13 September 2026
14 September 2026
16 September 2026
17 September 2026
መስከረም ፯ /7/
በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እናት፤ የከበረች ኤልሳቤጥ አረፈች።
ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ካህን ለሆነው ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት። ነገር ግን እስከ እርጅና ዘመናቸው ልጅ መውለድ አልቻሉም ነበር። የኤልሳቤጥ እድሜ 90 የዘካርያስም 100 ደርሶ ነበር። እግዚአብሔርም ትዕግስታቸውን እና ጽድቃቸውን ተመልክቶ በመልዐኩ ገብርኤል አብሳሪነት ታላቅ የሆነ ነቢይን ሰጣቸው።
የኤልሳቤጥ የስድስት ወር ጽንስም የድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማ ግዜ በደስታ ዘሏል። ቅዱስ ዮሐንስም 2 ዓመት ከ6 ወር በሞላው ግዜም ንጉስ ሔሮድስ የተወለደውን ንጉስ ለማጥፋት ተነሳ። አይሁዶችም ለንጉሱ
ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ ደግሞ የከፈተ ዮሐንስ የሚባል አለና እርሱን ግደል አሉት።
ቅድስት ኤልሳቤጥም ቅዱስ ዮሐንስን ይዛው ሸሸች። አባቱ ካህኑ ዘካርያስን ግን በቤተመቅደስ ውስጥ ገደሉት። ቅድስት ኤልሳቤጥም ዮሐንስን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 ዓመታት ቆየች። ቅዱስ ዮሐንስም 5 ዓመት በሞላው ግዜ በዚህች ዕለት ቅድስት ኤልሳቤጥ በዚያው በበርሃ አረፈች። በረከቷ ይደርብን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
418 ·