English
Open in Telegram
ብብርሃናችን 【 نــورنـا 】

ብርሃናችን 【 نــورنـا 】

@Our_light · channel · indexed since 2026-10-01
632subscribers
1 396posts in the index
𝒔
𝒔𝒖𝒎𝒆𝒚𝒂🤎
Reply◽️ኸውፍ ልብን ከውድቀት የሚጠብቅ ድንቅ ጋሻ! "ኸውፍ" ወይም አላህን መፍራት ስንል ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ? ብዙዎቻችን ፍርሃትን ስናስብ ከአደጋ ወይም ከሚያስፈራ ፍጡር መሸሽን እናስባለን። ነገር ግን አላህን መፍራት ከሌሎች ፍርሃቶች ሁሉ የተለየ ውብ ጥበብ ነው። ሌላን ነገር ሲፈሩ ከእሱ ይሸሻሉ፤ አላህን ሲፈሩ ግን ወደ እሱ ይሸሻሉ! ~ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦ ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና። [ሱረቱ አዝ-ዛሪያት 51፡
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ወደ አላህ የምትጓዘውን አማኝ ልብ በአስደናቂ ምሳሌ ሲያስቀምጡ እንዲህ ይላሉ፦ "ልብ ወደ አላህ በምትበር ወፍ ይመሰላል፤ 'መሐባ' (አላህን መውደድ) ራሷ ሲሆን፣ 'ኸውፍ' እና 'ረጃእ' ደግሞ ሁለቱ ክንፎቿ ናቸው። ራሷና ሁለቱ ክንፎቿ ሰላም ሲሆኑ ወፏ በጥሩ ሁኔታ ትበራለች፤ አንደኛው ክንፍ ከተቆረጠ ግን ወፏ መብረር አትችልም። ሁለቱም ክንፎች ከተቆረጡ ደግሞ ወፏ ለአዳኝ መጫወቻ ትሆናለች።"  የኸውፍ  ሁለተኛው ክንፍ እና ማሟያ የሆነውን "ረጃእ" የሚለውን ርዕስ በቀጣይ ክፍል እንድንመለከት ትፈልጋላቹ❔
323 ·
S
sυmεγα sτυdεητ
رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْوَهَّابُ (እነሱም ይላሉ)፡- «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፡፡ ከአንተ ዘንድ የኾነን ችሮታም ለኛ ስጠን፡፡ አንተ በጣም ለጋስ ነህና፡፡» 3÷8
2 · 289 ·
أحلام 🤍
ሐሰነል_በስሪይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ  : - «ሙዕሚን ዱንያ ላይ ልክ እንደ እንግዳ ነው፣ ስታዋርደው አይተክዝ ፣ በሷ ለመከበር አይፎካከር። እሱም የራሱ ጉዳይ አለው፣ ሰዎችም የራሳቸው ጉዳይ አላቸው።» 📚 ۞ الـغــربــاء للأجـري【9】۞
223 ·
Replyታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ወደ አላህ የምትጓዘውን አማኝ ልብ በአስደናቂ ምሳሌ ሲያስቀምጡ እንዲህ ይላሉ፦ "ልብ ወደ አላህ በምትበር ወፍ ይመሰላል፤ 'መሐባ' (አላህን መውደድ) ራሷ ሲሆን፣ 'ኸውፍ' እና 'ረጃእ' ደግሞ ሁለቱ ክንፎቿ ናቸው። ራሷና ሁለቱ ክንፎቿ ሰላም ሲሆኑ ወፏ በጥሩ ሁኔታ ትበራለች፤ አንደኛው ክንፍ ከተቆረጠ ግን ወፏ መብረር አትችልም። ሁለቱም ክንፎች ከተቆረጡ ደግሞ ወፏ ለአዳኝ መጫወቻ ትሆናለች።"  የኸውፍ  ሁለተኛው ክ
