┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #አይናፋሯ_ሊና ".
✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
. በ @tibeb_islaam የቀረበ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚
┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_አንድ {❶}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷
...ኢላሂ አንቺ ልጅ መጥረጊያውን አስቀምጪ እኔ ጥረጊልኝ አላልኩሽም ሊና ቶሎ ብለሽ ወደ ትምህርት ቤት ሂጂ ትምህርት ቤት ትምህርት ከተጀመረ ድፍን አንድ አምስት ቀን ሆነው እንደበፊቱ አንድ ወር ሲሞላሽ ለመሄድ አስበሽ ነው አይሆንም እኔ እኮ ሁሌ ሲጀመር ወር ሞልቶሽ እየሄድሽ እንዴት ከክፍል አልፎ ከትምህርት ቤቱ አንደኛ እንደምትወጪ ነው የሚገርመኝ እኮ ወይስ እኔ የማላውቀው ዘመድ አለን እ እስኪ ንገሪኝ ሊና
🧕 እህ እማዬ በደንብ እኮ አይጀመርም ለዛ ነው
ሊና ዝም በይ አሁን እኮ አስረ አንደኛ ክፍል ነው የምትሆኚው አይሆንም በቃ ዛሬ ሂጂ በጠዋቱ አታስጪሂኝ ሰላም እንዋል
ሊናም የእናቷ ንግግር ግራ እያጋባት እማ እኔ አሁን ብሄድ ተማሪዎቹ እራሱ ምን ሆና ነው ይላሉ በዛ ላይ ፋኢዛ ትምህርት ቤት ለቃለች አየሽ እማ አሁን ማንም ጓደኛ የለኝም ከማንም ጋር አልሆንም
ሊና እስከመቼ እንዲህ ሆነሽ ጓደኛ ቢሄድ ጓደኛ ይመጣል ቆይ ምናለ ባሁኑ አመት እንኳን ባታሳዝኚኝ ተይ ሊና እስከመቼ አንደትሽን ደፍተሽ አታበላት አታጠጣት ትበድላታለች ምታስብይኝ ከሰውስጋር ለምን አትጋባቢም ኧረ ተይ ሊናዬ አለች ሊናም በራሷ ባህሪ እምባ እያነቃት ወደ ክፍሏ ገብታ ቦርሳዋ ውስጥ አምስት ደብተሮችን ከታ ዩኒፎርሟን አርጋ እናቷን ለማስደሰት ስትል ከቤት ወጣች ቁርሷን እንኳን አልበላችም ተናዳለች አመቱን ሙሉ እንዴት ነው ምሆነው ማንም ጓደኛ የለኝም ከማንም ጋር አልግባባም አላውቅም ብቻ
ሊና ጀሚል ትባላለች በአሁኑ አመት የአስራአንደኛ ክፍል ተማሪ ናት አይናፋሯ ሊና በሚባለው ቅፅል ስሟ የምትጠራው ሊና የተወለደችው አዲስ አበባ ነው የምትኖረውም እዚሁ ነው ሊና በጣም ዝምተኛ አይናፋርና ጎበዝ ተማሪ ናት ለዛም ነው አይናፏሯ ሊና የሚል መጠሪያ የተሰጣት ሊና ለእናት እና ለአባቷ የመጀመሪያም የመጨረሻም ልጅ ናት አንድ ታናሽ እህት ነበረቻት እንደተወለደች ነው ወደ አሄራ የሄደችው
ሊና
በሀሳብ እንደተወጠረች ትምርህርት ቤት ደረሰች ሰአቱ ስለረፈደ ተማሪዎች ወደየክፍላቸው ገብተዋል እየፈራች ፎቁን ወጥታ አዲስ ከተመደበችበት ክፍል ገባች ተማሪዎች ይንጫጫሉ አስተማሪ እንደሌለ ተረዳች አንድ ልጅ ተነስታ እኔ አላምንም አይናፏሯ ሊና ትምህርት በተጀመረ በሳምንቱ መጣሽ አላምንም ሀሀሀሀ አቤት ሴት ሊና በትምሀርትቤታችን ውስጥ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከወኝዶች ቆንጆ ተብሎ በተፈረጀው በኢብሮ ምክናያት ነዋ ኢብሮ ጉድህን እያየህ ነው ስትል አንድ ልጅ ላይ አፈጠጠች...
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_ሁለት {❷} ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬
ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@tibeb_islaam
@tibeb_islaam
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