplishments of such individuals, yet deep within, there remains the painful awareness that they never truly fulfilled their purpose for being. The most important thing for anyone to do in this world is to discover and fulfil God’s purpose for their lives. And this can only come through a genuine relationship with Him. Purpose is not discovered through speculation, human philosophy, or personal ambition. It’s revealed through fellowship with the Lord and the ministry of the Holy Spirit.  When you truly come to know the Lord and walk in fellowship with Him, there comes a certainty in your spirit of the divine direction and the heavenly vision f
L
✨ Your life has a divine purpose. God did not create you to merely exist or be controlled by circumstances; He created you with a specific plan, gifts, abilities, and opportunities to fulfil His purpose and bring glory to His Name. 🕊 Don’t allow trends, pressures, or changing situations to determine the direction of your life. True fulfilment does not come from outward success but from discovering and walking in the purpose God has designed for you. 💪 Purpose is not found through human ambition or personal speculation; it is revealed through a genuine relationship with God and fellowship with the Holy Spirit. He gives you direction, clarity, and the power to fulfil your divine assignment. 🌟 You are here for a reason and your life carries eternal significance. Walk consciously in God’s plan, trusting the Holy Spirit to guide and empower you to fulfil your purpose to the glory of God. Hallelujah!
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Thursday 3rd, September 2026 ሀሙስ ፥ ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በህብረት ኑሩ ▬▬▬▬▬▬▬ “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና” (ሮሜ 8:14)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ቀደም ባለው ጥናታችን ላይ፣ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነጥብ አንስተናል፤ ይህም ማንኛውም ሰው በዚህ ዓለም ላይ ሊያደርገው የሚገባው ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ነገር የእግዚአብሔርን ዓላማ ማግኘትና መፈጸም መሆኑን ነው። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ፣ በሕይወት ጥሪያቸው መስመር ላይ ሆነው ሳለ፣ እግዚአብሔር ለዚያ እንደመረጣቸው የማያውቁ አሉ። ስለ ሕይወታቸው ስላለው የእግዚአብሔር ዓላማ በቂ ግንዛቤ ላይኖራቸው ይችላል፤ ነገር ግን ሕይወት ያቀረበላቸውን ጉዞ ዝም ብለው ይቀጥላሉ። ይህ በተወሰነ ደረጃ ሊረዳ ይችላል፣ ምክንያቱም ቢያንስ ከእጣ ፈንታቸው ጋር በተያያዘ አቅጣጫ እየተጓዙ ነውና። ነገር ግን በሕይወት ጉዞ ውስጥ ሁልጊዜ ተቃዋሚዎችና መከራዎች ይኖራል። ፈተናው ይህ ነው፦ እንቅፋቶች ሲፈጠሩ፣ ከዚያ ሁኔታ በላይ ለመራመድ ምን መደረግ እንዳለበት ከሚያውቀው አካል ጋር ካልተገናኙ፣ ጉዞአቸው ሊቋረጥ ይችላል። ያልተጠበቁ የሕይወት ክስተቶች ተስፋ ሰጭ የሚመስለውን መንገድ ሊያሰናክሉ ወይም ሊያጠፉ ይችላሉ። ይህ የሚሆነው ተሰጥኦ ስለሌላችሁ፣ ችሎታ ስለሌላችሁ ወይም ስላልተጠራችሁ ሳይሆን፣ ሕይወታችሁን ካቀደው ጌታ ሙሉ ዓላማው ምን እንደሆነና እንዴት ሙሉ በሙሉ መፈጸም እንደሚቻል በእውነት ስላላወቃችሁ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምናደርገው ኅብረት እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። የውጭ ጉዞአችሁ ምንም ያህል ስኬታማ ቢመስልም፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ሊገልጥላችሁ የሚችለው የላቀ ጥሪ፣ ታላቅ ዓላማና መለኮታዊ ሥርዓት አለ። እርሱ ፈጥሮአችኋል፤ ለምን እዚህ እንደሆናችሁም ያውቃል። የጥሪያችሁን ሙሉ ስፋትና ለክብሩና ለደስታው እንዴት መፈጸም እንዳለባችሁ ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ በራእይ 4:11 ላይ ሁሉም ነገሮች ለእርሱ ደስታ እንደተፈጠረ ይናገራል። የምንኖረው ለራሳችን ሳይሆን ለእርሱ ነው። ይህ ንቃተ-ህሊና ለሕይወታችሁ ትርጉም፣ ለጥረታችሁ ደግሞ መረዳትን ይሰጣችኋል። መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል እንደሚያስፈልጋችሁ እንድትገነዘቡ ይረዳችኋል። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በኅብረት ስትመላለሱ፣ ጥሪያችሁን በደስታና በድል ለመፈጸም መለኮታዊ አመራርን፣ ጥበብን፣ ጥንካሬን እና ጸጋን ትቀበላላችሁ። ስለዚህ ቃሉን በማጥናት፣ በጸሎትና ለምሪቱ በመገዛት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ኅብረት አሳድጉ። ምን ያህል እንደምትወዱትና በሁሉም ነገር ላይ የበላይ እንዲያደርጋችሁ በውስጣችሁ ባለው ማንነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ ላይ እንደምትደገፉ ሁልጊዜ ንገሩት። ሃሌ ሉያ! ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ ፍጹም በሆነው በፈቃድህ መንገድ ስለሚመራኝ ስለ መንፈስ ቅዱስ በረከትና አገልግሎት አመሰግንሃለሁ። በሁሉም ነገር ላይ የበላይ እንዲያደርገኝ፣ በውስጤ ባለው በመንፈስ ቅዱስ፣ በኃይሉና በክብሩ ላይ ስደገፍ፣ ሕይወቴ ዛሬም የአንተን ደስታ ይፈጽማል፣ አንዲሁም ለስምህ ክብርን ያመጣል። በኢየሱስ ስም አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:10 መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-6 የዮሐንስ ራእይ 4:11 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ አካውንት ዝርዝሮችን ከ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Friday 4th, September 2026 አርብ ፥ ነሀሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የትኩረታችሁን ማዕከል እርሱን አድርጉ ▬▬▬▬▬▬▬ “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን...” (ዕብራውያን 12:2)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ስነስርዓቶች አንዱ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለችሁን ትኩረት መጠበቅ ነው። ዓለም ትኩረታችሁን ከእርሱና ከቃሉ ለማራቅ በተቀናጀ መልኩ ትኩረትን በሚከፋፍሉ ነገሮች፣ ጫናዎች፣ አስተያየቶችና ሁኔታዎች የተሞላች ናት። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ፣  በቃሉ በኩል ጸንተን እንድንቆምና ትኩረታችን እንዳይከፋፈል ይመክረናል። የፓሽን ትርጉም በ2ኛ ጢሞቴዎስ 2:8 ላይ እንዲህ ይላል “...በሕይወታችሁንና በአገልግሎታችሁ ትኩረታችሁን የተቀባው ኢየሱስ ላይ አድርጉ...።” ይህንን አስተውላችኃል? ጌታ የትኩረታችሁ አካል ብቻ ሳይሆን ሙሉ ትኩረታችሁ መሆን አለበት። ሃሳቦቻችሁ፣ ጥረቶቻችሁ፣ ውሳኔዎቻችሁ፣ ጉልበታችሁና ምኞቶቻችሁ ሁሉ በእርሱና ለሕይወታችሁ ባለው መለኮታዊ ዓላማ ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው። ዕብራውያን 12:3 የጌታን ትኩረት እንደ ምሳሌ ያሳየናል፡- “የእርሱ ምሳሌ ይህ ነው፡-  ልቡ እናንተ የእርሱ እንደምትሆኑ በማወቅ ደስታ ላይ ያተኮረ ነበርና ነውርን ንቆ በፊቱ ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል...” (ቲፒቲ)። የተባረከ ሃሳብ! በሥቃይ፣ በውርደት፣ ባለመፈለግና በኀፍረት ውስጥ፣ እርሱ ከመከራው ባሻገር ተመልክቶ እይታውን በከበረው ውጤት ላይ አደረገ። መከሩን ተመለከተ፣ መከሩም አናንተ ናችሁ! በመታዘዙ የሚመጣውን ክብር አይቷል፣ እናም ተልእኮውን ሙሉ በሙሉ እስኪፈጽም ድረስ በትኩረት ቆየ። ሊኖራችሁ  የሚገባው አስተሳሰብ ይህ ነው። ለጌታ ያላችሁ ፍቅር መግለጫ በሆኑ ነገሮች ላይ በፈተናዎች፣ በስሜቶች፣ በጫናዎች ወይም በጊዜያዊ መሰናክሎች ለመናወጥ እምቢ በሉ። ትኩረታችሁን በእርሱ ላይና እንድትሰሩ በጠራችሁ ነገር ላይ አድርጉ። ትኩረት ጥንካሬን፣ አቅጣጫን እና ጽናትን ይሰጣል። አይኖቻችሁ በጌታ ላይ ሲያርፉና ልባችሁ በቃሉ ላይ ሲጸና ዘወትር በድል ትመላለሳላችሁ። እግዚአብሔር ለኢያሱ የሰጠው መመሪያ ይህ ነበር፡- “ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ በጥንቃቄ እንድትፈጽመውም ቀንም ሆነ ሌት ከሐሳብህ አትለየው፤ ይህን ካደረግህ ያሰብኸው ይቃናል፤ ይሳካልም” (ኢያሱ 1:8 አ.