ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
S

SEBA COMPUTER 💻

сообщение · 2023-08-11 17:59 UTC
I
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ ". #ጤዛዉ_ፍቅሬ ". ✍ፀሐፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ . በ @tibeb_islaam የቀረበ . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ━━━━━━━━❪❐❫━━━━━━━━ ╔════•| ✿ |•════╗ #ክፍል_ሁለት (➋) ╚════•| ✿ |•════╝ የሃቢብ ስድብ በየቀኑ ቢብስም ፎዚ ግን ቁብ ሳሰጠዉ እሱን ከማፍቀር አላስቆማትም ነበር፡፡ እየሰደባት ትወደዋለች፡፡ ከምንም በላይ የማትረሳዉ ነገር ቢኖር... አንድ ቀን ከስራ መመለሻዋ ሰአት ደርሶ ወደ ቤት እየሄደች ስልኳ ከቦርሳዋ ዉስጥ ሆኖ ይጠራ ነበር፡፡ ፎዚ አልሰማችዉም፡፡ በምትሄድበት መንገድ ዳር የነበረዉ ጫጫታና ሁካታ የስልኩን ድምፅ ሊያወጣዉ ስላልቻለ ፎዚ ስልኩን አንስታ ጥሪዉን ሳታስተናግድ ቀረች፡፡ ቤቷ እንደደረሰች ሃገር አማን - ቤቴ ሰላም ብላ የቤቷን የበር ቁልፍ ከፖርሳዋ አዉጥታ ስትሞክር እንዳጋጣሚ ሆኖ በሩ ክፍት ነበር፡፡ ሀቢብ ቀድሞ እንደገባ ስለተረዳች ሀሳቧን ሁሉ በሩ ላይ ጥላ ባሏን በአንዲስ መንፈስ ለመገናኘት በሙሉ ፈገግታና በሚያስቀና ደስታ እየተፍነከነከች የበሩን እጄታ ይዛ ከፈት ስታደርገዉ ያላሰበችዉ ነገር ገጠማት፡፡ ... ጣቶቹ ከብረት የጠነከሩ የሚመስሉ ሸካራ መዳፍ የፎዚ ፊት ላይ አረፈ "ጯ...." አይኗ እስኪሸፈን፤ የጉንጯ ቆዳ እስኪገፈፍ በጥፊ መታት፡፡ በድጋሜ 'ጯ...'፡፡ ሀቢብ ነበር፡፡ "ለምንድን ነዉ ስልክ ያላነሳሽዉ?" በሚል ጥያቄ አንባረቀባት፡፡ ፎዚ አይኖቿን በግድ ከገለጠቻቸዉ በኃላ በፍርክርክ መዳፎች ጥፊ የቆሰለዉን ጉንጯን በእጆቿ እያሻሸች፤ ለማልቀስ እየዳዳት አይኖቿ በመቅፅብት እምባ አዝለዉ በለሆሳስ ድምፅ . " ደዉለህ ነበር እንዴ?" አለችዉ፡፡ ሁሌም በመጥፎ ይጠረጥራት ኑሯልና... "አሃ.. አንቺ ከማንም ወንድ ጋር እየዘለልሽ አዉቀሽ ያላነሳሽዉን ልትዋሺ ነዉ??" ብሎ ደም ማንባት በቀራቸዉን አይኖቹ አፈጠጠባት፡፡ አይኖቹ ቀልተዉ ነበር አይገልፃቸዉም፡፡ ደም የለበሱ፤ በርበሬ የጎረሱ መስለዋል፡፡ ሞባይሏን ለማዉጣት እጇን ወደ ፖርሳዋ እየሰደደች "ወላሂ አልዋሸሁህም" አለችዉ፡፡ "ዝምም በይ .. ቀጣፊ!" ብሎ ጥፊዉን ሊደግመዉ ቃጣዉ፡፡ . ... ፎዚያ በሃቢብ ከቦክስ ያላነሰ ጥፊ ጉንጯ ላይ ጠባሳ የቀረ ይመስል ይሄን ክስተት አረሳችዉም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ፍቅሩ በልጦ፤ መዉደዷ ገጦ ይበልጥ ነበርና ሁሉንም ይሁን ብላ በተቀበለችበት፤ ፀቡንም ነገሩንም ወደ ፍቅር ለዉጣ ትዳሯን አቆይታለች፡፡ . ...የሀቢብን መጥፎ ጥርጣሬ ለማስወገድ ስትል የድሮዉ ፍቅሩን ቢመልሰዉ ብላ ከምትሰራበት መስሪያ ቤት የመልቀቂያ ደብዳቤ እንኳ ሳታስገባ ለቀቀች፡፡ ምክንያቷ ደግሞ በተደጋጋሚ ከመስሪያ ቤት ወንዶች ጋር ትቀብጫለሽ 'እኔን ቀይረሽኛል' እያለ መዉጫ መግቢያ ሲያሳጣት፤ በቤቷ ዉስጥ ሰላም ሲነሳት 'ወጥቼ እንድሰራ ካልፈለክና ካላስደሰተህ ቤቴ እዉላለሁ' ብላዉ ባሏን ለመንከባከብ ለሀቢብ ካላት ሙሃባ የተነሳ ስራዋን እርግፍ አድርጋ ትታ ቤት ዉላለች፡፡ . ... ይሄን ዱላና ተዳጋጋሚ የሆነዉ ስድቡ (ቀጣፊ...