◻️ረጃእ ረጃእ ማለት የኃጢአታችን ተራራ የቱንም ያህል ቢገዝፍ፣ የአላህ ይቅርታና እዝነት ግን ከዚያ በላይ መሆኑን በሙሉ ልብ ማመን ነው። 🔸እውነተኛው "ረጃእ" ምንድን ነው? በኢስላም ውስጥ ረጃእ ማለት ዝም ብሎ ተቀምጦ "አላህ ይምረኛል" ብሎ መመኘት አይደለም። እውነተኛ ተስፋ ማለት የተቻለንን ያህል መልካም ስራ ለመስራት እየጣርን፣ ስህተት ስንሰራ ወዲያውኑ ወደ አላህ እየተመለስን እና በእሱ ቸርነት ላይ ፍፁም እምነት ማሳደር ነው። ኸውፍ ከጥፋት መንገድ ሲያስቆመን፣ ረጃእ ደግሞ ወደ ጀነት እንድንሮጥ ኃይል የሚሰጠን ሞተር ነው። ይህ የተስፋ መንገድ በፈጣሪያችን አንደበት እና በነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ተስፋ ለቆረጡ ልቦች ያደረገው ጥሪ በቁርዓን ውስጥ ካሉ በጣም ልብ የሚነኩ አንቀጾች አንዱ ነው፦ በላቸው፦ «እነዚያ በነፍሶቻቸው ላይ ወሰን ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነውና።» [ሱረቱ አዝ-ዙመር፡ 53] ይህ አንቀጽ አላህ አሁንም "ባሮቼ" ብሎ እንደሚጠራን እና የይቅርታው በር ሁሌም ክፍት እንደሆነ ያረጋግጣል። የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህ እንዲህ ማለቱን አስተላልፈውልናል:- አላህ እንዲህ ይላል፦ «የአዳም ልጅ ሆይ! በለመንከኝና በተስፋ በጠበቅኸኝ ጊዜ፣ በውስጥህ ያለውን (ወንጀል) ሁሉ ምንም ሳልገደድ እምርልሃለሁ። የአዳም ልጅ ሆይ! ወንጀልህ የሰማይ ደመናዎችን እንኳ ቢነካ፣ ከዚያም ምሕረትን ብትጠይቀኝ እምርልሃለሁ።» [ሱነን አት-ቲርሚዚ 3540] የቀደሙት ደጋግ አባቶቻችን በአላህ እዝነት ላይ የነበራቸውን ፍፁም ተስፋ (ረጃእ) ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፦ ❑ ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ረሒመሁላህ)፦ በህመም አልጋ ላይ ተኝተው ሊሞቱ ሲቃረቡ ለልጃቸው እንዲህ አሉት፦ "ልጄ ሆይ! አላህ ለባሮቹ ያዘጋጃቸውን የእዝነትና የይቅርታ ሀዲሶችን አንብብልኝ፤ ልቤ በአላህ ላይ በጥሩ ተስፋና በረጃእ ሆና ወደ እሱ እንድትመለስ እፈልጋለሁ።" ❑ ሱፍያን አሥ-ሠውሪ (ረሒመሁላህ)፦ የአላህን እዝነት ስፋት ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፦ "በትንሳኤ ቀን የፍርዴ ስራ በወላጆቼ እጅ እንዲሆን አልፈልግም፤ ምክንያቱም አላህ ለእኔ ከወላጆቼ በላይ እጅግ አዛኝና ሩኅሩኅ እንደሆነ አውቃለሁ።" ❑ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ)፦ እንዲህ ይላሉ፦ "በትንሳኤ ቀን አላህ ሰዎችን የሚምርበት ትልቅ ምሕረት ያደርጋል፤ ያኔ በልቡ ውስጥ አንዳች እምነት (ኢማን) ያለው ሰው ሁሉ ከአላህ እዝነት ተስፋ አይቆርጥም።" 🔹የረጃእ ጥቅሞች በህይወታችን ➦ከጭንቀት ያድናል፦  ያለፈው ህይወታችን የቱንም ያህል የጨለመ ቢሆን፣ አዲስ ነጭ ገጽ ከፍተን ወደ አላህ እንድንመለስ ብርሃን ይሆንናል። ➦የአምልኮ ጣዕምን ይሰጣል፦  አላህ ሰላታችንን እና ዱዓችንን እንደሚቀበለን በተስፋ ስንጠብቅ፣ የምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ ደስታን ይፈጥሩልናል። ➦የልብ ሚዛንን ይጠብቃል፦  ከዚህ ቀደም እንዳየነው፣ በልባችን ውስጥ ኸውፍ (ፍርሃት) ወንጀል እንዳንሰራ አጥር ሲሆንን፣ ረጃእ (ተስፋ) ደግሞ ወድቀን እንዳንቀር ያነሳናል። ልባችሁ ሲሰበር እና መንገዱ ሲጠብባችሁ ያስታውሱ! እናንተ የምትለምኑት ጌታ ስህተትን ይቅር ማለት የማይሰለቸውን አር-ራሕማን ነው። ኃጢአታችሁ ምንም ያህል ትልቅ ቢሆን፣ የአላህ እዝነት ደግሞ ከሁሉም በላይ ታላቅ ነው። ዛሬውኑ የወደቀውን ልብባችሁን ይዛችሁ ወደ እሱ የተስፋ ማዕዘን ሩጡ! ወደ አላህ እንሽሽ!✨ فِي أَمَانِ اللَّهِ 🤗✨
226 ·
Reply﴿وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ﴾ (ሱረቱ አጥ-ጠላቅ 65:3) "በአላህ የሚመካ (ጉዳዩን ለእርሱ የሚያስረክብ) ሰው፣ አላህ በቂው ነው።" ተወኩል (التوكل) ማለት ምክንያቶችን አድርጎ ውጤቱን ለአላህ መተው ነው። እንጂ ምንም ሳያደርጉ መጠበቅ አይደለም። አላህ እዚህ አያ ውስጥ ታላቅ ቃል ገብቷል፦ "فَهُوَ حَسْبُهُ" "እርሱ (አላህ) በቂው ነው።" ማለትም፦ በጭንቀትህ ጊዜ ይበቃሃል፤ በድካምህ ጊዜ ይበረታሃል፤
﴿إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ﴾ በእርግጥ ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፤ መንገድንም ያሳየኛል።" ይህ አያ በቁርአን ውስጥ ከሚገኙ በጣም ኃይለኛ የተስፋ እና የተወኩል መልእክቶች አንዱ ነው። ይህን ቃል ማን ተናገረው? ይህን ቃል የተናገሩት ነቢዩ ሙሳ (ዐለይሂስ ሰላም) ናቸው። ከፊታቸው ቀይ ባሕር ነበር፤ ከኋላቸው ደግሞ ፈርዖን እና ሠራዊቱ በፍጥነት ይከተሏቸው ነበር። በዚያ ጊዜ በነቢዩ ሙሳ ዙሪያ የነበሩት ሰዎች፦ > ﴿إِنَّا لَمُدْرَكُونَ﴾ "በእርግጥ ይደርሱብናል!" ብለው ፈሩ፣ ተስፋም ቆረጡ። ነገር ግን ሙሳ (ዐ.ሰ.) የተመለከቱት ችግሩን ሳይሆን የችግሩን ፈጣሪ ጌታ ነበር። ስለዚህ በሙሉ እርግጠኝነት፦ > ﴿كَلَّا إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ﴾ "በፍጹም አይደለም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፤ መንገድን ያሳየኛል።" አሉ። ከዚያም አላህ ባሕሩን ከፍሎ ያልታሰበ መውጫ መንገድ ከፈተላቸው። ከዚህ አያ የምንማረው 1. ሙእሚን በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን በአላህ ላይ ይተማመናል ሰዎቹ ባሕሩን እና ሠራዊቱን ብቻ አዩ። ሙሳ (ዐ.ሰ.) ግን የአላህን ኃይል አዩ። እኛም በሕይወታችን ችግሮች ሲበዙ፣ በሮች ሁሉ የተዘጉ ሲመስሉ፣ አላህ አዲስ በር ሊከፍት እንደሚችል ማመን አለብን። 2. አላህ ያልጠበቅነውን መውጫ ይፈጥራል ሙሳ (ዐ.ሰ.) ባሕሩ እንደሚከፈል አያውቁም ነበር። ነገር ግን አላህ መንገድ እንደሚያሳያቸው አውቀው ነበር። እኛም ዛሬ የምንደክምበት ችግር ምናልባት መፍትሔው ከማናስበው ቦታ ሊመጣ ይችላል። 3. "ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው" የሚለው የእምነት ጫፍ ነው ሰዎች ሊተዉህ ይችላሉ፣ ወዳጆች ሊርቁህ ይችላሉ፣ ድጋፎች ሊቋረጡ ይችላሉ። ነገር ግን አላህ ባሪያውን አይተውም። ስለዚህ ሙሳ (ዐ.ሰ.) "ሠራዊት አለኝ" አላሉም፤ "መንገዱን አውቃለሁ" አላሉም። "ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው" አሉ። ልብ የሚነካ ነፀብራቅ አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ባሕር ከፊትህ ትቆማለች፤ ችግሮችም እንደ ፈርዖን ከኋላህ ይከተሉሃል። በዚያ ጊዜ የሙእሚን ቃል ይህ ነው፦ ﴿إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ﴾ "መንገዱን ላላይ እችላለሁ፤ ግን መንገዱን የሚያውቀውን ጌታ አውቃለሁ። ስለዚህ አልፈራም፣ ተስፋም አልቆርጥም።"
268 ·
ብ
ተስፋ🥀🥀 ይህ ቃል ስናየው ቀለል ያለ ይመስላል ነገር ግን ትልቅ ቱርጉም አለው፣የደከመን የሚያበረታ ፣አንገት የደፋን የሚያቀና።ባጠቃላይ ለኛ ደካሞች ባሪያ ለያንዳንዱ ወንጀል ላይ ላለ ለሰው ልጅ ሁሉ ይህ ቃል ትልቅ ትርጉም አለው ። እና አኛም ለወንጀላችን እጅ ሳንሰጥ ምህረት እንጠይቅ ። ወደ አለማቱ መሪ ወደ ሆነው አላህ እንመለስ ወደሱም እንቅረብ ።
248 ·
sυmεγα sτυdεητ
Voice message
IMG_5316.m4a · 367 KB · click to show
215 ·
S
Photo
ታላቅ የፓናል ውይይት ... በቲክቶክ መድረክ ! ! ! ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምናሰማባቸውን መድረኮች አብዝቶ ለፈጠረው አምላክ ምስጋና ይገባ። ታሪካዊውን የፓናል ውይይት በመስጂድ ልናከናውን ቀጠሮ የያዝን ቢሆንም የመሰብሰብ እና የመወያየት መብታችንን በመንፈግ እንደተከለከልን የሚታወስ ነው። ሆኖም እነርሱ ከለከሉን ማለት ዝም ብለን እንቀመጣለን ማለት አይደለም። በሰፊው፣ ሁሉም በያለበት ሆኖ ይታደም ዘንድ በተመቻቸ ሁኔታ፤ ርዕሶቹም ሰፋ ብለው፤ በቅርቡ በቲክቶክ ታላቅ የፓናል ውይይት የሚኖረን ይሆናል። የክብር እንግዶቻችን እንዳሉ ሆነው፤ መምጣት ሳይችሉ ቀርተው ሲቆጩ የነበሩት ባሉበት ሆነው እንዲሳተፉ በሚያስችል መድረክ፤ በውጭ ሀገርም ሆነው በሀገር ውስጥ ያሉ ተማሪዎች እና መላው ሕዝበ ሙስሊም የሚሳተፍ ይሆናል። እስከዚያው መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ። የቲክቶክ ገፃችንን https://www.tiktok.com/@aaumsu?_r=1&_t=ZS-97D9UHuTcGO በመግባት Follow አድርጉ። የሚታፈን ድምፅ የለም ! ለበዳዮች እጁን የሚሰጥ ትውልድም አይኖርም !! ጥያቄ አለን ... ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! @aaumsu
273 ·
كوني أوآبة
ስንቅ ክፍል 1 🤲ከድንገተኛ ሞት በአላህ እንጠበቃለን! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ مِنْ أماراتِ الساعَةِ أنْ يَظْهَرَ موتُ الْفَجْأَةِ﴾ “ከትንሳዔ መድረስ ምልክቶች ውስጥ ድንገተኛ ሞት መብዛት ነው።” 📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2296    https://t.me/Our_light
351 ·
☀️ኒቃብ ውስጥ ያለውን ሰላም ሴቶች ቢያቁት ያለ ኒቃብ ምትሄድ አንዲትም ሴት በዚች ምድር ላይ ባልኖረ ነበር!! ☀️ላደረጉት ፅናትን ላላደረጉት ደግሞ ማድረግን ይወፍቃቸው ሀቁንም ለመጠበቅ ያብቃን🤲
304 ·
أ
Video
11.0 MB
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: 1]👌 #ቁርኣን
293 ·
ٱحلام ✨
ልቤ ሲደክም አካሌም ሲዚል ውስጤ ቢጨነቅ በዝቶብኝ ወንጀል አንተን ጠራለውእያልኩኝ መውላ አግዘኝ ያረብ ማናለኝ ሌላ።😔😔 📝 Hania
264 ·
የአሹራ ቀን ፆም! ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾ “የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 1162 በሌላ ሀዲስ ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾ “የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 1134 ➲ ዘጠነኛው ቀን እሮብ 17/10/2018 ➲ አስረኛው ቀን ሀሙስ 18/10/2018 አላህ በሰላም አድርሶን ከሚፆሙ ያድርገን
2 · 406 ·
ٱ
እላሂ🥹 ምስጋና  ይድረስህ አንተ የኔ ጌታ የዋልክልኝ ነገር ቡዙ ነው ውለታ ከምን  ልጀምርው ጌታዬ መውላና ልነካካው እንጂ መች ተፅፎ  ያልቅና ብዕሬን አንስቼ ለመክተብ ስሞክር አዕምሮ  እና ልቤ ጀመሩ ክርክር በአዕምሮዬ ልክ አሰብኩኝ  እስከ ጥግ ቀጠለ መናገር ጀመረ እሱም ወግ ፈደል አገጣጥሞ በቃላት አስፍሮ የውስጡንም ሀሳብ ሳይደብቅም ደፍሮ ትንሽ ፈገግ አለ በሀሳብ ተጉዞ እኔን ሊያስተውሰኝ ውብ ቃለትን ይዞ ይለኝም ጀመረ አንቺ ልጅ አስተውሺ ፈገግ የእያልኩለት እኔም አልኩት እሺ ረህማኑ ሲወድሽ ብዙ አድሎሻል አካል ሳያጓድል ሙሉ አድረጎሻል ገንዘብ ማይገዛውን ድኑንም ሰቶሻል ታድያ ይሄ ሁሉ ለማን ይመስልሻል ? ልቤም አከታትሎ ሀሳቡን ደግፎ ምንም ሳያቅማማ በደስታ ከንፎ አው እውነትህን ነው ብዕር የማይገልፀው ቃል የታጣለት ነው የዋለልኝ ንዕማው አጅብ ሱብሀናአላህ የካሊቁ እዝነት እኔ አጥፍ ሁኜ አያልቅ የሱ ምህረት እንዲ አይነት ጌታ ከየትስ ይገኛል ከእናት በላይ ነው የእሱማ ይለያል ለባርያው አዛኝ ነው ያስገረማል ፍቅሩ ሁሉንም አዋቂ ከላይ እስከ ስሩ ቅርብ ነው ለኔማ ከሩህ ከጀሰድ ሁሌ አስታዋሼ ነውና ሰመድ እላሂ ስምህ እረጋታ አለው አፍን አልፎ ሄዶ ልብ ላይ ሚነግሰው ሰኪናንን የሚሰጥ ጀሊል ያንተ ስም ነው።     ✍Hania
2 · 422 ·
أ
أحلام 🤍
የሶላት ሶፉችን መሙላት ማስተካከል ያለው ደረጃ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿من سدَّ فُرجةً رفعه اللهُ بها درجةً، وبنى له بيتًا في الجنَّةِ﴾ “የሶላት ሶፉችን (ክፍተቶችን) የሚሞላ (በማስተካከል የሚቆም) አላህ በሱ ተግባሩ ደረጃውን ከፍ ያደርገዋል። በጀነት ውስጥም ቤትን ይገነባለታል።” [ሶሂህ አትርጊብ፡ 505]
1 · 463 ·
كوني أوآبة
የቀኑ መልዕክት 1 ስህተቶች ብልህ ያደርጉናል ህመሞች ደግሞ ጠንካራ      ያደርጉናል
254 ·
ስንቅ ክፍል 2 🌺 ከተመሰገኑ ተግባራቶች〽️ ረሱል (✨) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اللهُ في عونِ العبدِ ما كان العبدُ في عونِ أخيهِ﴾ “አላህ ባሪያውን በመርዳት ላይ ነው። ባሪያው ወንድሙን እስከረዳ ድረስ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2699
298 ·
𝓗
አዝነንም ተደስተንም፣ አግኝተንም አጥተንም፣ ከስረንም አትርፈንም ... ሁሌም አልሐምዱ ሊላህ!🌸
1 · 316 ·
ብርሃናችን 【 نــورنـا 】
Audio
የገበያ ላይ ዳዕዋ.mp3 · 4.8 MB · click to show
ለአላህ ብዬ ወድሃለሁ .... ኡስታዝ ሳዳት ከማል ( حفظك الله)
247 ·
ك
خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا "ለአላህ ትሁቶች (በፍርሃትና በመታዘዝ የሚገዙ) ሆነው፣ በአላህ አንቀጾች ትንሽ የዱንያ ጥቅምን አይለውጡም።" እውነተኛ ሙእሚን ልቡ ለአላህ ይታገሣል(እሱን በመታዘዝ እንዲሁም ከወንጀል በመጠበቅ )፤ የአላህን ቃል እና ዲኑን በገንዘብ፣ በዝና፣ በሥልጣን ወይም በማንኛውም የዱንያ ጥቅም አይለውጥም። ለእርሱ የአላህ ውዴታ ከማንኛውም የሚያልፍ የዱንያ ጥቅም የበለጠ ክቡር ነው። 🤲🏽አላህ ከእነዚህ ባሮቹ ያድርገን። https://t.me/Our_light
274 ·
𝓗
𝓗𝓲𝓵𝔀𝓪🤍
ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ
1 · 275 ·
𝓗
𝓗𝓲𝓵𝔀𝓪🤍
Link
click to show
📢 የምስራች!የክረምቱን እረፍት በቁርአን ብርሃን ልናድምቀው ለራስዎ እና ለልጆችዎ ታላቅ የዕድል በር ከፍተናል! ~የክረምት ወቅት ሲገባ፣ ብዙዎቻችን 'ዝናብ ነው🌧፣ ቅዝቃዜ ነው፣ የዕረፍት ጊዜዬ፣ቁርአን ቤት ሩቅ ጭንቅንቅ ነው፣ ልጆቼን ለመከታተል አመቺ አይደለም' በሚሉ ሀሳቦች ተታለን ጊዜን በከንቱ እናባክናለን። የትምህርት ቤት በር ዝግ ነው ብሎ ዝም ብሎ መቀመጥ ይብቃ! ይህን ውድ የክረምት እረፍት ለዲንዎ ዕውቀትና ለልብዎ ብርሃን ለመጠቀም ትልቅ ዕድል አለዎት! ይህንንም በማሰብ «ኑሩ ረይሀኒል ቁርአን» መድረሳ የክረምት ወቅት ፈተና ሳይሆን የዕድል ምንጭ መሆን አለበት ብሎ ዝግጅቱን ጨርሶ እኛን በመጠበቅ ላይ ነው። • 🏠 ባሉበት ሆነው፣ ከቤትዎ ሳይወጡ፣ ላናንተ ምቹ በሆነ ሰዓት እርሶንም ልጆቾንም ✔📖ቃኢዳ ለጀማሪዎች ✔📖ቁርአን ነዘር ✔📖ቁርአን ሂፍዝ በ online በተመቻቸ መልኩ መቅራት ይችላሉ!  ∴ኑ!  የክረምት ጊዜያችንን በቁርአን እናሳምር። ለመመዝገብና ለበለጠ መረጃ: – 📞+251984264583 📱የቴሌግራም ቻናላችን [https://t.me/nurureyhanil  ] ኑሩ ረይሀኒል ቁርአን መድረሳ — የምንግዜም የቁርአን አጋሮ!
294 ·
بنت إسلام
Aselamualyekum werahemetulhi weberekatehu እስልምና ሴትን ልጅ የጨቆነ ይመስልሀል?? ስም ማጥፋት ነው ምንም ነገርየለም ለሴቶች ስራ ከእስልምና በቀር ዋጋ የሰጠ 🥹 ለምሳሌ "ጀነት ከእናት እግር ስር ነች"🌺" ሴት ልጅ ወላጆቿን ከእሳት ትጠብቃላች" 🥰"ሚስት የኢማንን ግማሽ ትሞላለች 🫀 እስልምና ለሴቶች በጣም ለገስ ነው ።🍂"ለመጀመሪያ ጊዜ የሰለመችው ሴት ናት "✨"የመጀመሪያም ሸሂድ ሴት ናት" 🥹 እና እስልምና ለኛ እንዲህ ከሆነልን የታዘዝነውን መተግበር የተከለከልነውን መከልከል እንዴት ያቅተናል 😔😔 አላህን እንፍራ ያጀመአ 🥰🥰🥰
269 ·
𝓗
🎀ሰዉ የሪዝቁን እንጂ ምርጫዉን ኖሮ አያዉቅም የሚረዝቀን ደግሞ አላህ ነዉ 🍀አላህ ደግሞ ከማንም ከምንም በላይ ለኛ የሚጠቅመንን ያዉቃል ያረብ ሚጠቅመንን ሪዝቅ ስጠን አኼራ ዱንያችንም የሚያሳምርልንል ሪዝቅ ስጠን!! አሚን በሉ🫰🤲
309 ·
ብ
ብርሃናችን 【 نــورنـا 】
Photo
صلّوا على هذا النبي؛ ~ إنَّ الله ﷻ أمرنا أن نصلي على النبي ﴿ﷺ﴾ حيث يقول: إِنَّ ٱللَّـهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا ﴿٣٣:٥٦﴾ اللهم صلِّ وسلم على النبي المصطفى وعلى خير خلق الله المجتبى وعلى آله وصحبه ومن اقتفى! https://t.me/Our_light https://t.me/Our_light
174 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count