መ.ት)። በትኩረትና በስኬት መካከል ያለውን ግንኙነት ልብ በሉ። በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ስኬት በአጋጣሚ የሚመጣ ነገር አይደለም። የሚመጣው በቃሉ ላይ በመጽናት፣ በጌታ ላይ ትኩረትን በማድረግ፣ እና በቃሉና ለሕይወታችሁ ባለው ዓላማ ውስጥ በመኖር ነው። ሃሌሉያ! ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ በፈቃድህ ውስጥ ጸንቼ፣ በትኩረትና ተመሥርቼ እንድቆም ስለሚያደርገኝ ቃልህ አመሰግንሃለሁ። እይታዬ በአንተ ላይ ነው፣ ልቤም በእውነትህ ውስጥ ጽንቷል። ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮችን እምቢ እላለሁ፣ እናም ለእኔ በወሰንከው መንገድ ላይ ሳልናወጥ እቆያለሁ። በቃልህ መሠረት ስኖር፣ ዘወትር በድል፣ በብልጽግናና በስኬት እመላለሳለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ወደ ዕብራውያን ሰዎች 12:2 መጽሐፈ ኢያሱ 1:8 ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:2 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Saturday 5th, September 2026 ቅዳሜ ፥ ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ወደ ግቡ ሩጡ ▬▬▬▬▬▬▬ “...የኋላዬን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ ለማግኘት ወደ ግብ እገሰግሳለሁ” (ፊልጵስዩስ 3:13-14)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ የሐዋርያው ጳውሎስን ሕይወት ስታጠኑ፣ መለኮታዊ ዓላማውን በመከተል ረገድ ወጥነትና ቁርጠኝነት ታስተውላላችሁ። ትኩረቱ የተከፋፈለ አልነበረም። በአንድ ጊዜ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ለመሮጥ አልሞከረም። ዓይኖቹ ያረፉት በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን ከፍተኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ዋጋ ለማግኘት በግቡ ላይ ነበር። ይህ የጌታ የኢየሱስም አስተሳሰብ ነበር። ዕብራውያን 12:2 እንደሚነግረን፣ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሶ ውርደቱንም ንቆታል። ዓይኑን በዋጋው ላይ አደረገ። በሥቃይ፣ በመገለል፣ በውርደትና በመከራ መካከል ቢሆንም፣ ክብር ባለው ውጤት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ቆየ። ከሥቃዩ ባሻገር የእግዚአብሔርን የዘላለም ዓላማ ፍጻሜ ተመለከተ። በትኩረት በመቆየቱም፣ አሸነፈ። ከጌታ ጋር ባላችሁ ጉዞ ሊኖራችሁ የሚገባው አስተሳሰብ ይህ ነው። ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ለማለት እምቢ በሉ። የሕይወት ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች፣ ዓለማዊ ምኞቶች፣ ጫናዎች፣ ተስፋ መቁረጦች ወይም ጊዜያዊ ፍላጎቶች ትኩረታችሁን ከክርስቶስና በሕይወታችሁ ላይ ካለው ጥሪ እንዲያሸሻችሁ አትፍቀዱ። ዓይኖቻችሁ ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይመልከቱ። ብዙዎች በሥራ ተጠምደው ይንቀሳቀሳሉ፣ ነገር ግን የሚሮጡት ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ነው። ወደ መጨረሻው መስመር ሳይሆን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንደሚሮጥ ልክ እንደ አንድ ፈጣን ሯጭ። ፍጥነት ብቻውን ድልን አያመጣም። መሮጥ ብቻ በቂ አይደለም፤ ወደ ግቡ መሮጥ አለባችሁ። እግዚአብሔር በፊታችሁ ያስቀመጠውን ዓላማ፣ ራዕይ እና ጥሪ ማወቅ አለባችሁ። ሥራችሁ፣ ንግዳችሁ ወይም በሕይወት ውስጥ ያላችሁ ኃላፊነት ምንም ቢሆን፣ የትኩረታችሁ ማዕከል መሆን ያለበት ክርስቶስ ነው። እርሱ የምኞታችሁ፣ የውሳኔአችሁ፣ የጥረታችሁ እና የዓላማችሁ  ማዕከል መሆን አለበት። ልባችሁ በእርሱ ላይ ሲጸና፣ ሌላው የሕይወታችሁ ገጽታ ሁሉ ትክክለኛውን ሥርዓትና ትርጉም ያገኛል። ስለዚህ፣ በጌታና በሰጣችሁ የዘላለም ዓላማ ላይ ትኩረታችሁን አድርጉ። በቁርጠኝነት፣ በድፍረትና በማይናወጥ እምነት ወደ ግቡ ገስግሱ። ማሽነፍ ዋጋ አለው፣ እናም ዓይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ ካደረጋችሁና በቃሉ ከጸናችሁ፣ ጥሪአችሁን በክብርና በድል ትፈጽማላችሁ። ሃሌሉያ! ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ የክብር ጥሪንና ሰማያዊ ዓላማን በፊቴ ስላስቀመጥክ አመሰግንሃለሁ። ዓይኖቼ ባአንተ ላይ ናቸው፣ ልቤም ለሕይወቴ ባለህ ፍጹም ፈቃድ ላይ የጸና ነው። ጥሪዬን በድል እየተወጣሁ፣ በድፍረት፣ በእምነትና በቁርጠኝነት ወደ ግቡ እገሰግሳለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ወደ ዕብራውያን ሰዎች 12:2 መጽሐፈ ምሳሌ 4:25 1 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:24 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ አካውንት ዝርዝሮችን ከታች ማግኘት ይችላሉ፤ -Rhapsody of Realities/ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Believers LoveWorld (ROR) 1000466669826 አዋሽ ባንክ
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Sunday 6th, September 2026 እሁድ ፥ ጰጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምልክታዊ መታሰቢያ ያለፈ ▬▬▬▬▬▬▬    “ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና።“ (1ኛ ቆሮንቶስ 11፡29) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════    ቅዱስ ቁርባን ከሃይማኖታዊ ሥርዓት ወይም ከምልክታዊ መታሰቢያ እጅግ የላቀ ነው። ይህም በጌታ በኢየሱስ የታዘዘ፣ ታላቅ መንፈሳዊ ትርጉምና ኃይል የተሞላበት መለኮታዊ ሥርዓት ነው። ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጌታ እራትን ሲካፈል፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ጌታም እንጀራውን ወስዶ ባረከው፣ ቆረሰው፣ ሰጣቸውም እንዲህ አለ፦ "ይህ ሥጋዬ ነው።" (ማቴዎስ 26፥26፣ ማርቆስ 14፥24፣ ሉቃስ 22፥19)።    “ይህ ሥጋዬን ይወክላል” አላለም፤ ይልቅ በግልጽ ነበር የተናገረው። “ይህ ለእናንተ የተሰጠ ሥጋዬ ነው” አለ። እንዲሁም ስለ ጽዋው ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ እንዲህ ሲል ጻፈ፦ “የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?” (1ኛ ቆሮንቶስ 10፥16)      መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ ቁርባንን ተራ ምልክት ብቻ አድርጎ አንደማያቃልለው አስታወሱ። ይልቁን፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና አገልግሎት፣ ከክርስቶስ ሥጋና ደም ጋር እውነተኛ መንፈሳዊ መካፈልና ኅብረት አለ። ስለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ ቁርባንን በምንካፈልበት ጊዜ የጌታን ሥጋ እንድንረዳ የሚያሳስበን። መረዳት ማለት በትክክል ማወቅ፣ በመንፈስ መረዳት፣ እና በእምነት ምላሽ መስጠት ማለት ነው።    ቅዱስ ቁርባንን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ ያለውን መለኮታዊ ትርጉምና ኃይል በመረዳት ተቀበሉት። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚያስረዳው፣ የጌታን ስጋ በትክክል ባለመረዳታቸው ምክንያት የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም ህይወታችው አልፏል። (1ኛ ቆሮንቶስ 11፥30)። ነገር ግን ተቃራኒውም የዛኑ ያህል እውነት ነው፤ ቅዱስ ቁርባንን በእምነትና በመገለጥ ስትካፈሉ፣ ቅዱስ ቁርባኑ የመለኮታዊ ሕይወት መተላለፊያ ፣ የጤና፣ የብርታት እና የመንፈስ ጥንካሬ ይሆናል።    የምትመገቡት ምግብ ልክ ከሰውነታችሁ ጋር አንድ እንደሚሆን፣ በእምነት የምትቀበሉትም ቅዱስ ቁርባን፣ የመለኮታዊውን ሕይወት እውነታን ወደ ማንነታችሁ ያስገባል። ስለዚህ፣ ቅዱስ ቁርባንን በምትካፈሉበት ጊዜ፣ የክርስቶስ ኃይል በእናንተ ውስጥ እየሠራ መሆኑን በእምነት አውጁ። የክርስቶስ ሕይወት ተካፋዮች ስለሆናችሁ፣ ሕመም፣ ስቃይ፣ ደካማነት እና በሽታ በሰውነታችሁ ውስጥ ስፍራ እንደሌላቸው በእምነት አውጁ።   ቅዱስ ቁርባንን በፍጹም በቸልታ አትቅረቡት። ይልቁን፣ በአክብሮት፣ በደስታ እና በክርስቶስ መሥዋዕት አቅም ላይ ባለ የማይናወጥ እምነት ቅረቡት። ቅዱስ ቁርባንን በመካፈል፣ የክርስቶስን ድል፣ ሕይወት፣ ጤና እና ጽድቅ እውነታዎች እንደገና መልሳችሁ ታስትውሳላችሁ፤ እነዚህም በሕይወታችሁ ይገለጣሉ። ሃሌሉያ! ጸሎት ════════    ውድ አባት ሆይ፣ ስለ ቅዱስ ቁርባን በረከትና ኃይል አመሰግንሃለሁ። እንጀራውንና ጽዋውን ስካፈል፣ የጌታን ሥጋ በትክክል በማስተዋል፣ በመለኮታዊ ሕይወት እውነታ፣ የብርታት፣ የጤና እና የመንፈሳዊ ሕያውነት እውነታ ውስጥ እመላለሳለሁ። የክርስቶስ ሕይወት በሰውነቴ ስለሚገለጥ፣ ሕመም፣ ስቃይ፣ ደካማነት እና በሽታ በእኔ ውስጥ ስፍራ የላቸውም። በኢየሱስ ስም።  አሜን። ለተጨማሪ ጥናት 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡16 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡24-25 ዮሐንስ 6፡56-57
L
September The Month Of Growth!!!
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Monday 7th, September 2026 ሰኞ ፥ ጰጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. እርሱ ያለውን ተናገሩ ▬▬▬▬▬▬▬    “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን። (ዕብራውያን 13፡5-6)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════    እግዚአብሔር የመጻሕፍ ቅዱስን ጥቅሶች እንዲሁ ለመረጃ፣ ለመነሳሳት ወይም ለሥነ ምግባር ትምህርት ብቻ አልሰጠንም። ምንም እንኳን የመጻሕፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚያንጹን ወይም የሚያሳድጉንና የሚያስተምሩን ቢሆኑም፣ ዕብራውያን 13፥5-6 እግዚአብሔር ይህን ያለበትን ዋነኛውን ምክንያት ለምን እንደሆነ ጥልቅ እውነታ ያሳየናል። ቃሉ የሚናገረውን ነገር በውስጣችንና ለእኛ ያንኑ ፍሬ ያፈራል። ይህም እንዴት እንደሚሠራ እገልጻለሁ።    ቁጥር አምስት ላይ ይሄንን ካለ በኋላ፤ “... እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤” ቁጥር 6 እንዲህ ይላል፤ “ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።” ቅደም ተከተሉን አስታውሱ፤ እርሱም ተናግሯል ስለዚህ እናንተም መናገር ትችላላችሁ። ይህ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ካሉት እጅግ አስፈላጊ መርሆች አንዱ ነው። እግዚአብሔር ቃሉን የሚሰጣችሁ፣ በመንፈስሳችሁ እንድትቀበሉት እና ከእርሱ ጋር በስምምነት አንድ የሆነ ቃል እንድትናገሩ ነው።    ስለዚህ፣ በክርስትና፣ የእግዚአብሔርን ቋንቋ እንናገራለን፤ ቃሉንም በድፍረት እናውጃለን፤ የምንናገረውንም እናገኛለን። እግዚአብሔር አስቀድሞ በመንፈሱ በእናንተ ውስጥ ይኖራል። ፈቃዱ በአካላዊዊ መንገድ ሊቆጣጠራችሁ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ በመጻሕፍ ቅዱስ ጥቅስ አማካኝነት ሊናገራችሁ አያስፈልገውም ነበር። ነገር ግን ከእርሱ ጋር በአንድነት በመናገር፣ በመለኮታዊ ልምምድና በቃሉ አሠራር ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ ይፈልጋል።         እምነት የሚሠራው እንዲህ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መንፈሳችሁ ትቀበላላችሁ፤ ከዚያም በድምጽ ትናገራላችሁ። ስለ ጤንነታችሁ፣ ስለ ወደፊት ሕይወታችሁ፣ ስለ ገንዘባችሁ፣ ስለ ቤተሰባችሁ እና ስለ ሕይወታችሁ እያንዳንዱ ዘርፍ የእግዚአብሔርን እውነት ትናገራላችሁ። በአንደቤታችሁ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፣ ራሱ እግዚአብሔር ይናገራል ማለት ነው፤ የእርሱ ኃይል በእናንተ ቦታ መሥራት ይጀምራል፣ ሁኔታዎችንም ሁሉ ለእናንተ ጥቅም እንዲሰሩ ያስተካክላል።    ብዙዎች የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታቸው እንዲፈጸም ይመኛሉ፤ ነገር ግን ቃሉን አይናገሩትም። የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችሁ እና በሁኔታዎቻችሁ ውስጥ ውጤታማ የሚሆነው፣ በድፍረት በእምነት ስታውጁና ስትናገሩት ብቻ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ ሕይወትን፣ ድልን፣ ጽድቅን፣ ጤናን፣ ብልጽግናን እና ግዛትን ተናገሩ። ይህ የድል አድራጊ ክርስቲያን ሕይወት ምስጢር ነው። ጸሎት ════════    ውድ አባት ሆይ፣ እንድኖርበት እና በድፍረት እንድናገረው ስለ ሰጠኸኝ ቃልህ አመሰግንሃለሁ። ስለ ሕይወቴ ከእውነትህ ጋር በመስማማት እናገራለሁ፤ ቃልህም በእኔ ውስጥ በኃይል ይሠራል። ሕይወቴ በቃልህ ቁጥጥር ውስጥ ነው፤ እኔም ሁልጊዜ በድል፣ በእምነት፣ በሥልጣን እና በክብር እመላለሳለሁ፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።  ለተጨማሪ ጥናት ማርቆስ 11፡26 ሮሜ 10፡8 2 ቆሮንቶስ 4፡13 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥1
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Tuesday 8th, September 2026 ማክሰኞ ፥ ጰጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ድርሻችሁን በታማኝነት አከነውኑ ▬▬▬▬▬▬▬    “ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፤ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።” (ምሳሌ 4፡13) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════    ከእግዚአብሔር ጋር በምትጓዙበት ጊዜ፣ በሕይወታችሁ ያልተለመደና ታላቅ ነገር ሊያደርግ ሲፈልግ የተለዩና ግልጽ መመሪያዎችን የሚሰጣችሁ ጊዜያት አሉ። በእንደዚህ ያሉ ጊዜያት፣ ትኩረት እጅግ ወሳኝ ነው። መታዘዝ በአጠቃላይ ትክክለኛ ነገር ማድረግ ብቻ አይደለም፤ እርሱ ያለውን በትክክል፣ በዚያው በተናገረበት መንገድ ማድረግ ነው። ብዙዎች ይህንን ያስታሉ፤ ከዚያም የሚጠብቁት ውጤት ለምን እንዳልተገለጠ ይገረማሉ።           ሙሴን እንመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ጋር በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደቆየ ይነግረናል (ዘፀአት 34፥28)። ሠላሳ ስምንት ቀን ወይም ሠላሳ አምስት ቀን አልነበረም። እግዚአብሔር በእርሱ አማካኝነት ሊፈጽመው ላሰበው ነገር ያ ሙሉ ጊዜ መለኮታዊ ዓላማና ትርጉም ነበረው። ሙሴ ሂደቱን ከተወሰነው ጊዜ በፊት አስቀድሞ ቢያቋርጥ ኖሮ፣ እግዚአብሔር በቀባው ነገር ውስጥ ያለውን ተሳትፎ በራሱ ያቋርጥ ነበር።   ይህ መንፈሳዊ ነገሮች ከሚሠሩባቸው መንገዶች አንዱ ነው። እግዚአብሔር በመንገዶቹ ሁሉ ፍጹም ነው፤ የሚሰጣቸውም መመሪያዎች በፍጹም በዘፈቀደ አይደሉም። የሚነግሯችሁ እያንዳንዱ ነገሮች ዓላማ፣ ትርጉም እና መንፈሳዊ ፍጹምነት አላቸው። ስለ ጸሎት፣ በቃሉ ላይ ስለማሰላሰል፣ መስጠት፣ ነፍሳትን ማዳን ወይም ስለማንኛውም መንፈሳዊ ልምምድ መመሪያ ሲሰጧችሁ፣ እስከ መጨረሻው በታማኝነትና በሙሉ መፈጸም እጅግ አስፈላጊ ነው።    መጽሐፍ ቅዱስ በኢሳይያስ 1፥19 እንዲህ ይላል፦ “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤"። አስተውሉ፤ “እሺ ብትሉ” ብቻ አላለም፤ መታዘዝ የእምነት ተግባራዊ መገለጫ ነው። በእግዚአብሔር መለኮታዊ ዕቅድ ውስጥ የእናንተ ድርሻ ነው። እግዚአብሔር የእርሱን ድርሻ ሁልጊዜ በፍጹም ትክክለኛነት ይፈጽማል፤ እናንተ ግን የራሳችሁን ድርሻ እንዳትዘነጉ ማረጋገጥ አለባችሁ።    በመንፈስ ዓለም ሁሉም ነገር በመለኮታዊ ሥርዓትና በፍጹም ትክክለኛነት ይሠራል። በ1ኛ ቆሮንቶስ 14፥40 እንዲህ ይላል፦ "ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።" በእግዚአብሔር ዘንድ ድንገተኛ ወይም በአጋጣሚ የሚሆን ነገር የለም። እርሱ የሚናገረው እያንዳንዱ ቃል እንኳን ዓላማና ዋጋ አለው። ስለዚህ፣ በተለይም ከፍጻሜያችሁን፣ ከመንፈሳዊ እድገታችሁ እና ከአገልግሎታችሁ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ፣ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ በጥንቃቄ የማዳመጥ ልምድ አዳብሩ። መመሪያዎቹን ዋጋ ስጧቸው፤ እንደተናገረውም በትክክል ተግብሯቸው።    መንፈስ ቅዱስ “ጸልዩ” ቢሏችሁ፣ ጸልዩ። “ጠብቁ” ቢሏችሁ፣ ጠብቁ። “አሁን እርምጃ ውሰዱ” ቢላችሁ፣ አትዘግዩ። መመሪያዎቹን በቀጣይነትና በታማኝነት መከተላችሁ፣ የእርሱን ክብር በላቀ ደረጃ እንድትገልጡና እና ዓላማው በሕይወታችሁ እንዲፈጸም ያዘጋጃችኋል። ጸሎት ════════    ውድ አባት ሆይ፣ በመንፈስህ እንድመራ እና ለምትሰጠኝ እያንዳንዱ መመሪያ በመታዘዝ፣ በትክክለኛነትና በታማኝነት እንድመላለስ ስለሰጠኸኝ እድል አመሰግንሃለሁ። ልቤ ድምፅህን በጥሞና ያደምጣል፤ እናም በሁሉም ነገር የላቀ ውጤት እያፈራሁ እና ለሕይወቴም ያለህን ዓላማ እየፈጸምኩ ከፍጹም ፈቃድህም ጋር በሙሉ ተስማምቻለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Wednesday 9th, September 2026 ረቡዕ ፥ ጰጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. መንፈሱ በላያችሁ ላይ ፈስሷል ▬▬▬▬▬▬▬    “ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ …” (ኢዮኤል 2፡28) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════    በነቢዩ ኢዮኤል አማካኝነት እግዚአብሔር የተናገረው እንዴት ያለ ድንቅ መግለጫ ነው! እንዲህ አለ፦ "መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ።" ይህ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያዘጋጀውን ዘላለማዊ ዕቅዱን የገለጠበት ነበር፤ መንፈሱ ከእንግዲህ ወዲህ በተመረጡ ጥቂት ሰዎች ላይ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚገኝ የሚሆንበትን ዘመን አስቀድሞ እያሳየ ነበር።       እግዚአብሔር ይባረክ! ያ ትንቢት ተፈጽሟል። በባለሃምሳ ቀን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ … በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥" (የሐዋርያት ሥራ 2፥2-4)። ይህ ሁሉን ነገር ቀየረ። መንፈስ ቅዱስ ፈስሷል። እናም አሁን፣ ወንዶችና ሴቶች እውነትን መቀበልና ማመን እንደሚችሉ እርግጠኞች ስለሆንን፣ ወንጌል በዓለም ሕዝቦች ሁሉ እና ለእያንዳንዱ ሰው በድፍረት ሊሰበክ ይችላል።          አንድም ሰው ያለ መንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በእውነት ማወቅ ወይም ማመን አይችልም። መንፈስ ቅዱስ ነው የሰውን ልብ የሚያሳምነው፣ የክርስቶስንም ጽድቅና እውነተኛ ማንነት የሚገልጠው (ዮሐንስ 16፥7-8)። አስታውሱ፤ ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ " እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?" (ማቴዎስ 16፥16) ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ፣ ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ።" ብሎ መለሰ።    ከዚያም ጌታ ወዲያውኑ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ "በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።” (ማቴዎስ 16፥17)። በተጨማሪም፣ በዮሐንስ 6፥44 ጌታ እንዲህ አለ፦ “የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ " ታዲያ፣ አብ በዛሬው ዘመን ሰዎችን እንዴት ወደ እርሱ ይስባል? ይህ የሚሆነው በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። እርሱ በዓለም ዙሪያ ባሉ ሰዎች ልብ ውስጥ እየሠራ ያለው፣ ለወንጌል ልባቸውን የሚያዘጋጅ እና እውነቱን የማመን ችሎታ የሚሰጣቸው እርሱ ነው። ስለዚህም ወንጌልን በምትሰብኩበት ጊዜ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ ወይም አትሸነፉ። መንፈስ ቅዱስ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አስቀድሞ ፈስሷል። በእያንዳንዱ ከተማ፣ በእያንዳንዱ አገር፣ በእያንዳንዱም ባህል ውስጥ ባሉ ሰዎች ልብ ውስጥ እየሠራ ነው። የእናንተ ኃላፊነት፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በመልእክቱ አማካኝነት ሰዎችን እያሳመነ፣ እየወቀሰ፣ እየሳበ እና ሕይወታቸውን እየለወጠ እንደሆነ በሙሉ እርግጠኞች በመሆን እውነትን በድፍረትና በታማኝነት ማወጅ ብቻ ነው። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!   ጸሎት   ════════    ውድ አባት ሆይ፣ መንፈስህን በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ስለ አፈሰስህ አመሰግንሃለሁ። የወንጌል አገልጋይ እንድሆንና በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ተካፋይ እንድሆን ስለ ሰጠኸኝ መብት አመሰግንሃለሁ። ወንጌልን ሳውጅ፣ የሰዎች ልብ ይከፈታል፣ ሕይወታቸው ይለወጣል፣ ብዙዎችም ወደ ክርስቶስ እውቀት ይመጣሉ፤ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት የሐዋሪያት ስራ 2፡16-18 ዮሐንስ 16፡8 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡3 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Thursday 10th, September 2026 ሀሙስ ፥ ጰጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሰው ሁሉ የተሰጠ የከበረ ስጦታ ▬▬▬▬▬▬▬    “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፡23) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════    ለሰው ልጆች ሁሉ ያለው የጌታ ፍቅርና መልካምነት መግለጽ ከሚቻለው በላይ ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ፣ ፍላጎቱ ሁልጊዜ ሰውን ወደ ራሱ ኅብረት ማምጣትና የመለኮታዊ ሕይወቱና የክብሩ ተካፋይ ማድረግ ነበር። ለዚህም ነው ለሰው ልጆች ሦስት ድንቅና እጅግ የከበሩ ስጦታዎችን የሰጠው፤ እነዚህ ስጦታዎች ከፍ ያሉ ናቸው፣ የሰው ጥረትም ሆነ ማንኛውም ስኬት ፈጽሞ ሊያስገኛቸው አይችልም።    ከእነዚህ ስጦታዎች የመጀመሪያው የዘላለም ሕይወት ነው። በመክፈቻ ጥቅሳችን እንዳነበብነው፦ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። ይህ ስጦታ ለተመረጡ ጥቂቶች ብቻ የቀረበ አይደለም፤ ለክርስቲያኖች ብቻም የተጠበቀ አይደለም። አይደለም፤ ለዓለም ሁሉ ቀርቧል። በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ማንኛውም ሰው የዘላለምን ሕይወት ይቀበላል፤ እንደ አዲስ ይወለዳል። ይህ ሕይወት ከሰይጣን፣ ከሞት እና ከመቃብር ሁሉ የበላይ ነው።      ሁለተኛው የጽድቅ ስጦታ ነው። ሮሜ 5፥17 እንዲህ ይላል፦ "... ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።" ማንም ሰው በራሱ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ሊቆም አይችልም፤ ምክንያቱም የሰው ጽድቅ በእርሱ ፊት በቂ አይደለም። ስለዚህ፣ እግዚአብሔር በፍቅሩ የራሱን ጽድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለሰው ልጆች በነፃ ሰጠ።    የእግዚአብሔርን ጽድቅ ስትቀበሉ፣ በእርሱ ፊት ያለ ጥፋተኝነት፣ ያለ ኩነኔ፣ እና ያለ የበታችነት ስሜት ትቆማላችሁ። በክርስቶስ ተቀባይነትን ያገኛችሁ እና ልክ ኢየሱስ ጻድቅ እንደሆነ ሁሉ እናንተም ጻድቃን ሆናችሁ ትቆማላችሁ።    ሦስተኛው ስጦታ ደግሞ ውድ የሆነው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዮኤል አማካኝነት፣ "መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ..." (ኢዮኤል 2፥28) ብሎ ተናገረ። እንዴት ያለ ድንቅ በረከት ነው! “ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።" (የሐዋርያት ሥራ 2፥38)።   ነገር ግን፣ የሚያሳዝነው እውነታ፣ እነዚህን ውድ ስጦታዎች ሁሉም ሰው አለመቀበሉ ነው። ብዙዎች እግዚአብሔር በጸጋው በነፃ የሚሰጠውን ነገር አሁንም በራሳቸው ጥረት ለማግኘት ይሞክራሉ። በክርስቶስ ያለው መዳን፣ ከእርሱም ጋር የሚመጣው የዘላለም ሕይወት፣ የጽድቅ ስጦታ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፣ ሰው በሥራ ወይም በትግል የሚያገኘው ሳይሆን በእምነት የሚቀበለው የእግዚአብሔር ነፃ ስጦታ ነው። እነዚህ ለሰው ልጅ ከቀረቡት ስጦታዎች ሁሉ እጅግ የላቁ ስጦታዎች ናቸው። ዛሬ በሙሉ ልብ ተቀበሏቸው፤ በረከታቸውንም በሙላት እየተለማመዳችሁ ተመላለሱ። ጸሎት   ════════    ውድ አባት ሆይ፣ ወሰን ለሌለው ፍቅርህ እና ለሰጠኸኝ ውድ ስጦታዎች፦ ስለዘላለም ሕይወቱ፣ ስለ ጽድቁ እና ስለ መንፈስ ቅዱስ እጅግ አመሰግንሃለሁ። በሕይወት በድል እየነሳሁ እና በምሄድበትም ሁሉ ክብርህን እየገለጥሁ፤ ዛሬ በእነዚህን በረከቶች እውነታና ሙላት እመላለሳለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Friday 11th, September 2026 አርብ ፥ መስከረም 1  2018 ዓ.