ዉሸታም...) ሳይከብዳት ዛሬ የተነፈሳት "እርካሽ" ያላት 'ርካሽ' ቃል ፎዚን እያነፋረቀ ያስለቅሳታል፡፡ 'እኔ ነኝ?... እኮ እኔ?... እኔ ነኝ እርካሿ?" እያለች ታላዝናለች፡፡ የኔ ዉድ የሚለዉ ጥሪዉ ባንዴ ተወግዶ፤ የፍቅር ቃላቶች እንደ ስደተኛ ርቆ ተሰዶ ቤታቸዉ የፀብ አዉድማ ሁኗል፡፡ ሰሞኑን ያመጣዉ አዲስ ፀባይ ደግሞ ፎዚን እየተፈታተናትና ትዳር እንዲያንገሻግሻት ሊያደርጋት ምነንም አልቀሯትም፡፡ ለሱ ብላ ስራ እንዳቆመች፤ በፀብ የጠለሸዉን ትዳር ወደ ፍቅር ለመቀየር እየተጋች ባለበት ወቅት...."እኔ ማመጣዉን ተቀምጦ መብላት አይከብድሽም?" ይላት ጀምሯል፡፡ ምንም አትመልስለትም ይልቁንስ በሱ መጥፎ ንግግርና ፀያፍ ተግባሩ ብትማረርም ሀቢብን መንከባከቧ ከእለት ወደ እለት ጨምሯል፡፡ ከስራ መመለሻዉ ሰአት ሲደርስ በሚያማምሩ ልብሶች ተሽቀርቅራ፤ እሱን በሚያማልሉ ነገሮች ተዉባ፤ እሱዉ በመረጠዉ ሽቶ ጠረኗን አዉዳ ትጠብቀዋለች፡፡ ...".ሀቢቢ እንኳን ደህና መጣህልኝ!" ብላ እቅፏ ዉስጥ ልታስገባዉ እጇን ስትዘረጋ፤ የዘረጋችዉን እጇቿን በእጆቹ ገፍትሮና አመናቅሮ . ..."አንቺማ በደህና እንድመለስ አትፈልጊም ነበር. ያዉ ተመለስኩ" ብሎ ነገሩን ይጀምረዋል፡፡ አሁንም ግን... ነገሩን ወደ ነገር ቀይራ ቤቱን በፀብ ቦንብ ማጋይት ስለማትፈልግ በሙሉ ፈገግታ ፈግጋ ወደ'ሱ ጠጋ እያለች... ..." ሀቢቢ ንፍቅ ብለኸኛል!" ትለዋለች፡፡እንደምታፈቅረዉ ያዉቃል፡፡ ነገር ግን እሱ ጸቡን ስለሚፈልገዉ የሷ የፍቅር ቃል አይረታዉም፡፡ "ሀቢቢ...፤ የኔ ማር...፤ የኔ ፍቅር...፤ ዉዴ." እያለች የምትጠራዉ ነገር አይዋጥለትም፡፡ አጠገቡ ከተቀመጠች በኃላ ፀጉሩን እያሻሸች "ምን ሁነህብኝ ነዉ ዉዴ?" አለችዉ፡፡ እጆቿን ከፀጉሩ ላይ እያነሳ "ለምን ትነኪኛለሽ?" ብሎ አይኑን ጎለጎለባት፡፡ ፎዚ ይብስ እንዳይናደድ ብላ ዝም አለችዉ፡፡ ብቻ በስስት እያየችዉ አይኖቿን አይኖቹ ላይ ታንከባልላቸዋል፡፡ ግንባሩ ተጨማዶ ተኮሳትሮና ተቆጥቶ ከተቀመጠበት ምንጥቅ ብሎ ተመናጭቆ ተነሳና ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ፡፡ በአስተያየቷ ተናዷል፡፡ የፍቅሯ ሃያልነት አፉን ዘጋዉ እንጂ በስስት የምታዬዉን ሚስቱን "ምን ታፈጫለሽ?" ማለትም አስቦ ነበር፡.............ይቀጥላል ፡ ፡ ╔════•| ✿ |•════╗ #ክፍል_ሦስት (➌) ይቀጥላል... ╚════•| ✿ |•════╝ ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን። ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @tibeb_islaam @tibeb_islaam ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

All messages on 11 August 2023 · Whole feed · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog