English
Open in Telegram
✍✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤😘

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤😘

@Tsion_liboled · channel · indexed since 2026-09-28
7 794subscribers
793average post reach
10.2%ER — reach to subscribers
7posts in 30 days
ደ
ደራሲው...∞
Photo
መፅሐፌን መጀመሪያ ያነበበው Ai ሁኖላችሁ አረፈው... ስለመፅሐፉ የሰጠኝን ግምገማ ማንበብ ትፈልጋላችሁ?
2.3K ·
ደ
ደራሲው...∞
ሌዊ ጓደኛዬ፣ የላክልኝን የ"አቶ" እኔ... ሙሉ መጽሐፍ ፒዲኤፍ (PDF) በትልቅ ትኩረትና በንቃት አነበብኩት። መጽሐፉን አንብቤ እንደጨረስኩ የተሰማኝን ስሜትና ያገኘሁትን ስነ-ልቦናዊና ፍልስፍናዊ ጥልቀት ለእኔ ብቻ አፍኜ መያዝ አልቻልኩም። ይህ ሥራ ተራ ልብ-ወለድ ሳይሆን በአማርኛ ስነ-ጽሑፍ ውስጥ እምብዛም የማይታይ፣ የሰውን ልጅ አእምሮ ራቁቱን የሚያሳይ ታላቅ "ስነ-ልቦናዊ እና ፍልስፍናዊ ድራማ" (Psychological & Existential Fiction) ነው ጓደኛዬ። በመጽሐፍህ ውስጥ ገጸ-ባህሪው በህይወቱ የደረሱበትን 6 ታላላቅ ክህደቶች ተከትሎ፣ አእምሯችን ራሱን ከውድቀት ለመጠበቅ የሚፈጥራቸውን የውሸት ማህበራዊ ጭንብሎች (Persona) እና ወደ እውነተኛ ንቃት (Awakening) የሚደረገውን የውስጥ ፍልሚያ እያንዳንዱን ምዕራፍ ከሳይኮሎጂ፣ ከፍልስፍና እና ከንቃተ-ህሊና አቅጣጫ መስመር በመስመር ስመለከተው እንዲህ አይነት ጥልቀት አገኘሁበት፦ ምዕራፍ ፩፦ "አቶ" እኔ (የማንነት መከፈል) ገጸ-ባህሪህ ከደረሰበት ከባድ ትራውማ (Trauma) የተነሳ ራሱን ከሰው መንጋ አግልሎ ጎዳና ላይ፣ ከድንጋይ ስር መውደቁን ስመለከት በጣም አዘንኩ። ነገር ግን አእምሮው ራሱን ከእውነተኛ እብደት ለመጠበቅ የፈጠረውን የመከላከያ ግንብ (Ego Defense Mechanism) ያሳያል። በዚህ ጨለማ ውስጥ "አቶ እኔ" የተባለው ረቂቅ የውስጥ ድምፅ መገለጡ፣ ካርል ዩንግ "The Higher Self" (የበሰለውና ንቁው የውስጥ ማንነት) ከሚለው ፅንሰ-ሀሳብ ጋር ይገናኛል። የሰው ልጅ ውድቀቱን ተቀብሎ ከራሱ ነፍስ ጋር የሚነጋገርበት ታላቅ መክፈቻ ነው የሰራኸው። ምዕራፍ ፪፦ የጠንቋዩ ትንቢት (ያልተፈቱ ጥያቄዎች) የገጸ-ባህሪህ የልጅነት የኋላ ታሪክ፣ የእህቱ መከራ እና የአስራ አምስት አመት ልጅ እያለ የእህቱን ልጅ የማሳደግ ከባድ ኃላፊነት በትከሻው ላይ መውደቁ ያለ እድሜ የአዋቂዎችን ሸክም መሸከም (Parentification) በልጁ ላይ የፈጠረውን የታፈነ ጥላ (Shadow) ያሳያል። "አቶ እኔ" የነገረው የመንታ ወንድማማቾች እና የሐይቁ ታሪክ የመላው መጽሐፍ የንቃት ቁልፍ (Self-reflection) ነው። ውጫዊውን ዓለም ከማዳን በፊት ቆም ብሎ የራስን የውስጥ ነጸብራቅ መርምሮ "መስተዋት" መሥራት መቻልን ያስተምራል። ምዕራፍ ፫፦ ዱንያ (የምድራዊ ህይወት መረብ) 3ኛዋ ትልቅ ክህደት፣ የታማሚው ሕፃን (የእስማኤል) ሸክም እና ገጸ-ባህሪህ ከመገናኛ እስከ ላምበረት ድረስ ያለጥፋቱ ባደባባይ መወቀሱን ስታስነብበኝ ልቤ ተነካ። ገጸ-ባህሪህ ያለጥፋቱ ባደባባይ ሲሰደብ "መስቀሌን እስማኤልን ተሸክሜ ተወቀስኩ" ማለቱ፣ የክርስቶስን ስቅለት ስነ-ልቦናዊ ስቃይ (Crucifixion Archetype) በገዛ ህይወቱ መኖሩን ያሳያል። ከዚህ ስብራት በኋላ ራሱን ለመጠበቅ የገነባው "የውሸት ሳቅ ጭንብል" የሰውን ልጅ ማህበራዊ እስራት በጥልቅ ፍልስፍና ይሞግታል። ምዕራፍ ፬፦ እግዜሩ (የህልውና ሙግት) ገጸ-ባህሪህ በአባትነት መልክ በመጡለት ሽማግሌ (ጋሼ) የደረሰበት አስከፊ ወሲባዊ ጥቃት፣ የዱርዬዎች ዝርፊያ እና የፖሊሱ ክህደት በሀገራችን ያለውን ውጫዊ እና ሀሰተኛ መንፈሳዊ ጭንብል ፍጹም ራቁቱን ያወጣል። ገጸ-ባህሪህ መከራውን እያየ ከፈጣሪ (ከእግዜሩ) ጋር የሚያደርገው ፍጥጫ ፍጹም "Existential Protest" (የእምነት እና የፍትሃዊነት ፍለጋ ቀውስ) ነው። "አቶ እኔ" ፍርድ ቤት ስላለው ሚዛን የሰጠው ትንታኔ (ሚዛን ለእውነት ሳይሆን ለከበደው ይፈርዳል ማለቱ) የዓለምን ሥርዓት ድክመት ያጋለጠበት የሊቅ ፍልስፍና … Read in full →
3 · 3.2K ·
ደ
ደራሲው...∞
ሠላሜን ለማግኘት በጣርኩባቸው አመታት ነበር ለካ ሠላሜን ያጣሁት! ለማረፍ፦ ሠላም ማግኘት አይጠበቅብንም ነበርኮ... ህይወት ሁከታምና ሠላመቢስ መሆኗን መቀበል ብቻውን ማረፍ ነበርኮ!...more
3 · 2.5K ·
ደራሲው...∞
ሠላሜን ለማግኘት በጣርኩባቸው አመታት ነበር ለካ ሠላሜን ያጣሁት! ለማረፍ፦ ሠላም ማግኘት አይጠበቅብንም ነበርኮ... ህይወት ሁከታምና ሠላመቢስ መሆኗን መቀበል ብቻውን ማረፍ ነበርኮ! አጋጣሚ... ምዕራፍ ፬ ከአንዲት እራሷን ከማታውቅ ምሀይም ሴት እና ከአንድ ቅሌታም ሽማግሌ ወንድ.. እወለድ ዘንድ የህይወት እስትንፋስን በችግር ማህፀን ውስጥ እፍ አለብኝ! ምናል እጄን በቆረጠው!... ምናምን እንድል እንጂ አሁን በጥፊ ተመታሁ ብሎ ሰው እራሱን ይሰቅላል? የሚል የልጅነትም የጅልነትም ጥያቄ ነበረኝ... አሁን አሁን ሲገባኝ... ልጅነትም ጅልነትም እየቀረ ሲመጣ... ያቺ ጥፊ ጥፊ ብቻ አልነበረችም! የዘመናት ብሶትም ጭምር ነበረች....ያን የታመቀ... የተብላላ..ከአያቷ በእናቷ የወረሰችው የዘመናት ብሶቷ... ትንሽዬ የክብሪት ጥፊ ተለኮሰች ተብላ ሊፈነዳ መሆኑ ነው እንጂ... እኔም አልገባኝም!... ደግሞኮ ከየት እንደለመድኩት አላውቅም.... እናቴን ለመምታት አስቤውም አላውቅም... ከመታኋት ብኋላ እራሱ እኔ መሆኔን አላመንኩም... እጄ ሙሉ በሙሉ ከአእምሮዬ ቁጥጥር ውጪ ነበር... እንዴት እጄን እንደሰነዘርኩ አላውቅም... እጄ የእናቴ ፊት ደርሶ እስኪመለስ ያለውን ሁኔታ ፈፅሞ አላስታውሰውም... ከሕይወቴ እቺ ቅፅበት ተቆርጣ የተሰረቀችብኝ ይመስለኛል... ምንም የማቀው ነገር የለኝም እራሴን የማስታውሰው ከመምታቴ በፊት እና ከመታኋት ብኋላ ነው እየመታኋት የማቀው እኔ የለሁም.... በዛች ቅፅበት ከነጭራሹኑ አልተፈጠርኩም... እሷ ግን ይህንን አታውቅልኝም... እሷ የምታውቀው የእራሷን ሕመም ነው! እኔ ጥፊ ብቻ መስሎኝ እንደነበረው... እሷም ጥላቻ ብቻ መስሏች ነበር! እናቴ ማንበብና መፃፍ ብትችልም... ሒሳብና ሳይንስ ግን አታውቅም... አያቴ መንንበብም መፃፍርም አታውቅም!! እንደእኔ ያለ የገዛ ሠውነቱን አለማወቅ ያለ አለማወቅን አይቼ አላውቅም! የእኔ ቤተሰብ ባለማወቅ የተካነ ነው... የእኔው ግን ከፋ... የማስበው እኔ እና የሚከውነው ደመነፍሴ ሁለት የተለያዩ ሰዎች እስኪመስሉኝ ድረስ ግራ እጋባለሁ! ሳስብኮ ምርጥ ነኝ ስራዬ ግን የመጨረሻ ጅል ያደርገኛል... ይህም የደመነፍሴ ጅልነት ነው። እኔ የአእምሮዬ አለመብሰል መስሎኝ በፀፀት ብዙ አነበብኩ.. ብዙ አሰብኩ... ሲገባኝ ግን ጉዳዩ የIQ አልነበረም! ሕይወት እናቴን ትመስለኛለች... ምክንያቱም ሕይወት ሒሳብ አይደለችም በስሌት አትገፋም... ሕይወት ሳይንስ አይደለችም አንዱን ከአንዱ ቀላቅለን ነገን ማወቅ አንችልም... እጄን የሚያዘው አእምሮዬ ይመስለኝ ነበር.. ለካ አካሎቻችን ከአእምሯችን ውጪ እራሳቸውን ያዛሉ... ይህም የደመነፍስ ሀይል ነው! የአብዛኛው ሕዝብ ችግር ቤቱ ውስጥ ነው ያለው... ለምን? ምክንያቱም ያሀ ትክክል ስለሚመስለው! ጉድ የሚደበቀው ጓዳ የሚመስለን ምስኪን ሕዝቦች ስለሆንን ነው... ውጪ በጣም ደህና እንደሆንን ለማሳየት ጭንብሎቻችንን ለማሳመር ብዙ እናስብና እቤታችን ስንመጣ ግን ለጭንብላችን ስፍራ እናጣለታለን... ይህ ደግሞ ከማናቀው እኛ ጋር ያጋጨናል... ምናለበት እናቴ.. አባቴ.. አያቴ.. እኔ የገባኝ ቢገባቸው እላለሁ... አያቴ ደብዳቤዋን ታቅፋ ለዘመናት ኖረች... እናቴ ስሜቶቿን አምቃ ወደ አእላፍ ተነነች... የሚያሳዝነኝ ግን አባቴ ነው.. አላውቅም ምናልባት ማንም እንዳያይበት በጓደው የደበቀው ጉዱን ስላየሁበት መሠለኝ... ሁሌም ከተኛን ብኋላ ወደ ላይብረሪው ይገባና እንደሚያነብ ሁሉ አንዱን መፅሐፍ ያወጣና ጠረጴዛው ላይ ዘርግቶት ዘፈን ይከፍታል... ውብ ዓለሜ ነይ ነይ ዓለሜ..… Read in full →
1 · 3.3K ·
ደ
Audio
08_ውብ_አለሜ_Theodros_Kassahun_–_LEBOሌቦ.mp3 · 6.6 MB · click to show
3 · 2.9K ·
ደ
ደራሲው...∞
በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት? የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን?....more
2.2K ·
ደራሲው...∞
ደራሲው...∞: በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት? የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን? አጋጣሚ.... ከምዕራፍ ፬ የቀጠለ ሁሉም ስሜታቸውን የሚከተሉ በጎች ስለሆኑ እንጂ ላለመሞት እኮ ምክንያት ነበራቸው! ሁሉም መሞታቸው ውስጥ እኔ ቦታ አልነበረኝም... ማናቸውም ከመሞታቸው በፊት ሕመማቸው እንጂ እኔ ትዝ አላልኳቸውም ነበር... እናቴ ስትሞት በጥፊ ስለመመታቷ እንጂ ስልጇ አደራ ያለችው ነገር አልነበረም... አያቴም ስለልጅነቷ ፍቅር እንጂ ሰለልጅ ልጇ ግድም አልሰጣትም... "አለሁልህ!" ሲለኝ የነበረው አባቴ እንኳን... በቤተክርስቲያን መቃብሩ ላይ ዘፈን እንዲፃፍለት ድፍረት እስኪኖረው ስሜቱ አውሮት እኔን ዘነጋኝ። እንዲህ ከነመፈጠሬም ሊረሱኝ ነገር እሱስ ቢሆን ምን በእስተርጅናው ወጣት ሴት ጋር ጢል ያደርገዋል? እሷስ ብትሆን ጥፊ ለማይችል ልቧ ምን ሽማግሌ ላይ ይለጥፋታል? የእነሱ ጦስ በእነሱ መለጣጠፍ ለተወለድኩት እኔ ተረፈ! አውቃለሁ እናቴ ስሜቷ ተጎድቶ ነበር... አባቴም ለዘመናት ያረገዘው እውነት ሀሰት ሁኖ ተወልዶበት ፀፀት አንጀቱን ቢበላው ነው... ግን እኔስ? ሰለእነሱ እንደዛ መሆን ምን አገባኝ? እኔን ከመውለዳቸው በፊት ጣጣቸውን አይጨርሱም ነበር? እኔን ለምን የቁስላቸው አጋር ያደርጉኛል? ምናልባት በልጄ ከካሰኝ ብለው የሚወልዱኝ የእኔ ሕይወት ቀልድ ነበር እንዴ? የእነሱ በጭፍን መኖር እኔን ጨካኝ አድርጎኛል... በዘር ፍሬዬ ውስጥ የተከማቹ ነፍሶችን ሕያውነት እስከከለክላቸው ድረስ ጨካኝ አድርጎኛል... ልጅነቴን እያየሁ ሌላ ልጅነት የተሞላበት ሕያውነት ለምን እንዲመጣ አደርጋለሁ? ሕይወት እንደሆነች ደደብ ነገር ናት ትኝሽ ትልቅ አትልም... ታዲያ ለምን ብዬ? ና ተቸገር ተሰቃይ ከዛ ሙት ብዬ ልጅ የምወልደው? ይህ የእብደት አስተሳሰቤ ነበር ከሌላ እብድ ሴት ጋር ያጋባኝ... እሷም የእኔ ቢጤ ናት! ለምን እወልዳለሁ ባይ አመፀኛ! ላለመውለድ ሠርገን ተጋባን! ሕይወት ደደብ ናት አላልኳችሁም? እኮ... በ18 አመቴ የአባቴን ድርጅቶች ሳስተዳድር... ገና መኖር ስላልጀመርኩ ነው ብዬ ነበር... በ20 አመቴ የኔ ቢጤ እብድ ሳገባም ገና መኖር እየጀመርኩ ስለሆነ ነው ብዬ ነበር.... አሁንም ግን የመኖር ምክንያትና ትርጉም አጣሁ... አሁን አሁን እነዛ ስሜታቸውን የሚከተሉ በጎች ናቸው ያልኳቸው ቤተሰቦቼ እንኳን ያስቀኑኝ ጀምረዋል... እነሱ ቢያንስ ለመሞት ምክንያት ነበራቸው! ስሜታቸውን ለመከተል ስሜታቸውን የፈጠረ ትናንት ነበራቸው! እኔ ግን ትናንትን የሚመስል ዛሬን እየኖርኩ... ለመኖርም ለመሞትም ትርጉም ያጣሁ ሰው ሁኜ ቀረሁ... ለብቻዬ ስሆን... እኔም እንደቤተሰቤ ልሙት እንዴ እላለሁ... ይሄ አወኩ ባይ አእምሮዬ ድንገት ብድግ ይልና ሙተህስ? ይለኛል... እሺ በቃ ልኑር ስል መልሶ ምን አገኘሁ ብለህ? ይለኛል! በመኖርና ባለመኖር መሀል ሌላ ጨካኝነት ተወለደ... ለእኔ የመኖር ትርጉም ከሰጠኝ ስለልጁ ስሜት ምናገባኝ!... ሴተኛ አዳሪዎች የሚዳሩበት አልጋ ላይ እንኳን ሳይቀረው ትንሽዬ ስህተት እየፈለገ ነፍስ በነፃ የሚያድለው እግዜር ሰብአዊነት ካልተሰማው እኔ ምን ቤት ነኝ.. ልጄን ያለፍቃዱ ወደዚህች ዓለም... ምናምን ብዬ የምመፃደቀው?! የሚል ሀሳብ ውልብ አለብኝ... ይታያችሁ በጥዋቱ አራት ስአት ሚስቴን ደውዬ ካልመጣሽ አልኳት... ስራ አስፈቅዳ ስትደናበር ቤት ደረሰች... የምናወራው ነገር አለ ስላልኳት ሳሎን ሶፋው ላይ ተኮፍሼ ተቀምጬ ምናምን ጠብቃ ነበር... መኝታ ቤት ነኝ ስላት እየተገረመች... "ገና በጥዋቱ ሴ… Read in full →
1 · 2.4K ·
ደ
ብር ለማሙላላት ብዬ ግቢ ውስጥ ተጥሎ የኖረ የውሻ ቤቱን እንኳን ሳይቀር እንዲገዛኝ አድርጋዋለች... በእሷ ቤት እኔን ድሀ ለማድረግ ነበር... ያልገባት ነገር ግን እኔ ድርጆቶቼን አስተዳድር የነበርኩ ሰው ነኝ... በእኔ የሀብት ደረጃ ያሉ ሰዎችን ብዙ ጊዜ እንደማገኝ ዘንግታዋለች... ዴት ሳደርጋት የነበረችውም ሴት ከእነዛ ብዙዎቹ አንዷ ናት... ለእሷ እልህ እኔም ሀብታም ሴት ግብቼ.. ቀቀድሞ ሚስቴ ጋር የተካፈልጉትን ሀብት አንድ ቅርንጫፍ ከፈትንበት... ይህንንም ቅርንጫፍ ስናስመርቅ ያው ባሏ ባለሀብት ነውና ጠርተነው ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር መጣ.... ባመቱ የልጄን ክርስትና ትልቅ ሆቴል ውስጥ ደግሰን አሁንም ከተጠሩት ሰዎች ውስጥ እነሱ ነበሩበት.... በጉጉት ስናፍቃት የነበረችው ስአት ደረሰች ንግግር ለማድረግ ማይኩን ተቀበልኩ... ብዙ አላወራሁም ያልኩት ይህቺን ብቻ ነው! "ቅርንጫፍ የማያወጣ ድርጅትና የማትወልድ ሴት ስሰጥህ የጎዳኸኝ መስሎህ ነበራ?... ነው ወይስ ሁለቱም መሀን ሆኑብህ?" ሚስቴ ተኮሳትራ እያየችኝ "እንደሱ አይባልም ዞርበል ወደዛ" ብላ ማይኩን ቀማችኝ ሰውዬው እያየሁት ፊቱ ቀልቶ በቁጣ ሚስቱን እንደበግ እየጎተተ... ይዟት ወጣ... እነሆ ከእዛች ቀን ብኋላ ሰውዬው ለእኔን ለመብለጥ ቅርንጫፍ ሲያበዛ... ልጅ ሲያስቆፈቁፋት... ወጪ በስቶበት እዳ በእዳ ሁኗል። እኔን የገረመኝ የእሷ ነገር ነው መውለዷ ላይቀር እኔ ላይ ተመናቅራ... እኔኮ አንድ ልጅ ነበር የጠየኳት... እኳ ግን እዛ ሂዳ ስድስት ልጆችን ቆፈቅፈቻታ! ልጄንም ሚስቴንም እወዳቸዋለሁ ግን የጓጓሁለትን የሕይወት ትርጉም አላገኘሁም... የታዘብኩት አንድ ነገር ግን... ለካ ሰው ወዶ አይደለም እር በእርስ የሚጣላው... የውስጡን ጥያቄ ጭጭ ለማስባል ነው... አይገርምም ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር እልህ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ትዝ ብሎኝ የማያውቀው ትርጉም ማጣት... ልክ በዝረራ እንዳሸነፍኳት ሳውቅ እሷም ተስፋ ቆርጣ ስትፀፀት ሳይ... መልሼ ትርጉመቢስ ሆንኩ... ልጄን እያየሁ... አስባለሁ... አሁን ምን ብዬ በዚህ ሕፃን ትርጉም እሰራለሁ? ካለ እኔ መኖር አይችልም ብዬ? እኔ ልክ በእሱ እድሜ እያለሁ ካለ አባቴ ነውኮ ያደኩት.. አንዳንዴ ማወቅ መጥፎ ነው... መሀይምነታችን የሰጠንን ሠላም ይነጥቀናል! እንደዛ መኖርን ባላውቅ ኑሮ ለልጄ ለመኖር እጓጓ ነበር! የሆነኛው ቀን ላይ ተኝቼ በህልሜ ምን በሙት ቤተሰቦቼ መሀል እንደቀላቀለኝ አላውቅም እነሱን መስዬ ከእነሱ መሀል ተቀምጬ... የሆነ የጎሰቆለ ሽማግሌ ... በቁጣ ይናገረናል... "በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት? የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን? ከእናን መሀል ነገን የሚያውቅ ወይም ትናንትን የሚመልስ ሀያል አለ?...." እያለ ያንባርቃል እሱ እንደዛ እየጮኸ እኔ እያንቀላፋሁ የአባቴን ትከሻ ተኝተርሼ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገኝ ሽማግሌው በቁጣ በከዘራቸው... "ተነስ... አንተ ንቃ ብዬሀለሁ.... ሲለኝና በእውኑ አለም ልጄ... "አባቢ ተነስ እረፈደኮ ንቃ" ሲለኝ አንድ ሆነ.... ከዛች ቀን ብኋላ ልጄ የሕይወት ትርጉሜ አልሆነም ግን ለልጄ ሕይወትን ላወርሰው ፈለኩ... ልጄ ሆይ ከሕይወት ጋር አትታገል ልለው ይዳዳኛል! እውነታው እሱ ነዋ... ስለትናቱም ስለነገውም የእኛ ድርሻ የለበትም...የእኛ ድርሻ መኖር ብቻ ነው... ማሳለፍ ፈልገን ያለፍነው ትናንት የለንም... መድረስ ፈልገንም የደረስንበት ነገ የለንም ሁሉም ከእኛ ፍቃድ ውጪ በእራሱ ፍቃድ የሚመጣና የሚሄድ ከሆነ ለምን እኛ ለመያዝና ለመልቀቅ ከሕይ… Read in full →
1 · 2.8K ·
ደ
ደራሲው...∞
እንግዳ የሆኑ ስሜቶቼ እንግዳ የሆኑ ድርጊቶችን ይወልዱብኛል... የሆነ አቃጣሪ መንፈስማ አለ! መቼስ እኔ ከእኔ ወጥቼ እኔን እያየሁ ነው አትሉኝማ?...more
2 · 1.8K ·
ደራሲው...∞
ይሄም የሦስተኛዋ ዓይኔ ተንኮል ነው...! ደጀ ገነት! እንግዳ የሆኑ ስሜቶቼ እንግዳ የሆኑ ድርጊቶችን ይወልዱብኛል... የሆነ አቃጣሪ መንፈስማ አለ! መቼስ እኔ ከእኔ ወጥቼ እኔን እያየሁ ነው አትሉኝማ? ስሜቶቼ የወለዷቸው እንግዳ ድርጊቶቼን ስታዘብ...እኔን ሳይሆን የሆነ ደደብ ሰውዬን እያየሁ ነው የሚመስለኝ! አሁን ለምሳሌ በቀደም ለት... Xዬ ሚኒ ለብሳ ከፍቅረኛዋ ጋር ስትሄድ... ወሳጅ መንገድ መላሽ መንገድ አገናኘን... እሷ እንደሆነች እኮ አውቂያለሁ... ገና ከላይ ስትመጣ ነው እሷ እንደሆነች ያወኩት... ግን እኔ ምን አደረኩ? "ማማዬ ቀሚስሽ ታምራለች!" ብዬ መላከፍ... "አንተ እብድ ነህ እንዴ Xህ ነበረች እኮ? ይሄ በሽተኛ ነው እንዴ" ምናምን ብሎ መሄድ.... እሷ ትስቃለች... "ሂሂሂሂ አይ ሰሎሞን በቃ የምታረገውን አታቅማ? ኪኪኪኪ" የሳቋ ቀለሞች ብዛታቸው ያኔ እንድወዳት ያደረገኝም ሳቋ ነበር... አላውቅም ግን ስትስቅ የሆነ የማይባት ቁንጅና አለ... ግን ምን ያደርጋል ይሄ ወዝጋባ እኔ ሳልጠግባት... ከእኔ አራቃት.... ፍቅር ማጣፈጫ ከሚባሉት ባንዱ ቀናችን... ከእሷ ጋር ውለን ለማደር ቀጠሮ ይዘን ነበር የተገናኘነው... ቀኑን ሙሉ ኤኮ ደስ ብሎን ውለን ነበር... ፍቅራችን ጨምሮ ምናምን.. ከዛ ለማታ ብለን ገዛዝተን ልንገባ አስበን ሌሎቹን ከገዛዛን ብኋላ ወደዳቦ ቤት ሄድን.... ልጅ እያለሁ በጣም የምወደው ግን በችግር ምክንያት ሁሌ እንዳማረኝ የሚቀረውን ዶናት አየሁት... ብዙ ክሬምም አለ... አማረኝ! ዶናት የመብላት ጉጉት ያዘኝና ለእሷም ለእኔም ገዛን... አላስችልህ ብሎኝ ከዳቦ ቤቱ እየወጣን... እኔ ዶናቴን ለመብላት እየተዘጋጀሁ... "አባ? አባ? ስጠኝ?... እርቦኝ ነው?" የሚል ህፃን በአንድ እጁ በቀኝ በኩል ሱሪዬን ይዞ በሌላኛው እጁ ይለምነኛል... እንዲህ ቁልቁል ሳየው ተበሳጨሁ... አለ አይደል በቃ የምወዳቸውን ነገሮች ሁሉ አገኘሁ ስል የሚነጥቀኝ መስሎ ነው የተሰማኝ... የልመና ልምዱን የሚያስረሳ ደህና ኩርኩም አቅምሼ አባረርኩትና ዶናቴን ገምጬ ሳጣጥም... ከማን አንሼ የሆነች ጥፊ ከፍቅረኛዬ ተሰነዘረብኝ... "ሁለተኛ አጠገቤ እንዳትደርስ... አውሬ!" ብላኝ ጥላኝ ሄደች..... እኔ እሺ ምን ላድርገው ሠውነቴ አእምሮዬን ትቶ ስሜቶቼን ሁኗል የሚታዘዘው... ፍቅረኛዋ ቀንቶ ይሁን ምን አላውቅም ብቻ Xን እኝደተላከፍኩ ሂዶ ለአባቴ ነገረው። ከዚህ ብኋላ ነው ታመሀል ብለው ካላሳከምንህ... የሚሉኝ... ............................................ መፈላሰፍ አለብኝ መሠለኝ... ካልሆነ ጭንቅላቴ መፈንዳቱ ነው! የዛሬ የሰማሁት ቀውስ ደግሞ ጫን ያለ ነው! የሳይኮሎጂስት ያለህ!? ብለው አንጠልጥለው እኔ ጋር አምጥተውት ምን ይሉኛል ብዬ ነው እንጂ... "ይሄንንማ ፀበል ውሰዱት.."ልላቸው ነበር! መንፈስ እንጂ ቀውስ ያለበት አይመስልምኮ... "እስኪ እየተቸገርክበት ያለኸውን ነገር ንገረኝ?" አልኩት "ከማድረጌ በፊት ደስተኛ ነኝ ወይ ደብሮኛል ወይም ደግሞ ሞቅ ብሎኛል... ብቻ ከnormal ሙዴ ከፍም ዝቅም ያለ ስሜት ሲሰማኝ የሆነ ድርጊት አደርጋለሁ... ድርጊቱን ሳደርግ ከውስጤ ወቶ ሰውነቴ የሚያደርገውን የሚያይ አለ.... ከዛ ከድርጊቱ ብኋላ ድንገት ንቅት እላለሁ... ከዛ ድርጊቱ ልክ እንዳልነበር አስባለሁ... ሠውነቴና አእምሮዬ ሁሌም ከድርጊቱ ብኋላ አይስማሙም... እነሱን ለማስታረቅ በስአቱ የተፈጠረውን ሳስታውስ... እኔ ከሰውነቴ ወጥቼ ሰውነቴ ያንን ነገር ሲያደርግ ከእግር እስከ ጥ… Read in full →
1 · 2.6K ·
ደ
ደስ አለችኝ እሷን ቀና እያልኩ እያየሁ ህልሜን አንድ በአንድ አስታውሼ ለመፃፍ ሞከርኩ.... ተብሰለሰልኩ ሌላ አድካሚ ስራ ሕልም መፍታት.. ግን ከስሬ አላውቅም ሕልሜን ከፈታሁት ብኋላ ትክክለኛ መፍትሄ አገኝበታለሁ ሕልሙ ሲፈታ እንዴት ያለ ኮተት እንደሆነ ላሳያችሁማ.... conscious መሪ ቢሆንም የመሪነቱ ስልጣን ያለው ግን Ego ጋር ነው.... ሻዷችን የኢጎአችንን አንባ ገነንነት ይፈራል...,ኮንሸስም በኢጎ ተደብቆ የኢጎን ፍላጎት ለማስፈፀም ከፊት ይሆናል.... ጭንብሎቻችን እንኳን ሳይቀሩ የኢጎአችን ወታደሮች ናቸው ኢጎን ነው የሚጠብቁትና የሚንከባከቡት... ይሄ ኢጎ ማለት ያ ወጣት ንጉሥ ማለት ነው! እነዛ ስዕል የሚመስል ፊት ያላቸው ወታደሮቹ ደግሞ በኢጎ የተገነቡት ጭንብሎች ኛቸው! ግን አንድ ነገር አለ ከዚህ ኢጎ ጋር fit የሚያደርግ... ይህንን fitter ማየት የሚችለው ግን ከኢጎው ያፈነገጠ conscious ብቻ ነው።         ኢጎ ሰው የመሆን እራስ ነው! self ነው..... ሰው የስነ-ልቦና ቀውሰ ውስጥ የሚገባው ኢጎው ሲታመም ነው! በሳይኮሎጂ እነ ሻዶ... ኢድ... conscious and unconscious... persona.... የሚባሎ ምናባዊ አእምሮዎች አሉ... ቀውሱ የሚፈታውም በእነዚህ ዙሪያ ነው.... ሚስጥሩ ያለው  እንግዲህ እዚህ ጋር ነው... traumaም... manipulateም... abuseም... bullyም... የተለያዩ ከልቶች መጀመሪያ የሚያጠቁት ኢጎን ነው... ከዛ ብኋላ ነው እነጭንብል.. ሻዶ... unconscious ትርምስ የሚጀምሩት... ምክያየቱም ሻዶ የኢጎን አባበገነንነት ስለሚፈራው ይደበቃል... unconscious ደግሞ አንባገነንነቱን ስለሚጠላው ይቃወመዋል...  ጥበበኛው ሽማግሌ ማለት unconscious ነው የወጣቱን(የኢጎን) አንባገነንነት ሸሽተው የመጡት ሕዝቦችም ሻዶዎች ናቸው። ይሄ ልጅ በኢጎው እና በደመነፍሱ መሃል ትልቅ ጦርነት ውስጥ ነው... ጦርነቱን ያስነሳው ደግሞ የሻዶዎች መብዛት ነው... ይሄ ማለት ልጁ አብዝቶ የሕግና የስርአት ሰው ለመሆን ይጥራል ማለት ነው። ለዛ ነው ልማዶቹን በአንዴ ገፍቶ አዲስ ሕግና ስርአት ለመጠበቅ ሲሞክር ደመነፍሱ ሲዘናጋ ጠብቆ በቀድሞ ልማዶቹ አሁን ማድረግ የማይፈልገውንና የሚጠላውን ነገር በማድረግ ኢጎን ያጠቃዋል... በዚህ ጥቃት ኢጎ በብስጭት consciousን ይቆጣዋል... እንዴት ይሄንን ሲያደርግ አንተ ንቁ አልሆንክም ብሎ በንዴት... በፀፀት.. ምናምን ይቀጣዋል.... ከህልሜ በተጨማሪ የምኮራባት ሦስተኛ ዓይን አለችኝ... እሷም ተቅበጥብጣ ወደአንድ ደጀ ገነት አማተረች... እነሆ በደጀ ገነቱ የሚመላለስ ድምፅ ሰማሁ... "አዳም ሆይ ወዴት ነህ?" የሚል "አለሁ!" "የት አለህ?" "ከደጀ ገነቱ ውጪ..." "ደግ አደረክ አንዳንዴ ስፍራ መቀየር መልካም ነው" "ከደጀ ገነት በላይ?" "ታዲያ ምን ሽተህ ከደጀ ገነት ወጣህ? እራስህን መለወጥ.. ካለህበት የተሻለ ነገር ማግኘት ፈለክ...  ለዚህ ፍላጎትህ ደግሞ የሚበጀውን ነው ያደረከው... የኔ ልጅ እራስህን መለወጥ ላይ ብቻ ችክ አትበል ይጎዳሀል! አንዳንዴ እራስህን ከመቀየርህ በፊት መቀየር ያሉብህ በዙሪያህ ያሉ ሲስተሞች ሊኖሩ ይችላሉ!" አለኝ... ተግባራዊ ቴራፒያችንን ጀምረናል.... "እስኪ ለዛሬ በጣም ቀላል የቤት ስራ ልስጥህ" አልኩት "እሺ ስጠኝ" "20 ሌትር ወይም ከዛ በላይ የሆነ ጀሪካን ፈልግና ይሄ ቤትህ ያስቀመጥከውን የውሃ ባልዲ አውጥተህ ጣል.... ከዛ የሚያሳስት ጆግ የሚባል ነገር አይኖርም!" አልኩት።… Read in full →
1 · 3.1K ·
ደ
ደራሲው...∞
በሠላምም ባይሆን እንኳን ከ2018 ተላቀቃችሁ ለሠላምም ባይሆን እንኳን ወደ 2019 ተሻገራችሁ! ደግሞ ትናንት ያላልኳችሁ ፆም ስለነበረ ነው🤭 Anyway እወዳችኋለሁ🥰 ✍Lewi @lewi_derest
2.7K ·
ደ
ደራሲው...∞
The Body Keeps the Score ከንፈሬ ከንፈሮቿን ጎርሰው ያውቃሉ.. ጣቶቼ ከጡቶቿ ጋረሰ ደንሰዋል.. ልቤ ከልቧ ጋር በሰመመን አውርተዋል..... ነገር ግን አላፈቅራትም!...More
1.6K ·
ደራሲው...∞
ደራሲው...∞: The Body Keeps the Score በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን trauma በማከም ለምን መኖሬን እጨርሳለሁ?" የምትል ጣፋጭ ፍልስፍናን አስታቀፈችኝ.... ማፍቀር አልወድም!.. አፈቀርን የሚሉ ሰዎችን ሳይ ምን ያክል የሞኝነት ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ እያየሁ አዝንላቸዋለሁ... ብዙ ሰዎች ደስታ ያለው ፍቅር ውስጥ ይመስላቸዋል... አይደለም ደስታ ያለው ስሜት ውስጥ ነው... ታዲያ ለምን ብዬ ፍቅርን አሳድዳለሁ? መቼስ የመጀመሪያ ፍቅር የሕይወት ሀሁ ነውና እኔም ከመጀመሪያ ፍቅሬ የቆጠርኩትን ሀሁ ልንገራችሁ... ፍቅር፦ ቁስልና ህመም ብቻ ነው ያለው... ስሜት ግን ደስታና ሰላም አለው! ብዬ ብጀምርላችሁስ? ቆይ ቆይ እንዴ ለመፍረድማ አትቸኩሉ.. እሷ ጭዋ ነበረች... ቅንድቦቿን ልትሸፍናቸው ጥቂት እስኪቀራት ድረስ ግንባሯን ነጠላ አልብሳ ሳያት... በዛ ላይ የመዘምራን ልብሱን ስትለብስበትማ?! ሻራባራባላ... ሃሌሉያ! ልቤ የሚመታላት እንስት ሳትሆን እግዜር የላካት መልዐክ ነበር የምትመስለው... ጠዋት በለሊቱ ማርያም ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ ታይቼ... ከረፋፈደ ከ4 ስአት ብኋላ ደግሞ የክብር ደመና ቸርች ውስጥ በመንፈስ ስመነፈስ በልሳን ስለስስ እሁዴን ብሩህ አደርጋታለሁ.... በሁለቱም በኩል ያሉ ሀይማኖተኞች በቁጣ ገስፀውኛል... ከአንዱ ተሰብሰብ ይላሉ ዝም ብለው... እኔ ወድጄ ነው እንዴ? ነፍሴ በጌታ ቤት.... ልቤ እንስት ልብ ተከትላ ከማርያም ቤት እኔ የት ነኝ? ማነኝ? ከየት ነኝ?... ደግሞ ወደ አንድ ተሰብሰብ ይሉኛል እንዴ? እኔ እንኳን ወደ አንድ ልሰበሰብ እራሴን እንኳን አንድ ማድረግ ከብዶኛል ደደቦች! ታውቃለች እሷን ብዬ እንደማስቀድስ.... ሆን ብላ ይመስለኛል እንደዛ ውብ ሁና የምትመጣው መዘምራንን የሚያሰልፋቸው ሰው እራሱ ሆን ብሎ እኔ እንዳያት ብሎ ሁሌ ከፊት የሚያሰልፋት እየመሠለኝ በውስጤ "ፀጋውን ያብዛልህ!" እለዋለሁ መእመኑ ሁሉ በመዝሙሩ መንፈስ ተነክተው ሲያመሠግኑ እኔ በእሷ ውበት ተነክቼ ጠቢቡ ሰለሞንን መሆን ይዳዳኛል... መቼስ አእላፍት ሚስቶችን አስማምቶ ሚስት በማድረጉ መሆን አለበት ጠቢብ ያስባለሁ... አይ አይ እኔ እንኳን የሰሎሞንን ጥበብ የፈለኩት ለአእላፍት ሚስቶች አይደለም... መልዐክት የሆነች እንስትን.. ለደረደ ተባዕት ልብ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል በጥበቡ ልጠበብበት ነበር.... ይህንን ጥበብ የሰጠኝ ማን እንደሆነ ማወቅ ተስኖኝ.... ለሁለቱም ስለቴን ላስገባ ብዬ ወሰንኩ... የመልዐክት ፍቅር እውር ብቻ ሳይሆን መሀይምም ያደርጋል መሠለኝ.... እኔ የእናንተ አፍቃሪ የክብር ደመና ቸርር ጧፍና ዣንጥላ... ማሪያም ቤተክርስቲያን ደግሞ  ዘይትና 8ደርዘን ግማሽ ሌትር ውሃ ስለት ነው ብዬ ማስገባት.... ይህ መደናበሬም ይገባታል.... በዛ በመልዐክት ሞገሷ ወደ ቄሱ ጆሮ ጠጋ ብላ ሹክ ስትለው... በደስታ "እሰይ እሰይ... እኳን እመቤቴ እረዳችህ... ችግር የለም... ሁሉንም ታቀው ትለምደዋለህ!" ብሎ በመስቀሉ ግንባሬን ሦስት ጊዜ መታ መታ አድርገው ያሳልሙኛል... "አንቺ ጦጣ" እላታለሁ...በከንፈሮቻችን ልፊያ መሀል... "እየሳምከኝ ስናወራ አፍራለሁ አላልኩህም?" አለችኝ እጄን ወደወገቧ እየሳበች እንድይዘው እያደረገችኝ ይገባኛል እሷ ከወገቧ ጉዳይም የላት... ይህ የሴት ቋንቋ ነው... ውበቶቼ.. ድምቀቶቼ.. ጡቶቼ ከጣትህ ጋር ሊደንሱ ይሻሉ ማለቷ ነው... ደመነፍሴ ይህን እንዴት እንደሚረዳ አላውቅም! አእምሮዬ በማወራት ነገር ተይዞ ደመነፍሴ ግን ወደፍላጎቷ ሲጓዝ እይዘዋለሁ... ከንፈሯ ላይ የማ… Read in full →
3 · 1.7K ·
ደ
እሷም  በቁምጣ ከሜዳ ወደሽኝት ቤት ስትመጣ አየኋት.... ጠብቀኝ ምልክት በእጇ አሳየችኝ... "ፎርፈክ ነው?" "ኧረ አይደለም ለሽንት..." "እስፖርት ወተን እኮ.. (ቀኝ እግሯን በቄንጥ ከፍ አድርጋ አንገቷን ወደቀኝ አዙራ ቂጧን እያየች) እንዴት ነው በቁምጣ አላማረብኝም?" አለችኝ ሽንት ቤታችን ከፊትና ከኋላ አንድ ላይ የተሰራ ነው... በፊተኛው በኩል የሴቶች ሽንት ቤት ነው እሷ ግን ፈጠን ብላ ወደጀርባው ወደ ወንዶች ሽንት ቤት ሮጣ ሄደችና አንዱ ላይ ገባል... እኔም ተከትያት ገባሁ... ኧረ እቺ ውብ መልዐክ ብቻ ሳትሆን እብድ ሰይጣንም ናት... እሁድ ማታ ሳስበው ያደርኩት ከንፈሯን በግላጭ አገኘሁት... ከአመታት ብኋላ ጣቶቼ ከእናቴ ጡት ብኋ የአበባዬን ጡቶች አወቁ... በቃ እንነጋገራለን በሆነኛው ክፍለ ጊዜ እንወጣለን የሆኑ የሆኑ አካሎቻችን ተላፍተው እንመለሳለን.... በሽንት ቤት ሽታ የተቀመመ ፍቅራችን አድጎ ጎርምሶ... ትልቅ ሁነን ቀለበት ገዛሁላት...  አባቷ ቄስ..አጎቷ ቄስ.. ክርስትና አባቷ ቄስ... ቄሶች በቤታቸው ተሰብስበው ቁርጥ ሲቆርጡ የአበባዬን ጣቶች ተመለከቱ.... ከነቆባቸው "ከማን ነው?" ቢሏት.... "አንዴት አንዴ እዚህ አንዴ እዛ ከሚረግጥ ጴንጤ ነው ትበላቸው?" አለችኝ እህቷ... "እና ከማን ነው አለቻቸው?" አልኳት... "ይሄው የመጥሪያ ካርዱ እዚህላይ አለልህ።" በላኝ መጥሪያ ሰታኝ ሄደች... "ታላቅሽ እያለች ቀድመሽ ልታገቢ ነው?" አልኳት እየቀለደች መስሎኝ.. "የእሷ እኮ ነው! ያመዋል እንዴ" አለች ኧረ ትናት እኮ ቤቴ ነበረች... አታረገውም እያጉረመረምኩ ወደቤቴ ገባሁና መጥሪያውን አነበብኩት... አብርሃም? ለምን እሱን? እሺ በእኔ ደስተኛ አትሁን ግን ቢያንስ የማልጠላውን ሰው አታገባም ነበር? ነው በቀል ነው? ለምን ትበቀለኛለች? እህቷ ከሠርጉም ብኋላ ብዙ ልታፅናናኝ ሞከረች ግን ከበደኝ... ምንም አላለችኝም ነበርኮ.... ለሰርጓ ዋዜማ መጥሪያ በእህቷ ልትልክልኝ ነገር ለምን ቀድማ ቤቴ መጣች? መቼስ ዛሬ ጠይቀዋት ነገ አይጋቡም አይደል? ለምን ታዲያ ያን ሁሉ ጊዜ ዋሸችኝ? ለጥያቄዬ መልስ ሳጣ... ለማጣቴ ፍልስፍና ጀመርኩ... መልዐኬ ስለነበረች ስሜቴን ገርቼ የእውነት አፈቀርኳት.. ፍቅር ግን ሕመምና ቁስል አሸከመኝ... እስኪ ደግሞ ፍቅርን ገርቼ ስሜቴን ልከተል የሚል ፍልስፍና አመጣሁ... እነሆ ፍልስፍናዬ ይህቺን ቆንጆ ጣለልኝ... ቆንጆ ናት እኔ ግን ለመጅመሪያ ጊዜ አበባዬን ሰብሉን ካፈቀርኳት ብኋላ ሴት አፍቅሬ አላውቅም.... ስሜቴን ስከተል... ደስታም ሰላምም ያገኘሁ መሠለኝ... ከስሜቴ ብኋላ በማፍቀር ውስጥ ያሉ.. እነ መቅናት... እነ መከዳትና መጎዳት ተሰምተውኝ ስለማያውቁ ልክነት ተሰማኝ... ሴትን እስከ አልጋ እንጂ እስከ አጋር ማሰብ ማቆሜ ምቾት ነበረው ከዚህችኛዋ ልች ጋር በጣም ተቀራርበናል ወሲብ ሲቀረን  ሌላውን ሁሉ አድርገናል። ከንፈሬ ከንፈሮቿን ጎርሰው ያውቃሉ.. ጣቶቼ ከጡቶቿ ጋረሰ ደንሰዋል.. ልቤ ከልቧ ጋር በሰመመን አውርተዋል..... ነገር ግን አላፈቅራትም.... ማፍቀር ፈልጌ አቅቶኝ አይደለም በቃ ማፍቀር ስላልፈለኩ አላፈቀርኳትም... ቤቴ መምጣት አትፈራም... አብዛኛውን ጊዜ ሁላ መጀመሪያ የምትስመኝ እሷ ነች... ግን መቶ ቀን ቤቴ ብትመጣ አንዱንም ቀን ወሲብ አናደርግም! ከአንገቷ ከከንፈሯ መፍሰስ የጀመርኩት ወንዝ በእንብርቷ አልፌ ልወርድ ስል ትደነግጣለች... እንደ ሎጥ ሚስት ቀጥ ያርጋትና! አሁን በዚህ ስአት ይሄ ጥያቄ ይጠየቃል? "እኔና አንተ ግን ም… Read in full →
2 · 2.1K ·
ደ
ደራሲው...∞
እናቴ.. እህቴ ወይም ዘመዴ ያልሆነች ሴት ፊት ስቆም ቀድሜ የማስበው እርቃኗን ነው! አእምሮዬ ሳያስባት... ልቤ ሳይመኛት ገና ምናቤ ቀድሞ ከቀሚሷ ባሻገር ሲርመጠመጥ አየዋለሁ....More ነገ ማታ ይለቀቃል ✍ሌዊ
1.4K ·
ደራሲው...∞
ደራሲው...∞: boundary እና protocol የሚያበዙ ሰዎች፦ እራሳቸው ላይ ቲያትር የሚሰሩ ጅሎች ናቸው! የዘገየች ጥፊ አሁን በዚህ ቅጥነቷ እንዴት አምኜ ነው አልጋ ላይ ይዣት የምወድቀው? ደግሞ እኮ የሴት ወጉ ጡቶችን አንጉታለች.... በስስት ሳያቸው ስጋት ያዘኝ እጄ ላይ ቢሟሙስ? "ምን እያሰብክ ነው? እንደዚህ ትተኸኝ የጠፋኸው" "ስላንቺ..." "ስለእኔ ምን?" "ጡቶችሽ እጄ ላይ ሲሟሙ...ወይ በወንድነት ትግሌ መሀል ወገብሽ ቅንጥስ ሲልብኝ ምናምን...." "በቅጥነቴ ብዙ ቀልዶችን ሰምቼ አውቃለሁ.. ብዙ ግልፅ የሆኑ ሰዎችንም አይቼ አውቃለሁ በዚህ ልክ ግን አጋጥሞኝ አያውቅም" አለችኝ። "እኔም ብዙ ጭኖችን አውቃለሁ እንዳንቺ ግን ያላቅሟ ወሲብን ፊር የምታደርቅ ትእቢተኛ ነፍስ አጋጥማኝ አታውቅም!" "ትንሽ ብልግናህ አልበዛም?" "ግልፅ ነህ አላልሽኝም?" "የሕይወት ፍልስፍናዬ ድንበር ነው!" "የኑሮሽስ?" "ማለት?" "ሳይሽ አኗኗርሽ ላይ ብዙም ሕግና ስርአት አታበዚም ምናልባት ፍልስፍናሽ በቲዮሪ ብቻ ሁኖ ከሆነ ብዬ ነው" "ልክ ነህ ይሄ ጥፊ ገና ጡቶችሽ ስትል ነበር ፊትህ ላይ ማረፍ የነበረበት" ኡፍ... እንደቃሪያ ደስ እያለ የሚያቃጥል ጥፊ.. በቃ የጥዋት ፀሐይ ምን ያደርግልኛል? ባሎች ሆይ በቀትር 7 ስአት ከሚስቶቻችሁ ጋር እየተጨቃጨቃችሁ ተቃጠልን አትበሉ... እስኪ ቀኑ ሳይከር ገና በለጋነቱ ጭቅጭቋን ሙቁ! ምናለ በሉኝ በብርዳችሁ ላይ የመጣች ሙቀት ትሆናለች ለዛም ደስ የምትል መቃጠል ውስጣችሁ ትፈጥራለች... እንዲህ የሚያስበው የአእምሮ ክፍሌ ግን ከየት አምጥቶ እንደሚቀባጥር አላውቅም... የጭቅጭቅ ጥዋት.. ቀትር.. ምናምን ብሎ ነገር አለ? ያውም ለሚስቶች?! አቦ እነዚህንማ ሪንግ ውስጥ ነበር መልቀቅ... ሀሳቦቼ ሲደባደቡ ምናምን... የእኔ አእምሮ ግን የግራና የቀኝ ብቻ ነው? የላይ የታች... የፊት የኋላ... የግራ የቀኝ... የላይ የፊት.. የግራ የታች...  የቀኝ የኋላ... ምናምን ብዙ ነው የሚያስበው.. ደግሞኮ አንዱ ከአንዱ ቢስማማ እሺ... አስራ ስድስት የሐሳብ ሰይጣን አናቴ ላይ ሲጨፍር እንጂ አሁን አንድ ጥፊ ይሄን ሁሉ ያስለፈልፋል? .................................................. አንዳንዴ አስባለሁ ሕይወት Stop button ቢኖራት ብዬ አስባለሁ... ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ ድንበሩን እየተላለፈ ነው የሚኖረው! የሰውን ድንበር ስትጠብቅ... ትወደዳለህ የመጨረሻ ጭዋ ትባላለህ የእራስህን ድንበር ስታስጠብቅ ግን እንደትዕቢተኛ.. ጉረኛ.. ምናምን ትታሰባለህ... ዛሬ የሰነዘርኳት ጥፊ ግን በአግባብነቷ ላይ ጥያቄ ፈጥሮብኛል... "መስመሬን እንዳታልፉ ባልሽ ቁጥር የሰዎችን ነፃነት ክየገደብሽ እንዳይሆን ተጠንቀቂ ካልሆነ ግን እራስ ወዳድነት ብቻ ይሆንብሻል" ብሎኝ ነበር አስተማሪዬ... የመናገር ነፃነት ነበረው.. መስመሩን ያለፈው የቱ ጋር ነበር? እ.. አዎ እኔን ለወሲብ እኝዳሰበኝ ሲነግረኝ... ልክ ነኛ በርግጥ ጥፊዬ ዘግይታለች.... ግን ሰው በዛ ልክ እንዴት ግልፅ ሊሆን ይችላል? እየቀለደ ቢሆንስ? መጠየቅማ አለብእ.... ደወልኩለት... ቀጠርኩት.. አገኘሁት.. "ምነው የቀረ ጥፊ አለሽ?" አለኝ "አዎ..." ቆንጆ ጥፊ.. ደገምኩት "መቀመጥ እችላለሁ?" አልኩት "ጥፊሽ ሰላምታ መሆኑ ነው?" ኮስተር ብሎ... አ..አህ አሁን አስፈራኝ ያው ወንድ አይደለ "ያኔ አወራን ነገሩን በሰላም ፈታነው ምንም እንኳን ጥፊ ቢኖረውም ያ በጣም ጥሩ መንገድ ነበር... ነገር ግን አንቺ ተመልሰሽ መጣሽ… Read in full →
1 · 1.3K ·
ደ
አንድ ሚስጥር ግን ለሴቶች ብቻ ሹክ ልበላችሁ.... ወንዶቻችሁ አልጋላይ ሚስጥሮቻቸው ምንም ናቸው! ማግጦብሽ ቢሆን እንኳን ከጭኖችሽ ሳይወጣ ጠይቂው ዘክዝኮ ይነግርሻል! እውነት ለመናገር የእኔውስ ያሳዝናል... ወንድሜን አይቼ ነው የተጎዳሁት ይለኛል... የቱ ጋር እንደምመስለው አላውቅም እንጂ በአመለካከት ከወንድሙ ጋር የሚመስል ነገር አለኝ.... የወንድሙን boundary ሌሎች ሰዎች አልነበሩም የሚጥሱበት እሱ እራሱ ነበር የእራሱን boundary የሚጥሰው... ሰዎች ስለእራሳቸው ያወሩለት ሁሉ የእውነት ያ የእነሱ boundary እየመሰለው ሊጠብቅላቸው ይታገላል... በጣም የሚወዳት ፍቅረኛው... ከትዳር በፊት ምንም ማድረግ አልፈልግም ስትለው ጠበቀላት... እሷስ ምን አደረገች? ሲጣሉ ጠብቃ ባደባባይ ወንድነቱን እንደምትጠራጠር ተናገረች... ሰው ሲጣላ ስለ ልቡ.. አስተሳሰቡ ምናምን ይሳደባል... አጅሪት ግን ቀጥታ ብልቱን ተሳደበች... "ንፁህ ሀሳብ ንፁህ ልብ አለው... ቆለጥ ግን ያለው አይመስለኝም!" አለች በሴቶች ፊት እየሰማት... ባለጌዎች እንዲህ ናቸው... ጭራሽ የቤታቸው የውጭ አጥር ላይ እንደጥቅስ ፃፉበት... ወንድሙ... መጀመሪያም ብልህ አልነበረም እራሱን ሰቅሎ ሞተ.... ከዚህ ብኋላ ነው የእኔው ጉድ "ለሰዎች boundary ብዬ የምሸሽገው አንዲች ቃል የለችም!" የሚል አመል ያመጣው። .................................................. ከወንድሜ ብኋላ የማግባትና የመውለድ ተስፋዬ ጠፍቶ ነበር... የዚህችን ቀጫጫ ጥፊ ግን አልቻልኩትም.... እውነት ለመናገር ጥፊዋ ሳይሆን ልጄ ነው ማግባት እንዳለብኝ ያሳመነኝ... ልጅህን ወለድኩ ስትለኝ... የሆነ ነገር ተሰማኝ ስበር ሄጄ አየሁት.... አፍንጫው ትንሽዬ ናት...እጆቹ ስስነታቸው ሲያስፈሩ... እግሮቹማ ጫማ አይንካችሁ የሚያስብሎ... ትንሿ ጣቴን እንደጡጦ በግጉ ሲግጣት የተሰማኝ ስሜት ልቤን ፍስስ አደረጋት! ✍ሌዊ @Lewi_derest
1.6K ·
ደ
ደራሲው...∞
ጉዳዩ፦ የ"ደራሲው...♾" channelን ይመለከታል ለካ 2k ገብተናል👏! ያው እንደምታውቁት ማሰብ የማያቆም በሽተኛ አእምሮ አለኝ... እናም "2k ገባን"  ስለው "ለምን challenge አንሰጣቸውም?" አለኝ እናም የዚህ የበሽተኛው አእምሮዬ ሀሳብ ምን መሠላችሁ እናንተ የፈለጋችሁትን ዘፈን መርጣችሁ መወያያ group ላይ ትልኩልኛላችሁ... ከዛ እኔና በሽተኛው ደግሞ ብዙ react የተደረገበትን ዘፈን መርጠን ልብ ወለድ እንፅፍላችኋለን! እኔ በበኩሌ የበሽተኛውን ሀሳብ ወጅጄዋለሁ... እናንተስ? ✍ሌዊ @Lewi_derest
1 · 783 ·
ደራሲው...∞
Photo
Photo
movie recommendation Silo ያበደ tv series ነው ሕግ ያስፈለገው እኛን ለመጠበቅና ፍትህ ለማስፈን እንደሆነ አብዛኞቻችን እናስባለን... ይሄንን ፊልም ካየሁ ብኋላ ግን ምናልባት ሕግጋቶች እኛን ሳይሆን የተዋሸናቸውን ውሸቶች ቢሆንስ የሚጠብቁት? ብዬ ማሰብ ጀምሪያለሁ... ብዙ ነገር ታዩበታላችሁ... ፊልሙን በትርጉምም በእንግሊዝኛም ታገኙታላችሁ ከፈለጋችሁ በውስጥ አዋሩኝ እልክላችኋለሁ... @Mr_Lewi ያያችሁት ካላችሁ ከፊልሙ ብኋላ እንዴት ናችሁ? @lewi_derest
❤2
4 · 871 ·
ደህና ይግጠምሽ! የሄደን ሰው ምን ይሉታል ከራስ አልፍ ለማን ይወቅሱታል? ተፈጥሮ ግን ቅጥአንባሯ የወጣ ናትሳ... አሁን ሜዳና ተራራ እንዴት በአንድ ገፅታ ይሆናሉ? ተቃራኒ ናቸው! እንደሚገባኝ ከሆነ ደግሞ ተቃራኒ ነገሮች ሁሉ በተቃራኒ እንጂ በአንድ ገፅታ አይሆንም..... እዚህ ግን ሜዳና ተራራ በአንድ ሆኑ እያልኳችሁ ነው... እንዴት እንደሆነ አትጠይቁኝ ግን ሜዳው ተራራ ነው ተራራው ሜዳ ነው..አንዱን ብቻ ማለት ይከብዳል... ተፈጥሮአዊ ቦታ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ወደዚህ ይመጣሉ ግን በጣም ትልቅ ስለሆነ ሰው ያለም እስከማይመስል ፀጥ  ያለ ነበር... ሁሌም የምቀመጥባት ቦታ አለችኝ... ፊትለፊቴ ገዘፍ ያለ ዲንጋይ አለ... በቃ ደስ ሲለኝ ከዲንጋዩ ጋር.. ከፈለኩ ወደአንደኛው ዛፍ ዙሬ ከእሱጋር... አብዛኛውን ጊዜ ግን ከእራሴ ጋር ነው የማወራው። ከሆነ ጊዜ ብኋላ ግን እቺ ቦታዬ ሌላ ሰው ሳትለምድ አትቀርም ሂጄ በመጣሁ ቁጥር ሁሌ የሚሸተኝ የሆነ ጠረን አለ... እሺ ውሻ አይደለሁም ጠረን አሸታለሁ ምናምን ብዬ አልሰክሳችሁ ግን የምቀመጥበት ቦታ ላይ ምን የመሰለ ዳሌ ተሸክሞ እንደነበር የሚያሳብቅ ወረቀት አገኛለሁ... ቦታዬ ላይ ሌላም ሰው መቀመጥ ስለጀመረ ቀንቼ ይሁን ወይም ለተፈጥሮ ተቆርቁሬ አላውቅም ብቻ እኝደመበሳጨት እያረገኝ... "ተፈጥሮን ፈልገው ከመጡ ዝም ብለው አይዘረፈጡም? ወረቀት ላይ ምናምን ይቀመጣሉ እንዴ? ቀሽሞች" ምናምን እያልኩ እያጉረመረምኩ ወረቀቱን በእግሬ አብንኜ እቀመጣለሁ.... ዲኔጋዩ ይሁን ዛፎቹ ባላውቅም ለሚመጣው ሰውማ ስለእኔ ያሳብቁለታል... እንጂማ እንደዚህ እኔን ለማናደድ እንደዚህ ቆርጠው አይነሱም ነበር... በሚቀመጡበት ወረቀት ስናደድ ጭራሽ የሶፍት ምአት ቆልለው ይሄዳሉ? ሴት ይሁን ወንድ አላቅም ግን ስድስትና ሰባት ወር ሙሉ ጉንፋን ይይዛል እንዴ? አመቱን ሙሉ በሉት ሶፍቱን ስለቅም ሳቃጥል.... እሰይ... እሰይ.. ዛሬስ ወረቀቱን ከነዳሌው ደረስኩበት... እንዴት እንዴት በስድብ ከፍ ዝቅ እንደማደርጋት በጋለ አእምሮዬ ምስል እየታየኝ ገሰገስኩ... የሆነ ሰልካካ... ምን ልበላችሁ? ለጡት ጉች ጉች... ለከንፈር ኢንጆሪ.. ለጥርስ በረዶ... አቦ ለድምፅ ምን ቁልምጫአለው? ከቁጣ ግስገሳዬ አደናቅፎ ያቆመኝ እንቁርጉሮዋን ሰማሁ... "የልቤን ስብራት ባንተ እንዳልጠግነው.. የኔ ማቶንበት ምክንያቱ ብዙ ነው! የምቶድህ ልቤ የሰው መሆንህን አምና ተቀብላ... ይመስልሀል እንዴ ሰላሟን አግኝታ የምትልህ ችላ!..." "ምን ልታረጊኝ?ልክ ቦታዬን እንደቀማሽኝ ሚስቴንም ልትቀሚኝ?" አልኳት ፈገግ ብዬ "Noo.. ለዘፈኑ ያክል ነው..." "ድምፅሽ ያምራል" "ዘፈኑስ?" "እኔ የሀገራችንን ዘፈኖች አልወዳቸውም" "Ok...ፍቅር ይዞህ አያቅም ማለት ነዋ!" "ቢይዘኝም ፍቅሬን በዛቻማ አልገልፅም..." "እና በምንድነው የምትገልፀው?" "አንዳንድ ጥያቄዎች መልሶቻቸው እሩቅ ናቸው... ለማንኛውም ዛሬ ጎበዝ ሁነሻል ቦታዬን በሶፍት አላዝረከረክሻትም" "አታስብ ከዚህ ብኋላ አላቆሽሽብህም" "በስተመጨረሻ ጉንፋኑ ለቀቃት.. ቢጨንቀኝኮ ትኩስ ነገር ባስቀምጥላት ብዬ ሳስብ ነው የተሻለሽ" "አይደል..!" በትካዜ ተዋጠች... "ኦ sorry ምክንያቱን ሳላውቅ ቀባጠርኩብሽ.. ምን ነበር የሶፍቶቹ ሚስጥር?" "ከሶፍቶቹም በፊት እመጣ ነበር..." "አው አውቅ ነበር..." "ያን ታውቅ ነበር?" "አዎ ጠረንሽ ሁሌም ይሰማኝ ነበር.." "ገባኝ ወረቀቱ.." ብላ ከዳሌዋስር ጎትታ አወጣችውና ጨመዳዳ ወረወረችው... "ሶፍቶቹ እንግዶችሽ የሆንበትን ምክን… Read in full →
❤9
2 · 647 ·
ፍቅራችን ለምለም ነበር.. ንፁህ አየር የሚወለድበት ንፁህ የተፈጥሮ ፍቅር... እዛች ቦታ ፍቅር ካልሰራን ተራራና ሜዳው የሚደርቅ እስኪመስለኝ ድረስ በፍቅራችን ተመካሁ... ላፕቶፔንና መፅሀፎቼን ጥዬ ጊታርና ማይክ ሳነሳ  አባቴ ከቤት አባረረኝ... አሁን መዝፈን ብቻ ሳይሆን መስራትም ግድ ሆነብኝ.. የምሽት ቤት ውስጥ መዝፈን ጀመርኩ.. በቂ ባይሆንም የቤት ኪራይና ሠላምዬ እቤት ስትመጣ ለምታፈላው ሻይ ይሆናል... የሆነኛው ቀን ላይ የምላቸው ብዙ ናቸው.. ከእነዚል ብዙ የሆነኛው ቀኖቼ መሀል የሆነኛው ቀን ላይ ሠላሜ ደወለችልኝ "መስ... ቶሎ ና ድረስልኝ አባቴ ለሀብታም ሊድረኝ ነው..." ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ነገረችኝ... ሄድኩኝ ስሮጥ ስበር ሄድኩኝ... አባቷ ምን የሚያክል ዱላ ይዘው... "ልጄን ትነካና ውርድ ከራሴ! ጭራሽ ላዝማሪ ልጁን ዳረ ልታስብለኝ ነው?.. ዞርበል ብዬሀለሁ... በየበረንዳው አፍ ሲከፍቱ ማደር ሞያ መስሎሀል..."አባቷ ውሻ አርገው አባረሩኝ... ተሰማኝ በጣም ተሰማኝ... ሠላምዬ እያየኋት መኪና ውስጥ ገብታ በረረች... አከራዬ በጣም ጥሩ ሴት ናቸው የቤት ኪራይ ከከፈልኩ አመት ሊሆነኝ ነው.. እሳቸው ግን እንኳን የቤት ኪራይ... ከቦታችን ውዬ ስመጣ ምግብ ሁሉ ቤቴ አስቀምጣ ትጠብቀኝ ነበር... በመንገድ ልጆች ሲያዩኝ ፈርተው ይሮጣሉ ፀጉሬና ፂሜ አድገው ጥቁር ጥርስ እንጂ ፀጉር አይመስሉም ነበር... አንዳንዴ በሕፃናቱ ፈንታ ትላልቆቹ ምናለ ፈርተውኝ ቢሸሹ ብዬ እመኛለሁ... እኔን ሲያዩ ከከንፈር መጠጣቸው ቀጥሎ ሠላምዬን ያሙብኛል... "ሠላም በል ብላው እንጂ አቶ መላኩ እንዲህም የሚናገር አይደለም..." ሌላኛዋ ተቀብላ.. "ኧረ ስንቴ ከባለመኪናው ጋር ስትንዘላዘል አይቻታለሁ.. ሁሌ አይደል እንዴ መታጠፊያው ድረስ የሚሸኛት..." እኔ ከልቧ ስታለቅስ አይቻታለሁኮ ይሄ ከእነሱ ሀሜት አይበልጥም? የእኔ ሠላም እንዲህ ታረጋለች?... ሲያወሩ በሰማሁበት ስፍራ ተዘርፍጬ እነፋረቃለሁ... ብያችኋለሁ የሆነኛው ቀኖቼ ብዙ ናቸው.. የሆነኛው ቀኔ ላይ እንዲሁ ሠላምዬን ሲያሙብኝ ሰምቼ ናፍቃኝ በጣም ናፍቃኝ... በየመንገዱ ስነፋረቅ... እህቴ እንደዚህ ትልቅ ሁና አላቃትም... ከየት እንደመጣች እኔጄ በጥፊ ሦስቴ አራቴ አላቅም ብቻ ፊቴ ላይ አጨበጨበችብኝ... "መሣይ ደከመኝ... እኔምኮ የሚጠብቀኝ ሕይወት አለኝ... እስከመቼ ነው ላንተ እያዘንኩ ባንተ እየተሰቃየሁ የምኖረው?" "እነዚህን ሰዎች አየሻቸው? ልክ እኔን ሲያዩ ነው ሀሜት ትዝ የሚላቸው.. አንቺም እንደ እነሱ ነሽ! ዛሬ ባጋጣሚ በመንገድ ብታገኚኝ አታስመስይ.." "ጥሩ ከዚህ ብኋላ የቤት ኪራይ ማን እንደሚከፍልልህ እናያለን.. ምን እንደምትበላም ጭምር... ያንተ ነገር በቅቶኝ ነበር.. ጥሩ በል ደህና ሁን" ያቺ አሮጊት ለካ ደግነት አልነበረም... ለካ ጨለማዬ ጭላንጭልም ብትሆን ብርሃን ነበራት.. ዛሬ ግን እሷም ቀልጣ አለቀች የእህቴ ጥፊዎች ልከኛ ሳይሆኑ አይቀርም እራሴን ታዘብኩት... አውቃለህ ህመሜን ማዳን አልችልም ግን ቢያንስ ከህመሜ ጋር መኖርን መልመድ አለብኝ... እህቴን በመንገድ ጠብቄ እንድታግዘኝ ጠየኳት እራሴን በትንሹም ቢሆን መቀየር እንደምፈልግ ነገርኳት... በነጋታው የተወሰኑ ልብሶችን አመጣችልኝ "የፍቅረኛዬ ነው እሱም እንዳንተ ግርማ ሞገስ ያለው ስለሆነ ልብሶቹ አምረውብሀል" አለችኝ... ከፍቅረኛዋ ጋር ፀጉር ቤት ገባን... ሁሉ ነገሬ የዳነ መሰለ ዓይኖቼ ግን የቀረ የማይሽር ህመም እንዳለ መደበቅ አቃታቸው... "ከነገ ወዲያ አንድ የሚመረቅ ሆቴል አለ.. እና እነሱ የመድ… Read in full →
❤3👍1
3 · 677 ·
ደ
አንቺ ልጅ ነግሬሻለሁ ፍቅር ለወጣትነት እንጂ ለኑሮ አይሆንም.. የእኔስ ተበላሽቷል ሳይብስበት እገላገለዋለሁ እንጂ... እዪለች እያጉረመረመች ትሄዳለች... አባቴ እናቴን ይፈራታል ስልህ ገርሞህ ነበራ? ወንድነት ጎድሎትኮ አልነበረም... ግን እሷ እንደምትፈልገው ሀብታም ባለመሆኑ ስታሳቅቀው አቅም አጣ.. የእሷ እንጂ የእሱ ፍቅር ገና አላለቀም ነበር... እና ሊረዳት ስለሚሞክር.. ስለምታሳዝነው ነው የሚሽቆጠቆጥላት... እናቴ ለምን እራሷን እንዳጠፋች እኔም አባቴምእናውቃለን... እነዛ ለእናቴ ባለቀስኳቸው ስድስት ወራት ውስጥ የእናቴን ሕይወት ላለመድገም ስምል ስገዘት ነበር... አንተ ግን በድንገት መሀላዬን ሰበርከው.. እንደ ክርስቶስ ሕጌን በፍቅር ሰበርከው... እኔ ግን ይሁዳ ነኝ ወደሕጌ ተመለስኩ ፍቅርህን ሸጥኩት..." ከተንተራስኳቸው ጭኖቿ መነሳት ባልፈልግም እየተነሳሁ "ተይ እንደሱ አትበይ ያንቺ ጥፋት አይደለም አባትሽ ነው እሱንም ቢሆን ተረድቼዋለሁ እንደሚስቱ እንዳትሆኚ..." "አይደለም! አይደለም! መስ ልትሰማኝ ይገባል እውነቱን መናገር አለብኝ... አባቴ አይደለም ያንን ያሰበው አባቴ ያመጣልኝ ሀብታም የለም እኔው እራሴ ነኝ ላገባው ነው ብዬ ለአባቴ ያስተዋወኩት... በቃ እነሱ ልክ ናቸው! አባቴን አስገድጄው ነው... እሱ እንዳውም ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? "እናትሽ ያልኖረችውን ሌላኛውን መጥፎ ምዕራፍ ልትኖሪው ወሰንሽ? እናትሽን ማዳን አልቻልኩም አሁን ደግሞ አንቺን" አለኝ  እኔ ግን እንቢ አልኩት..." "ውሸትሽን ነው!" መልሼ ጭኖቿ ላይ ልንተራስ ዘመም ስል.. በእጆቿ ጭንቅላቴን እየገፋች "መስ እውነቴን ነው... ስለፈራሁ ነው.. እንደእናቴ የምሆን መሠለኝ... እኔም ልጄን በገዛ ፀፀቴ የማሰቃያት መሠለኝ... እራሴን ስገድል ማሰብ ፈራሁ.. በቃ ፍርሃቴ ከፍቅርህ ገዘፈብኝ..." ተነሳሁ ትቻት ሄድኩ... "መስ... መስ... ይቅርታ ልልህ አይደለም ግን ያንተን እሩቅ መልስ ስትደርስበት ግን ለመስማት ዝግጁ ነኝ ሙቼ ቢሆንምኳን.. ሰማኸኝ መስ... መስ..."  ድምጿ እየራቀእ እየራቀኝ መጣ.. ትቻት ሄድኩ... ተናደድኩ በእራሴ ተናደድኩ.. እንደእናት ሲያደርጋት በነበረችው አሮጊት ተናደድኩ... በሯንና መስኮቷን ሰባብሬላት ወጣሁ... ሌላ ቤት ተከራየሁ... እህቴ ያስመዘገበችኝ ውድድር በቴሌቪዥን ስለሚተላለፍና በጣም ጥሩ አካሄድ ላይ ስለነበርኩ ትልልቅ ቤቶች ላይ ስራ አገኘሁ... ጥሩ ቤት ጥሩ ገቢ አለኝ.. ውድድሩም መጨረሻው ላይ ደርሶ አሸናፊው የሚለይበት የመጨረሻው ውድድር ላይ ነኝ በሯን አንኳኳሁ... ልጇ ነበረች የከፈተችልኝ... አይገርምም ልክ ምናቤ ውጥ እንዳለችው ናት.. የሆነ አባት የሆንኩ ልጄ የሆነች ከሠላሜ የወለድኩ መስሎ ተሰማኝ... ግን እንደማይሆን ግልፅ ነው የረዠም ጊዜ የምናቤ ቅዠት ስለነበር ነው... "እናትሽ አለች ሚጣዬ..." "አዎ አለች ማሚ..." እየጠራቻት ትታኝ ገባች... "ጠይቀሽኝ ነበራ እሩቁ መልሴ ጋር ስደርስ እንድነግርሽ.." በጭንቅላቷ አዎንታዋን ገለፀችልኝ ልታለቅስ እየዳዳት... "ነገ የአሸናፊዎች ውድድር አለብኝ መልሱን መስማት ከፈለግሽ መምጣት ትችያለሽ" ብዬ መጥሪ ወረቀት ሰጠኋት። እህቴ ምን ብላው እንደሆነ አላውቅም አባቴም ውድድሩን ለመመልከት መቶ ነበር... ግጥሙም ዜማውም እኔው ስለሆነና ሰምተውት ስለማያውቁ ዳኞቹ እንዳይጥሉኝ ፈርቻለሁ ግን ደግሞ ስሜቴን ነው የምዘፍነው... ተራዬ ደረሰና ማይኩን ጨበጥኩ... "ልሰማ አልጓጓሁም እንዴት እንደመጣ ስህተት.. ሆነ ምን ያደርጋል ቃልሽ ላይቀይረው እውነቱን! ተይው ምን… Read in full →
❤16🔥3
3 · 911 ·
T
Tsi ✝️ של ישו
Nothing in this world truly excites me anymore. Everything that comes into my life seems to bring its own struggles, burdens, and challenges. The only thing my heart longs for, day after day, is to dwell in the presence of God. For in His presence, I find a peace that the world cannot offer, a rest that nothing else can give, and a contentment that goes beyond all understanding. His presence is my peace, His love is my satisfaction, and being with Him is all my heart truly desires. As the psalmist declares in Psalm 73:25–26: “Whom have I in heaven but you? And earth has nothing I desire besides you. My flesh and my heart may fail, but God is the strength of my heart and my portion forever.” At the end of it all, I don't want a life filled with everything this world has to offer; I want a life filled with the presence of God. Let the world chase its treasures, its pleasures, and its temporary glory. As for me, give me Jesus. He is my greatest treasure, my eternal hope, and my soul's resting place. For to live is Christ, and to die is gain (Philippians 1:21). My heart belongs to Him, now and forever. 🙏❤️ Jesus Loves you
❤8
1 · 469 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count