ም. መንፈስ ቅዱስ—የእግዚአብሔር የመጨረሻው መፍትሔ ▬▬▬▬▬▬▬ “…እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።” (ዮሐንስ 14፥16-17)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ የክርስትና ሕይወት ያለ መንፈስ ቅዱስ የማይቻል ነው። ማንም ሰው በሕይወቱ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ሳይኖር የእግዚአብሔርን ፈቃድ በትክክል መፈጸም፣ ወጥ በሆነ ድል ውስጥ መመላለስ ወይም ለጌታ ውጤታማ ሆኖ መኖር አይችልም። ለዚህም ነው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለሰው ልጅ ከተሰጡት ታላላቅ በረከቶች አንዱ የሆነው። መንፈስ ቅዱስ ከተጽዕኖ ወይም ከመንፈሳዊ ልምምድ በላይ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር የመጨረሻ መፍትሔ ነው። አንድ ሰው በሕይወቱ ውስጥ የሚያጋጥመው ተግዳሮቶች፣ ገደቦች ወይም ችግሮች ምንም ይሁን ምን፤ እግዚአብሔር ለሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ስጦታው ምላሽ ሰጥቷል። መንፈስ ቅዱስ ወደ ሕይወታችሁ ሲመጣ፣ ተራ መሆናችሁ አብቅቷል። የእግዚአብሔር መለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋዮች ሆናችኋል። ሐዋርያው ጳውሎስ በ (ፊልጵስዩስ 4፥13)  ላይ፣ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።” በማለት ሲናገር የተረዳው ይህንን ነበር። መንፈስ ቅዱስ ብርታታችሁ፣ ጥበባችሁ፣ መሪያችሁ እና ረዳታችሁ ነው። ከመለኮታዊ አቅም ጋር እንድትንቀሳቀሱ ያደርጋችኋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ ከአብ ጋር ወደ ጥልቅ ኅብረት ያመጣችኋል፣ እንዲሁም በጽድቅ መንገድ ይመራችኋል። የእግዚአብሔርን ፍጹም ፈቃድ እንድታውቁ እና እንድትመላለሱበት ይረዳችኋል። ከእርሱ ጋር ሆናችሁ፣ ፈጽሞ በግራ መጋባት፣ በጥርጣሬ ወይም በሽንፈት ውስጥ አትመላለሱም። በመለኮታዊ ጥበብ ይመራችኋል እንዲሁም ዘላቂ ወደሆነ ድል ይመራችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ በ (ኤፌሶን 5፥18) ላይ፦ “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤” በማለት ዘወትር በመንፈስ እንድንሞላ የሚያዘን ለዚህ ነው። ይህ ቀጣይነት ያለው ትዕዛዝ መሆኑን ልብ በሉ። አልፎ አልፎ ወይም በልዩ ስብሰባዎች ወቅት ብቻ እንድትሞሉ አይፈልግም። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ነው። በየቀኑ፣ የእርሱን መገኘት ንቃተ-ህሊና ይኑራችሁ፤ እናም ሁልጊዜ በእርሱ ለመሞላት ራሳችሁን አስገዙ። አብዝታችሁ በልሳኖች ጸልዩ። በቃሉ ላይ አሰላስሉ። ለእርሱ ምሪት ራሳችሁን አስገዙ። በፍቅር ተመላለሱ። አብዝታችሁ በእርሱ በተሞላችሁ ቁጥር፣ የመለኮታዊውን ሕይወት ክብር፣ ጥበብ እና ልህቀት በይበልጥ ትገልጣላችሁ። ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ ለሁሉም የሰው ልጆች ፍላጎት የመጨረሻ መፍትሔህ ስለሆነው ስለ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታህ አመሰግንሃለሁ። እኔ በመንፈስ የተሞላሁ ነኝ፣ እናም በጥበብ፣ በድል እና በልህቅት እመራለሁ። በወንጌል በረከቶች ሙላት እና በአንተ ፍጹም ፈቃድ ውስጥ እመላለሳለሁ፤ እናም ዛሬ በሁሉም ስፍራ የክርስቶስን ሕይወት እና ክብር እገልጣለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ዮሐንስ 14:16-17 ሮሜ 8:14 1ኛ ቆሮንቶስ 2:12 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Saturday 12th, September 2026 ቅዳሜ ፥ መስከረም 2  2018 ዓ.ም. በመንፈስ ሙላት ውስጥ ኑሩ ▬▬▬▬▬▬▬ “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤” (ኤፌሶን 5፥18)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ብዙዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ጉዞ መንፈሳዊ ውጤታማነት የሚመጣው አልፎ አልፎ በሚደረጉ ከፍተኛ የዝግጅት ጊዜያት ብቻ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ስለዚህ፣ ለእግዚአብሔር አንድ ጉልህ ነገር ማድረግ ሲያስፈልጋቸው፣ ውጤታማ በሆነ መንገድ ከመሥራታቸው በፊት በመጀመሪያ መንፈሳዊ “ዝግጅት” ማድረግ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ያሳየን ወይም ያንጸባረቀልን ሕይወት እንደዚያ አይደለም። ጌታ ኢየሱስ ከአንድ መንፈሳዊ ጥድፊያ ወደ ሌላ አልኖረም። እርሱ ከአብ ጋር ባልተቋረጠ ኅብረት ውስጥ ነው የኖረው። ለእርሱ ጸሎት አድካሚ “ዝግጅት” አልነበረም ምክንያቱም ሰዎችን ማገልገል ያስፈልገው ነበር፤ ለእርሱ ጸሎት ሕይወቱ ነበር። አንድ ሁኔታ በተከሰተ ቁጥር መንፈሳዊ ብቃትን ለማግኘት በድንገት ራሱን ማግለል አያስፈልገውም ነበር። እርሱ ሁልጊዜም በውስጡ የአብን መገኘት እና ኃይል እየተገነዘበ፣ በመንፈስ ተሞልቶ ይኖር ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን 5፥18 ላይ ያስተላለፈው ግንዛቤ ይህ ነው። “በመንፈስ ተሞሉ” የሚለው አገላለጽ በግሪክ ቋንቋ ዘወትር እና በቀጣይነት የመሞላትን ሃሳብ ይዛል። ይህ የአንድ ጊዜ ተሞክሮ ወይም አልፎ አልፎ የሚከሰት ክስተት አይደለም። የሕይወት መንገድ ነው። አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስ ሐዋርያት በመንፈስ ተሞልተው አንድ ነገር እንዳደረጉ በሚናገርባቸው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ክፍሎችን በተሳሳተ መንገድ ተረድተዋል። ለምሳሌ የሐዋርያት ሥራ 4፥8 ሲናገር፣ “በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው…” ይላል። ይህ ማለት ጴጥሮስ በአንድ ወቅት ባዶ ነበር እናም በድንገተኛ ሁኔታ ምክንያት በድንገት በመንፈስ ተሞላ ማለት አይደለም። በፍጹም አይደለም። ሐዋርያት ይኖሩ የነበረው ቀጣይነት ባለው የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ እና ሙላት ስር ነበር። በየዕለቱ ሕይወታቸው ለእርሱ የተገዛ ነበር። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የሚፈልገው ሕይወት ይህ ነው። ዛሬ በመንፈሳዊ ሁኔታ ስትታገሉ ውላችሁ ከዚያ ደግሞ ነገ ለማገገም እንድትሞክሩ አይፈልግም። እርሱ እናንተ ዘወትር በመንፈስ የምትቀጣጠሉ፣ ለምሪቱ ሁልጊዜ ንቁ የሆናችሁ፣ ሁልጊዜም በእምነት፣ በጥበብ፣ በኃይል እና በመለኮታዊ ንቃተ-ህሊና የተሞላችሁ እንድትሆኑ ይፈልጋል። ዘወትር ያለማቋረጥ በመንፈስ የተሞላችሁ ስትሆኑ፣ ተግዳሮቶች በሚነሱ ጊዜ አትሸበሩም። ከመንፈሳዊ የብርታት እና የገዢነት ስፍራ ሆናችሁ ምላሽን ትሰጣላችሁ። እንዴት ነው ይህንን ቀጣይነት ያለው ሙላት የምታስጠብቁት? ከቃሉ ጋር ባለ ኅብረት፣ በልሳኖች በመጸለይ፣ በአምልኮ፣ እና በየቀኑ ራሳችሁን በንቃት ለመንፈስ ቅዱስ በማስገዛት ነው። ዘወትር በእርሱ ተጽዕኖ ስር ለመኖር ምኞታችሁ ይሁን። በክርስቶስ ያለው ከፍተኛ ሕይወት ይህ ነው፦ ዘላቂ የሆነ የድል፣ የኃይል እና ከጌታ ጋር የማይቋረጥ ኅብረት ያለው ሕይወት። ሃሌሉያ! ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ በሕይወቴ ውስጥ ስላለው የመንፈስ ቅዱስ በረከት እና አገልግሎት አመሰግንሃለሁ። ከአንተ ጋር በቋሚ ኅብረት ውስጥ በመራመድ፣ እንዲሁም ጥበብህን፣ ልህቀትህን እና ኃይልህን በመግለጥ፣ ዘወትር በመንፈስ ተሞልቼ እኖራለሁ። ሕይወቴ በክብርህ የተቀጣጠለ ነው፣ ሁልጊዜም ከድል ስፍራ ሆኜ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Sunday 13th, September 2026 እሁድ ፥ መስከረም 3  2018 ዓ.ም. እኛ በፍጹም አንደርቅም ▬▬▬▬▬▬▬ “በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።” (ዮሐንስ 7፥38)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ አንድ ሰው በአንድ ወቅት ለጌታ በትጋት ስትሰሩ፣ ስታገለግሉት እና ለእርሱ ነገሮችን ስታደርጉ ልክ እንደ ነዳጅ ማቃጠል ነው ብሎ ነበር። እንዳትደክሙ መጠንቀቅ አለባችሁ። ስለዚህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደገና መሞላት ወይም መታደስ ያስፈልጋችኋል ይላሉ። ይህ የስሜት ህዋሳት እውቀት ነው። ጥሩ ይመስላል ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት የሚሉት ያንን አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ በ2ኛ ቆሮንቶስ 4፥16 ላይ፣ “ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።” በማለት እንደማንደክም፤ ይልቁንም ጥንካሬአችን ከቀን ወደ ቀን እንደሚታደስ በተለየ መልኩ ይነግረናል። ስታገለግሉ፣ ከእናንተ ውስጥ ምን ያህል ኃይል ቢወጣም ምንም ለውጥ አያመጣም፤ ያለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ እንደገና ትታደሳላችሁ! ጌታ ኢየሱስን ተመልከቱ፤ የደም መፍሰስ የነበረባት ሴት ስትነካው እርሱም በ (ሉቃስ 8፥46) ላይ፣ “…ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና…” በማለት ሲናገር፣ እርሱ በኃይል ጎደልኩ ወይም ኃይል አጠረኝ ማለቱ አልነበረም። ጌታ በመንፈስ የተሞላ ነበር፤ እርሱም በፍጹም የማይደርቀው የኃይል ምንጭ ነው። እናንተም መንፈስ ቅዱስን ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ያላችሁ እውነታ ይህ ነው። በዮሐንስ 7፥38 ላይ፣ “በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል…” የሚለውን የጌታን ቃል አስታውሱ። እርሱ ወንዞች ማለቱን ልብ በሉ፣ ጠብታዎች ወይም ውስን አቅርቦት አላለም፣ ወንዞች! ይህ ማለት የማያቋርጥ ፍሰት፣ ቀጣይነት ያለው መፍሰስ፣ የማያልቅ አቅርቦት ማለት ነው። በውስጣችሁ ያለው የመንፈስ ፍሰት መቼም አይደርቅም። እግዚአብሔር ለሕይወታችሁ ያለው እቅድ ይህ ነው። ዛሬ ተሞልታችሁ ነገ ባዶ እንድትሆኑ በፍጹም አላሰበም። ጠዋት ቢሆን፣ በቀትር እና በምሽት ቢሆን፣ የትም ብትሆኑ ወይም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ራሳችሁን ብታገኙ፣ ዘወትር በመንፈስ ተሞልታችሁ እንድትኖሩ ይፈልጋል። ይህ የማይቻል ቢሆን ኖሮ፣ ቃሉ በዚያ መንገድ እንድንኖር መመሪያ አይሰጠንም ነበር። ዛሬ ስለዚህ ነገር ንቁ ሁኑ። የምትናገሩት እያንዳንዱ ቃል እና የምታደርጉት እያንዳንዱ ድርጊት በእናንተ ውስጥ እና በእናንተ በኩል ከሚሠራው ከመንፈስ ቅዱስ የሚመነጭ መሆኑን ልብ በሉ። ጌታ ኢየሱስ በ (ዮሐንስ 6፥63) ላይ፣ “…እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” በማለት ተናግሯል። የእናንተም ሕይወት እንዲሁ ነው። ቃላቶቻችሁ ሕይወትን፣ ጸጋን፣ ጥበብን፣ እና ኃይልን ያስተላልፋሉ፤ በጸጋ እና በጽድቅ የተሞሉ ናቸው። የሕይወት ውኃ ወንዞች ከውስጣችሁ ያለማቋረጥ ይፈስሳሉ። ሃሌሉያ! ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ በሕይወቴ ውስጥ ስላለው ሁልጊዜ ስለሚፈስሰው የመንፈስ ቅዱስ መገኘት እና አገልግሎት አመሰግንሃለሁ። የሕይወት ውሃ ወንዞች ያለማቋረጥ ከመንፈሴ ይፈስሳሉ፣ በሁሉም ስፍራ ሕይወትን፣ ጥበብን፣ ብርታትን እና ለውጥን ያመጣሉ። ዘወትር በመንፈስ ተሞልቼ እኖራለሁ፣ ቃላቶቼም ለሚሰሙኝ ሁሉ ጸጋን እና ጽድቅን ያገለግላሉ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ኤፌሶን 3:14-16 ኤፌሶን 5:18 ኢሳይያስ 58:11 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Monday 14th, September 2026 ሰኞ ፥ መስከረም 4  2018 ዓ.ም. እርሱ ራእያችሁን ያሰፋዋል ▬▬▬▬▬▬▬ “የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።” (1ኛ ሳሙኤል 10፥6)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ እግዚአብሔር ሳኦልን በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን በመረጠው ጊዜ፣ በዚያ መለኮታዊ ጥሪ ውስጥ መሥራት ከመጀመሩ በፊት በሕይወቱ ውስጥ ለውጥ መምጣት ነበረበት። ምንም እንኳን በእስራኤል ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ትከሻ ያለው፣ እና በአካል አስደናቂ ቢመስልም፣ ስለ ራሱ እና ስለ ሕይወት የነበረው ራእይ ጠባብ ነበር። የመጣው ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ታናሽ ከሆነችው ከብንያም ነገድ ስለነበረ፣ አስተሳሰቡ እነዚያን ገደቦች ያንጸባርቅ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ከኋላ ታሪኩ፣ ካደገበት ሁኔታ፣ ወይም ለራሱ ካለው ግምት በላይ ለሆነ ታላቅ ነገር መርጦት ነበር። ለዚህ ነው ነቢዩ ሳሙኤል፦ “የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል…እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።” በማለት ለእርሱ የተናገረው። ያ ለውጥ አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሔር የሳኦልን ራእይ ማስፋት፣ አቅሙን መጨመር እና በመለኮታዊ ዓላማ መሠረት እንዲያይ፣ እንዲረዳ እና እንዲሠራ ማብቃት ነበረበት። መንፈስ ቅዱስን ስትቀበሉ በሕይወትሁ ውስጥ ከሚሆኑት ነገር ውስጥ ይህ አንዱ ነው። የምታዩበትን መንገድ ይለውጠዋል። ራእያችሁን ያሰፋዋል። ሌሎች ሊረዱት የማይችሉትን እንድታስተውሉ እና ነገሮችን ከእግዚአብሔር እይታ አንጻር እንድትረዱ ያስችላችኋል። ይህ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ብዙ ሰዎች አንድን ነገር ሊመለከቱ ይችላሉ ነገር ግን በተመሳሳይ መንገድ ላይረዱት ይችላሉ። ሰዎች ባላቸው የራእይ፣ የመረዳት እና የማስተዋል ደረጃ ምክንያት ሕይወትን በተለያየ መንገድ ይተረጉማሉ። ነገር ግን በሕይወታችሁ ውስጥ ካሉት ውብ የመንፈስ ቅዱስ በረከቶች አንዱ ሌሎች በፍጹም ሊገነዘቧቸው የማይችሉትን እውነታዎች ዓይኖቻችሁን መክፈቱ ነው። ጥበብን፣ አርቆ ማስተዋልን፣ መረዳትን፣ እና መለኮታዊ ትርጓሜን ይሰጣችኋል። ምናልባት ራሳችሁን የተመለከታችሁት ከሰውኛ ችሎታችሁ፣ ከቤተሰባችሁ ታሪክ፣ ወይም አሁን ካላችሁበት ሁኔታ አንጻር ብቻ ሊሆን ይችላል። ራሳችሁን በተለየ መንገድ የምታዩበት ጊዜ አሁን ነው። መለኮታዊ ዓላማችሁን እንድትፈጽሙ እና የማይቻለውን፣ የማይታሰበውን፣ እና የማይገመተውን እንድታከናውኑ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሰጥቷችኋል እንዲሁም ታጥቃችኋል። አሁንም ቢሆን፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ እየሠራ ነው። ለበለጠ ተጽዕኖ፣ ለበለጠ ኃይል እና ለበለጠ ስኬት አቅማችሁን እያሳደገው ነው። በሕይወታችሁ ውስጥ ለእናንተ ካለው የእርሱ ዓላማ ጋር ከሚስማሙ ሰዎች፣ ዕድሎች፣ እና ሀብቶች ጋር እያገናኛችሁ ነው። ብዙዎች አከናውናችሁ ከፍፃሜ ያደረሳችሁትን ነገር እንዴት እንዲህ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሊሆን እንደቻለ ይደነቃሉ። ይህም በውስጣችሁ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ጥበብ እና ጸጋ ውጤት ነው። እርሱ ተልእኮውን የሚፈጽምበትን እና በምድር ላይ ጽድቁን የሚያጸናበትን መንገድ በእናንተ ውስጥ አግኝቷል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! ጸሎት   ════════ ውድ አባት ሆይ፣ በሕይወቴ ውስጥ ስላለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት አመሰግንሃለሁ። ራእዬ ሰፍቷል፣ መረዳቴ ጨምሯል፣ እናም እኔ ከእይታህ አንጻር አያለሁ። ለሕይወቴ ያለህን ዓላማ በክብር እየፈጸምኩኝ፣ ዛሬ በመለኮታዊ ጥበብ፣ በልህቀት፣ እና ከተፈጥ
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Wednesday 16th, September 2026 ረቡዕ ፥ መስከረም 6  2018 ዓ.ም. ከቃሉና ከመንፈሱ ተወልዳችኋል ▬▬▬▬▬▬▬ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ (1ኛ ጴጥሮስ 1፡23) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ክርስትና ሃይማኖት አይደለም። ለእሴት መሻሻል የሚሆን መዋቅር ወይም በሰው ጥረት የተሻለ ለመሆን የሚደረግ ሙከራ አይደለም። ይልቁንም፣ ሰው ክርስቶስን ሲቀበል በሰው መንፈስ ውስጥ የሚካሄድ ተጨባጭ ለውጥ የሆነ ከውስጥ ወደውጪ የሚገለጥ መለኮታዊ ውልደት ነው። ዳግመኛ በተወለዳችሁ ጊዜ የሆነውን በሙላት መረዳት ያስፈልጋችኋል። ከእግዚአብሔር መንፈስ የተወለዳችሁ እንጂ ቤተ-ክርስቲያንን ብቻ የተቀላቀላችሁ ወይም አዲስ የሕይወት ስልት ብቻ የተቀበላችሁ አይደላችሁም። እርሱ መለኮታዊ ሕይወትን ለእናንተ በማካፈል በአዲስ መገኛ፥ በአዲስ ባህሪና በአዲስ ማንነት አዲስ ፍጥረት አደረጋችሁ እንጂ ይህ ምልክት ወይም ምሳሌያዊ አይደለም። አካላዊ ውልደታችሁ የሰው ልጅ አድርጓችኋል፤ ነገር ግን በክርስቶስ የሆነው አዲስ ልደት የመለኮት ባህሪይ ተካፋይ አድርጓችኋል። በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ዳግመኛ የተወለድነው ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አንብበናል። እንዲሁም ያዕቆብ 1፡18 እንዲህ ይላል፡ "ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።" ይህም ከቃሉ በመወለዳችሁ ምክንያት፣ የቃሉ ሕይወት አላችሁ ማለት ነው። የክርስቶስ መልእክቶች ተብለን የተጠራነው በዚህ ተመሳሳይ ምክንያት ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 3፡3)። ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ 3፡6 ላይ፡ "ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።" አለ። ሐዋርያ ጳውሎስ በመንፈስ ይህን በሮሜ 8፡10-11 ላይ ፡ ምንም እንኳን ስጋችሁ በሀጢያት ምክንያት ለሞት የተገዛ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን መንፈሱ በጽድቅ ምክንያት ሕይወትን ይሰጠዋል በማለት የበለጠ ያብራራዋል። በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳችሁ ሕይወት ለስጋችሁ ደግሞ ሕይወትን የሚሰጥ ነው። ክርስትና በሰው ውስጥ የሚገለጥ መለኮታዊ ሕይወት የሆነው ከዚህ የተነሳ ነው። እንደ ኢየሱስ መለኮታዊ ናችሁ። እግዚአብሔር እንዲኖራችሁ የሚፈልገው አስተሳሰብ ይህ ነው። ከቃሉና ከመንፈሱ ተወልዳችኋል። በውስጣችሁ ያለው ሕይወት ከበሽታ፥ ከፍርሃት፥ ከውድቀት፥ ከድካምና ከጥፋት በላይ ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር የራሱ ሕይወት ነው። በዚህ መሰረት አስቡ፥ ተናገሩ እንዲሁም ኑሩ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! የእምነት አዋጅ ════════ ከቃሉና በጌታ መንፈስ ተወልጃለሁ። ስለዚህ መገኛዬ መለኮት ነው። መለኮተዊ መገኛዬንና በክርስቶስ ያለኝን ማንነት በንቃት በማሰብ እመላለሳለሁ። የእግዚአብሔር ሕይወት በእኔ ውስጥ እየሰራ ነው። እንዲሁም ጽድቁን፥ ልቀቱን፥ ድሉንና ክብሩን ዛሬ እገልጣለሁ፤ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት፡ የዮሐንስ ወንጌል 3፡3-6 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17 የዮሐንስ ወንጌል 1፡12-13 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ አካውንት ዝርዝሮችን ከታች ማግኘት ይችላሉ፤ -Rhapsody of Realities/ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Believers LoveWorld (
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Thursday 17th, September 2026 ሀሙስ ፥ መስከረም 7  2018 ዓ.ም. በእርሱ ተሟልተናል ▬▬▬▬▬▬▬ “ የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።” (ኤፌሶን 3:19)። 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ ቀደም ባለው ጥናታችን፣ ከእግዚአብሔር በመወለዳችን፣ እንደ ኢየሱስ መለኮታዊ መሆናችንን በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነጥብ አንስተናል። ይህ እውነት ባይሆን ኖሮ፣ ኢየሱስ የመጣበት ተልእኮ አልተሳካለትም ማለት ነው። እግዚአብሔር ግን የተባረከ ይሁንና፣ ይህ አልሆነም። “ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲበዛላቸውም መጥቻለሁ” ብሏል (ዮሐንስ 10:10)። ያ ሕይወት ለመንፈሳችሁ የተሰጠ የእግዚአብሔር ሕይወትና ተፈጥሮ ነው። በእግዚአብሔር ተሟልታችኋል! ይህ ብዙዎች ፈጽሞ ያልተረዱት እውነታ ነው።፣ እግዚአብሔር ፣ እንደ ተራ ሰዎች በሕይወት ስንታገል ከሰማይ ብቻ እንደሚረዳን ያህል፤ አሁንም ክርስትናን ከሩቅ ያስባሉ። ግን ያ ወንጌል አይደለም። ወንጌል እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አንድነት እንዳመጣችሁና በሱ ሙላት እንደሞላችሁ ነው።           ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ይህንን መገለጥ ተረድቷል። ለዚህም ነው፣ በኤፌሶን ምዕራፍ 3 ላይ፣ እግዚአብሔር እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን፣ በውስጣዊ ሰውነታቸው በመንፈሱ ኃይል እንዲጠነክሩ ያደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ላሉ ክርስቲያኖች የጸለየው። አስቀድሞ በዚህ እውነታ ውስጥ ይኖር ስለነበር፤ ይህንን ለራሱ አልጸለየም። ከዚያም ጸሎቱን በሚያስደምም መልኩ ይደመደመዋል፡- “... በእግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ” (ኤፌሶን 3፡19)። ይህ ባይቻል ኖሮ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለእኛ ባልተጻፈ ነበር። በእግዚአብሔር ሙላት ሁሉ እንዲሞሉ ፈልጎ ነበር። ዛሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁበት እውነታ ይህ ነው። እግዚአብሔር በራሱ፣ በመንፈሱ ያለ ልክ ሞልቶአችኋል (ዮሐንስ 3፡34)። በመለኮት ሙሉ በሙሉ የተሟላ፣ የእግዚአብሔርን ከፍተኛ ሸክም ይዛችኋል። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጌታ ኢየሱስ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ቆላስይስ 1፡19 “ሙላት ሁሉ በእርሱ እንዲኖር አብ ፈቅዶአልና” ይላል። ከዚያም ቆላስይስ 2፡9 “የበእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።” ይላል። እርሱ የመለኮትን ሙላት በሥጋ ተሸክሞአል። የሚቀጥለው ጥቅስ እንዲህ ይላል፣ “ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።” (ቆላስይስ 2:10)። በዮሐንስ 20:21 ላይ “...አባቴ እንደላከኝ እንዲሁ እልካችኋለሁ” ብሏል። እግዚአብሔር ኢየሱስን በራሱ ሞልቶ ወደ ዓለም ላከው። ከዚህ ያነሰ ነገር አላካችሁም። መለኮታዊ ልህቀት፣ ክብር፣ ጥበብና ኃይል በእናንተ ውስጥ አለ። ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ አላችሁ (2 ጴጥሮስ 1:3)። እወቁትና በዚሁ መሠረት ኑሩ። ጸሎት ════════ ውድ አባት ሆይ፣ ከአንተ ጋር አንድ ስላደረግኸኝና በሙላትህ ስለሞላኸኝ አመሰግናለሁ። በክርስቶስ ባለኝ የመለኮታዊ አጀማመር፣ ተፈጥሮና ማንነት ንቃተ ህሊና እመላለሳለሁ። ጥበብህ፣ ችሎታህ፣ ልህቀትህና ክብርህ ዛሬ በእኔ ውስጥና በእኔ በኩል ተገልጠዋል። በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት ቆላስይስ 2:9-10 ዮሐንስ 10:10 2 ጴጥሮስ 1:3-4 👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Friday 18th, September 2026 አርብ ፥ መስከረም 8  2018 ዓ.ም. ከሀጢያት-ነፃ እና ከሞት-ነፃ ▬▬▬▬▬▬▬ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና (ሮሜ 8:1-2) 👤 ፓስተር ክሪስ        ════════ የክርስቲያን ሕይወት በክርስቶስ ውስጥ የሆነ የፍፁም ነፃነት ሕይወት ነው። ዳግመኛ በተወለዳችሁበት ጊዜ፣ በሀጢያትና በሞት ላይ ወደምትገዙበት አዲስ የመኖር አለም እንድትመጡ ተደርጋችኋል። ሐዋርያ ጳውሎስ በሮሜ 8፡1-2 ላይ የሚገልጠው ይህንን ነው። ልዩነቱን አስተውሉ፡ በክርስቶስ የሆነ ሰው እንደ ስጋ ፈቃድ መመላለሱ ቀርቶ እንደ መንፈስ ፈቃድ ይመላለሳል። ለምን? መልሱ በሁለተኛው ጥቅስ ላይ አለ፡ አሁን አዲስ ህግ በውስጡ እየሰራ ነው፡ "በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ" ይህ ሕግ ከሞትና ከሀጢያት ሕግ ነፃ አውጥቷችኋል። የሐዋርያ ጳውሎስ "አርነት አውጥቶኛል" የሚለው አገላለፅ ከሆነ ነገር ነፃ ከመውጣት ብቻ የጠለቀ ነው። የመለየትን ሃሳብ ይሸከማል፤ ይህም ከሀጢያትና ከሞት ግዛትና ተፅእኖ ሙሉ በሙሉ መለየት ነው። ቃል በቃል ከሀጢያት-ነፃ እና ከሞት-ነፃ ናችሁ ማለት ነው። ይህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊረዳ የሚገባው አስፈላጊ እውነት ነው። ብዙዎች አሁንም ተፈጥሯዊ ሰውን በሚገዙት ተመሳሳይ ገደቦች፥ ፍርሃቶች፥ ጥፋትና ሞት ተጠቂ ሊሆኑ የሚችሉ አድርገው ራሳችሁን ያስባሉ። ነገር ግን ቃሉ የሚለው በተቃራኒው ነው። በወንጌል ወደ ጽድቅ፥ ወደ ሕይወትና ያለመጥፋት አለም እንድትመጡ ተደርጋችኋል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡9-19 ጌታ ኢየሱስ ያደረገውን ይነግረናል፡ "ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና... እርሱ ሞትን ሽሮአልና... በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።" አሁን በውስጣችሁ ያለው ሕይወት የክርስቶስ ትንሳኤ ሕይወት ነው። በሀጢያት፥ በጨለማ፥ በበሽታ፥ በፍርሃት፥ በውድቀትና በሞት ላይ የበላይ ነው። ከሀጢያትና ከሞት ባርነት በታች እንዳለ ሰው በጭራሽ ማሰብ፥ ማውራትና ማድረግ የሌለባችሁ በዚህ ምክንያት ነው። በውስጣችሁ ያለው የእግዚአብሔር ሕይወት የራሱ የሀጢያት የለሽነትና የሞት የለሽነት ባህሪዎች አሉት! ይህን በንቃት በማሰብ ተመላለሱ። በየትኛውም አይነት መልክ ክስን፥ ሽንፈትን፥ ኩነኔን ወይም ሞትን ማስተናገድን አትፍቀዱ። እናንተ ከሀጢያት-ነፃ እና ከሞት-ነፃ ክልል የሆነው የሌላ አለም ናችሁ። ሃለሌያ! ጸሎት   ════════ ውድ አባት ሆይ፤ ከሀጢያት-ነፃ እና ከሞት-ነፃ ስላደረገኝ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለው የሕይወት መንፈስ ሕግ አመሰግንሃለሁ። የዘላለም ሕይወትን፥ ድልን፥ መግዛትንና ጽድቅን በንቃት በማሰብ እመላለሳለሁ። ፍርሃት፥ ኩነኔ፥ በሽታና ሞት በእኔ ዘንድ ስፍራ የላቸውም፤ በኢየሱስ ስም። አሜን። ለተጨማሪ ጥናት፡ ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡1-2 የዮሐንስ ወንጌል 5፡24 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡14  👤 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24፥14) ለራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ሕትመት ዘርዎን ለመዝራት እንዲመችዎ፣ የባንክ አካውንት ዝርዝሮችን ከታች ማግኘት ይችላሉ፤ -Rhapsody of Realities/ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Believers LoveWorld (ROR) 1000466669826 አዋሽ ባንክ Believers Loveworld Publishin
L
Love world
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫 (Amharic) Saturday 19th, September 2026 ቅዳሜ ፥ መስከረም 9  2018 ዓ.ም. የተገለጠው መለኮታዊ መተካካት ▬▬▬▬▬▬▬ “እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው” (2 ቆሮንቶስ  5 :21 ) ። 👤 ፓስተር ክሪስ        ═══════ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መለኮታዊውን ልውውጥ የሚገልጥ ነው። እናንተ የእርሱን ቦታ ትወስዱ ዘንድ ጌታ ኢየሱስ የእናንተን ቦታ ወስዷል። የክርስትና ኃይል፣ ቀናነት እና ውበት ይህ ነው። እግዚአብሔር ሰውን እራስህን አድን ወይም ወደ ፅድቅ ለመምጣት መሥራት አለብህ አላለውም። ይልቁንስ፣ ኢየሱስን ለሰው ዘር ሁሉ ምትክ ነው ያደረገው። የመግቢያ ጥቅሳችን የሚለው፥ “ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው” ከዚያም በጥቅሱ ማጠቃለያ  እግዚአብሔር ለምን ይህን እንዳደረገ እንዲህ ብሎ ይነግረናል፥ እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን! ኢየሱስ ፈፅሞ ኀጢአት አልሰራም፣ በሰይጣን ተፅዕኖ ውስጥ ፈፅሞ አልወደቀም። ይህም ሆኖ ግን፣ እኛ ጻድቅ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር እርሱን ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው። ይህ ነው ታላቁ መተካካት። ቋንቋውን በጥንቃቄ አስተውሉ። ጻድቅ ለመሆን መሞከር አለብን አይልም ነገር ግን በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተደርገናል ነው የሚለው። ኢየሱስን በተቀበላችሁበት ቅፅበት፣ ይህ የእናንተ እውነታ ሆኗል። ጽድቅ የጸጋ ስጦታ ሆኖ ለመንፈሳችሁ ተሰጥቷችኋል። ስለ ብልፅግናችሁም ተመሳሳይ የሆነ እውነት በ 2 ቆሮንቶስ 8:9 ላይ ይታያል። እንዲህ ይላል፥“የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ” (2 ቆሮንቶስ  8 :9 )። በድጋሚ እዚህ ጋር ያለውንም መተካካት አስተውሉ። እናንተ በብልፅግና፣ በእግዚአብሔር መንግስት በረከቶች እና አቅርቦቶች ሁሉ ትኖሩ ዘንድ እርሱ የእናንተን የድህነት ቦታ ወሰደ። ይህ መሰረተ ሃሳብ እንደ ትንቢት አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ዘመን ታይቷል ይህም የሆነው የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ላይ በማመጻቸው ምክንያት በመርዘኛ እባቦች በተነደፉ ጊዜ ነው። ጌታ ሙሴን የነሃስ እባብ እንዲሰራ እና በምሰሶ ላይ እንዲሰቅለው አዞት ነበር። ከዛም ጌታ እንዲህ ብሎ አወጀ ወደ ተሰቀለው የነሃስ እባብ የሚያይ ሁሉ ይኖራል (ዘኁልቁ 21:8-9)። እግዚአብሔር እንዴት ቀላል አድርጎላቸው እንደነበር አስተውሉ። ፈውሳቸውን እንዲቀበሉ መታገል፣ መንከባለል ወይም ሥራ መስራት አለባቸው አላለም ጌታ። በቀላሉ ያላቸው “ተመልከቱ እና ኑሩ” ነው። አንዳንዶች ይህማ በጣም ቀላል ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ ሆኖም እንደዚህ የሆነው ከሞት ይድኑ ዘንድ እግዚአብሔር በነፃ ያቀረበላቸው እድል ስለነበር ነው። ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ፣ ከዘላለም ሞት መዳን፣ ጽድቅ፣ ፈውስ እና የዘለዓለም ሕይወት የሚገኘው ወደ ኢየሱስ በእምነት በማየት ነው። ሥራው አስቀድሞ ተሰርቷል። አስፈላጊው መስዋዕት ተከፍሏል። የእናንተ ኀላፊነት ማመን እና መቀበል ብቻ ነው። ኤፌሶን  2 :8 -9  እንዲህ ይላል፥ “በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም::” ክርስትናን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የሚደረግ የሰው ጥረት ነው ብላችሁ ፈፅሞ እንዳታስቡ። ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ የእናንተን ቦታ ወስዷል። አሁን በክርስቶስ፣ ጽድቅን፣ ሕይወት
Archive by month
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog