Web appOpen in Telegram
YYalcodes

Yalcodes

@Yalcodes · channel · indexed since 2026-09-29
210subscribers
139posts in the index
Yalcodes
What i'm thinking now is ... ዛሬ ክላስ ባይኖር ጥሩ ነው I wanna give some criteria to continue 😁 1. Lets add active and interested members 2. The goal is to reach 250 ...There is no giveaway for those who added thousands😂 ብቻ 250 እንሙላና እንቀጥላለን ። በነገራችን ላይ 1000ም ይቻላል 🙏
182 ·
Y
አንድ ሀሳብ ላጋራቹ ፈልጌ ነበር ከ AI ጋር በተገናኘ፦ ስለ Threats of AI (ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋት )ነክ የሆኑ ነገሮች ለማየት እየሞከርኩ ነበር እና ከተቀመጡት ሀሳቡች መሀል Super Artificial intelligence ነበር ማለትም በልህቀት ደረጃ ከሰው ይበልጣል ተብሎ የታሰበው የ AI future type እናም ስጋት እንደሆነ ይነሳል ለሰው ልጆች ህልውና ባነበብኩት ፅሁፍ ላይ። በዚ መሀል ነው እንግዲህ እንዴት ይሆን እኛው የሰራነው እኛውኑ ሚበልጠን የሚል ሀሳብ የመጣልኝ እናም ትንሽ ግር አሰኘኝ ። 🎲 የሰው ልጅ Unlimited የሆነ የ Creativity አቅም አለው በዚ ሁኔታ ውስጥ እየተጓዝን ታድያ እኛ creativity አችንን እስካላቆምን ድረስ ላይደርስብን ከዛም ባለፈ ላያልፈን ይችላል የሚል ሀሳብ መጣልኝ። 🎲 ሌላኛው ጥያቄዬ የነበረው ደግሞ ...እኛስ creative መሆናችንን እያቆምን ነው ወይ የሚል ጥያቄ አነሳው ለራሴ ? ያኔ ነው እንግዲ መልሱ የጠጠረብኝ....ለመጣልኝ ጥያቄ ያገኘውት መልስም 😞 ለተሰጡን Tasks, Exercise, every workouts, hard thinking issues and new ideas ሁሉ ወደ AI እየሄድን መሆኑን ትዝ አለኝ። ይህም ብቻ አደለም የአዲስ አመት፣ የበዓላት እና የመልካም ልደት ምኞቶች ሁሉ በ AI agents ማፃፍ ጀምረናል ታድያ በዚህ ምክንያት Creativity አችንን እየገደልነው አደለም ትላላቹ ? ይህ ነገር ነው May be እንዲበልጠን ሊያደርገው ሚችለው። ለማንኛውም AIን (እኛው ምንሰራው) አስቁመህ ሳይሆን ሮጠህ ድረስ ልንለው ይገባል። NB :- ከ AI ጋር ፉክክር ፍጠሩ አልወጣኝም ግን use it wisely ...ኋላ ትበላሻለህ። እንጠቀመው እንጂ Dependent እንዳንሆን የዛሬው መልዕክቴ ነው 🤝
212 ·
Y
Yalcodes
"Invest in your skills and the market will be yours."
201 ·
Yalcodes
Add member ባልኩት እስካሁን ማንም ያረገ የለም። Anyways Programming with mosh የሚል You tube channel አለ ከሱ ላይ አጫጭር Course time ይኖረናል ከአሁን በኋላ ባለው። በደንብ ተከታተሉት በሱ ምንዘልቅ ይሆናል። IRAN internet አቋርጣለው cable በጥሼ ያለችው እስካላደረገች ድረስ ከአሁን በኋላ ያለው class አይቋረጥም ። Deal ? If yes 🤝 Else Why Stay tuned 👍
166 ·
አዳዲስ Join ያረጋቹ ልጆች ። Welcome ብለናል።🫡 በዚሂ Channel currently Python PL እየተማርን ሲሆን ግባችን ለ Ai World ራሳችንን በማዘጋጀት በአስተዋይነት ምንጓዝበትን skill በመገንባት ላይ ነን። እስካሁን ጥቂት Sessions ነበሩን ፤ በእነዚሂም Video በራስ እና በአማርኛ record ተደርገው ስንጓዝ ነበር። አሁን ግን Programming with mosh ከሚል Youtube ቻናል ጋር ትምህርታችንን ምንቀጥል ይሆናል። Session days 1. Monday 2. Wednesday 3. Friday ቀጠሮ አንሰጥም ለመማር Video አንከምር ለመመልከት። Be Disciplined. This isn't abt me it's abt You. እናም ጠንከር ብላቹ ተማሩ ። Again Welcome ብለናል🤝
177 ·
Y
One thing ልነግራቹ ምፈልገው በተጨማሪ Python ምንማረው Programming language ለመሸምደድ አደለም... Problem Solving (ችግር አፈታት )ን ለመረዳት እንጂ። እሱን እርገጠኛ ስንሆን ወደ ሌሎች ምንሄድ ይሆናል ። መልፋት ነው ወገን 🫡🫡
208 ·
Yalcodes
ኢራን Internet cable ቆርጣዋለች ስለዚሂም በሚቀጥሉት ሰዓታት ከ ዓለም ሙሉ በሙሉ ለ 3 ወራት Internet የሚቋረጥ ይሆናል። April fool's day ነው today አይዞአቹ አደንግጡ።😅
255 ·
ዛሬ Class አለን አይረሳ Our time is flexible ከ 8:00 በኋላ ሁሌም ይለቀቃል ከዛ U learn ... complex ነገር የለውም ።
249 ·
ReplyPoll
ከ 14 ሰው 7 የለሊት ሰው አግኝተናል🫡 7ታቹ ግን ተመለሱ።😁 Anyways በለሊት መነሳት ጥሩ ነው።
200 ·
Y
Video ተመችቶኛል 👍 አይ እንደድሮው ይሻላል 👎
202 ·
Y
Photo
click to show
ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ወጥተው ወደ ቤታቸው የሚሄዱት ከምሽቱ 4 ሰዓት  በኋላ ነው ብትባሉ ታምናላችሁ? 🌙 እኛ ፈተና ሲቃረብ "እስከ 4 ሰዓት አነበብን" ብለን ልንፎክር እንችላለን፤ ለእነሱ ግን ይሄ መደበኛ ከት/ቤት የመውጫ ሰዓታቸው ነው! የደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በቀን እስከ 16 ሰዓት ድረስ የት/ት እና ጥናት ሰአት አላቸው። ከጠዋቱ 2 ሰዓት ትምህርት ቤት ገብተው መደበኛ ክፍለ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ፣ በቀጥታ "ሀጓን" (Hagwon) ወደሚባሉ የግል አካዳሚዎች ይተማሉ። የሚገርመው ነገር፣ እኩለ ሌሊት ላይ አውቶቡሶች በእነዚህ ተማሪዎች ተጨናንቀው ይታያሉ፤ ሁሉም ወደ ቤታቸው የሚሄዱት በዚያ ሰዓት ነው። እኛ የከሰዓት ትምህርት ኖሮን እንኳን 8 ሰዓት ሲሆን "መቼ ነው የምንወጣው?" ብለን ለምንቸኩል ተማሪዎች ይህ ነገር እንደ ቅዠት ሊመስለን ይችላል። ለኮሪያውያን ግን የዕለት ተዕለት ኑሯቸው ነው! From Lenege hub.
223 ·
Y
Yalcodes
Photo
click to show
ሚስጥራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራትዎ በፊት ሊያውቁት የሚገባ ጉዳይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት ሥራችንን እጅግ እያቀለለልን ቢሆንም፣ ከእድገቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶች ግን አልቆሙም። በቅርቡ በChatGPT የሶፍትዌር ሥርዓት ላይ በተገኘ ከፍተኛ የደህንነት ክፍተት፣ ጥቃት አድራሾች በአንድ "አደገኛና አጥፊ ትእዛዝ" (Malicious Prompt) ብቻ የግልና የተቋማትን መረጃዎች መዝረፍ የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጥሮ እንደነበር የቼክ ፖይንት (Check Point) ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል። ይህ የደህንነት ስጋት፣ አጥፊ የሆኑ የጽሁፍ ትእዛዞችን በመጠቀም የChatGPTን የመከላከያ አጥር በመጣስ፣ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች ሰርቨር (Server) ማስተላለፍ ያስችላል። ይህም ተጠቃሚዎች ወደ AIው የሚጭኗቸውን ልዩ ልዩ ፋይሎች፣ የግል መልእክቶች እና ሚስጥራዊ የድርጅት ሰነዶች ለከፍተኛ አደጋ አጋልጦ ቆይቷል። ራስዎን እንዴት ይጠብቁ? 👉 ትእዛዞችን (Prompts) ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፦ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ "ምርጥ ውጤት ያስገኛሉ" ተብለው የሚሰራጩ የትእዛዝ አይነቶችን ሳያረጋግጡ አይጠቀሙ። እነዚህ ትእዛዞች መረጃዎን በድብቅ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች የሚልኩ ድብቅ መመሪያዎችን ሊይዙ ይችላሉ። 👉ሚስጥራዊ ፋይሎችን ከመጫን ይቆጠቡ፦ የባንክ መረጃዎችን፣ የጤና ሰነዶችን ወይም የተቋማትን ሚስጥራዊ ፋይሎች ወደ AI ሲስተሞች ከመጫንዎ በፊት በደንብ ያስቡ። AIው መረጃውን ለሌላ ወገን እያጋራ መሆኑን ራሱ እንኳ ላያውቀው እንደሚችል ልብ ሊባል ይገባል።
237 ·
Y
Yalcodes
Photo
click to show
🔅 Deep Learning with Python: Optimizing Deep Learning Models 📝 Leverage techniques for optimizing deep learning models and implementing them using Python. 🌐 Author: Frederick Nwanganga 🔰 Level: Intermediate ⏰ Duration: 2h 1m 📋 Topics: Deep Learning, Python 🔗 Join Artificial intelligence for more courses
227 ·
Yalcodes
Photo
click to show
የዓለማችን የመጀመሪያው በሮቦት ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልክ (Robot Phone) ይፋ ሆነ ስማርት ስልኮች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ መሆኑን የሚያሳይ አስገራሚ ዜና ወጥቷል። HONOR የተባለው ኩባንያ የዓለማችንን የመጀመሪያውን በሮቦት ቴክኖሎጂ የታገዘ ስልክ (Robot Phone) ለገበያ አቅርቧል። ይህ ስልክ ከወትሮው በተለየ መልኩ ራሱን ማንቀሳቀስ የሚችል እና ለተጠቃሚው ምላሽ የሚሰጥ ነው። ስልኩ በውስጡ እጅግ ጥቃቅን የሞተር ሲስተም (Gimbal system) የያዘ ሲሆን፣ ይህም ካሜራው ሰዎችን ተከትሎ እንዲዞር እና በቪዲዮ ጥሪ ወቅት ተጠቃሚው ቢንቀሳቀስ እንኳ ሳይቋረጥ እንዲከታተል ያስችለዋል። በተጨማሪም AI Object-tracking የተባለ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ ምስሎችን በከፍተኛ ጥራት መቅረጽ ይችላል። ከቴክኒካዊ ብቃቱ በተጨማሪ፣ ስልኩ እንደ ሰው ስሜቱን በእንቅስቃሴ መግለጽ ይችላል። ለምሳሌ በአንድ ነገር ሲስማማ ራሱን በአዎንታ መነቅነቅ (Nodding )፣ ካልተስማማ ደግሞ ራሱን መነቅነቅ (Shaking) ይችላል። እንዲሁም ሙዚቃ ሲከፈት ከዜማው ጋር አብሮ የመንቀሳቀስ ብቃት አለው። ይህ ግኝት ስልኮች ከመሣሪያነት አልፈው የሰዎች የቅርብ ረዳትና አጋር የሚሆኑበትን ጊዜ አቅርቦታል። ምንጭ፦ HONOR News From balageru tech
205 ·
Yalcodes
Photo
click to show
How can i say አንድ ቀን ይሂ Ai ይበልጠናል after watching this 🤔🤔
162 ·
Do u know ለምን እንደዚ እንደሚፈጠር????
164 ·
Y
Local decoding inconsistency ይባላል Ai chatbot ያጋጥመዋል ይህ ችግር። Ai chatbot ብቻም አይደለም ችግሩ ዘርፈ ብዙ ነው in the field. I will explain it. ግን React አርጉ👍
172 ·
Y
Yalcodes
Photo
click to show
ከይለፍ-ቃል (Password) ወደ ማለፊያ-ቁልፍ (Passkey)፡ የዲጂታል ደህንነታችንን እናሳድግ! Passkey (የማለፊያ-ቁልፍ) ምንድን ነው? ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በስልካችን ወይም በኮምፒውተራችን ላይ የሚቀመጡ ክሪፕቶግራፊክ (Cryptographic) ቁልፎችን የሚጠቀም ሲሆን፤ የጣት አሻራን (Fingerprint) ወይም የፊት ገጽታን (Facial recognition) በመጠቀም በቀላሉ ወደ አካውንታችን እንድንገባ ያስችለናል። ይህ ማለት ከዚህ በኋላ ረጅም እና ውስብስብ የይለፍ-ቃላትን ማስታወስ ላያስፈልገን ይችላል። በአሁኑ ወቅት እንደ አፕል (Apple)፣ ጉግል (Google)፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) እና ኤክስ (X) የመሳሰሉ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት ይህንን አሰራር በስፋት እየደገፉት ይገኛሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እና አገልግሎቶች በፍጥነት እያደጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የሳይበር ጥቃቶች እና የመረጃ ስርቆቶችም በተመሳሳይ እየጨመሩ ይገኛሉ። በመሆኑም የማለፊያ-ቁልፎች (Passkeys) አጠቃቀም ከማጭበርበር (Phishing) እና ከመለያ ስርቆት የላቀ ጥበቃን ይሰጡናል። ይሁን እንጂ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፤ ይህ ቴክኖሎጂ ገና በሁሉም ድረ-ገጾች እና መተግበሪያዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ስላልተተገበረ ብቻውን የመጨረሻ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። እንዴት ልንጠቀመው እንችላለን? አብዛኛዎቻችን በስማርት ስልኮቻችን ላይ የምንጠቀማቸው የጉግል እና አፕል አካውንቶች የ Passkey አገልግሎትን ጀምረዋል። በስልካችሁ “Security Settings” ውስጥ በመግባት "Passkeys" የሚለውን በመምረጥ ማስተካከል ትችላላችሁ።
160 ·
Yalcodes
Link
click to show
የ2018 ኢመደአ ሰመር ካምፕ የምዝገባ መስፈርቶች – INSA Cyber Talent Challenge 2026 • ምዝገባ በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይደረጋል (ከውጪ ዜጎች በስተቀር) • በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከተመዘገቡ/ማራጋገጫ ከጨረሱ ቡሀላ ወደዋናዉ የምዝገባ ፖርታል ገብተዉ ፎርሙን መሙላት እንዳይረሱ • ከ11 ዓመት ጀምሮ ያለ ማንኛውም ታለንት ያለው ኢትዮጵያዊ መሳተፍ ይችላል - ምዝገባው የሚቆየው እስከ ግንቦት 8 • ሰመር ካምፑ በ6 ዩኒቨርሲቲዎች ይካሄዳል፡ 1) አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 2) ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3) ሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ 4) ጅማ ዩኒቨርሲቲ 5) ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ 6) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ • በሳይበር ደህንነት፣ ዴቨሎፕመንት፣ ኢምቤድድ ሲስተም፣ ኤሮስፔስ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ላይ ፍላጎት እና ተሰጥኦ (Talent with passion) ያላቸው • የተቋሙን ፈተና/ቻሌንጅ ማለፍ የሚችሉ • አዲስ ነገር የመማር ፍላጎት እና ተግባራዊ ስራ ላይ የመሳተፍ ፈቃደኝነት/ዝግጁነት • ችግር ፈቺ እና በራስ የመስራት/የመማር ማይንድሴት ያላቸው • የስነ-ምግባር ችግር የሌለባቸዉ የስልጠና ዘርፎች • ሳይበር ደህንነት • ሶፍትዌር ልማት • Embedded Systems • Aerospace • Emerging Technologies በምዝገባዉ መሳተፍ የማይችሉ/የማይመለከታቸዉ 1. በሳይበር ደህንነት እና ተዛማጅ ዘርፎች ላይ ፍላጎት እና ታለንት የሌላቸዉ 2. በኢመደአ የ4ዙር የሰመር ካምፕ/ፕሮግራም የተሳተፉ ድጋሜ መመዝገብ አይቻልም ⚠️ ማሳሰቢያ፡ ፎርሙ ስትሞሉ ሙሉ በሙሉ በAI የተፃፈ ይዘት መጠቀም አይፈቀድም። ከአንድ ጊዜ በላይ መሞከር ከምዝገባዉ ሊታገዱ ስለሚችሉ። 🎯 ተሳታፊዎች በINSA የመስራት እድል ፣ የስታርታፕ እድል እና ሌሎች ተጨማሪ እድሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ 👉 ተጨማሪ መረጃ: https://t.me/insactc 👉 ለመመዝገብ: https://ctc.insa.gov.et/registration
153 ·
Y
📌 Registration Requirements – INSA Cyber Talent Challenge 2026 • Registration must be completed using a National ID (except for foreign nationals). • After completing National ID verification/registration, applicants must proceed to the main portal and complete the application form. • Any Ethiopian citizen aged 11 years and above with talent and passion is eligible to apply. . Registration Deadline ⏰ May 17 • The summer camp will be hosted at the following universities: 1. Addis Ababa Science and Technology University 2. Bahir Dar University 3. Haramaya University  4. Jimma University 5. Debre Berhan University 6. Wolaita Sodo University Preferred Fields/Streams Applicants should demonstrate interest, talent, and passion in areas such as: • Cybersecurity • Software Development • Embedded Systems • Aerospace • Emerging Technologies Selection Criteria Applicants should: • Successfully pass the INSA’s selection test/challenge • Be willing and ready to learn new skills and participate in practical activities • Have strong problem-solving ability and self-learning discipline • Maintain good ethical behavior and discipline ❌ Individuals Not Eligible for Registration 1. Applicants who do not have genuine interest, passion, and talent in Cybersecurity and related technology fields. 2. Individuals who previously participated in the 4-round INSA summer camp/program are not eligible to register again. ⚠️ Important Notice: Submitting fully AI-generated responses in the application form is strictly prohibited. The system only provides a one-time warning and will not tolerate repeated attempts. Continued violations may result in automatic disqualification from the registration process. 🎯 Benefits for Participants Selected participants may gain access to: • Employment opportunities at INSA • Startup and innovation opportunities • Additional training and career development benefits 👉 More information: https://t.me/insactc 👉 Registration Portal: https://ctc.in
2 · 202 ·
Y
Yalcodes
Photo
click to show
ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሳቸውን እንዲያንጹ ታስቦ በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ፦ 🤖 በፈንዳሜንታል ኦፍ ኤ.አይ፣ 💻 ፕሮግራሚንግ፣ 🧠 ማሽን ለርኒንግ፣ ⚙️ በሮቦቲክስ እና IOT፣ 📊 ዳታ ሳይንስ እና በሌሎችም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ስልጠናል ይሰጣል። ተማሪዎች ተቋሙ ባዘጋጀውን ይፋዊ ድረ-ገጽ https://aii.et/summercamp በመጠቀም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም @tikvahethiopia
1 · 147 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count